Penal Reform Ethiopia _ፔናል ሪፎርም ኢትዮጵያ

Penal Reform Ethiopia _ፔናል ሪፎርም ኢትዮጵያ Penal Reform Ethiopia is a non governmental organization which works on prisoners rehabilitation and reintegration in Ethiopia

23/04/2025

It is with great sadness that we inform you of the passing of Dr. Comdr. Demelash Kassaye an Associate Professor at the School of Social Work of Addis Ababa University.

Dr. Demelash dedicated over 15 years to education, profoundly shaping the lives of many students. His funeral was held today, April 23, at Jamo Trinity Church - Alem Bank.

Amongst other prominent roles, Dr. Demelash served as Managing Director of the former Akaki Campus of AAU, as the Graduate Program Coordinator and the Head of the School of Social Work, and served as Chairman of the Ethiopian Police Doctrine.

His funeral was held today, April 23, at Jamo Trinity Church - Alem Bank.
We at Addis Ababa University extend our heartfelt condolences to his family, friends, colleagues and students.

May his soul rest in eternal peace.

23/04/2025
የሐዘን መግለጫ😭😭😭😭😭😭😭የድርጅታችን ፔናል ሪፎርም ኢትዮጵያ የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት ዶክተር ኮማንደር ደመላሽ ካሳዬ ድንገት በደረሰባቸው አደጋ ሚያዝያ 15ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በ...
23/04/2025

የሐዘን መግለጫ
😭😭😭😭😭😭😭
የድርጅታችን ፔናል ሪፎርም ኢትዮጵያ የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት ዶክተር ኮማንደር ደመላሽ ካሳዬ ድንገት በደረሰባቸው አደጋ ሚያዝያ 15ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ዶክተር ኮማንደር ደመላሽ ካሳዬ ከድርጅታችን ምስረታ ጀምሮ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ትልቅ ምሁር ነበሩ።

የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸውም ሚያዝያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት አለም ባንክ ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ተፈፅማል፡፡

ፔናል ሪፎርም ኢትዮጵያ በዶክተር ኮማንደር ደመላሽ ካሳዬ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል።
ሚያዝያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

የድርጅታችን ፔናል ሪፎርም ኢትዮጵያ  ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር  ፍፁም መሠረት ወላጅ እናት ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው በትላንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በስጋ ተለ...
22/02/2025

የድርጅታችን ፔናል ሪፎርም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር ፍፁም መሠረት ወላጅ እናት ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው በትላንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በስጋ ተለይተዋል። ደግ እና ሩህሩህ እናታችንን በማጣታችን ጥልቅ ሀዘን የተሰማን ሲሆን ልዑል እግዝአብሔር ለወንድማችን እና ለቤተሰቡ መፅናናት አንዲሰጥልን እየተመኘን የደጓ እናታችንን ነፍስ በአፀደገነት ያኑርልን።
#ስርዐተ ቀብር
ቅዳሜ የካቲት 15/2017ዓ.ም ከቀኑ 8:00 በሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ቤተክርስቲያን ስርዐተ ቀብር ይፈፀማል።
ነፍስ ይማር!!

አርባምንጭ  ዴሪክ ሆቴልጥር 27-30/2017ዓ.ምፔናል ሪፎርም ኢትዮጵያ ከአለም አቀፉ የህፃናት አድን ድርጅት(Save the Children International) ጋር በመተባበር በደቡብ ኢት...
10/02/2025

