ERCS - Gedeo Zone Branch

ERCS - Gedeo Zone Branch Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ERCS - Gedeo Zone Branch, Non-Governmental Organization (NGO), Dilla Town, Dilla.

ይህ የጌዴኦ ዞ/ቀይ መስቀል ቅ/ጽ/ቤት ትክክለኛ የፌስቡክ ገጹ ነው።በገጹም ስለ ቅ/ጽ/ቤት አጠቃላይ መረጃዎችን ፣ ትምህርቴ መስቀል ፣ ማስታወቂያዎች ፣ ሰብዓዊ ስራዎች ማግኘት ይችላል።
ስልክ:- +251909145440/Gedeozoneredcross(Tg)
Email:- [email protected] ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ:- ዲላ ከተማ ፣ ማሞ ኮሞልቻ አደባባይ ከፍ ብሎ

31/08/2026
31/08/2026
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የጌዴኦ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአባላትን ቁጥር መጨመር በሚያስችሉና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በዲላ ከተማ አካሄደ።‎‎በኢትዮጵያ ቀይ መስቀ...
22/08/2026

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የጌዴኦ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአባላትን ቁጥር መጨመር በሚያስችሉና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በዲላ ከተማ አካሄደ።

‎በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የጌዴኦ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአባላትን ቁጥር ለመጨመር የሚያስችሉ ሥራዎችን ጨምሮ በ2019 በጀት ዓመት ደረሰኝ ስርጭት እና አመላለስ ላይ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በዲላ ከተማ አካሂዷል።

‎የጌዶኦ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳንኤል ፀጋዬ በመክፈቻ ንግግራቸው የሰብዓዊነት ጉዳይ የሁላችንም በመሆኑ ማህበሩ በበጎ ፍቃደኝነት የሚያደርጋቸው ብዙ ስራዎችን እንዲያሳካ የጋራ ንቅናቄ በማድረግ የማህበሩን የአባላትን ቀጥር መጨመርና የፋይናንስ ጉዳይ መቅረፍ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል ።

‎የብልጽግና ፓርቲ ከማህበሩ ጋር በመቀናጀት ከሰብዓዊ ድጋፍ ባለፈ የተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ በመሳተፍ የሀገራችን ብልፅግና ለማረጋገጥ እየሠራ መሆኑን አንስተዋል ።

‎ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የጌዴኦ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ወንደወሰን ዳካ በተያዘው በጀት ዓመት ላይ የተሰሩ በርካታ ስራዎች እንዳሉ ጠቅሰው ለ2019 በጀት ዓመት የአባላትን ቁጥር ለመጨመርና የደረሰኝ ስርጭት ለማሻሻል የተዘጋጀ መድረክ እንደሆነ ገልፀዋል ።

‎የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ ከ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅ/ጽ/ቤት የመጡት አቶ ሮቤል ኦሪሳንጎ አጠቃላይ የማህበሩን አፈፃፀም ሪፖርት አቅርቧል ።

‎በተያዘው በጀት ዓመት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ዞን ቀይ መስቀል ማህበር በአባላት ቁጥር ሁለተኛ ደረጃ መያዙን በሪፖርቱ አመላክቷል ።

‎በፋይናንስ ላይ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የገቢ ማስገቢያ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ከመንግሥት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ለውጦችን ማምጣት እንደሚገባም ተገልጿል ።

‎በመድረኩም ከአባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ላይ ውይይት በማድረግ ለቀጣይ ዓመት የተሻለ አፈፃፀም እንድመዘገብ አባላትም ሆነ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው ተጠቁሟል ።

‎በብሌን ተገኔ
‎ፎቶ ፦ ብሩክ ፈለቀ
‎Via:- ጌዴኦ ቴለቪዥን
ERCS - Gedeo Zone Branch

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የዕድሜ ልክ አባል በመሆን ከሰብዓዊ ሥራው ጎን ይቁሙ!//በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የጋሞ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አመራር ቦርድ አባላት ሁሉም የማህበሩ...
22/08/2026

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የዕድሜ ልክ አባል በመሆን ከሰብዓዊ ሥራው ጎን ይቁሙ!//

