በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፋና በጎ አድራጎት ማኅበር/Adu Fana Charity Association

  • Home
  • Ethiopia
  • Adigrat
  • በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፋና በጎ አድራጎት ማኅበር/Adu Fana Charity Association

በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፋና በጎ አድራጎት ማኅበር/Adu Fana Charity Association Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፋና በጎ አድራጎት ማኅበር/Adu Fana Charity Association, Nonprofit Organization, Adigrat University, Adigrat.

👇ትግርኛእኒሆ!!! (3) "ንዘናጋዕ ንፅጉማት ንሓግዝ"!!! ብማሕበር ምግብረ ሰናይ ፋና ዩኒቨርሲቲ ዓዲግራት "እናተዘናጋዕና ንዝተፀገሙ ወገናት ንሓግዝ" ብዝብል ጭርሖ(መሪሕ ቃል) ንተከታታሊ...
03/01/2026

👇ትግርኛ
እኒሆ!!! (3) "ንዘናጋዕ ንፅጉማት ንሓግዝ"!!!
ብማሕበር ምግብረ ሰናይ ፋና ዩኒቨርሲቲ ዓዲግራት "እናተዘናጋዕና ንዝተፀገሙ ወገናት ንሓግዝ" ብዝብል ጭርሖ(መሪሕ ቃል) ንተከታታሊ ንኽልተ መዓልታት ዝፀንሕ ኣዝዩ ዘዘናግዕን ዘነቓቓሕን ፀወታ ተዳልዩ ኣሎ። ኣብዚ ዓብዪ ናይ ሕልናን መንፈስን ስራሕ ብኣካል ክትሳተፉን ኣካል ናይዚ ዓቢ ናይ ምግባረ ሰናይ ተግባር ክትኮኑን ብኽብሪ ንዕድም።
"50 ለሚን ንሓደ ሰብ ሸክሚ ን50 ሰብ ጌፂ እዩ"!!
ብማሕበር ምግባረ ሰናይ ፋና ዩኒቨርስቲ ዓዲግራት

👇ኣማርኛ
እነሆ!!!(3) "እየተዝናናን ነደያንን እናግዝ"!!!
በሚል መሪ ቃል በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፋና በጎ አድራጎት ማኅበር ለሁለት ቀናት የሚቆይ በጣም አዝናኝ እና አነቃቂ ጭውውቶችን ተዘጋጅቷል።እርሱዎም የዚህ ታላቅ የህሊና እና የመንፈስ ስራ በአካል ተገኝተው የምግባረ ሰናይ ተግባርን ተቋዳሽ ለመሆን በታላቅ ደስታና አክብሮት ተጋብዘዋል።
"50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሽክሙ ለ50 ሰው ጌጡ ነው"!!!
በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፋና በጎ አድራጎት ማኅበር

👇English
Here are!!!(3) "Let's have fun and help the needy"!!!
The Adigrat University Fana Charity Association has organized a very fun and inspiring games for two consecutive days under the slogan of "Let's help the needy while having fun" So We would like to invite you to participate in person in this great work of conscience and spirit and be a part of this great act of philanthropy.
"50 Lomon is a burden for one person and an ornament for 50 people"!!!
By the Adigrat University Fana Charity Association

ቀን ታህሳስ 25&26 2018ዓ/ም
ቅዳሜ ጥዋት ከ2:30-5:30 ከሰአት ከ9:00-11:30
እሁድ ጥዋት ከ3:00-5:30 ከሰአት ከ8:30-11:3
🙏🙏

ክቡራን እና ክቡራት በቅርብም ሆነ በሩቅ በመላ ኢትዮጵያ የምትኖሩ የዓዲግራ ዩኒቨርስቲ ፋና በጎ አድራጎት አባላትና ወዳጆች በሙሉ ሰላማችሁ ይብዛልን።በአሁን ግዜ በጣም በርከት ያሉ ነደያንና ...
26/12/2025

