26/05/2026
መንዝ ጓሳ
መንዝ ጓሳ ከደብረ ብርሃን 152 ኪ.ሜ ከመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ዋና ከተማ መሃል ሜዳ 18 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ የማህበረሰብ አቀፍ ጥብቅ ስፍራ ነው፡፡ ጥብቅ ስፍራው ስያሜውን ያገኘው በአካባቢው በብዛት ከሚበቅለው የጓሳ ሳር ሲሆን በውስጡም ቀይ ቀበሮ እና ጭላዳ ዝንጀሮን ጨምሮ የተለያዩ የዱር እንሰሳት፣ 14 የሚሆኑ ብርቅዬ አዕዋፍት እና በዛ ያሉ የዕፅዋት ዝርያዎችን ይገኙበታል፡፡
ድንቅ መልክዓ ምድራዊ ገጽታ ያለው የመንዝ ጓሳ ጥብቅ ስፍራ ብዝሃ ሕይወት ሀብት ከ400 ዓመታት በላይ የተጠበቀው እና ዛሬን የደረሰው በአካባቢው ማህበረሰብ ነው፡፡ ማህበረሰቡ አካባቢውን ከመጠበቅ ባሻገር ጎብኝዎችን የሚያስተናግድ የማህበረሰብ ሎጅ በጥብቅ ስፍራው ያለው ሲሆን ለእንግዶች ተወዳጅ ባህላዊ ምግቦች በማቅረብ ይታወቃል፡፡