Gamo Development association Arba Minch zuria branch ጋልማ አርባ ምንጭ ዙሪያ ቅርንጫፍ

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Minch'
  • Gamo Development association Arba Minch zuria branch ጋልማ አርባ ምንጭ ዙሪያ ቅርንጫፍ

Gamo Development association Arba Minch zuria  branch ጋልማ አርባ ምንጭ ዙሪያ ቅርንጫፍ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gamo Development association Arba Minch zuria branch ጋልማ አርባ ምንጭ ዙሪያ ቅርንጫፍ, Community Organization, Secha sub city, Arba Minch'.
(1)

Gamo Development Association is legally registered indigenous Charity Association
striving to change the lives of its people through holistic and integrated development interventions.

እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ! ጋሞ ልማት ማህበር 60 ሰዎችን የመጫን አቅም ያለው "ሀይላሾ" የተሰኘ ዘመናዊ የሞተር ጀልባ ማስገባቱን ገለፀ!የጋሞ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻ...
11/06/2026

እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!

ጋሞ ልማት ማህበር 60 ሰዎችን የመጫን አቅም ያለው "ሀይላሾ" የተሰኘ ዘመናዊ የሞተር ጀልባ ማስገባቱን ገለፀ!

የጋሞ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኢ/ር ማንደፍሮት ዱባለ እንደገለጹት በተቋሙ ስትራተጂክ ዕቅድ የቱሪዝም ተደራሽነትና መስፋፋት ላይ የየብስና የውሃ ላይ የመዳረሻዎችን አገልግሎት ማስፋፋት አንዱ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ገልጸዋል:: በዚህም ረገድ እየተከናወኑ ከሚገኙ በርካታ ስራዎች አንዱ በአባያ ሃይቅ ላይ የውሃ ትራንስፖርትና መዝናኛ መሆኑን የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው ተደራሽነቱን ለማሳደግ 60 ሰዎችን መጫን የሚችል "ሀይላሾ" የተሰኘውን የሞተር ጀልባ ግዢ ፈጽሞ በዛሬው እለት ሰኔ 4/2018 ዓ.ም ማስገባቱን ተናግረዋል::

"ሀይላሾ" የጋሞኛ ቃል ሲሆን ትርጉሙም አዞ ማለት ነው፡፡ ጀልባው ይህንን ስያሜ ያገኘው በምስራቅ አፍሪካ ቀዳም የሆነ አዞ ራንችን ከማስተዋወቅ ባሻገር በአባያ ሀይቅ ከሚገኙ በርካታ የብዝሃ ህይወት መካከል የናይል አዞ ዝርያ በስፋት መገኘቱን ለማሳየት ታስቦ እንደተሰየመ ዶ/ር ኢ/ር ማንደፍሮት ተናግረዋል፡፡ በቀጣይ ተቋሙ በቱሪዝም ዘርፍ የጀመራቸውን አዲስና ነባር መዳረሻዎች ግንባታ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዶ/ር ኢ/ር ማንደፍሮት ገልጸዋል::

የጋሞ ልማት ማህበር ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚና የቢዝነስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳዊት ዳኜ እንደገለጹት ማህበሩ ቱሪስቶችን መሳብ የሚያስችሉ በርካታ አዲስ መዳረሻዎችን በማልማት ለአገልግሎት ዝግጁ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል:: በአባያ ሃይቅ ላይ የሞጬ ደሴት፣ የአርባምንጭ አዞ ራንች እድሳትና አገልግሎት መስፋፋት፣ 40-42/አርባ አርባ አርባ ሁለት/ ደረጃ መንገድ እንዲሁም በአባያ ሃይቅ ላይ የውሃ ላይ ጉዞና መዝናኛ የሚጠቀሱ አዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች መሆናቸውን አቶ ዳዊት ገልጸዋል::

