የአማራ ክልል ጠበቆች ማኅበር/ Amhara Region Bar Association

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • የአማራ ክልል ጠበቆች ማኅበር/ Amhara Region Bar Association

የአማራ ክልል ጠበቆች ማኅበር/ Amhara Region Bar Association The association is statutorily established by Proclamation No. 293/2025 and commenced its work on March 31, 2026.

የአማራ ክልል ጠበቆች ማህበር ፕሬዝዳንት ሰሎሞን ጎራው በሰሜን ሸዋ ዞን የጠበቆች ማህበር አመራሮች ጋር  በደብረ ብርሃን ከተማ ውይይት አድርገዋል።👇     👇    👇   ⛩️     👇    ...
30/05/2026

የአማራ ክልል ጠበቆች ማህበር ፕሬዝዳንት ሰሎሞን ጎራው በሰሜን ሸዋ ዞን የጠበቆች ማህበር አመራሮች ጋር በደብረ ብርሃን ከተማ ውይይት አድርገዋል።
👇 👇 👇 ⛩️ 👇 👇 👇
የክልሉ ጠበቆች ማኅበር አመራሮች በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ ከዞኑ ጠበቆች ተወካዮች ጋር ያደረጉትን ተራማጅና ፍሬያማ ውይይት አሳይተዋል።
❗️ ይህ መድረክ የጠበቆችን መብትና ጥቅምን ለማስከበር ብቻ ሳይሆን፣ የፍትህ ሥርዓቱን ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ የተደረገ ታሪካዊ እርምጃ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

​በውይይቱ ላይ የተነሱትን ዋና ዋና ነጥቦች ከዓለም አቀፍ መርሆች ጋር በማዛመድ እንደሚከተለው በዝርዝር ተተንትኖ ነበር፦

​1ኛ:- የጠበቆች የሙያ ስነ-ምግባር እና የፍትህ ስርዓት ትስስር (Legal Ethics and the Administration of Justice)

​❗️ የጠበቆችን የሙያ ስነ-ምግባር ማሻሻል ከፍትህ ስርዓቱ ጋር ያለውን የጋራ ግንኙነትና በፍትህ አካላት መካከል የሚኖረውን ሚና ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑ፣

​❗️ በዓለም አቀፍ የጠበቆች ማህበር (IBA) መርሆች መሰረት፣ ጠበቃ የደንበኛው ተሟጋች ብቻ ሳይሆን "የፍትህ ስርዓቱ መኮንን" (Officer of the Court) ናቸው። ጠበቆች ከፍተኛ ስነ-ምግባር ሲኖራቸው የህዝብ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ያለው እምነት ይጨምራል። የሙያ ስነ-ምግባርን ማሻሻል የህግ የበላይነትን (Rule of Law) ለማስፈን መሰረት መሆኑ።

​2ኛ. ጠንካራና ራሱን የቻለ የጠበቆች ማህበር መዋቅር (Independence of the Bar)

​❗️ በአዋጅ ቁጥር 293/2017 (በአዲሱ አዋጅ) መሰረት የሚወጡ ደንቦች ላይ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በንቃትና በብቃት እንዲሳተፉ ማድረግ፣ የፋይናንስ አቅምን ማጠናከር እና የማህበሩን መዋቅር በዞን ደረጃ መዘርጋት እና እስከ ወረዳ ድረስ እንዲተሳሰር ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣

​❗️ የጠበቆች ማህበር ነጻና ራሱን የቻለ (Independent Bar Association) መሆን አለበት። ይህ ነጻነት የሚረጋገጠው ደግሞ ማህበሩ ጠንካራ የውስጥ መዋቅር፣ የውስጥ ዲሞክራሲ (የአባላት ንቁ ተሳትፎ) እና ራሱን የቻለ የፋይናንስ ምንጭ ሲኖረው ነው።
የተጠቀሱት የማጠናከሪያ ስራዎች ማህበሩ ተቋማዊ ነጻነቱን ጠብቆ አባላቱን በብቃት እንዲያገለግል ያስችለዋል በሚል ታምኖበታል።

​3ኛ. የፍትህ ተደራሽነት እና የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ (Access to Justice & Fair Trial)

​❗️ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በቪዲዮ ኮንፈረንስ (በአይቲ መረብ) መዘርጋቱ የሰብአዊ መብትን፣ ፍትህ የማግኘት መብትን እና የውሳኔ ግልባጭን በፍጥነት የማግኘት ችግሮችን እንደሚቀርፍ መግባባት ላይ መደረሱ እና በክርክር ላይ ለጠበቆች ለአፈፃፀም አልመች የሚሉትን የአሰራር እንቅፋቶች ካሉ እየለዩ ችግሩን መፍታት ወሳኝ መሆኑና ይህንን ተከትሎ በሰበር የሚቀርቡ ጉዳዮች ለጠበቆች ወይም ለባለጉዳዮች ምቹ አሰራር እንዲኖረው ማድረግ፣

​❗️ ፍትህ የማግኘት መብት (Access to Justice) መሰረታዊ የሰብአዊ መብት ነው። ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሰበር ችሎትን ተደራሽ ማድረግ የደንበኞችን የጊዜና የገንዘብ ወጪ ከመቀነሱም በላይ፣ ጉዳዮች በአጭር ጊዜ ውሳኔ እንዲያገኙ (Right to a Speedy Trial) በማድረግ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችን በተግባር የሚተረጉም እጅግ ዘመናዊ አካሄድ መሆኑ ታምኖበታል።

​4ኛ. የሙያ ነጻነት እና የግብር/ተርን ኦቨር ታክስ (TOT) ተግዳሮቶች (Financial Autonomy & Protection of Profession)

​❗️ የጠበቆች ስራ ግብር ከደረጃ "ሐ" ወደ ደረጃ "ሀ" በመሸጋገሩ ምክንያት የመጣውን ከፍተኛ የግብር ጫና ከክልሉ ገቢዎች ቢሮ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ተግዳሮቶችን ከገንዘብ ሚንስቴር ጋር በጥናት ላይ የተመሰረተ ውይይትና መፍትሄ ፍለጋ ማድረግ እንደሚያስፈልግ እና ማህበሩ ከኋላ ሁኖ ጠበቆች በአንድ ላይ ሁነው ችግሩን ለዚህ አመት እንዲወጡ መደገፍ ማስፈለጉ ትኩረት ተሰጥቶታል።

​❗️ እንደመነሻም የህግ ሙያ እንደ ማንኛውም ተራ የንግድ ስራ (Commercial Business) ሊታይ አይገባም። ጠበቆች ህዝባዊና ህጋዊ ግዴታን የሚወጡ የፍትህ አካላት በመሆናቸው፣ በላያቸው ላይ የሚጣሉ የኢኮኖሚና የግብር ጫናዎች ህብረተሰቡ የህግ ምክርና ጥበቃ እንዳያገኝ እንቅፋት መሆን የለባቸውም።

❗️ ማህበሩ የግብር ጉዳይ በጥናት አስደግፎ ከገቢዎች ባለስልጣን ጋር ለመደራደር ማቀዱ- የግብር ግደታን ላለመውወጣት የሚደረግ ጥረት ሳይሆን- የባለሙያዎችን መብት ለማስከበርና የህግ አገልግሎት ዋጋ እንዳይንር (ተመጣጣኝ ሆኖ እንዲቀጥል) ለማድረግ የሚጥሩ የዓለም አቀፍ ማህበራት ዋነኛ ተግባር (Advocacy for the Profession) ነጸብራቅ በመሆኑ ነው።

❗️❗️​በአጠቃላይ የክልሉ ጠበቆች ማህበር የአባላቱን መብትና ጥቅም ከማስከበር ባለፈ፣ የፍትህ ሥርዓቱን ውጤታማነት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን እና የሙያ ሥነ-ምግባርን ከፍ ለማድረግ የሚተጋ ንቁ፣ ተራማጅና ተቋማዊ ራዕይ ያለው ማኅበር መሆኑን በግልጽ እንዲያሳይ ተደርጎ ለመስራት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በደብረ ብርሐን በተደረገው ውይይት ተነስቷል።

የአማራ ክልል ጠበቆች ማህበር
ደብረ ብርሃን

27/05/2026
29/04/2026
የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአማራ ክልል ጠበቆች ማህበር ጋር ዛሬ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የመወያያ አዳራሽ የጋራ ውይይት አድርጓል።⚖️     ⚖️     ⚖️  ...
29/04/2026

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአማራ ክልል ጠበቆች ማህበር ጋር ዛሬ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የመወያያ አዳራሽ የጋራ ውይይት አድርጓል።
⚖️ ⚖️ ⚖️ ⚖️ ⚖️ ⚖️

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነጻነቱን ባከበረ መንገድ የፍትህ ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ በፍትሕ ስርዓቱ ውስጥ ሚና ካላቸው ከተለያዩ አካላት ጋር በጋራ በመስራት ላይ ይገኛል። በዛሬው እለትም የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው በህግ ከተቋቋመው የክልሉ የጠበቆች ማህበር አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ፣ ጠበቆች የፍትሕ አካሉ አጋር እና በፍትሕ አገልግሎት ውጤታማነት ላይ ትልቅ ድርሻ ያላቸው ናቸው ያሉት ክቡር ፕሬዘዳንቱ፣ ጠበቆች የፍትህ ተደራሽነትን ማረጋገጥ እና የወከሏቸውን ዜጎች መብት ማስከበር ዋና ስራቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ጠበቆች በፍትሕ ተቋማት የሪፎርም ስራዎች፣ በዳኝነት እና የፍትሕ አካላት የትብብር መድረክ፣ እንዲሁም በነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት በመስጠት ትልቅ አስተዋጾ የሚኖራቸው መሆኑን አንስተዋል።

በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በህግ አስገዳጅ ሆኖ እና እራሱን እንዲያስተዳድር ተደርጎ የተቋቋመው የጠበቆች ማህበር ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራቸው ከሚገባቸው ጉዳዮች ውስጥ የጠበቆችን የሙያ ብቃት እና ስነ ምግባር ማሳደግ ግንባር ቀደሙ መሆኑን ክቡር አቶ አለምአንተ አንስተዋል። ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሆነው የክልሉ የፍትሕ እና የህግ ምርምር ኢንስቲቲዩት እና በክልሉ ከሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች ጋር በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የማህበሩ አመራሮችም ማህበሩ አዲስ እንደመሆኑ ብዙ ኃላፊነቶች የሚኖሩባቸው ቢሆንም የተሰጣቸውን ስልጣን እና ኃላፊነት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በሀገር አቀፍ ደረጃ ተምሳሌት የሆነ ተቋም እንዲሆን ለማስቻል መስራት የሚገባ ስለመሆኑ ክቡር አቶ አለም አንተ አግደው አሳስበዋል።

በዉይይቱ የተሳተፋት የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሀኑ ጎሽም በበኩላቸው፣ የጠበቆችን አዋጅ በ2017 ዓ/ም ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመሆን ማውጣት የተቻለ መሆኑን አውስተው፣ የጠበቆች ማህበር ከፍርድ ቤት እና ከፍትህ ቢሮ ጋር በመተባበር የፍትሕ ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ ሊሰራ የሚገባው መሆኑን ገልጸዋል።

የጠበቆች ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ሰለሞን ጎራው በበኩላቸው፣ የጠበቆች ማህበር በህግ በአስገዳጅ ሁኔታ እንዲቋቋም መደረጉ መልካም መሆኑን ገልጸው፣ የሙያ ስታንዳርድ እና ስነ-ምግባር በዋነኝነት የሚሰሩበት ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ጠበቆች የፍርድ ቤቶችን የዘመናዊ ዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ የለውጥ ሂደቶች ተከትለው እንዲሄዱ ማድረግ የሚገባ መሆኑን አንስተው፣ አዋጅ እንዲወጣ በማድረግም ሆነ የአመራር ምርጫ ሲካሄድ ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።

በውይይቱ የክልሉ የፍትሕ እና ህግ ኢንስቲቲዩት ፕሬዘዳንት ዶክተር ደሴ ጥላሁን፣የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራሮች እና የጠበቆች ማህበር አመራሮች ተሳትፈዋል።

ከጠበቆች ማኅበር የተሰጠ የመጀመሪያ መልዕክትክቡራትና ክቡራን፦ለአማራ ክልል ጠበቆች በሙሉለክቡር ምክትል ፕሬዚዳንት አደራው አዲሱለክቡር የሥራ አስፈጻሚ ከሚቴው ሰብሳቢ ተመስገን ሲሳይለክቡርት...
05/04/2026

ከጠበቆች ማኅበር የተሰጠ የመጀመሪያ መልዕክት
ክቡራትና ክቡራን፦
ለአማራ ክልል ጠበቆች በሙሉ
ለክቡር ምክትል ፕሬዚዳንት አደራው አዲሱ
ለክቡር የሥራ አስፈጻሚ ከሚቴው ሰብሳቢ ተመስገን ሲሳይ
ለክቡርት የሥራ አስፈጻሚ ከሚቴ ሰብሳቢዋ ጸባይ ይላቅ
መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም እኔ የአማራ ክልል ጠበቆች ማኅበር በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ በሚገኘው የብሉ ናይል ሪዞርት በክልሉ ጠበቆች ጠቅላላ ጉባኤ የማቋቋሚያ ስብሰባ በደማቅ ሥነ ሥርዓት መቋቋሙን ሳበሥር ከፍ ያለ ደስታ እየተሰማኝ ነው። የምርጫ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጨምሮ ክቡራን እንግዶችም በተገኙበት በክልሉ የፖሊስ ማርሽ ባንድ በድምቀት ጀምሯል።
የመጀመሪያ ነጥብ፦ የአማራ ክልል ጠበቆች ማኅበር በአዋጅ ቁጥር 293/2017 በክልሉ ምክር ቤት ሲቋቋም፣ በህግ የተቋቋመው የፌዴራል የጠበቆች ማኅበርን በቀጣታ ወደ ክልል ሁኔታ በመውሰድ አመራርነቱን የፕሬዚዳንታዊ ዋና ሥራ አስፈፃሚነት ሞዴል ተከትሏል። በአዋጁ አንቀጽ 65(1) መሰረትም የፕሬዝዳንቱ እና ምክትል ፕሬዝዳንቱን ስልጣንና ተግባር ሲጠቅስ "ፕሬዝዳንቱ አጠቃላይ የማኅበሩን ሥራ የሚሰራ..." በሚል ሰፊ አስተዳደራዊ ሥልጣን የሚሰጥ በመሆኑ፣ በንፅፅራዊ ሁኔታ ልክ እንደ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንታዊ አመራርን የመረጠ አስተዳደራዊ መዋቅር መሆኑን መረዳት አያዳግትም።
ሁለተኛው ነጥብ፦ በሕግ አውጭነት እና ቁጥጥር ዘርፍ ላይ የጠበቆች በጠቅላላ ጉባኤ እና በጠቅላላ ጉባኤው ስም የተሾመው 7 አባላት ያሉበት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ደግሞ ደንብ እና/ወይም መመሪያ በማውጣትና ፕሬዝዳንቶችን የሚሰሩትን አስተዳደራዊ ሥራዎችን የመቆጣጠር ሥልጣን እንዳለው አዋጁ ይደነግጋል። ኮሚቴውም ማኅበሩን በቅርበት በበላይነት ከመቆጣጠሩ በተጨማሪ የኮሚቴው ሰብሳቢዎች ጠቅላላ ጉባኤውን የሚጠሩ እና የጉባኤውም ሰብሳቤ በመሆን የሚያስተዳደር በመሆኑ ለማኅበሩ ፕሬዚዳንታዊ አመራር ሰጪነት ክትትልና ቁጥጥር መር (check and balance) መዋቅር እንዲኖረው ተደርጎ የተመሰረተ ነው። ይህ አወቃቀርም ለክልል ምክር ቤት(council) እና ቋሚ ኮሚቴ በኩል ለምክር ቤት ተጠሪ የሆኑ ተቋማትን ክትትልና ቁጥጥር የማድረግ ማስተዳደር ጋር ቅርበት ያለው የአመራር ዘይቤ ነው።
ሶስተኛው ነጥብ፦ የጠበቆች አዋጁም የሙሉነት ባሕሪ ለመያዝ በሚመስል መልኩ ከፊል የዳኝነት አካላት (quasi-judicial bodies) ያላቸውን የጠበቆች ዲስፕሊን ጉባኤ እና የጠበቆች ቦርድ በሚባሉት አካላት ውስጥ የፍትህ ቢሮ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚገኙበት ውሳኔ የሚሰጡ አስተዳደራዊ መዋቅር ይዟል። በሌላ መልኩ የጠበቆች ማኅበርም በፍርድ ቤት ዳኞች አስተዳደር፣ ዓቃቤ ሕግ ጉባኤዎች ላይ እንደመሳተፉም፣ የመንግሥት አካላት በጠበቆች ማኅበር ላይ መሳተፋቸው የጋራ አስተዳደር የተመረጠ መሆኑን እንረዳለን።
