Eyu-Ethiopia

Eyu-Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Eyu-Ethiopia, Nonprofit Organization, Bahir Dar.

በ እዩ-ኢትዮጵያ
በምርምር፣ በስልጠና፣ በህክምና እና በአስፈላጊ እንክብካቤ መከላከል ከሚቻሉ የአይን ጤና ጉዳዮች የፀዳች ኢትዮጵያን ለመገንባት እንጥራለን።

At Eyu-Ethiopia
We strive for an Ethiopia free from preventable eye health issues through research, training, rehabilitation, and essential care.

እዩ-ኢትዮጵያ ነጻ የዓይን ሞራ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ሰጠ ::      እዩ-ኢትዮጵያ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በደ/ወሎ ዞን በአርጎባ ልዩ ወረዳ  በመዲና ከተማ  የዓይን ሞራ...
29/04/2026

እዩ-ኢትዮጵያ ነጻ የዓይን ሞራ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ሰጠ ::

እዩ-ኢትዮጵያ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በደ/ወሎ ዞን በአርጎባ ልዩ ወረዳ በመዲና ከተማ የዓይን ሞራ ቀዶ ህክምና እና ሌሎች አገልግሎቶችን ሰጥቷል ።

የህክምና አገልግሎቱም የአካባቢው እና አጎራባች ቦታዎች የሚኖሩ የዓይን ሞራ (Cataract)፣ የዓይን ግፊት (Glaucoma) እና ሌሎች መሠል ችግሮች ተጠቂ የሆኑ ማህበረሰቦችን ያካተተ ነበር። የዓይን ቀዶ ህክምና አገልግሎቱም ከ 120 በላይ ሰዎችን ያሳተፈ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ ከ38% በላይ የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ፤ እንዲሁም ሌሎች በዓይን ጠብታዎች ህክምና ከተደረገላቸው 530 ሰዎች መካከል ደግሞ ከ33% በላይ ሚሆኑት የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ሴቶች ነበሩ::

ህክምናውን ያገኙ ታካሚዎችና ቤተሰቦቻቸዉ እይታቸው በመመለሱ በጣም ደስተኛ እንደሆኑ ገልጸው ከዚህ ቀደም ህክምናውን ለማግኘት ቦሮ ሜዳ ድረስ መሄድ እንደሚያስፈልጋቸው ይህን ለማድረግ ደግሞ አቅም እንዲሁም የትራንስፖርት እንግልቱና ወጪ መሸፈን ከባድ እንደሆነባቸው ገልፀዉ ይህ አገልግሎት በወረዳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በቅርብ በማግኘታቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልጸው ለእዩ-ኢትዮጵያ ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

የሶሻል ሚዲያችን ይቀላቀሉ:-
🌍 Website: www.eyuethiopia.org
🐦 Twitter/X: https://x.com/Eyu_Ethiopia
📘 Facebook: https://web.facebook.com/EyuEthiop/
🔗 LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/eyuethiopia
📢 Telegram: https://t.me/+tPeu-xg9T_w4OTFk

እዩ-ኢትዮጵያ
ለተሻለ እይታ እንሰራለን !




እዩ-ኢትዮጵያ ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት እዩ-ኢትዮጵያ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  አዘጋጅነት በተካሄደው ለ ‘’6ኛው ዓለም አቀፍ...
29/04/2026

እዩ-ኢትዮጵያ ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት

እዩ-ኢትዮጵያ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዘጋጅነት በተካሄደው ለ ‘’6ኛው ዓለም አቀፍ የጤና ምርምር ኮንፈረንስ’’ ላበረከተው የገንዘብ ስፖንሰርሽብ ድጋፍ የምስጋና ምስክር ወረቀት የተበረከተለት ሲሆን ኮንፈረንሱ ለተከታታይ ሁለት ቀናት “Building Bridges: Synergizing Research, Education, and Healthcare for a Resilient Tomorrow,” በሚል መሪ ቃል ተካሂዶዷል ። ኮንፈረንሱ በዘርፉ ያሉትን ወቅታዊ የጤና ችግሮች በመለየት፣ በሳይንሳዊ ጥናት የተደገፉ መፍትሄዎችን በማፍለቅ እና በባለሙያዎች የተሞክሮ ልውውጥ ዓላማው ያደረገ ነው።

ድርጅታችንም ለተበረከተለት የምስጋና የምስክርወረቀት ምስጋና እያቀረበ በቀጣይነት በጋራ ለመስራት ያለውን ፍላጎት ይገልጻል።

የሶሻል ሚዲያችን ይቀላቀሉ:-
🌍 Website: www.eyuethiopia.org
🐦 Twitter/X: https://x.com/Eyu_Ethiopia
📘 Facebook: https://web.facebook.com/EyuEthiop/
🔗 LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/eyuethiopia
📢 Telegram: https://t.me/+tPeu-xg9T_w4OTFk