በውሃ ላይ ጉዞና መዝናኛነት አገልግሎት ተደራሽነትን ለመጨመር ተቋሙ ከዚህ ቀደም 30 ሰዎችን መያዝ የሚችል የጀልባ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ መሆኑን ያወሱት አቶ ዳዊት ተደራሽነቱን ለማስፋት በአሁኑ ወቅት 60 ሰዎች የመጫን አቅም ያለውን ዘመናዊ ጀልባ በግዢ መገዛታቸውን ተናግረዋል::

ጀልባው ወደፊትም ወደ ኋላም ጉዞ ማድረግ የሚችል መሆኑ በአይነቱ ዘመናዊ እንደሚያደርገው የገለጹት አቶ ዳዊት በተጨማሪም ባለ ሁለት ደረጃ ወለሎች ያሉት 48 ሰው ከታችኛው ወለል እና 12 ሰዎችን ከላይኛው ወለል የመጫን አቅም እንዳለው አስታውቀዋል::

በጋሞ ልማት ማህበር የቱሪዝም ልማትና አገልግሎት ኢንተርፕራይ ሥራ አስኪያጅ አቶ ደጉ ደሳለኝ ጋሞ ዞን የበርካታ መስህቦች ባለቤት ሲሆን አበዛኞዎቹ መስህቦች በአግባቡ ያልለሙ በመሆኑ በዞኑ ወስጥ ያሉ ፀጋዎችን ወደ ኢኮኖሚ ለመቀየርና ለአካባቢው ህበረተሰብ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ማህበራትቸን እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል:: ዘርፉን ለማሳደግ ሁሉም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ከማህበሩ ጋር ተባብሮ እንዲሰራ አቶ ደጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!
ሰኔ 4/2018

እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ! ውድ የጋሞ ልማት ማህበር አባላትና ደጋፊዎች በሙሉልማት ማህበራችን በነገው ዕለት ሰኔ 4/2018 ዓ/ም በጋሞ ልማት ማህበር የቱሪዝም ልማትና አገልግ...
10/06/2026

እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!
ውድ የጋሞ ልማት ማህበር አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ

ልማት ማህበራችን በነገው ዕለት ሰኔ 4/2018 ዓ/ም በጋሞ ልማት ማህበር የቱሪዝም ልማትና አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ አማካኝነት 60 ሰው የመጫን አቅም ያለው "ሀይላሾ" የተሰኘ ዘመናዊ የሞተር ጀልባ የሚያስገባ ስለሆነ ጀልባው ከተማውን ስደርስ በደስታ አቀባበል እንድታደርጉ ጥሪ እናስተላልፋለን::

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!

የጋሞ ልማት ማህበር በአባያ ሀይቅ “ሞጨ ደሴት” የተደረገ ጉብኝት በምስል
16/05/2026

የጋሞ ልማት ማህበር በአባያ ሀይቅ “ሞጨ ደሴት” የተደረገ ጉብኝት በምስል

ጋሞ ልማት ማህበር ከአይዲኤች/IDH/ ፕሮጄክት ጋር  በመተባበር በጋሞ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት በምርጥ ዘር  ብዜትና በድህረ ምርት አሰባሰብ ሂደት ላይ ያተኮረ ስል...
14/05/2026

ጋሞ ልማት ማህበር ከአይዲኤች/IDH/ ፕሮጄክት ጋር በመተባበር በጋሞ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት በምርጥ ዘር ብዜትና በድህረ ምርት አሰባሰብ ሂደት ላይ ያተኮረ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል

በስልጠናው መርሃግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጋሞ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢ/ር ማንደፍሮት ዱባለ እንደገለጹት ጋሞ ልማት ማህበር በጋሞ ዞን የበለጸገ ማህበረሰብ ተፈጥሮ የማየት ራዕዩን መሠረት ካደረገባቸው 9 ዘርፎች አንዱ ግብርና ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ መሆኑን ገልጸዋል::

