20/07/2026
ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተከናወነ።
አርባ ምንጭ ፦ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት)፦
በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ደጋ ኦቾሎ ቀበሌ ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተከናውኗል።
አቶ ገዛኸኝ ጋሞ የጋሞ ዞን ዋና የመንግሥት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ አቶ ማጌሶ ማሾሌ የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ፣ አቶ አበበ ፔዣ የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መርዶክዮስ ከርባ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ፣ አቶ መኮንን ተስፋዬ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም ፎካል ፐርሰን እንዲሁም በቀበሌው በኩታ ገጠም የተደራጁ አርሶአደሮች ተሳታፊ ሆነዋል።
በወረዳው ብሔራዊ አቮካዶ ልማት ፕሮግራም በአራት ቀበሌያት በ 8 ክላስተር ለተደራጁ ለ240 አርሶ አደሮች በእያንዳንዱ ግለሰብ 20 እግር የተሻሻለ የሀስ የአቮካዶ ዝርያ ተከላ እንደሚደረግ ተገልጿል።
ቀበሌያቱም ደጋ ኦቾሎ፣ ጋንታ መይጨ፣ ደጋ ሻራ እና ደጋ ጨንጌ መሆናቸው ተብራርቷል።
በዛሬው ዕለትም በደጋ ኦቾሎ ቀበሌ 1,200 የሀስ የአቮካዶ ዝርያ ችግኝ ተከላ በተመረጡ 60 አርሶአደር ማሳ ላይ በኩታ ገጠም ተተክሏል።