እዩ-ኢትዮጵያ በ eCHIS የአይን ጤና ሞጁል ላይ የምክክር አውደ ጥናት አካሄደ ።እዩ-ኢትዮጲያ, ከኢትዮጲያ ጤና ሚኒስቴር ጋር በ መተባበር eCHIS የዓይን ሞጁል በሚመለከት የአንድ ቀን የ...
16/04/2026

እዩ-ኢትዮጵያ በ eCHIS የአይን ጤና ሞጁል ላይ የምክክር አውደ ጥናት አካሄደ ።

እዩ-ኢትዮጲያ, ከኢትዮጲያ ጤና ሚኒስቴር ጋር በ መተባበር eCHIS የዓይን ሞጁል በሚመለከት የአንድ ቀን የምክክር አውደ ጥናት አካሂዷል ፡፡

የአውደ ጥናቱ ዓላማም የመጀመሪያ ደረጃ ዓይን ጤናን በመጀመሪያ ደረጃ የጤና አሃድ ውስጥ ለማስረጽ እየተተገበረ የሚገኘውን eCHIS የ ዓይን ሞጁልን (eCHIS Eye Health Module) በተጠቃሚዎች ያለው ምቹነትን ለመመልከት ነው፡፡

ይህም በሲዳማ ክልል እየተሰራ የሚገኘውን የመጀመሪያ ደረጃ ዓይን ጤናን በመጀመሪያ ደረጃ የጤና አሃድ ውስጥ ማስረጽ የተሰኘውን ፕሮጀክት ከeCHIS የዓይን ሞጁል ጋር ለመተግበር ያለመ ነው፡፡

በምክክር ዓውደ ጥናቱ ላይ ከ ጤና ሚኒስቴር የሚመለከታቸው የፕሮግራም ሃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ እንዲሁም የ በሲዳማ ክልል ውስጥ የሚሰሩ የeCHIS እና ጤና ኤክስቴንሽን ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በዓይን ጤና ዘርፍ በተሰማሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ሌሎች የሚመለከታቸው አጋር አካላት ከተውጣጡ አባላት ተሳትፈውበታል፡፡

በ ውይይቱም አሁን ስራ ላይ ያለው eCHIS እና የዓይን ጤና ሞጁል መሻሻል እንደሚገባው መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን፣ ለዚህም ቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡

የሶሻል ሚዲያችን ይቀላቀሉ:-
🌍 Website: www.eyuethiopia.org
🐦 Twitter/X: https://x.com/Eyu_Ethiopia
📘 Facebook: https://web.facebook.com/EyuEthiop/
🔗 LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/eyuethiopia
📢 Telegram: https://t.me/+tPeu-xg9T_w4OTFk


እዩ-ኢትዮጵያ ስልጠና እና ግምገማ አካሄደ ፡፡                                              እዩ-ኢትዮጵያ በሜጫ ፣ ደንበጫ፤ አርጎባና ዳዋ ጨፋ ወረዳዎች የተቀናጀ ...
17/03/2026

እዩ-ኢትዮጵያ ስልጠና እና ግምገማ አካሄደ ፡፡

እዩ-ኢትዮጵያ በሜጫ ፣ ደንበጫ፤ አርጎባና ዳዋ ጨፋ ወረዳዎች የተቀናጀ የቅርብ እይታ ችግር በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የተሰኘ ፕሮጀክት በ 7 ጤና ጣቢያዎች ላይ የቅርብ እይታ ችግርን በመነጸር የማከም ስራ እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል ። ይህንን ስራ በቀጣይነት በተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ተጨማሪ 3 ጤና ጣቢያዎች በማካተት ወደ 10 በማሳደግ ለ 3 ቀናት የስራ እንቅስቃሴ ግምገማ እና ስልጠና በኮምቦልቻ እና ባህርዳር ከተማ አካሄዷል።

ሶሻል ሚዲያችን ይቀላቀሉ:-
🌍 Website: www.eyuethiopia.org
🐦 Twitter/X: https://x.com/Eyu_Ethiopia
📘 Facebook: https://web.facebook.com/EyuEthiop/
🔗 LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/eyuethiopia
📢 Telegram: https://t.me/+tPeu-xg9T_w4OTFk

እዩ-ኢትዮጵያ በአርጎባ ልዩ ወረዳ የአይን ምርመራ እና ህክምና  አገልግሎት ሰጠ ።እዩ-ኢትዮጵያ በአርጎባ ልዩ ወረዳ  ሁሉንም ማህበረሰብ ያሳተፈ የአይን ጤና ትምህርት እንዲሁም  ነጻ የአይን...
11/03/2026

