18/08/2026
በድል የታጀበ ህዝባዊ ተሳትፎ ለዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ"በሚል መሪ ሀሳብ ከወረዳው አመራር ጋር ውይይት እየተካሔደ ነው
ነሀሴ 12/2018 ዓ.ም (ይልማና ዴንሳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን
በሰሜን ጎጃም ዞን ይልማና ዴንሳ ወረዳ "በድል የታጀበ ህዝባዊ ተሳትፎ ለዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ" በሚል መሪ ሀሳብ ከወረዳው አመራር ጋር ውይይት እየተካሔደ ነው።
የመድረኩ ዋና ዓላማ የሰላምና የልማት ስራዎችን በህዝብ ተሳትፎ የበለጠ ማጠናከር ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ በዕለቱም የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ መለሰ ታፈረ የመነሻ ሰነድ ለተሳታፊዎች እያቀረበ ይገኛል።