Dire Dawa Development Association

Dire Dawa Development Association Dire Dawa Development Association

13/08/2026
የድሬዳዋ ልማት ማህበር ከኤልኔት ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በአስተዳደሩ የህፃናት ማቆያ ማዕከል ስር ለሚገኙ ህፃናት የአልባሳት፣ የምግብ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።  ...
08/08/2026

የድሬዳዋ ልማት ማህበር ከኤልኔት ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በአስተዳደሩ የህፃናት ማቆያ ማዕከል ስር ለሚገኙ ህፃናት የአልባሳት፣ የምግብ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።
| ነሐሴ 02 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
የድሬዳዋ ልማት ማህበር በአስተዳደሩ የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ስር ባለው የህፃናት ማቆያ ማዕከል ለሚገኙ ወላጅ አልባ ህፃናት የሚውል የአልባሳት፣ የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።
በህፃናት ማቆያ ማዕከሉ ተገኝተው ድጋፎቹን ያበረከቱት የድሬዳዋ ልማት ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ከተማ ተሰማ እንደገለፁት ማህበሩ በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ላይ ወላጅ አልባ ህፃናትን መደገፍ አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።
በዚህ የሚገኙ ህፃናት የሁላችንም ልጆች ናቸው ያሉት አቶ ከተማ እነሱን መደገፍ የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ሰው ኃላፊነት ብቻ አለመሆኑን ተረድተን ሁላችንም በተቻለን አቅም ከጎናቸው መቆም ይገባናል ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ድጋፉን የተረከቡት በድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ የህፃናት መብትና ደህንነት ሥራ ሂደት አስተባባሪ ወ/ሮ ሳፊያ ዮሱፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ፤ በተለይም የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች በስፋት በሚከናወኑበት በዚህ ወቅት ህፃናቱን በመደገፍ ረገድ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አደራ ብለዋል።
ወ/ሮ ሳፊያ አያይዘውም ለህፃናቱ የሚደረገው ድጋፍ በተቋሙ ብቻ ሊሸፈን የሚችል ባለመሆኑ በዚህ የበጎ ፈቃድ ወቅት ግለሰቦች ፣ ተቋማትና የተለያዩ አካላት ለህፃናቱ በተቻላቸው መጠን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
የህፃናቱን ኑሮ ለማሻሻል እና የእኔ የሚሉት ቤተሰብ እንዲኖራቸው አቅም ያለው ዜጋ ሁሉ በጉዲፈቻ በመውሰድ የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ ጨምረው ገልፀዋል።
የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች የሚተገበሩበት ይህ ወቅት በተለይም ወላጅ አልባና ተጋላጭ ህፃናትን በመደገፍ የበጎነትና የሰብዓዊነት እሴቶችን በተግባር ለማሳየት የሚያስችል ወሳኝ ጊዜ መሆኑም ተገልጿል።
ሳራ አብዱራሂም
አብይ ግዛው
ለተጨማሪ መረጃዎች የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችንን ይቀላቀሉ:-
ፌስቡክ:- Dire tv አማርኛ:-
https://www.facebook.com/share/17ywq7woZg/ (https://www.facebook.com/share/1G8QtyPabv/)
ለኦሮምኛ:-
https://www.facebook.com/share/1B8KihEAkt/
ለሶማልኛ:-
https://www.facebook.com/share/199s1kp4Sr/
ቲክቶክ:- Diretv አማርኛ News:-
tiktok.com/.tv7
ዩቲዩብ:- Dirr tv:-
https://youtube.com/...
FM ድሬ 106.1:-
https://www.facebook.com/profile.php?id=61584275412874
ቴሌግራም
https://t.me/+6C5aVWGZeL4wOWM0
See less

Mobile  # 09136741
06/08/2026

Mobile # 09136741

Address

Dire Dawa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Development Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Dire Dawa Development Association:

Shortcuts

Share