ኢትዮጵያዊነት የበጎ አድራጎት ማህበር ዲላ
በሀገራችን የተለያዩ ቦታዎች ማህበራዊ ድጋፍ የሚሹ በሚልዮን የሚቆጠሩ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዳሉ ይታወቃል። ምንም እንኳን አባይን በማንኪያ መጨለፍ ቢመስልም ይህንን ማህበራዊ ችግር ሁላችንም የተቻለንን በማድረግ መቅረፍ ይቻላል ብለን በዲላና አካባቢዋ ባሉ ቅን እና የመልካም ልብ ባለቤት ወጣቶች ይህንን ማህበር በ2012 ዓም የመሰረትን ሲሆን ዘር፣ ብሄር፣ ሀይማኖት እና ቦታ ሳይገድበው በኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያውያንን የሚረዳ ነው
ከማህበራችን ዘርፈ ብዙ ስራዎች መካከል:-
በዲላ እና በአካባቢው የሚገኙ ጧሪ የሌላቸውን አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች ፣ በከፊል በጎዳና ያሉ ወገኖችን፣ ታ
ራሚዎችን፣ በሆስፒታል እና ቤታቸው ተኝተው የሚታከሙ እና ሌሎች የማህበሩን እገዛ ለሚፈልጉ ሁሉ
፟- ቤት ማደስ፣ ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ፣ ማስታመም፣ ንፅህና መጠበቂያዎችን ማደል፣ ማጠብ
- የወር አስቤዛ መስጠት፣ በየቀኑ ምግብ ማደል፣የቤት ክራይ መክፈል፣ በዓላትን ከአረጋውያን እና ከጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር ማሳለፍ፣
- በተለያየ ምክንያት ወደጎዳና የወጡ ልጆችን ወደቤተሰባቸው እንዲመለሱ እና ባሉበት እገዛ እንዲያገኙ ማድረግ፣ የአልባሳት እና የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረግ እና
-ሌሎች ያልተጠቀሱ እገዛዎችን ማድረግ
አላማችሁ አላማችን ነው ብላችሁ ከጎናችን እንደምትሆን ተስፋ እናደርጋለን
በጉልበት፣ በሀሳብ፣ ገንዘብ እንዲሁም በቁሳቁስ ማገዝ ለምትሹ:-
+251936450843 ነብዩ
+251976060511 ማስተዋል
0461312600 የቢሮ
እንዲሁም በንግድ ባንክ አካውንታችን 1000342158707( ኢትዮጵያዊነት የበጎ አድራጎት ማህበር) የቻላችሁትን መላክ ወይም ማስገባት ትችላላችሁ
“ መኖራችን የሚሰማን ለሌሎች ስንኖር ነው ”
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮጲያዊነት የበጎ አድራጎት ማህበር ዲላ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.