ክቡራን እና ክቡራት በቅርብም ሆነ በሩቅ በመላ ኢትዮጵያ የምትኖሩ የዓዲግራ ዩኒቨርስቲ ፋና በጎ አድራጎት አባላትና ወዳጆች በሙሉ ሰላማችሁ ይብዛልን።
በአሁን ግዜ በጣም በርከት ያሉ ነደያንና ተፈናቃዮችን የሚላስ የሚቀመስ ኣጥተው በራብ አለንጋ እየተገረፉ በየአደባባዩ እና በየመጠልያ ቤቱ እየሞቱና እያለቁ ይገኛሉ። ስለሆነም በዓዲግራት ፋና በጎ አድራጎት በተቻለን አቅም ከተማሪዎች የቁርስ ዳቦና ሩዝ በመሰባሰብ ወደ ነደያኑ በማድረስ እንዲሁም ከክኖርና ከቃርያ ሽያጭ ያገኘው ትርፍ ሁሉ ለነደያኑ እያገዘና እየረዳ መጥቷል እያገዘም ይገኛል። እና የዚህ ቅዱስ ተግባር ተቀጥያ የሆነ የገቢ ምንጭ በትንሹ ለመቅረፍ እና ነደያኑ በተሻለ አቅም ለማገዝ ታስቦ ትኬን(ሎቶሪ) ተዘጋጅቶአል። እንደሚታወቀው ይህ ትኬት ሙሉ ገቢዉን ለነደያን ለልደት ፍስክ ማስፈሰክያ ማለት እንደ ገቢያችን እና እንደየሰው ኅይላችን መጠን እራሳችን ኣባላቱ ምግቡ በመስራት ወይም ራሳቸው ነዳያኑ እንዲሰሩት በንዋይ በመስጠት ሙሉ ገቢውን ለተቸገሩ ወገኖችን የሚውል መሆኑን አይዘነጋም።
እናም ይህ መሰረት በማድረግ ደግሞ አንድ ሰው ወይም አባል በተለይ ደግሞ በቅርብም ይኑሩ በሩቅ ባሉበት ሁኖው ብዙ አባላትን ከ5 እስከ 30 ትኬቶችን እየቆረጡ (እየገዙ) ይገኛሉ። እንዲሁም አንድ አንድ ታታሪ አባላትና አማራር የተሰጣቸው 100 ትኬት በአንድ ቀን ውስጥ ጨርሰው እየሸጡ ይገኛሉ እና ሁላችንም አጠናክረን እንቀጥሉበት እላለሁኝ። በመሆኑም ክቡራንና ክቡራት አባሎቻችን ትኬት በመቁረጥ እና በማስቆረጥ ብቻ አይደለም ተጠምደን ያለነው ለነዳያኑ የሚሆን አልባሳትንና እና ጫማዎችን በመሰብሰብ እንዲሁም ክኖርና ቃርያ በመሸጥ ረገድም ከነበረው ግዚያት በበለጠ መልኩ ተጠናክሮ እየተሰራ ይገኛል።
ስለሆነም በተለይ የዚህ ማህበር አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ ተማሪዎችም ብንሆን፣ ሰራተኞችም ብንሆን፣ ስራ ፈላጊዎችም ብንሆን በግቢው ውስጥም ብንሆን በውጭ፣ በቅርብም ብንሆን በሩቅ፣ ሁላችን ኢትዮጵያውያንና ደጋግ ማህበረሰቦች ለነደያኑና ለተቸገሩ ወገኖቻችን ስንል በተቻለን አቅም ያለንን ሁለት ልብስና ሁለት ጫማ አንዱ ለነደያኑ በርህራሄ እንስጥ እንዲሁም በገንዘብ፣በጉልበት፣በሃሳብ በቻልነው አቅምና ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ነደያንን እናግዝ።
ትኬቱን በተቻለ መጠን ደጋግመን እንቁረጥ።
እድላችን እየሞከርን ነደያንን እንደግፍ።
#ነደያን በተቻላችሁ አቅም ለመደገፍ የምትፈልጉ በሩቅ ያላችሁ አባላት የማህበሩ ሒሳብ ቁጥር
* ወጋገን ባንክ 1070735730101
#እንዲሁም በሩቅ ሁናችሁ ትኬት ለመቁረጥ የምትፈልጉ ደግሞ
* CBE 1000167515518
"50 ሎሚ ለኣንድ ሰው ሸክሙ ለ50 ሰው ጌጡ ነው"!!!

25/12/2025
24/12/2025

34.3K likes, 980 comments. “ሁላችንም ባቅማችን እናግዝ 🙏❤ቤተሰቦቼ 50 ጊዜ ኮፒ ሊንክ ፎሎ ❤🥰”

23/12/2025

ሰው በየቦታው እያለቀ ነው በተለይ ደግሞ በደቡብ ምዕራብ ትግራይ በሕፅፅ ቀበሌ የሚገኙ ተፈናቃዮች እባካችሁ በቻልነው አቅም እንተጋገዝ ከቃላት በላይ ነው፣ ከሚነገር በላይ ነው፣ በጣም የሚዘገንን ሁኔታ ላይ ናቸው ምስሉን እዩትና ሼር እና ላይክ በማድረግ ሁሉም ጋ እንዲዳረስ ማድረግ እራሱ የቻለ ታላቅ እርዳታ ነው።

ይህ በዓዲግራት ከተማ ለሚገኙ ጧሪ እና ረዳት የሌላቸው ነደያንን በፋና በጎ አድራጎት ማኅበር የተደረገ የፅዳት ፕሮግራም ነው።ይህ የመሰለ መልካም ተግባር እና የህሊና ስራ ደጋፊዎች እና ቅን ...
22/12/2025

