11/04/2026
ውድ የሲዳማ ክልል ወጣቶች እና መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የትንሣኤ በዓል የአዲስ ጅምር፣ የተስፋ እና የድል ምልክት ሲሆን ይህ በዓል በተለይም ለወጣቶች አዲስ እድሎችን ለመፍጠር፣ በፈጠራ ሀሳብ ለመንቀሳቀስ እና ለማህበረሰብ ልማት ተግባራዊ ሚና ለመወጣት የሚያነሳሳ መንፈሳዊ እሴት አለው።
በዚህ የትንሣኤ ወቅት ወጣቶች የሰላም፣ የአንድነት እና የመተሳሰብ እሴቶችን በማጠናከር ለማህበረሰባችን ተስፋ የሚሆኑ ተግባራትን እንድንፈጽም፤ ወጣቶች የዛሬ ኃይል እና የነገ ተስፋ እንደመሆናችን በሰላም ግንባታ፣ በልማት ስራዎች እና በማህበራዊ አብሮነት ውስጥ ያለንን ሚና እንድንወጣ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ይህ የትንሣኤ በዓል ለሁላችን አዲስ ተስፋ፣ ሰላም፣ ፍቅር እና ስኬት ያምጣልን። በአንድነት ቆመን የክልላችንን እና የሀገራችንን ብሩህ ተስፋ ወደፊት እንገንባ።
እንኳን አደረሳችሁ!
መልካም የትንሣኤ በዓል!
ወጣት በቃሉ መሠረት
የሲዳማ ክልል ወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት