Sidama Region Youth Association - የሲዳማ ክልል ወጣቶች ማህበር

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • Sidama Region Youth Association - የሲዳማ ክልል ወጣቶች ማህበር

Sidama Region Youth Association - የሲዳማ ክልል ወጣቶች ማህበር Official page of Sidama Region Youth Association.

“Empowering, Uniting and Inspiring Youth”

ሲዳማ ክልል ወጣቶች ማህበር 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ በሆነ ሁኔታ መካሄዱ ለሀገሪቱ የዴሞክራሲ ግንባታ ጉልህ እመርታ ያለው መሆኑን ገለፀ።የማህበሩ ፕሬዝዳንት ወጣት በቃሉ ...
03/06/2026

ሲዳማ ክልል ወጣቶች ማህበር 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ በሆነ ሁኔታ መካሄዱ ለሀገሪቱ የዴሞክራሲ ግንባታ ጉልህ እመርታ ያለው መሆኑን ገለፀ።

የማህበሩ ፕሬዝዳንት ወጣት በቃሉ መሰረት በተላለፈው መልዕክት፣ ምርጫው በሕዝብ ሰፊ ተሳትፎ፣ በሰላማዊ መንፈስ እና በሕግ የበላይነት ተከናውኖ መጠናቀቁ የዴሞክራሲ ባህል እየጎለበተ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑን አስታውቋል።

በመልዕክቱ ውስጥ ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች የሚኖራቸውን ሚና በተግባር እያሳዩ መሆናቸውን በመግለጽ፣ የሲዳማ ክልል ወጣቶች ማህበር አባላት ከክልሉ ወጣቶች ፌዴሬሽን ጋር በመቀናጀት በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ታዛቢዎችን በማሰማራት ሂደቱን በቅርበት መከታተላቸውን ጠቁመዋል።

በዚህ ተግባር ወጣቶች በምርጫ ሂደት ያላቸውን ንቁ ተሳትፎ፣ ሀገራዊ ኃላፊነት እና ለዴሞክራሲ ያላቸውን ቁርጠኝነት በግልፅ ማሳየታቸው ተገልጿል። የታዛቢዎቹ ተሳትፎም የምርጫ ሂደቱ ግልፅነትና ተዓማኒነት እንዲጠናከር አዎንታዊ አስተዋፅኦ ማበርከቱ ተጠቅሷል።

ፕሬዝዳንቱ በመጨረሻ ወጣቶች በቀጣይም በሰላም ግንባታ፣ በልማት ስራዎች እና በዴሞክራሲያዊ ሂደቶች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የክልሉንና የሀገሪቱን እድገት እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የወጣቱ ሚና ምንድን ነው?******************በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 38 ላይ የተደነገገው ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ ዜጋ ሁሉ የመምረጥ እና የ...
17/05/2026

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የወጣቱ ሚና ምንድን ነው?
******************
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 38 ላይ የተደነገገው ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ ዜጋ ሁሉ የመምረጥ እና የመመረጥ መብት እንዳለው የሚገልጸው ድንጋጌ፣ ወጣቱን ዋነኛ የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪ ያደርገዋል።

በተጨማሪም በዘር፣ በብሔር፣ በጾታ፣ በሃይማኖት ወይም በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳይደረግበት ማንኛውም ወጣት በፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ የመሳተፍ መብት አለው። በአንቀጽ 25 መሠረትም በእኩልነት የመታየት ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና ተሰጥቶታል።

ወጣቱ በምርጫ ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ እንዲችል ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ እና የመደራጀት መብቶች በአንቀጽ 29 እና 31 በቅደም ተከተል ተሰጥተውታል።

በዚህም ስለ ዕጩዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፖሊሲዎች እና አጠቃላይ ምርጫው ሀሳቡን በነፃነት ማካፈል እንዲሁም የራሱን ፓርቲ ማቋቋም ወይም የመረጠውን በነጻነት መቀላቀል ይችላል።

ከዚህም ባሻገር በአንቀጽ 41 መሠረት መንግሥት የትምህርት፣ የጤና እና የሥራ ዕድሎችን የማመቻቸት ኃላፊነት ያለበት ሲሆን፣ የተማረ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ ተሳትፎ ያለው ወጣት ደግሞ በምርጫ እና በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ላይ ይበልጥ የነቃ ሚና መጫወት ይችላል።

እነዚህ ሕገ መንግሥታዊ መብቶች የሚተገበሩበት ዋነኛው አውድ ደግሞ ምርጫ ነው። በዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ50 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የምርጫ ካርዳቸውን ወስደዋል።

ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም ዜጋ በሕግ ፊት ራሱን የቻለ፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ሰጪ እና ኃላፊነትን መውሰድ የሚችል ነው።

በኢትዮጵያ አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር ውስጥ አብዛኛውን ድርሻ የሚሸፍነው ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል ነው። በመሆኑም ወጣቱ የሀገር ተረካቢና የነገዋ ኢትዮጵያ ባለቤት ከመሆኑ አንፃር፣ የሀገራችንን ፖለቲካዊ አቅጣጫ በመወሰን ረገድ ያለው ሚና እጅግ የጎላ ነው።

ይህ የወጣቱ ሰፊ ተሳትፎ በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የዴሞክራሲያዊ መብቶች እና የዜጎች እኩልነት ማዕቀፍ ሥር በግልጽ ተረጋግጧል።

ካርድ ከወሰደው ሕዝብ ውስጥ አብዛኛውን ቁጥር የሚሸፍነው ወጣቱ ኃይል ሊገነዘበው የሚገባው ጉዳይ፣ ኃላፊነቱ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ብቻ የሚያበቃ አለመሆኑን ነው።

ወጣቱ የምርጫ ካርድ ከመውሰድ ባሻገር፣ ሕገ መንግሥቱ የሰጠውን መብት ተጠቅሞ በምርጫው ሂደት ውስጥ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅበታል።

ወጣቱ የነገዋ ሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆን የዛሬዋ ሀገር አንቀሳቃሽ ሞተር በመሆኑ፣ በምርጫው ወቅት የፖለቲካ ፓርቲዎችን አማራጮች፣ ፖሊሲዎችና ማኒፌስቶዎች በጥንቃቄ ሊከታተል ይገባል።

የትኛው ፓርቲ ለሀገር እና ለወጣቱ የተሻለ ራዕይ አለው የሚለውን በንቃት በመመዘን፣ በካርዱ የራሱን እና የሀገሩን መጻኢ ዕድል ሊወስን ግድ ይለዋል።

ወጣቱ ነገ በሚረከባት ሀገር ላይ ዛሬ በምርጫው ንቁ ተሳታፊና ውሳኔ ሰጪ መሆን ካልቻለ፣ ሌሎች በመረጡለት የፖለቲካ አቅጣጫ ተገዥ ለመሆን ይገደዳል።

በምርጫ ሂደት ውስጥ ወጣቱ ከተራ መራጭነት ባለፈ ፖለቲካዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት ማኅበረሰቡን በማስተማር ረገድ ትልቅ ኃላፊነት አለበት።

ወጣቶች ዘመኑን በመዋጀት ማኅበራዊ ሚዲያን ተጠቅመው የሰላም መልዕክቶችን በማስተላለፍ፣ ሀሰተኛ መረጃዎችን በመዋጋት እንዲሁም በቀጥታ ወደ ውሳኔ ሰጪነት ደረጃውን በማሳደግ መጻኢ ዕድላቸውን የመወሰን አቅም አላቸው።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ስሜታዊነትን አስወግደው፣ በዕውቀት እና በሰላማዊ መንገድ ይህንን ድርብ ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ምርጫው የልማትና የዕድገት መሠረት ይሆናል።

ስለሆነም ወጣቱ በቀጣዩ ጠቅላላ ምርጫ፣ ከራሱ ዓላማ እና ራዕይ ጋር የሚሄደው ፓርቲ የትኛው ነው? የሚለውን በአእምሮው ይዞ፣ ሕገ መንግሥታዊ መብቱን በመጠቀም እንዲሁም የፖለቲካ አማራጮችን በማመዛዘን ድምፁን ለነገዋ ኢትዮጵያ በነቂስ ወጥቶ ሊሰጥ ይገባል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የትውልድን የተሻለ መፃኢ እጣ ፋንታ የሚወስን ወሳኝ መድረክ ነው አዲስ አበባ፤ ግንቦት 1/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የትውልድን የተሻለ መፃኢ እ...
10/05/2026

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የትውልድን የተሻለ መፃኢ እጣ ፋንታ የሚወስን ወሳኝ መድረክ ነው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 1/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የትውልድን የተሻለ መፃኢ እጣ ፋንታ የሚወስን ወሳኝ የጋራ መድረክ መሆኑ ተገለጸ።

ወጣቶች በሀገራዊ ምክክር ዋና ጉባኤ ሀገራዊ መግባባትን በሚፈጥሩ የመፍትሔ ሃሳቦች ላይ ግንባር ቀደም ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በኢትዮጵያ ለዘመናት የቆዩ የልዩነት ሃሳቦችን በምክክር በመፍታት በሃሳብ የበላይነት የሚያምን ትውልድ ለመፍጠር ሀገራዊ ምክክር አዲስ ምዕራፍ ጀምሯል።

በሁሉም ክልሎች፣ በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮችና በውጭ ከሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችና አደረጃጀቶች የአጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታ በስኬት ተጠናቋል።

በዚህም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታ ማጠናቀቁን ተከትሎ ዋናውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ የመጨረሻ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

የክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ ሀገራዊ ምክክሩ በኢትዮጵያ ብሔራዊ መግባባትን በማስፈን ዘላቂ ሰላምና አንድነትን ለማምጣት ወሳኝ መድረክ ነው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የፈጠረውን ዕድልም በታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና መሰል ጉዳዮች በሚስተዋሉ ዋና ዋና ሀገራዊ የሃሳብ ልዮነቶች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ኮሚሽነር ማርቆስ ማቲዎስ፤ ሀገራዊ ምክክር ጠንካራ ሀገረ መንግስት መገንቢያ መሳሪያ ነው ብለዋል።

ወጣቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችም ሀገራዊ ምክክር የፈጠረውን ዕድል በመጠቀም የኢትዮጵያን መፃኢ እጣፋንታ የተሻለ ለማድረግ በትብብር መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የሲዳማ ክልል ወጣቶች ማኅበር ፕሬዝዳት በቃሉ መሰረት፤ በክልሉ የሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ ሥራዎች ላይ በንቃት መሳተፋቸውን አስታውሷል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክርም በዜጎች መካከል ብሔራዊ መግባባትን በመፍጠር ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጿል።

በቀጣይም ዋናውን ሀገራዊ ምክክር በማካሄድ ሂደት ገንቢ ሚና እንደሚወጡ ተናግረዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሱልጣን አሊ፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የትውልድን መፃኢ እጣ ፋንታ የሚወስን ወሳኝ መድረክ ነው ብለዋል።

በዚህም በሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታ ሂደት ወጣቶች ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል።

በቀጣይም ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሚካሄድበት ወቅት ወጣቶች ገንቢ ሚና እንዲወጡ ለማስቻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስራ አሰሪ እና ሰራተኛ መምሪያ ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለሀዋሳ ከተማ ወጣቶች የስራ ፈጠራ እና የልቦና ውቅር (Mindset) ስልጠና ተሰጠ።ስልጠናው ወጣ...
09/05/2026

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስራ አሰሪ እና ሰራተኛ መምሪያ ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለሀዋሳ ከተማ ወጣቶች የስራ ፈጠራ እና የልቦና ውቅር (Mindset) ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናው ወጣቶች በስራ ፈጠራ ዘርፍ የተሻለ አቅም እንዲገነቡ፣ የንግግር እና የተግባቦት እንዲያሳድጉ፣ በራሳቸው የመተማመን ስሜት እንዲያዳብሩ እና ለስራ ዓለም የሚያስፈልጉ አመለካከቶችን እንዲያጎለብቱ ታልሞ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በተለይም የራስ አቅምን አውቆ እና አጎልብቶ የበቃ የስራ ፈጠራ፣ የንግድ ሀሳብ ማመንጨት፣ የቡድን ስራ ክህሎት እና አዎንታዊ የአስተሳሰብ ግንባታ መፍጠር ላይ ትኩረት ተሰጥቶበታል።

በዚሁ ወቅት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስራ አሰሪ እና ሰራተኛ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሽታ ኤቢሶ እንደገለፁት፣ ወጣቶችን በክህሎት እና በአመለካከት ማብቃት የስራ እድል ፈጠራን ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ እንደዚህ ያሉ ስልጠናዎች ወጣቶች ራሳቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲያዩ እና ከስራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል።

አቶ ሽታ አክለውም መምሪያው ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመስራት ወጣቶችን በኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ለማበረታታት እና የራስ ስራ እንዲፈጥሩ የሚያግዙ ፕሮግራሞችን በቀጣይነት እንደሚያስፋፋ ገልፀዋል።