ይህ በዓዲግራት ከተማ ለሚገኙ ጧሪ እና ረዳት የሌላቸው ነደያንን በፋና በጎ አድራጎት ማኅበር የተደረገ የፅዳት ፕሮግራም ነው።ይህ የመሰለ መልካም ተግባር እና የህሊና ስራ ደጋፊዎች እና ቅን ሓሳቢዎች በሙሉ ይህ ማኅበር ለመደገፍ እና ተስፋ ለመሆን በአማቅችሁ በገንዘብ ፣በጉልበት እና በሓሳብ እንዲሁም የማህበሩ የዩቱብ እና የፌስቡክ ቻናሎችን ላይክ፣ሼር እና ሳብስክራይቭ በማድረግ ሃሳባችሁ እና ድጋፋችሁን እንድትሰጡን እንዲሁም አባል እንድትሆኑ ስንል በነደያኑ እና በማኅበሩ ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ለበለጠ መረጃ
#ርግበ ወሚካኤል ሰብሳቢት +251 99 036 1226
#ካሕሳይ ብርሃኑ ምክትል +251962566654
# ሹሻይ ሓጎስ ሚድያ ክፍል አስተባባሪ 0938777731

Fana charity association in adigrat university helps sonless elders so all members get high satisfaction because we clean thier home and clothes.This charity...

በ 30/07/2017 ዓ/ም በዓዲግራት ከተማ ቀበሌ 01 በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፋና በጎ አድራጎት አባላት የተደረገው የነደያን የልብስ እና የቤት ፅዳት ፕሮግራም ይህ ይመስላል።
10/04/2025

በ 30/07/2017 ዓ/ም በዓዲግራት ከተማ ቀበሌ 01 በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፋና በጎ አድራጎት አባላት የተደረገው የነደያን የልብስ እና የቤት ፅዳት ፕሮግራም ይህ ይመስላል።

በዛሬው ቀን መጋቢት 23 2017 ዓ/ም የፋና በጎ አድራጎት አባል የሆነ የማርኬቲንግ ተማሪ ወንድማችን ዲ/ን ሃይለ ኪሮስ ለ15 ኣባላት ፋና በጎ አድራጎት ደከመኝ ሰላቸኝ ሳይሉ በትጋት ለሚሰ...
01/04/2025

በዛሬው ቀን መጋቢት 23 2017 ዓ/ም የፋና በጎ አድራጎት አባል የሆነ የማርኬቲንግ ተማሪ ወንድማችን ዲ/ን ሃይለ ኪሮስ ለ15 ኣባላት ፋና በጎ አድራጎት ደከመኝ ሰላቸኝ ሳይሉ በትጋት ለሚሰሩ እና በመስራት ላይ ለሚገኙ አባላት ለመበርታትና ለመጠንከር እንዲሁም ከነበራቸው አብልጦው እንዲሰሩ በማሰብ ለእያንዳንዳቸው 400 ብር በአጠቃላይ 6000 ብር ሽልማት አድርገዋል። ተሸላሚዎችም በበኩላቸው ለዚህ ሽልማት የበቃን የግላችን ጥንካሬና ብርታት ሳይሆን የሁላችንም አባላት አንድነትና በጎነት ታክሎበት የተገኘ ውጤት ሲሆን ይህ ቅዱስ ተግባር የጽናታችንና ጥንካሬአችንን ተምሳሌት ነው በማለት ደግሞም ከነበረን ጠንካራ ስራ በበለጠ ጠንክረንና በርትተን እንድንሰራ የሚያደርግ ቅዱስ ተግባር ነው ብለዋል። ተሸላሚዎች አክለው ይህም ሽልማት ለሰጠን ለወንድማችን ተማሪ ዲ/ን ሃይለ ኪሮስ ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል።

ለሁሉም የእስልምና እምነት ተከታዮች በተለይ ደሞ ለሙስሊም አባሎቻችን ፋና በጎ አድራጎት ማኅበር እንኳን ለዒድ አልፈጥር በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ። በአሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ...
30/03/2025

ለሁሉም የእስልምና እምነት ተከታዮች በተለይ ደሞ ለሙስሊም አባሎቻችን ፋና በጎ አድራጎት ማኅበር እንኳን ለዒድ አልፈጥር በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ። በአሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና የመልካምነት መአል ያድርግላችሁ እያልን በአሉ ለተቸገሩ ወገኖቻችን በማገዝ እና በመርዳት እንድናከብረው መልእክታችንን እናስተላልፋለን🙏🙏🙏
መልካም ዒድ ሙባረክ!!!

በዓዲግራት ዩንቨርሲቲ ፋና በጎ አድራጎት ማኅበር አባላት በግቢው ውስጥ የሚደረገው የክኖርና ቃርያ የሚሸጡ እና የቁርስ ዳቦ በመሰብሰብ ወደ ነደያኑ እና በ ነባር የአየር ማረፊያ የሚገኙ ተፈና...
27/03/2025

በዓዲግራት ዩንቨርሲቲ ፋና በጎ አድራጎት ማኅበር አባላት በግቢው ውስጥ የሚደረገው የክኖርና ቃርያ የሚሸጡ እና የቁርስ ዳቦ በመሰብሰብ ወደ ነደያኑ እና በ ነባር የአየር ማረፊያ የሚገኙ ተፈናቃዮች የሚያደርሱ አባላት ስም ዝርዝር። 50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለ50 ሰው ጌጡ ነው!!!

Address

Adigrat University
Adigrat

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፋና በጎ አድራጎት ማኅበር/Adu Fana Charity Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share