በዚህም ረገድ ተለምዷዊ የምርት አሰራር ሂደትን በማሻሻልና በማዘመን በምርት አሰባሰብ ብክነትን መቀነስ እና እሴትን በመጨመር የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ዋነኛ የስልጠናው ማጠንጠኛ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ኢ/ር ማንደፍሮት የስልጠናው ተሳታፊዎች በዚህ ረገድ ውጤት እንዲመጣ በየአካባቢያቸው የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል::

የጋሞ ልማት ማህበር ምክትል ሥራ አስፈፃሚና የፕላንና ፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለምሰገድ ሉቃስ እንደገለጹት ልጠናው በጋሞ ዞን ምርትና ምርታማነት በማሻሻል አርሶአደሮች በምርጥ ዘር ማባዛት ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማዳበር ያለመ መሆኑን ገልጸዋል:: ለዚህም ጋሞ ልማት ማህበር ከአይዲኤች(IDH) ጋር በመተባበር የበቆሎ ምርታማነትን ከፍ ለማድረግ፣ የአርሶአደሮችን ገቢ ለማሻሻል እና የዘር ጥራት ለማሻሻል እንዲሁም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በጋሞ ልማት ማህበር የIDH ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ተመስገን በሪሁን እንደገለጹት ስልጠናው በጋሞ ዞን 9 ቆላማ ወረዳዎች ላይ በተለይም ትኩረት ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል:: በስልጠናው ላይ በየአካባዎቹ የሚገኙ የግብርና ጽ/ቤት ባለሙያዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ እንደሚሚገኙ ገልጸዋል::

ቅድሚያ ለጋራ ልማት
6/9/2018

የጋሞ ልማት ማህበርና ፓርትነር አፍሪካ ኢትዮጵያ በኦርጋኒክ ጥጥ ልማትና ገበያ ትስስር ላይ ያተኮረ ስልታዊ ስምምነት ተፈራረሙየጋሞ ልማት ማህበር (ጋልማ) የአካባቢውን የተፈጥሮ ፀጋ ወደ ላቀ...
11/05/2026

የጋሞ ልማት ማህበርና ፓርትነር አፍሪካ ኢትዮጵያ በኦርጋኒክ ጥጥ ልማትና ገበያ ትስስር ላይ ያተኮረ ስልታዊ ስምምነት ተፈራረሙ

የጋሞ ልማት ማህበር (ጋልማ) የአካባቢውን የተፈጥሮ ፀጋ ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ጥቅም ለመለወጥ በሚያደርገው ጥረት ከዓለም አቀፉ ፓርትነር አፍሪካ ኢትዮጵያ (PAE) ጋር በኦርጋኒክ ጥጥ ምርት፣ አቅርቦትና የገበያ ትስስር ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን ታሪካዊ ስምምነት በአርባ ምንጭ ከተማ በይፋ ተፈራርሟል።

የስምምነቱን አስፈላጊነት አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡት የልማት ማህበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወካይና የፕላንና ፕሮግራም ኃላፊ አቶ አለምሰገድ ሉቃስ፣ ስምምነቱ በዞኑ የሚገኙ እንደ ሼሌ መላ እና ኡጋዩሁ ያሉ የጥጥ አምራች ማህበራት ከምርት ሂደት እስከ ዓለም አቀፍ የገበያ ትስስር ድረስ ባለው ሰንሰለት ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉና ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

የልማት ማህበሩ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚና የቢዝነስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳዊት ዳኜ በበኩላቸው፣ ይህ ትብብር የአርባ ምንጭ እርሻ ልማት የጥጥ መዳመጫ ፋብሪካን በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ለማስገባትና ምርትን በቀጥታ ከአምራቾች በመረከብ እሴት በመጨመር ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ቁልፍ ሚና እንዳለው አፅንዖት ሰጥተዋል።