በስልጠናው የተሳተፉ ወጣቶች በበኩላቸው ያገኙት ዕውቀትና ተሞክሮ በቀጣይ ህይወታቸው እና በስራ መስካቸው ጠቃሚ እንደሚሆን ገልፀው፣ እንደዚህ ያሉ ስልጠናዎች በተከታታይነት መሰጠታቸው ለወጣቶች የተሻለ ተስፋ እና አቅጣጫ እንደሚፈጥር አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የተሰጠው ስልጠና ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በተገኘ ድጋፍ የሚተገበረው “የኛ ጊዜ” ፕሮጀክት አካል ሲሆን፣ ስልጠናው በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ እና በገርልስ ኢፌክት ትብብር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

ለምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒነት የሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀቶች የድርሻቸውን ይወጣሉሀዋሳ፤ ሚያዚያ 30/2018(ኢዜአ)፡-ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ በስኬ...
08/05/2026

ለምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒነት የሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀቶች የድርሻቸውን ይወጣሉ

ሀዋሳ፤ ሚያዚያ 30/2018(ኢዜአ)፡-

ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ አባሎቻቸው የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን የሲዳማ ክልል የሴቶች እና የወጣቶች አደረጃጀቶች ገለጹ።
ኢዜአ በሀዋሳ ከተማ ያነጋገራቸው የክልሉ የወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶች እንደገለጹት ከቅድመ ምርጫው ጀምሮ በተለያየ መንገድ ተሳትፏቸውን ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወኑ ነው፡፡

የክልሉ ወጣቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ወጣት በቃሉ መሰረት እንዳለው ወጣቱ በምርጫው ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ ድምጹን ለፈለገው ፓርቲ እንዲሰጥና ለምርጫው ስኬታማነት የበኩሉን እንዲወጣ ሲሰራ ቆይቷል።

በዚህም በክልሉ የማህበሩ አባል የሆኑ ወጣቶች በምርጫው መሳተፍ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ በወቅቱ እንዲወስዱ መደረጉን ገልጿል።

የምርጫ ካርድ መውሰድ ብቻ በቂ አይደለም ያለው ወጣት በቃሉ፣ በድምጽ መስጫው እለትም ድምጻቸውን በነጻነት መስጠት እንዲችሉ የማስገንዘብ ሥራ መሰራቱን ተናግሯል።

ህብረተሰቡ በምርጫው ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ወጣቶች የመቀስቀስና የማስተማር ሥራ ከመስራቱ ባለፈ ለምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒነት የበኩሉን እንዲወጣ የማስገንዘብ ስራም መከናወኑን አመልክተዋል።

የክልሉ ሴቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ገነት ማርቆስ በበኩላቸው እንዳሉት የክልሉ ሴቶች በምርጫው በንቃት እንዲሳተፉ ለማድረግ በተሰጠው የግንዛቤ ስልጠና በርካቶች ለመራጭነት ብቁ የሚያደርጋቸውን ካርድ ወስደዋል።

ከዚህ ባለፈ ፌዴሬሽኑን ወክለው በታዛቢነት የሚያገለግሉ 65 ሴቶችን በመመልመል ከኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ጋር በትብብር ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉን ጠቁመዋል።

ሴቶች በቤተሰብ ውስጥ ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው ያነሱት ወይዘሮ ገነት፣ ለምርጫው አሳታፊነትና ሰላማዊነት ወጣቶች የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ከቤተሰብ ጀምሮ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ የማስገንዘብ ስራ መሰራቱንም ተናግረዋል።

የክልሉ ወጣቶች ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ወጣት ጋማርሳ ዲዳ እንዳለው፣ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ እስከ ወረዳ ባሉ የወጣት አደረጃጀቶች በቅንጅት እየተሰራ ነው።

ወጣቱ በምርጫው ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ለመራጭነት የሚያበቃውን ካርድ እንዲወስድ ተደርጓል ያለው ፕሬዚዳንቱ፣ በካርዱም ይበጀኛል የሚለውን ለመምረጥ ዝግጅት እንዲያደርግ የማስገንዘብ ሥራ መሰራቱን ተናግሯል።

ለበለጠ መረጃ
https://www.ena.et/web/amh/w/amh_8800074

02/05/2026
የሲዳማ ክልል ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የወጣት አደረጃጀቶች ፎረም ውይይት ተካሄደየሲዳማ ክልል ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በወጣቶች አደረጃጀቶች አቅም ማጠናከርና በሀገራዊ...
23/04/2026

የሲዳማ ክልል ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የወጣት አደረጃጀቶች ፎረም ውይይት ተካሄደ