በመሆኑም ምክትል ፕሬዝዳንቱንም ጭምር በመወከል ማኅበሩ በአዋጁ የተቀመጠውን መዋቅራዊ ቅደም ተከተል እና የመዋቅር ሰንሰለት በማክበርና በማስከበር ለማኅበሩ ውጤታማ ሥራ በታታሪነትና በቅንነት እንደምንሰራ አረጋግጣለሁ። እንዲሁም የጠቅላላ ጉባኤ እና የማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በዋናነትም የኮሚቴው ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢዋ ለሥራው መሳካት የበኩላቸውን ሚና በመወጣት ለማኅበሩ ሥራ ስኬታማነት እንደሚያግዙን አልጠራጠርም።
ማኅበሩም ሥራውን በሚሰራበት ጊዜም ያለ ክልሉ ጠበቆች ንቁ ተሳትፎ የሚቻል አይሆንም። እንደሚታወቀው የጥብቅና ሙያ የተከበረ ሙያ ሲሆን፦ ከዳኝነት፣ ከዓቃቤ ሕግነት፣ ፖሊስና ሌሎች የፍትህ አካላት ልምድ ያካበቱ ጉምቱ ምሁራን ያሉበት ተቋም ነው። በመሆኑም ማኅበራችን ከአባላት ጋር በመተባበር በአማራ ክልል በሚኖረው ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያው ለውጥ ውስጥ የሕግ አወጣጥ ላይ በመሳተፍ እና ሕጎች ላይ የንቃተ ሕግ ሥራ ላይ በመሳተፍ፣ ገለልተኝቱን ሳይዘነጋ፣ የሕግ የበላይነትን ለማስፈን ያላሰለሰ ጥረት ማድረጉን ይቀጥላል። ለዚህ ዓላማም ጠበቆች የሙያ ብቃታቸውን በተከታታይነት በማሳደግ የራሳችን የሕግ ጆርናል እንዲኖረን በማድረግና በሌሎች ሕጋዊ ፎረሞች ላይ በንቃት የምንሳተፍ ይሆናል። በዚህ ሂደትም በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ ጠበቆችና ማኅበሩ በጣምራ በሚሰሩት ሙያዊ ሥራ ምክንያት፤ ጥብቅና ማህበረሰባዊ ዓይነታዊ የላቀ ተጠቃሚነትን እንደሚያመጣ እተማመናለሁ።
እንደትኩረት አቅጣጫ፣ ጠበቆች የሙያ ሥነ ምግባራቸው የሚጠይቀውን ግደታ አክብረው እስከሰራችሁ ድረስ- የሙያ ነጻነታቸው ላይ ከሚደረግ ማንኛውም ጣልቃ ገብነት እና ሕገ ወጥ ተግባርን ለመጠበቅ አጥብቀን የምንሰራ መሆኑን አረጋግጣለሁ። ሌሎች የፍትህ አካላትም ለዚህ ተግባራችን እንደሚደግፉን እምነቴ የጸና ነው።
የጠበቆች ማኅበር በሕግ አውጪው እንደአዲስ የተቋቋመ (statutorily established) ማኅበር እንደመሆኑ መጠን- የገንዘብና ቁሳዊ ድጋፍን በከፍተኛ ሁኔታ ሥራ ለመጀመር የሚፈልግበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። በመሆኑም ጉዳዩ የሚመለከታችሁ የመንግሥት አካላት፣ ተባባሪ አካላት እና የማኅበሩ አባላት ተገቢውን ድጋፍ በተቻለ ፍጥነት እንድታደርጉልን በማኅበሩ ስም ጥሪየን አቀርባለሁ። እንደምትደግፉንም እተማመናለሁ።
ክቡራትና ክቡራን ወዳጆቸ፣ የሙያ ባልደረቦቸ እና የክልል ፍትህ ተቋማት ለእኔ፣ አዲስ ለተመረጡ የማኅበሩ አመራሮች እና ለማኅበሩ ምሥረታ መልካም ምኖታችሁን ስለገለጻችሁልን ከፍተኛ ከበሬታችን በማኅበሩ ስም እገልጻለሁ።
የአማራ ክልል ጠበቆች፣ ክልል ፍትህ ቢሮ እና ማህበረሰብ ለጣላችሁብን እምነት፣ እስከ ሥራ ባልደረቦቸ፣ እጅግ አመሰግናለሁ። ለስኬታችን ቀጣይነት ባለው ድጋፍዎ ላይ እርግጠኛ ነኝ።
በአማራ ፍትህን፣ የህግ ተሟጋችነትን እና የሙያ ብቃትን ለማሳደግ እንተባበር!
አመሰግናለሁ።
ሰሎሞን ጎራው አዳነ
የአማራ ክልል ጠበቆች ማኅበር
ፕሬዝዳንት

Address

Amhara Region
Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአማራ ክልል ጠበቆች ማኅበር/ Amhara Region Bar Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share