ይህ የአጋርነት ስምምነት ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ባለፈ የጋሞ ልማት ማህበርን ስትራቴጂካዊ ተጠቃሚነት የሚያጎላ ሲሆን፣ በተለይም ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችንና የፋይናንስ አቅምን ለመገንባት፣ የአምራቹን ገቢ የሚያሳድግ አስተማማኝ የገበያ ዋስትና ለመፍጠርና ለበርካታ ወጣቶችና ሴቶች የሥራ ዕድል ለማመቻቸት ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል።

የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ መሰለ መኩሪያ የጋልማን ሰፊ የማህበረሰብ ተሰሚነት ለሥራው ስኬታማነት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል::

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!
ግንቦት 3/2018 ዓ/ም

ጋሞ ልማት ማህበር አ/ምንጭ ዙርያ ወረዳ ቅርንጫፍ 2ኛውን በዞናችን ደግሞ 15ኛውን የማህበረሰብ ፋርማሲ በኦቾሎ ላንቴ አስመረቀየጋሞ ልማት ማህበር በጤናው ዘርፍ እያከናወነ ያለውን የልማት እ...
05/05/2026

ጋሞ ልማት ማህበር አ/ምንጭ ዙርያ ወረዳ ቅርንጫፍ 2ኛውን በዞናችን ደግሞ 15ኛውን የማህበረሰብ ፋርማሲ በኦቾሎ ላንቴ አስመረቀ

የጋሞ ልማት ማህበር በጤናው ዘርፍ እያከናወነ ያለውን የልማት እንቅስቃሴ በማጠናከር 15ኛውን የማህበረሰብ ፋርማሲ በኦቾሎ ላንቴ ከተማ በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ አስመርቋል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጋሞ ልማት ማህበር የሥራ አመራር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢና የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ እንደገለጹት ልማት ማህበሩ ከመንግሥት ጋር በመቀናጀት በህብረተሰቡ ዘንድ የሚታዩ የልማት ክፍተቶችን በመለየት በስፋት እየሰራ ይገኛል። በተለይም በጤናው ዘርፍ የማህበረሰብ ፋርማሲዎችን ተደራሽ በማድረግ ረገድ ማህበሩ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመዋል።

የጋሞ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢ/ር ማንደፍሮት ዱባለ በበኩላቸው የጤና ልማት የማህበሩ አንዱ ዋነኛ የትኩረት መስክ መሆኑን ገልጸው፣ ዛሬ የተመረቀው ፋርማሲ በአካባቢው የሚታየውን የመድኃኒት እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀርፍና ለህብረተሰቡ ጥራት ያላቸውን መድኃኒቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርብ አረጋግጠዋል። በተጨማሪም በቀበሌ ለሚገነባው የእናቶች ማቆያ ግንባታ 2000 ብሎከት ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል::

የልማት ማህበሩ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የበጎ አድራጎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበባየሁ ሳጳ ማህበሩ ፋርማሲዎችን ከመክፈት ባለፈ፣ የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ከ2,000 በላይ ዜጎችን የጤና መድን መዋጮ በመክፈል ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ለፋርማሲው መመረቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ የመንግሥት አካላትን አመስግነው እያንዳንዱ የክልሉ ተወላጅና ወዳጅ የማህበሩ አባል በመሆን የልማት አጋርነቱን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል።

በጋሞ ልማት ማህበር የአርባምንጭ ዙሪያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መልካ ጩአ ከዚህ ቀደም ልማት ማህበር በርካታ ልማት ሥራዎችን በወረዳ የሰራ መሆኑን ገልፀው ቅርንጫፉ በወረዳው 2ኛውን ፋርማሲ በላንቴ ቀበሌ አስመርቋል ብለዋል::

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የልማት ማህበሩ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!
ሚያዝያ 27/2018 ዓ/ም

የጋሞ ልማት ማህበር የ2026-2030 ስትራቴጂክ ዕቅድ ትግበራን የሚያሳልጥ የክትትልና ሪፖርት ሥርዓት ላይ ተወያየየጋሞ ልማት ማህበር (2026-2030) የሚቆየውን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ስኬታማ...
25/04/2026