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የጋሞ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አመራር ቦርድ አባላት ሁሉም የማህበሩ በመሆን የዚህን አንጋፋ ሀገራዊ ማህበራችንን ሰብዓዊ ተልዕኮውን በመደገፍ ግንባር ቀደም አርአያ ሆነዋል።

ሰለሆነም እርስዎም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የዕድሜ ልክ አባል በመሆን ሰብዓዊነትን እየደገፉ ፕሮፋይልዎን ያዳብሩ።

ለሰብዓዊነት እንኖራለን!
የጋሞ ዞን ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት።
አርባ ምንጭ

በጨለለቅቱ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪነት እና የቀይ መስቀል በጎ ፈቃደኞች የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የጽዳት ዘመቻ በጨለለቅቱ ከተማ ሁለተ...
21/08/2026

በጨለለቅቱ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪነት እና የቀይ መስቀል በጎ ፈቃደኞች የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የጽዳት ዘመቻ በጨለለቅቱ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግብ ውስጥ የጽዳት ዘመቻ አከናውኗል ።
ERCS - Gedeo Zone Branch

21/08/2026
"በጎነት ለአብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"የወናጎ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት እና የቀይ መስቀል በጎ ፈቃደኞች በክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ በወናጎ ወረዳ ሀሴ ሀሮ ጤና ጽ/ቤት በመገኘት በጤና ተ...
20/08/2026

"በጎነት ለአብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"

የወናጎ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት እና የቀይ መስቀል በጎ ፈቃደኞች በክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ በወናጎ ወረዳ ሀሴ ሀሮ ጤና ጽ/ቤት በመገኘት በጤና ተቋማት ወልደው የተኙትንና ህሙማንን ጉብኝትና ማዕድ የማጋራት መርሀ ግብር አካሄዱ።
ERCS - Gedeo Zone Branch

በ9400 አጭር መልዕክት ቁጥር ላይ  ''Ok'' ብለው ''በተለያዩ  ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ለመደገፍ የመላክ   ተቀላቅለዋል?     ብለዉ መልዕክ...
19/08/2026

በ9400 አጭር መልዕክት ቁጥር ላይ ''Ok'' ብለው ''በተለያዩ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ለመደገፍ የመላክ ተቀላቅለዋል?

ብለዉ መልዕክት ይላኩ በቀን አንድ ብር ብቻ ድጋፍ ያደርጉ❗️
ለሰብዓዊነት እንኖራለን!
ERCS - Gedeo Zone Branch

19/08/2026

መግለጫ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የኢትዮጵያ ሚዲያ አገልግሎት (EMS) ነሐሴ 11፣ 2018 ዓ.ም. “ዕለታዊ” በተሰኘው የቴሌቪዥን መርሃ ግብሩ ላይ ስለማኅበሩ አምቡላንሶች ያሰራጨውን ዘገባ ተመልክቷል። በዘገባውም፣ “በአዲስ አበባ … የቀይ መስቀል አምቡላንሶች የኤርትራ፣ የትግራይ፣ የአማራ ተወላጆችን … ወደ ማሰልጠኛ እያጓጓዙ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል” የሚል መረጃ ተላልፏል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አምቡላንሶች ከማኅበሩ የሰብዓዊነት፣ ገለልተኝነት፣ አለማዳላት እና ሌሎች መሠረታዊ የቀይ መስቀል መርሆች ጋር በሚጣረስ መልኩ ሰዎችን ለማጓጓዝ ወይም በመሰል ተግባራት ለመሳተፍ እንደማይውሉ በግልጽ ለማሳወቅ ይወዳል። ማኅበሩ የሚያከናውነው የአምቡላንስ አገልግሎት በሰብዓዊ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ የብሔር፣ የቋንቋ፣ የፖለቲካ አመለካከት ወይም ሌላ ማንኛውም ልዩነት ሳይደረግ የሰው ሕይወትን ማዳንና ስቃይን ማስታገስ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ስለሆነም በተጠቀሰው ዘገባ የተገለጸውን ዓይነት ተግባር የሚያከናውን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አምቡላንስ እንደሌለ ማኅበሩ ያረጋግጣል። በመሆኑም ማኅበሩ በመሠረታዊ የሰብዓዊነትና የገለልተኝነት መርሆቹ ላይ በመመሥረት የሚያከናውነውን ሰብዓዊ ተግባር ከሌሎች ዓላማዎች ጋር ማደባለቅ ወይም በተሳሳተ መልኩ ማቅረብ ትክክል ነው ብለን አናምንም።

