የእግዚአብሔር አብ ልጆች የተራራው ሥር ምርጦች

የእግዚአብሔር አብ ልጆች የተራራው ሥር ምርጦች It is not a private profit or business making. It is for social religious service.

The purpose is coordinating to contribute our part to construct the church on the indicated place together

የልዑል እግዚአብሔር አብ ወዳጁና ሙሉ ሕይወቱን ለእርሱ ሰጠሁኝ ያለው ወንድማችን ይስሃቅ ማጮ ሕንጻውን እስከፍጻሜው አብረን እንሠራለን በማለት ከዚህ በፊትም እየተሣተፈ ቢቆይም አሁንም ብር 1...
22/01/2026

የልዑል እግዚአብሔር አብ ወዳጁና ሙሉ ሕይወቱን ለእርሱ ሰጠሁኝ ያለው ወንድማችን ይስሃቅ ማጮ ሕንጻውን እስከፍጻሜው አብረን እንሠራለን በማለት ከዚህ በፊትም እየተሣተፈ ቢቆይም አሁንም ብር 10,000(አሥር ሺህ ብር) ሠጥቶናል ።
ሌሎች አጋሮቻችንንም በቅደም ተከተል እናደርሳለን ፤
ሃሳብ አስተያየታችሁ እጅጉን ይጠቅመናል ጻፉልን ።

እግዚአብሔር አብ በወጣ ይተካልን ፤
በረከት ቸርነቱን ያድልልን ።

✝️የተከበራችሁ የእግዚአብሔር አብ ልጆች ፤ የተራራው ሥር ምርጦች እንደምን ቆያችሁ?✝️❤እንኳንለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስትቶስ ልደት (2018) በሰላም አደረሰን !!!እነሆ ለዚ...
06/01/2026

✝️የተከበራችሁ የእግዚአብሔር አብ ልጆች ፤ የተራራው ሥር ምርጦች እንደምን ቆያችሁ?✝️
❤እንኳንለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስትቶስ ልደት (2018) በሰላም አደረሰን !!!
እነሆ ለዚህ ያደረሰን ልዑል እግዚአብሔር የተመሠገነ ይሁን !!!
አሜን !!!

ዛሬም ደግሞ ልዑል እግዚአብሔር ያስጀመረውን ሕንጻ ቤ/ቤያን እስከዚህ አድርሶልናልና ክብርና ምስጋና ለርሱ ይሁን !!!
አሜን !!!

እነሆ ደግሞ ለፍጻሜ ሥራዎች በየከተማው ካሉ ወንድምና እህቶቻችን ጋር አብረን መወያየት አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ በቅድሚያ አ/ምንጭ ካሉ ወገኖቻችን ጋር ለመወያየት ጥር 2/2018 ዓ.ም ከጧቱ በ3:00 ሰዓት አ/ምንጭ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ያን ቅጥር ግቢ ለመገናኘት የቤ/ያኒቱ ካህናት ፣ ሕንጻ አሠሪና ሰበካ ኮሚቴ እንዲሁም የተለያዪ የቤ/ያኒቱ አመራሮች ቀጠሮ ስለያዙ አ/ምንጭ ከተማ ላይ የምትገኙ ወገኖቻችን ባለመቅረት በተባለው ቦታ እንድንገናኝ መልካም ፍቃዱ ይሁንልን እያልን፦

በተቻለ መጠን ከታች በምስሉ ላይ የተለጠፈውን የጥሪ ደብዳቤ ለማዳረስ ጥረት እያደረግን መሆኑን በመገንዘብ ለመልዕክቱ መዳረስ ስልክ በመደዋወልና ይህንን መረጃ ሁላችሁም ሼር በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃችኋለን !!!

እርሱ ልዑል እግዚአብሔር መልካም ፍቃዱ ሆኖ ሁላችንንም ለሕንጻው ፍጻሜ ያድርሰን !!!
አሜን !!!

ሼር አይረሳ

21/12/2025

ለአዳዲሶቹ ዋና አድናቂዎቼ ታላቅ ምስጋና! Mekdi Chora

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜንየልዑል እግዚአብሔር አብ ልጆች የተራራው ሥር ምርጦች እንደምን ከረማችሁ?እርሱ እግዚአብሔር ዛሬም ለዘለዓለሙ የከበረና የተመሠገነ ይሁን!...
03/08/2025

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
የልዑል እግዚአብሔር አብ ልጆች የተራራው ሥር ምርጦች እንደምን ከረማችሁ?
እርሱ እግዚአብሔር ዛሬም ለዘለዓለሙ የከበረና የተመሠገነ ይሁን!
አሜን!!!
አነሆ በእርሱ መልካም ፍቃድ ይሄው እስከዚህ ደርሰናል እርሱ ለዘለዓለሙ የተመሠገነ ይሁን ።
እስከዚህ ድረስ ጊዜያችንን እርሱ ፈቅዶ በዚህ ሕንጻ ሥራ ላይ በረከቱን ለማግኘት የተጋችሁ ፦