እዩ-ኢትዮጵያ በአርጎባ ልዩ ወረዳ የአይን ምርመራ እና ህክምና አገልግሎት ሰጠ ።

እዩ-ኢትዮጵያ በአርጎባ ልዩ ወረዳ ሁሉንም ማህበረሰብ ያሳተፈ የአይን ጤና ትምህርት እንዲሁም ነጻ የአይን ምርመራ እና ህክምና አገልግሎት ለ 408 ወንዶች እና ለ 417 ሴቶች የሰጠ ሲሆን በምርመራው ወቅትም የአይን ጠብታ ለሚያስፈልጋቸው 180 ሰዎች የአይን ጠብታዎች ተሰጥቷል ። እንዲሁም ቀዶ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው የተለዩ ሲሆን በቀጣይ ሚያዚያ 15 ጀምሮ ነጻ የቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚሠጥ ይሆናል።

ሶሻል ሚዲያችን ይቀላቀሉ:-
🌍 Website: www.eyuethiopia.org
🐦 Twitter/X: https://x.com/Eyu_Ethiopia
📘 Facebook: https://web.facebook.com/EyuEthiop/
🔗 LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/eyuethiopia
📢 Telegram: https://t.me/+tPeu-xg9T_w4OTFk

14ኛ ወር የአጥራ ፕሮጀክት መረጃ ስብሰባ ተካሄደእዩ ኢትዮጵያ ከአማራ ጤና ቢሮ፣ ከካርተር ሴንተር እና ከለንደን ስኩል ኦፍ ሃይጂን እና ትሮፒካል ሜዲሲን ጋር በመተባበር በአማራ ክልል፣ በአ...
10/03/2026

14ኛ ወር የአጥራ ፕሮጀክት መረጃ ስብሰባ ተካሄደ

እዩ ኢትዮጵያ ከአማራ ጤና ቢሮ፣ ከካርተር ሴንተር እና ከለንደን ስኩል ኦፍ ሃይጂን እና ትሮፒካል ሜዲሲን ጋር በመተባበር በአማራ ክልል፣ በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የሚያከናውነው የአጥራ ፕሮጀክት ጥናት 14ኛ ዙር የመረጃ ስብሰባ አካሂዷል።

ጥናቱ በዋነኝነት ለትራኮማ ተጋላጭ የሆኑ ከ1 እስከ 9 አመት እድሜ ክልል ላይ ያሉ ህጻናት ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን ለ14 ተከታታይ ወራት ወርሃዊ ክትትል እየተደረገ ይገኛል ። በጥናቱ ከሁሉም የወረዳው ቀበሌዎች የተወጣጡ ከሁለት ሺህ በላይ ህፃናት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ሶሻል ሚዲያችን ይቀላቀሉ:-
🌍 Website: www.eyuethiopia.org
🐦 Twitter/X: https://x.com/Eyu_Ethiopia
📘 Facebook: https://web.facebook.com/EyuEthiop/
🔗 LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/eyuethiopia
📢 Telegram: https://t.me/+tPeu-xg9T_w4OTFk

እዩ-ኢትዮጵያ 29ኛውን የቦርድ ስብሰባ አካሄደ::   እዩ-ኢትዮጵያ 29ኛውን የቦርድ ስብሰባ  በአዲስ አበባ በቤስት ዌስተርን ሆቴል  አካሄዷል።በእለቱም የእዩ -ኢትዮጵያ የ6 ዓመት (ከ 20...
01/03/2026

እዩ-ኢትዮጵያ 29ኛውን የቦርድ ስብሰባ አካሄደ::

እዩ-ኢትዮጵያ 29ኛውን የቦርድ ስብሰባ በአዲስ አበባ በቤስት ዌስተርን ሆቴል አካሄዷል።

በእለቱም የእዩ -ኢትዮጵያ የ6 ዓመት (ከ 2020-2025) እና የ2025 የፕሮግራም እና የፋይናንስ የስራ አፈፃፀም የተገመገመ ሲሆን የ 2026ን የድርጅታዊ እቅድ ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል።
በመጨረሻም የአዲስ አበባውን አዲሱን የድርጅቱን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በመጎብኘት የእለቱ ስብሰባ ተጠናቋል ።

13ኛ ወር የአጥራ ፕሮጀክት መረጃ ስብሰባ ተካሄደእዩ ኢትዮጵያ ከአማራ ጤና ቢሮ፣ ከካርተር ሴንተር እና ከለንደን ስኩል ኦፍ ሃይጂን እና ትሮፒካል ሜዲሲን ጋር በመተባበር በአማራ ክልል፣ በአ...
03/02/2026