በሌላ በኩል፣ ማኅበሩ እየተጋፈጠ ያለው አንዱ አሳሳቢ ጉዳይ የማኅበሩን አርማ ያለአግባብ የመጠቀም ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ በማኅበሩ የሰብዓዊ አገልግሎት ሂደት ላይ ፈተና እየሆነ ይገኛል። የቀይ መስቀልን አርማ እንዲጠቀሙ ያልተፈቀደላቸውና አርማውን ያለአግባብ የሚጠቀሙ አንዳንድ አካላት ከማኅበሩ የሰብዓዊ ተልዕኮና መርሆች ውጪ የሆኑ ተግባራትን ሲያከናውኑ መታየታቸው፣ በርካቶች እነዚህን ተግባራት ከማኅበሩ ጋር እንዲያያይዙት እያደረገ ይገኛል፡፡

የቀይ መስቀል አርማ የተለየ ሰብዓዊ ትርጉምና ጥበቃ ያለው ምልክት በመሆኑ፣ ያለተገቢ ፈቃድ መጠቀም ወይም አርማውን በማኅበሩ ስምና ተልዕኮ ላይ ጥርጣሬ ሊፈጥር በሚችል መልኩ ማሳየት ተገቢ አይደለም። ማኅበሩ ማንኛውም ግለሰብ፣ ተቋም ወይም ሌላ አካል የማኅበሩን አርማ፣ ስም ወይም መለያ ያለተገቢ ፈቃድ እንዳይጠቀም እና ማኅበሩን በማይወክል ተግባር እንዳያስተሳስር አጥብቆ ይጠይቃል፡፡

በተጨማሪም፣ ማኅበሩ የራሱን ስም፣ አርማ፣ ተሽከርካሪዎች ወይም ሌሎች መለያዎች በመጠቀም ከማኅበሩ የሰብዓዊ ተልዕኮና ከተቀመጡት መርሆች ውጪ የሚከናወን ማንኛውንም ተግባር አይታገስም። ማኅበሩ ከአሠራር መርሆቹ ወይም ከሥነ-ምግባር ደንቦቹ ውጪ የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ሠራተኛ፣ አሽከርካሪ ወይም ሌላ የማኅበሩ ተወካይ ቢኖር፣ ጉዳዩ በተገቢው መንገድ ተጣርቶ በማኅበሩ የውስጥ አሠራርና ተፈጻሚ ሕጎች መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ያረጋግጣል።

የሚዲያ ተቋማትና ሌሎች መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከማኅበሩ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዘገባ ከማቅረባቸው በፊት የመረጃውን ትክክለኛነት ከማኅበሩ በማረጋገጥ መረጃን ለሕዝብ እንዲያቀርቡ ጥሪ እናቀርባለን። በተለይም ከማኅበሩ አምቡላንሶች ወይም አርማ ጋር በተያያዘ አሳሳች ወይም ያልተረጋገጠ መረጃ ማሰራጨት በማኅበሩ ሰብዓዊ አገልግሎት ላይ አላስፈላጊ ጥርጣሬ እንዲፈጠርና ለሕዝብ ያለው እምነት እንዲጎዳ ሊያደርግ ስለሚችል በጥንቃቄ እንዲዘገብ እንጠይቃለን፡፡

በተጨማሪም፣ የቀይ መስቀልን አርማ ወይም ተሽከርካሪ በመጠቀም የማኅበሩን ስምና ተልዕኮ በሚያጠለሽ ተግባር ላይ ተሰማርተው ሲመለከቱ የተሽከርካሪውን ታርጋ ቁጥር፣ ቦታ፣ ቀን እና ተያያዥ መረጃዎችን በመግለጽ ለማኅበሩ እንዲያሳውቁ ጥሪ እናቀርባለን። ማኅበሩ እንደዚህ ያሉ ጉዳዮችን በተገቢው መንገድ በማጣራት ሕጋዊና የውስጥ አሠራሩን ተከትሎ እርምጃዎችን ይወስዳል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ለሕይወት አድን፣ ስቃይን ለማስታገስ እና ለሰብዓዊነት ቆርጦ የቆመ ተቋም ነው። ይህንን ተልዕኮ በአለማዳላት እና ገለልተኝነት ማስቀጠል የማኅበሩ ቁርጠኛ አቋም ነው።

