08/11/2025
የሲዳማ ክልል ፕሬዚዳንት ለመሆን ለኢትዮጵያ ሪፐብሊክ መንግስት ልዩ መልዕክተኛ እና በጋና የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት አምባሳደር ተፈሪ ፍቅሬ ጎሳዬ በልዩ ትኩረት ከምርጫ ጋር ተያይዞ እና በክልሉ የነበረው መንግሥታዊ ሌብነት እና ውብድናን በመከታተል ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ የፌደራል መንግስት እያሳሰቡ ይገኛል።
የቀድሞ የሲዳማ ዞን የኮሚንኬሽን ሃላፊ፥ የሀዋሳ ማዘጋጃ ሃላፊ፥ የኤጀንሲዎች ሃላፊ፥ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስቴር በመሆን የሲዳማ ክልል ተወካይ በመሆን የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በመሆን ያገለገሉት አምሳደር ተፈሪ ፍቅሬ ወደ ሲዳማ ክልል በፕሬዝዳንትነት ሊመጡ እንደሆነ ታውቋል።
በቀጣይነትም በክልሉ የፖርቲ ኋላፊነት ሊመደቡ ዝርዝር ውስጥ ካሉት የኋላእሸት በቀለ፥ ዘነበ ገዳ፥ ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ ኦረንቴሽን እየተሰጣቸው ይገኛል።
በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ሆነው ተመድበው በክልል አመራር የተመሩ የመሬቶችን መረጃ እንዳይጠፋ ትዕዛዝ በተሰጣቸው ተልዕኮ መሰረት ትላንት ወደ ሀዋሳ ገብተዋል።
የመሬት አስተዳደር መምሪያ ሃላፊ ተደርገው የተሾሙት የደስታ ሌዳሞ እና የአብርሃም ማርሻሎ የመሬት አዳይ እና መረጃ ሰዋሪው አቶ ገዛሃኝ አርስቻ የሁለቱ የተመሩ ህገወጥ የመሬት ምሪቶችን ወደ ካዳስተር በመቀየር ህጋዊ ለማድረግ ቢሮ ውስጥ እያደረ ይገኛል።
አምባሳደር ተፈሪ ፍቅሬ ጎሳዬ የሲዳማ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው ሊሾሙ ነው!!!