አርባምንጭ ዴሪክ ሆቴል
ጥር 27-30/2017ዓ.ም

ፔናል ሪፎርም ኢትዮጵያ ከአለም አቀፉ የህፃናት አድን ድርጅት(Save the Children International) ጋር በመተባበር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ኮሚሽን እና በስሩ ለሚገኙ ተቋማት ለተውጣጡ ለማረምና ማነፅ ባለሙያዎች፤ የ1ኛ ደረጃ ት/ት ቤት ርዕሰ መምህራን እና የጤና ክሊኒክ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች የጉዳይ አያያዝ እና የህፃናት ጥበቃ(Case Management & Child Protection) ስልጠና ከጥር 27--30/2017ዓ.ም በአርባምንጭ ከተማ ዴሪክ ሆቴል ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው መክፈቻ የ Save the Children ተወካይ አቶ ጋሻው ሙሉጌታ ስለተቋሙ እንዲሁም ለስልጠናው ድጋፍ ስላበረከተው "Education & Child Protection" ፕሮጀክት አጠቃላይ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ስለስልጠናው ፋይዳ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የፔናል ሪፎርም ኢትዮጵያ ፋ/አስ/ር ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ጌታሁን በበኩላቸው ተቋሙ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በታራሚዎች ሰብአዊ መብት አያያዝ እንዲሁም የማረምና ማነፅ ስርዐት እንዲሻሻል የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ እና ከዚህ ቀደም ለአራት ማረሚያ ተቋማት ከ3 ሚሊዬን ብር በላይ የሚገመት የሴቶችና ህፃናት የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በተጨማሪም ለዲላ ማረሚያ ተመሳሳይ የጉዳይ አያያዝ ስልጠና መስጠታቸውን በመግለፅ አሁንም ስልጠናው ከዚህ አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስረድተዋል። ለስልጠናው መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተውን Save the Children Ethiopia ምስጋና በማቅረብ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።
የተዘጋጀውን ስልጠና የደቡብ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት አርባምንጭ ቅርንጫፍ በቦታው ተገኝቶ የሚዲያ ሽፋን ሰጥቷል::

ጥር 2017ዓ.ም
አርባምንጭ ኢትዮጵያ

06/02/2025
06/01/2025
አርባምንጭ  #2ፔናል ሪፎርም ኢትዮጵያ ከዓለምአቀፉ የህፃናት አድን ድርጅት(Save the Children) ጋር በመተባበር በደቡብ ኢትዮጵያ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በአርባምንጭ ማረሚያ ተቋም በመ...
05/01/2025

አርባምንጭ #2
ፔናል ሪፎርም ኢትዮጵያ ከዓለምአቀፉ የህፃናት አድን ድርጅት(Save the Children) ጋር በመተባበር በደቡብ ኢትዮጵያ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በአርባምንጭ ማረሚያ ተቋም በመታረም ላይ ለሚገኙ ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሴት የህግ ታራሚዎች እንዲሁም በቀጣይ ሁለት ዓመታት የሚገቡትን ታሳቢ በማድረግ በአጠቃላይ ለ500 ሴቶች ከሁለት እስከ ሶስት ዓመት የሚበቃቸውን የንፅህና መጠበቂያ ሪዩዘብል ሞዴስ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን አስመልክቶ ከፔናል ሪፎርም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር ፍፁም መሠረት እንደተናገሩት ከአጋር ተቋማት ጋር በትብብር በመስራት በታራሚዎች በማረምና ማነፅ እና መልሶ መቀላቀል ተግባራት እንዲሁም የሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ማረሚያ ተቋማትን በመደገፍ በትኩረት ለመስራት ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል ።

ከሴቭ ዘ ችልድረን የህፃናት ድጋፍ ፕሮግራም ማናጀር አቶ ጋሻው ሙሉጌታ በበኩላቸው በአርባምንጭ ማረሚያ ተቋም የማረምና ማነፅ ተግባራትን በመዘዋወር ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በቀጣይነትም በሴቶችና ህፃናት እንዲሁም በትምህርት ላይ የተጠናከረ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
የአርባመምንጭ ማረሚያ ተቋም ሃላፊ ኮማንደር ዓለሙ ኬንቶ ድጋፉን ላበረከቱ አካላት በተቋሙና በህግ ታራሚዎች ስም ልባዊ ምስጋና በማቅረብ አመስግነዋል።

በዕለቱም የፔናል ሪፎርም የፋይናንስና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ጌታሁን እንደገለፁት ለጨንቻ ማረሚያ የተበረከተው የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ 300,000 ብር የፈጀ እንደሆነ እና ስርጭቱን በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው ለዚህም በድርጅቱ በኩል የቅርብ ክትትልና ግምገማ እንደሚደረግ ገልፀዋል።
ታህሳስ 2017 ዓ.ም
አርባምንጭ ኢትዮጵያ

Address

Woldeamanuel Godana
Awassa

Telephone

+251911755863

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Penal Reform Ethiopia _ፔናል ሪፎርም ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Penal Reform Ethiopia _ፔናል ሪፎርም ኢትዮጵያ:

Share