ለሰብዓዊነት እንኖራለን!
-------------------------------
STATEMENT

The Ethiopian Red Cross Society (ERCS) has taken note of a report broadcast by the Ethiopian Media Service (EMS) on its television program “Eletawi” on 17 August 2026, concerning the Society’s ambulances. The report stated that “in Addis Ababa … we have received information that Red Cross ambulances are transporting Eritrean, Tigrayan, and Amhara people … to a military training center.”

The Ethiopian Red Cross Society would like to clearly state that its ambulances are not used to transport people or engage in any activities that are contrary to the Society’s Fundamental Principles, including humanity, neutrality, impartiality, and other fundamental Red Cross principles. The ambulance services provided by the Society are based on humanitarian needs and are focused on saving lives and alleviating suffering, without discrimination based on ethnicity, language, political opinion, or any other distinction.

Accordingly, the Society confirms that it does not have any Ethiopian Red Cross Society ambulance engaged in the type of activity described in the aforementioned report. Therefore, we do not believe it is appropriate to confuse or misrepresent the humanitarian activities carried out by the Society based on the fundamental principles of humanity and neutrality with other purposes or activities.

On the other hand, one of the serious concerns currently facing the Society is the improper use of its emblem. This situation is becoming a challenge to the delivery of the Society’s humanitarian services. Some individuals or entities that are not authorized to use the Red Cross emblem have been observed carrying out activities outside the Society’s humanitarian mission and principles. This has led many people to associate such activities with the Society.

The Red Cross emblem is a distinctive symbol with a specific humanitarian meaning and legal protection. Therefore, its use without appropriate authorization, or its display in a manner that could create doubt about the name and mission of the Society, is unacceptable. The Society strongly calls upon any individual, institution, or other entity not to use the Red Cross’s emblem, name, or other identifying marks without proper authorization, and not to associate the Society with activities that do not represent it.

Furthermore, the Society does not tolerate any activity carried out using its name, emblem, vehicles, or other identifying marks that is contrary to its humanitarian mission and established principles. If any employee, driver, or other representative of the Society is found to be acting outside the Society’s operational principles or code of conduct, the Society confirms that the matter will be properly investigated and that the necessary measures will be taken in accordance with the Society’s internal procedures and applicable laws.

We call upon media organizations and other information disseminating entities to verify the accuracy of information with the Society before reporting on matters related to the Ethiopian Red Cross Society and to provide verified information to the public. In particular, we urge media outlets to exercise due care when reporting information related to the Society’s ambulances or emblem. The dissemination of misleading or unverified information may create unnecessary doubts about the Society’s humanitarian services and undermine public trust in the Society.

Furthermore, anyone who observes a vehicle using the Red Cross emblem or other identifying marks while engaging in activities that tarnish the name and mission of the Society is encouraged to report the matter to the Society, providing the vehicle’s plate number, location, date, and any other relevant information. The Society will properly investigate such cases and take appropriate legal and internal measures in accordance with its procedures.

The Ethiopian Red Cross Society is an institution firmly committed to saving lives, alleviating suffering, and serving humanity. Upholding this mission through the principles of impartiality and neutrality remains the unwavering commitment of the Society.
We Live for Humanity!


Ethiopian Media Services
----------------------
📌Website: https://redcrosseth.org/
📌Instagram፡ https://www.instagram.com/ercs1935/
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/ethiopian-red-cross-society/
📌YouTube: https://www.youtube.com/
📌X(Twitter): https://x.com/EthioRedCross
📌Telegram: https://t.me/ERCSHQ
📌 Tiktok: https://www.tiktok.com/
📌 Flickr፡- 137615657@N05/" rel="ugc" target="_blank">https://www.flickr.com/photos/137615657@N05/

Address

Dilla Town
Dilla

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ERCS - Gedeo Zone Branch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share