የጋሞ ልማት ማህበር የ2026-2030 ስትራቴጂክ ዕቅድ ትግበራን የሚያሳልጥ የክትትልና ሪፖርት ሥርዓት ላይ ተወያየ

የጋሞ ልማት ማህበር (2026-2030) የሚቆየውን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ፣ የክትትልና ሪፖርት ማቅረቢያ ቅጾች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሂዷል።

የጋሞ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢ/ር ማንደፍሮት ዱባለ በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ላይ መካተት ያለባቸውን ግብዓቶች የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ለይተው እንዲልኩ አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን፣ እነዚህም ግብዓቶች ተሰባስበው በጠቅላላ ጉባኤ እንደሚፀድቁ ገልጸዋል። ዋና ሥራ አስፈፃሚው አክለውም በድርጅቱ ውስጥ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን ሁሉም ወረዳዎችና የንግድ ተቋማት የፋይናንስ እንቅስቃሴያቸውን በወቅቱ ኦዲት ማስደረግ እንዳለባቸው ያሳሰቡ ሲሆን፣ ለጋሞ ባይራ ትምህርት ቤት መጠናከርም ሁሉም ቅርንጫፎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በጋሞ ልማት ማህበር ምክትል ሥራ አስፈፃሚ የበጎ አድራጎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበባየሁ ሳጳ በበኩላቸው፣ አዳዲስ አባላትን ማፍራትና የነባር አባላትን ተሳትፎ ማሳደስ የዘርፉ ዋነኛ ትኩረት መሆኑን ገልጸው፤ ማንኛውም የሀብት ማሰባሰብ ሥራ ቀጥታ ለህብረተሰቡ የሚተርፉ የልማት ፕሮግራሞች ላይ ማተኮር እንዳለበት አሳስበዋል።

በጋሞ ልማት ማህበር ምክትል ሥራ አስፈፃሚ የቢዝነስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳዊት ዳኜ ቅርንጫፎች ራሳቸውን መቻል እንዲችሉ አዋጭ የሆኑ የንግድ ዘርፎች ላይ መሰማራት እንዳለባቸው ጠቁመው፣ የሥራ ውጤቶችም በተዘጋጀው አዲሱ የዕቅድና ሪፖርት ቅጽ አማካኝነት በተቀናጀ መልኩ መቅረብ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!
ሚያዝያ 17/2018 ዓ/ም

ጋሞ ልማት ማህበር  በቀጣይ አምስት ዓመታት (2026-2030) የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ሲያካሂድ የቆየውን የውይይት መድረክት አጠናቀቀየጋሞ ልማት ማህበር (ጋልማ) በቀጣይ አምስት ዓመታት የሚ...
25/04/2026

ጋሞ ልማት ማህበር በቀጣይ አምስት ዓመታት (2026-2030) የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ሲያካሂድ የቆየውን የውይይት መድረክት አጠናቀቀ

የጋሞ ልማት ማህበር (ጋልማ) በቀጣይ አምስት ዓመታት የሚመራበትን የተቀናጀ የልማት ስትራቴጂክ ዕቅድ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት ጋር ጥልቅ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ አጠናቅቋል።

በውይይት መርሃግብሩ ላይ የጋሞ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢ/ር ማንደፍሮት ዱባለ እንደገለጹት ማህበሩ በተለያዩ መስኮች ያነደፋቸውን ውጥኖች ከህብረተሰቡ ጋር መምከሩ ለጠንካራ ተቋም ግንባታ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል:: በዚህም ረገድ ከተሳታፊዎች ለቀረቡት ገንቢ አስተያየቶች ዋና ስራ አስፈጻሚው ምስጋናቸውን አቅርበዋል::

