ድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት Dire Dawa Customs Branch office

ድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት Dire Dawa Customs Branch office የድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የመረጃ ቻናል

28/05/2026
26/05/2026
በታክስና ጉምሩክ ህጎች እና አሰራሮች ላይ  ስልጠና ለወሰዱ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂዎች የምዘና ፈተና ተሰጠድሬዳዋ— ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም=====================የ...
25/05/2026

በታክስና ጉምሩክ ህጎች እና አሰራሮች ላይ ስልጠና ለወሰዱ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂዎች የምዘና ፈተና ተሰጠ

ድሬዳዋ— ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም
=====================
የታክስና የጉምሩክ ህጎችን ጠንቅቆ የተረዳ ንቁ ትውልድ ለመፍጠር በተጀመረው አገራዊ ተልዕኮ በታክስና ጉምሩክ ህጎች እንዲሁም አሰራሮች ዙሪያ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለሚማሩ የህግ፣ የቢዝነስ እና የኢኮኖሚክስ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ላለፉት ተከታታይ ሳምንታት ሲሰጥ የነበረው መሰረታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መጠናቀቁ ይታወሳል።

ይህንን ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ላጠናቀቁ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ማለትም በ17/9/2018 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው አዳራሽ የምዘና ፈተና ተሰጥቷል።

የድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከገቢዎች ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ መርሃ-ግብር ሰልጣኞቹ በስልጠና ቆይታቸው ያገኙት እውቀትና ግንዛቤ የሚለካበት ሲሆን በምዘና ፈተናው 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘግቡ ሰልጣኞች በቀጣይ የሽልማትና የሰርተፊኬት ፕሮግራም የሚዘጋጅላቸው ይሆናል።

========================
# የድሬዳዋ ጉ/ቅ/ጽ/ቤትን የሚመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Telegram:
https://t.me/DDCbo1
Facebook:
https://web.facebook.com/Diredawacustoms17
በደንበኞች ትምህርት ቡድን
ድሬዳዋ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

በታክስና ጉምሩክ ህጎች እና አሰራሮች ላይ  ስልጠና ለወሰዱ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂዎች የምዘና ፈተና ተሰጠድሬዳዋ— ግንቦት 15ቀን 2018 ዓ.ም=====================የታ...
23/05/2026

በታክስና ጉምሩክ ህጎች እና አሰራሮች ላይ ስልጠና ለወሰዱ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂዎች የምዘና ፈተና ተሰጠ

ድሬዳዋ— ግንቦት 15ቀን 2018 ዓ.ም
=====================
የታክስና የጉምሩክ ህጎችን ጠንቅቆ የተረዳ ንቁ ትውልድ ለመፍጠር በተጀመረው አገራዊ ተልዕኮ በታክስና ጉምሩክ ህጎች እንዲሁም አሰራሮች ዙሪያ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለሚማሩ የህግ፣ የቢዝነስ እና የኢኮኖሚክስ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ላለፉት ተከታታይ ሳምንታት ሲሰጥ የነበረው መሰረታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መጠናቀቁ ይታወሳል።

ይህንን ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ላጠናቀቁ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ማለትም በ15/9/2018 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው አዳራሽ የምዘና ፈተና ተሰጥቷል።

የድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከገቢዎች ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ መርሃ-ግብር ሰልጣኞቹ በስልጠና ቆይታቸው ያገኙት እውቀትና ግንዛቤ የሚለካበት ሲሆን በምዘና ፈተናው 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘግቡ ሰልጣኞች በቀጣይ የሽልማትና የሰርተፊኬት ፕሮግራም የሚዘጋጅላቸው ይሆናል።

========================
# የድሬዳዋ ጉ/ቅ/ጽ/ቤትን የሚመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Telegram:
https://t.me/DDCbo1
Facebook:
https://web.facebook.com/Diredawacustoms17
በደንበኞች ትምህርት ቡድን
ድሬዳዋ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

በኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ መከላከል ዙሪያ በሐረር ከተማ የምክክር መድረክ ተካሄደድሬዳዋ — ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም========================የድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤ...
19/05/2026

በኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ መከላከል ዙሪያ በሐረር ከተማ የምክክር መድረክ ተካሄደ

ድሬዳዋ — ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም
========================
የድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የኮንትሮባንድ እና የንግድ ማጨበርበር ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከልና የቅንጅት ሥራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ የምክክር መድረክ በሐረር ከተማ አካሂዷል። በዚሁ መድረክ ላይ ከሐረሪ ክልል፣ ከምስራቅ ሐረርጌ ዞን እና ከማያ ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የጸጥታ አካላት እንዲሁም በአካባቢው ያሉ የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች ተሳትፈዋል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀምበሬ ምትኩ የኮንትሮባንድ ወንጀል ተራ ድርጊት አለመሆኑን ገልፀው ሀገር ልታገኝ የሚገባትን ቀረጥና ታክስ በማሳጣት፣ የገበያ ውድድርን በማዛባት እና የአገር ውስጥ አምራቾችን ተስፋ በማስቆረጥ በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ አደጋ እየደቀነ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

አያይዘውም ኮንትሮባንድ ለሀገር ሰላምና ደህንነት ስጋት የሆኑ ህገ-ወጥ ቁሶችን ለማስገባት ዋነኛ መሸጋገሪያ በመሆን ማህበራዊ ቀውሶችን እንደሚያስከትልና ይህንን ለመግታት የጸጥታ አካላት የተቀናጀ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት የሰጡ ሲሆን "የዚህ ውይይት መድረክ ዋና ዓላማ እስከአሁን በሰራናቸው ስራዎች ላይ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖቻችን በግልጽ በማየት ያሉብንን የአሰራርና የቅንጅት ክፍተቶችን ለመለየት እና ቀጣይ የማሻሻያ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ ነው" ብለዋል።

በመድረኩ ላይ በኮንትሮባንድ ወንጀሎች ሳቢያ በሀገር ላይ የሚደርሰውን ጫና እና እየተወሰዱ ስላሉ ህጋዊ እርምጃዎች የሚያሳይ የውይይት መነሻ ጽሑፍ ቀርቧል። በዚህም መሠረት፦
ባለፉት 10 ወራት ብቻ በቅ/ጽ/ቤቱ እና በጸጥታ አካላት የጋራ ቅንጅት ከ2.9 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የገቢና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉ እና በዚህ ህገወጥ ተግባር ተሰማርተው የተያዙ 50 ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በህግ እንዲታይ መደረጉ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው እንዲህ ያሉ መድረኮች የነበሩ ክፍተቶችን ለመለየትና የጋራ አሠራርን ለማጠናከር ጠቃሚ መሆናቸውን በመግለጽ ወደፊትም ተከታታይ ውይይቶች ሊዘጋጁ እንደሚገባ አስተያየት ሰጥተው በቅንጅት ስራው ላይ እያጋጠሙ በነበሩ ክፍተቶች እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን በቅ/ጽ/ቤቱ የሕግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ በሆኑት በአቶ ፈጅሩድን ሙሳ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

በመጨረሻም የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አህመድ አብዲ ባስተላለፉት መልዕክት "የኮንትሮባንድ ንግድ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ እና እጅግ አሳሳቢ በመሆኑ ይህን ህገ-ወጥ ተግባር መከላከል የአንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል" ያሉ ሲሆን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከጉምሩክ ጋር ያለውን አጋርነት ወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

******************************
# የድሬዳዋ ጉ/ቅ/ጽ/ቤትን የሚመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Telegram:
https://t.me/DDCbo1
Facebook:
https://web.facebook.com/Diredawacustoms17
በደንበኞች ትምህርት ቡድን
ድሬዳዋ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

Address

Dire Dawa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት Dire Dawa Customs Branch office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share