13ኛ ወር የአጥራ ፕሮጀክት መረጃ ስብሰባ ተካሄደ

እዩ ኢትዮጵያ ከአማራ ጤና ቢሮ፣ ከካርተር ሴንተር እና ከለንደን ስኩል ኦፍ ሃይጂን እና ትሮፒካል ሜዲሲን ጋር በመተባበር በአማራ ክልል፣ በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የሚያከናውነው የአጥራ ፕሮጀክት ጥናት 13ኛ ዙር የመረጃ ስብሰባ አካሂዷል።

ይህ ፕሮጀክት በዋነኝነት ስር የሰደደ ትራኮማን ለመከላከል የሚያስችሉ መንገዶችን መፈተሽ እና ለበሽታው የሚያጋልጡ መንስኤዎችን መለየትን ዓላማ ያደረገ ነው።

Join Us :
Website: www.eyuethiopia.org
Twitter/X: https://x.com/Eyu_Ethiopia
Facebook: https://lnkd.in/dHrYkYcS
LinkedIn: https://lnkd.in/dEniRAHv
Telegram: https://lnkd.in/dBb6xi8D

12ኛ ዙር የአጥራ ፕሮጀክት መረጃ ስብስባ ተካሄደ  እዩ-ኢትዮጵያ ከ ተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ላይ እያደረገው ያለው ትራኮማን እንዴት መከላከል እን...
19/12/2025

12ኛ ዙር የአጥራ ፕሮጀክት መረጃ ስብስባ ተካሄደ

እዩ-ኢትዮጵያ ከ ተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ላይ እያደረገው ያለው ትራኮማን እንዴት መከላከል እንደሚቻል እና አጋላጭ መንስኤዎቹ ምን እንደሆኑ መለየት አላማው ያደረገ አጥራ የተሰኘው ፕሮጀክት 12ኛ ዙር የመረጃ እና የደም ናሙና ስብሰባ አካሄዷል።

Join Us :
🌍 Website: www.eyuethiopia.org
🐦 Twitter/X: https://x.com/Eyu_Ethiopia
📘 Facebook: https://web.facebook.com/EyuEthiop/
🔗 LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/eyuethiopia
📢 Telegram: https://t.me/+tPeu-xg9T_w4OTFk


እዩ-ኢትዮጵያ  በቃሉ ወረዳ ለሚገኙ ተማሪዎች ነጻ የአይን ምርመራ እና የመነፀር እደላ አካሄደ።                                                            ...
19/12/2025

እዩ-ኢትዮጵያ በቃሉ ወረዳ ለሚገኙ ተማሪዎች ነጻ የአይን ምርመራ እና የመነፀር እደላ አካሄደ።
እዩ-ኢትዮጵያ በአማራ ክልል በቃሉ ወረዳ ስር ባሉ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች ነፃ የአይን ምርመራ ያካሄደ ሲሆን ምርመራውን ካደረጉ ተማሪዎች ውስጥ በመነፀር የሚስተካከል የአይን ችግር ላለባቸው 42 ተማሪዎች ነፃ መነፀሮችን አበርክቷል።

Join Us :
🌍 Website: www.eyuethiopia.org
🐦 Twitter/X: https://x.com/Eyu_Ethiopia
📘 Facebook: https://web.facebook.com/EyuEthiop/
🔗 LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/eyuethiopia
📢 Telegram: https://t.me/+tPeu-xg9T_w4OTFk


እዩ-ኢትዮጵያ በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው በ4ተኛው የዓለም አቀፍ የምርምር ጉባኤ ላይ  ተሳተፈየአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በአማራ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረ...
08/12/2025

እዩ-ኢትዮጵያ በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው በ4ተኛው የዓለም አቀፍ የምርምር ጉባኤ ላይ ተሳተፈ

የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በአማራ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ባዘጋጁት በ4ተኛው የዓለም አቀፍ የምርምር ጉባኤ ላይ እዩ-ኢትዮጵያ በመሳተፍ ሁለት የምርምር ጥናቶቹን አቀረበ። በምርምር ጉባኤው ላይ የዩንቨርስቲ ማህበረሰብ ፣ ተመራማሪዎች ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ከሀገር ውስጥና ከውጭ ተካፋይ ሲሆኑ ኢዩ-ኢትዮጵያም ለጉባኤው ስኬት ከተሳትፎ በተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ደማቅ ተሳትፎ አድርጓል።

Join Us :
🌍 Website: www.eyuethiopia.org
🐦 Twitter/X: https://x.com/Eyu_Ethiopia
📘 Facebook: https://web.facebook.com/EyuEthiop/
🔗 LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/eyuethiopia
📢 Telegram: https://t.me/+tPeu-xg9T_w4OTFk

Address

Bahir Dar
6000

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:30
Tuesday 08:00 - 05:30
Wednesday 08:00 - 05:30
Thursday 08:00 - 05:30
Friday 08:00 - 05:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eyu-Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share