የሲዳማ ክልል ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በወጣቶች አደረጃጀቶች አቅም ማጠናከርና በሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ውስጥ የወጣቶች ተሳትፎ ማሳደግ ዓላማ በማድረግ የፎረም ውይይት አካሂዷል።

የፎረሙን ውይይት የመሩት የቢሮው ም/ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደስታ ለገሰ ሲሆኑ፣ በንግግራቸው ወጣቶች በዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ የሀገር ልማትና ሰላም መሠረት መሆኑን ገልጸዋል።

በፎረሙ ላይ የተነሱ አጀንዳዎች በተለይም በሰባተኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ዙሪያ በስፋት ውይይት ተደርጓል፤ ውይይቱም ወጣቶች በምርጫ ቀን ብቻ ሳይሆን ከምርጫ ቀድሞ የሚካሄዱ ዝግጅቶች እና ከምርጫ በኋላ የሚከተሉ ሂደቶች ላይ ንቁ ሚና እንዲወስዱ አስፈላጊነቱ ተገልጿል።

ወጣቶች በምርጫ ቀድሞ የሚካሄዱ የምርጫ ምዝገባ ላይ ያሳዩትን ተሳትፎ በምርጫ ቀን ሰላማዊና ህጋዊ ሂደት እንዲጠበቅ በንቃት መሳተፍ እና ሁኔታዎችን በሰላማዊ መንገድ ማስተካከል
በድህረ ምርጫ ወቅት ባሉ ጊዜያት ሰላምን በማጠናከር ረገድ ሚናቸዉን መወጣት እንዲችሉ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ተጨማሪም የወጣቶች አደረጃጀቶች መደበኛ ስራዎች በተደራጀ መልኩ እንዲከናወኑ በአባልነት ማጠናከር፣ በአመራር ብቃት ማሻሻል፣ የፕሮግራም እቅድ እና ክትትል ስርዓት ማበረታታት እንዲሁም ከተለያዩ አጋሮች ጋር ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ በውይይቱ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳቦችን እና ተሞክሮዎችን በመጋራት ወጣቶች በሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ውስጥ አግባብ ያለ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚያግዙ የተግባር አቅጣጫዎችን አቅርበዋል።

ፎረሙ በመጨረሻ የወጣቶች አደረጃጀቶች በተቀናጀና በተጠናከረ መልኩ እንዲሰሩ እና በሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ውስጥ የሚገባ ድርሻ እንዲወስዱ አጠቃላይ ግብዓቶችን በማስቀመጥ ተጠናቋል።

12/04/2026
11/04/2026
ውድ የሲዳማ ክልል ወጣቶች እና መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የትንሣኤ በዓል የአዲስ ጅምር፣ የተስፋ እና የድል ምልክት ሲሆን ይህ በዓል በ...
11/04/2026

ውድ የሲዳማ ክልል ወጣቶች እና መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የትንሣኤ በዓል የአዲስ ጅምር፣ የተስፋ እና የድል ምልክት ሲሆን ይህ በዓል በተለይም ለወጣቶች አዲስ እድሎችን ለመፍጠር፣ በፈጠራ ሀሳብ ለመንቀሳቀስ እና ለማህበረሰብ ልማት ተግባራዊ ሚና ለመወጣት የሚያነሳሳ መንፈሳዊ እሴት አለው።

በዚህ የትንሣኤ ወቅት ወጣቶች የሰላም፣ የአንድነት እና የመተሳሰብ እሴቶችን በማጠናከር ለማህበረሰባችን ተስፋ የሚሆኑ ተግባራትን እንድንፈጽም፤ ወጣቶች የዛሬ ኃይል እና የነገ ተስፋ እንደመሆናችን በሰላም ግንባታ፣ በልማት ስራዎች እና በማህበራዊ አብሮነት ውስጥ ያለንን ሚና እንድንወጣ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ይህ የትንሣኤ በዓል ለሁላችን አዲስ ተስፋ፣ ሰላም፣ ፍቅር እና ስኬት ያምጣልን። በአንድነት ቆመን የክልላችንን እና የሀገራችንን ብሩህ ተስፋ ወደፊት እንገንባ።

እንኳን አደረሳችሁ!
መልካም የትንሣኤ በዓል!

ወጣት በቃሉ መሠረት
የሲዳማ ክልል ወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት

Address

Awassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidama Region Youth Association - የሲዳማ ክልል ወጣቶች ማህበር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share