✝️ በመላው ዓለማችን የምትገኙ ወገኖቻችን ፥ አባት እናቶቻችን ፥ ወንድም እህቶቻችን፤
✝️ በሀገራችን በተለያዩ ከተሞች የምትኖሩ፤
✝️ በተለይም በአዲስ አበባ የምትገኙ
✝️ በአዲስ አበባ ዙርያ (ሸገር ከተማ)የምትኖሩ
✝️ በደብሩ አቅራቢያ ክልል እና በመሣሠሉ ቦታዎች እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ሕይወታችሁን የምትመሩና ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ ሳትታክቱ የምትተጉ ወገኖቻችን ሁሉ፦

ልዑል እግዚአብሔር አብ ከሃጢአት በቀር የልብ መሻታችሁን መልካም ፍቃዱ ሆኖ እንዲሞላላችሁና ከታች በተለጠፈው ፖስተር እንደተመለከተው ቀሪ ሥራዎች ስለሚኖሩን ለነዚህ ሥራዎች እንዲያነሳሳን መልካም ፍቃዱ ይሁንልን!
አሜን!!!

✞🇪🇹እንኳን ለደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ🇪🇹✞✞🇪🇹የልዑል የእግዚአብሔር አብ ቤተሰቦች ሆይ🇪🇹✞✞🇪🇹በያላችሁበት ሁሉ እግዚአብሔር ይጠብቃችሁ🇪🇹✞ቀደም ሲል የነሃሴ 26/2016 ቱን መንፈሳ...
18/08/2024

✞🇪🇹እንኳን ለደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ🇪🇹✞

✞🇪🇹የልዑል የእግዚአብሔር አብ ቤተሰቦች ሆይ🇪🇹✞

✞🇪🇹በያላችሁበት ሁሉ እግዚአብሔር ይጠብቃችሁ🇪🇹✞

ቀደም ሲል የነሃሴ 26/2016 ቱን መንፈሳዊ ጉዞ በዚሁ በቤ/ያናችን ገጽ ለጥፈን ማሳወቃችን ይታወቃል።

ፖስቱን ሼር በማድረግ ላጋራችሁ ሁሉ የእዚአብሔር አብ በረከቱ እንዲደርሳችሁ ከልብ እንመኛለን። በእጅጉም እናመሠግናለን።

እነሆ አሁንም ደግሞ ደብራችን እንደ እንግዳ ተቀባይ ይህንን ታላቅ መንፈሳዊ ፕሮግራም "ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ" በማለት ክርስቲያን ወገኖቻችን ዕለቱን በጉጉት በመጠበቅ በጥሪው መሠረት ተገኝታችሁ በረከቱን ለማግኘት የበለጠ አስታውሳችሁ እንድትዘጋጁ ጥሪያችንን በልዑል እግዚአብሔር አብ ስም በድጋሚ እናስተላልፋለን።

የልዑል እግዚአብሔር አብ በረከቱና ቸርነቱ ከሁላችን ጋር ይሁን ።
አሜን!!!!!!!!

አሜን! እያላችሁ ===ኮሜንት=== ሼር==አርጋችሁ እንድታሰራጩ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!የተከበራችሁ ወገኖቻችን ሁሉ እንደምን ቆያችሁ?በያላችሁበት ሁሉ ልዑል እግዚአብሔር አ...
05/08/2024

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!
የተከበራችሁ ወገኖቻችን ሁሉ እንደምን ቆያችሁ?
በያላችሁበት ሁሉ ልዑል እግዚአብሔር አብ መልካም ፈቃዱ ሆኖ ሰላማቾሁን ያብዛው።

እነሆ ወዶና ፈቅዶ ለሕንጻ ሥራ ያነሳሳን ፈጣሪያችን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ዛሬ ደግሞ የሕንጻ ሥራውን እስከዚህ አድርሶልናል።

ለቀሪ ሥራው ደግሞ እስከፍፃሜው በመልካም ፍቃዱ ረድቶን ቤቱ ተጠናቆ በዓይናችን እንድናይና በዉስጡ እንድናስቀድስበት እርሱ ይርዳን አሜን!!!

ደግሞም የሕንጻ ሥራውን በመርዳት በረከት ያገኙ ዘንድ ቅዱሳን ማህበራትንም በመልካም ፈቃዱ አነሳስቶ ወደ ቤ/ያናችን መንፈሳዊ ጉዞ በቀን 26/12/2016 ያደርጉ ዘንድ ጠርቶልናልና ክብርና ምስጋና ለርሱ ለዘለዓለሙ ይሁን ።

ስለዚህ ሁላችሁም ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር አብ ልጆች ሆይ፦
በዚሁ ዕለት የተቻላችሁ በአካል ወደ ቤ/ያናችን በመምጣት ያልተቻላችሁ ደግሞ በያላችሁበት ሆናችሁ በፖስተሩ በተለጠፈው የባንክ አካውንታችን የቻላችሁን ያህል በማስገባት ለሕንጻ ሥራው ተባብራችሁ ከበረከቱ እንድትሳተፉ በልዑል እግዚአብሔር አብ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ሼር በማድረግ መልእክቱን እንድትቀባበሉም አደራ እንላለን።
የእግዚአብሔር አብ በረከቱ ቸርነቱ ከኛ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!!!!!

Address

Chencha, Zozo
Arba Minch'
MUTA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የእግዚአብሔር አብ ልጆች የተራራው ሥር ምርጦች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የእግዚአብሔር አብ ልጆች የተራራው ሥር ምርጦች:

Share