ስትራተጂክ ዕቅዱ መሠረታዊ በሆኑ ትምህርት፣ በጤና፣ ግብርናና ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያን ጨምሮ በ9 ዋነኛ የልማት ዘርፎችን በዲጂታላይዜሽንና ሌሎችም ዘመናዊ የማስፈጸሚያ ስልቶች በህብረተረሰቡ ኑሮ በጎ ተጽእኖ ለመፍጠር ትኩረት መደረጉን የገለጹት ዶ/ር ማንደፍሮት ለዚህም ተፈጻሚነት ሁሉም ባለድርሻ የበኩሉን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስለላልፈዋል::

የጋሞ ልማት ማህበር ምክትል ሥራ አስፈፃሚና የፕላንና ፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለምሰገድ ሉቃስ ለስትራተጂክ እቅዱ የተቋሙ ራዕይ ተፈጻሚነት ላይ ትኩረት ያደረጉ በመሆኑ የተሰጡ ገንቢ አስተያየቶችን በግብዓትነት እንደሚጠቀሙት ገልጸዋል:: በቀጣይም ለዕቅዱ ተፈጻሚነት ከህብረተሰባችን የሚነሱ ሃሳቦችን መቀበል ተጠናክሮ የሚቀጥሉ አሰራሮች እንደሆኑም አቶ አለምሰገድ ጨምረው ገልጸዋል::

የትምህርት ግብዓት፣ አረንጓዴ አሻራና ደን ልማት፣ የፋይናንስ ዲጂታላይዜሽን፣ የኑሮ ማረጋጊያ ስራዎች፣ የሰው ሃይል ልማት፣ የቱሪዝም ስራዎች ትስስር መፍጠር፣ የአበልና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የደንብ ማሻሻል ስራዎች፣ የግብርና ምርትና ምርታማነት ላይ በደጋው አካባቢ በሚገኙ ምርቶች ላይ ትኩረት ቢደረግ የሚሉ አስተያየቶች በመድረኩ ተሳታፊዎች ተነስተዋል::

በዞኑ በየአካባቢው ሁኔታ የገቢ ማሰባሰብ ስልቶች ትኩረት ቢሰጣቸው፣ የአፈጻጸም ግምገማ ስርዓት መንደፍ፣ የእንስሳት ክሊኒክ ግንባታ እንዲሁም በግብርናው ዘርፍ የተቀናጀ የተባይ መከላከል ስርዓትና ተፈጥሯዊ ይዘትን በጠበቀ መልኩ የማልማት ስራዎች በተጨማሪ ከተሳታፊዎች የተነሱ ዋነኛ ሃሳቦች ናቸው::

የ5 ዓመት መሪ ዕቅድ ሲጸድቅ ማህበሩ በሀብት አሰባሰብ፣ በሰው ኃይል ልማት፣ በጤና፣ በትምህርትና በመሰረተ ልማት ዘርፎች ላይ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋግራል ተብሎ ይጠበቃል።

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!
ሚያዝያ 17/2018 ዓ/ም

የጋሞ ልማት ማህበር በቀጣይ አምስት ዓመታት (2026-2030) ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት እያካሄደ ይገኛል የጋሞ ልማት ማህበር (ጋልማ) በቀጣይ አ...
25/04/2026

የጋሞ ልማት ማህበር በቀጣይ አምስት ዓመታት (2026-2030) ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት እያካሄደ ይገኛል

የጋሞ ልማት ማህበር (ጋልማ) በቀጣይ አምስት ዓመታት የሚመራበትን የተቀናጀ የልማት ስትራቴጂክ ዕቅድ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት ጋር ጥልቅ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

የጋሞ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢ/ር ማንደፍሮት ዱባለ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት ማህበሩ በ2030 በጋሞ ዞን ውስጥ ሁለንተናዊ ብልጽግና የተረጋገጠበት ማህበረሰብ የማየት ራዕይ መሰነቁን ገልፀዋል::

ዕቅዱ ከወረቀት ባለፈ መሬት ላይ ወርዶ ለውጥ እንዲያመጣ የባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎና የባለቤትነት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው የሁላችንም የድርሻችንን ስንወጣ የጋሞን ብልጽግና ዕውን እናደርጋለን ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የማህበሩ ምክትል ሥራ አስፈፃሚና የፕላንና ፕሮግራም ኃላፊ አቶ አለምሰገድ ሉቃስ በበኩላቸው፣ አዲሱ የስትራቴጂክ ዕቅድ ያለፉት አምስት ዓመታት አፈፃፀም፣ ወቅታዊ መረጃዎችና ተጨባጭ የህዝብ ፍላጎቶች ላይ ተመስርቶ በሳይንሳዊ መንገድ መዘጋጀቱን አብራርተዋል።

የመድረኩ ዋነኛ ዓላማ የጋሞ ዞንን የልማት አድማስ የሚያሰፉ መሪ ሃሳቦችን ማሰባሰብ ሲሆን በመድረኩ ከዞኑ መምሪያ፣ ባለሀብቶች፣ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆችና የሀብት አሰባሰብ ባለሙያዎች እና ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የተወከሉ ግለሰቦች እየተሳተፉ ነው::

የ5 ዓመት መሪ ዕቅድ ሲጸድቅ ማህበሩ በሀብት አሰባሰብ፣ በሰው ኃይል ልማት፣ በጤና፣ በትምህርትና በመሰረተ ልማት ዘርፎች ላይ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋግራል ተብሎ ይጠበቃል።

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!
ሚያዝያ 17/2018 ዓ/ም

የጋሞ ልማት ማህበር  ከ300 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለ100 የማህበረሰብ አባላት የፉርኖ ዱቄት እና ዘይት ድጋፍ አደረገየጋሞ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኢ/ር ማንደፍሮት ...
07/04/2026

የጋሞ ልማት ማህበር ከ300 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለ100 የማህበረሰብ አባላት የፉርኖ ዱቄት እና ዘይት ድጋፍ አደረገ

የጋሞ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኢ/ር ማንደፍሮት ዱባሌ በስጦታ መርሃግብሩ ላይ እንደገለጹት የማህበሩ ዋነኛ ተልእኮዎች አንዱ በጎ አድራጎት እንደመሆኑ በዛሬው እለት የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ 100 በኢኮኖሚ ዝቅተኛ የሆኑ ግለሰቦችን መደገፍ የዚሁ ስራ አካል መሆኑን አስታውቀዋል::

አብሮ በመተሳሰብ በዓልን ማሳለፍ የተለመደ ባህላችን እንደመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ይህንን ፈለግ ሊከተል እንደሚገባ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ዋና ስራ አስፈጻሚው ለመላው የልማት ማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች ለፋሲካ በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል::

የጋሞ ልማት ማህበር ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የበጎ አድራጎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበባየሁ ሳጳ እንደገለጹት የዘንድሮን ፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ማህበሩ ከ300,000 ብር በላይ ወጪ በማድረግ የዘይትና ፉርኖ ዱቄት ስጦታ ማበርከቱን ገልጸዋል:: ለስራው ስኬት ትብብር ላደረጉ አካላት በሙሉ አቶ አበባየሁ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::

ድጋፍ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ለማህበሩ ያላቸውን ምስጋና ገልጸዋል፣ እንዲህ ያሉ ተነሳሽነቶች ቁሳዊ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ትስስርን እና የአባልነት ስሜትን እንደሚያጠናክሩም ተናግረዋል።

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!
ታህሳስ 29/2018 ዓ/ም

Address

Secha Sub City
Arba Minch'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo Development association Arba Minch zuria branch ጋልማ አርባ ምንጭ ዙሪያ ቅርንጫፍ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gamo Development association Arba Minch zuria branch ጋልማ አርባ ምንጭ ዙሪያ ቅርንጫፍ:

Share