MSI Ethiopia Reproductive Choices

MSI Ethiopia Reproductive Choices We deliver quality family planning and reproductive healthcare to millions of the world's poorest and most vulnerable women.

29/05/2026

🎙 Don’t miss this inspiring conversation!

Join us tomorrow, Saturday at 10:00 AM (4:00 ሰዓት ጠዋት) on Abbay TV as Dr. Abebe Shibru shares the remarkable journey of MSI Ethiopia and its impact on improving the health and well-being of women, children, and youth across the country.

Learn how MSI Ethiopia achieved self-sustainability, expanded its reach, and the key lessons gained along the way. Hear more about our strong commitment to client experience and our contact center services through 8044.

📺 Tune in, get inspired, and be part of the conversation!

70 በመቶ ያህል ከውጪ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ ጥገኝነት ተላቅቄያለሁ ሲል  ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ሪፕሮዳክቲቭ ቾይዝ አስታወቀየስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ለማህበረሰቡ በማቅረብ የሚታወቀ...
26/05/2026

70 በመቶ ያህል ከውጪ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ ጥገኝነት ተላቅቄያለሁ ሲል ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ሪፕሮዳክቲቭ ቾይዝ አስታወቀ

የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ለማህበረሰቡ በማቅረብ የሚታወቀው ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ከውጪ ድርጅቶች የሚያገኘውን የገንዘብ ድጋፍ ለመቀነስ የቢዝነስ ሞዴልን ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል። የሜሪ ስቶፕስ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ዶክተር አበበ ሽብሩ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የእናቶችን፣ የህፃናትን፣ የወጣቶች እና የአፍላ ወጣቶችን ጤና ለማረጋገጥ ተቋሙ ላለፉት 35 ዓመታት በርካታ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ።

ተቋሙ ከዚህ ቀደም እስከ ፈረንጆቹ 2000 ዓመት ድረስ ከአሜሪካ እና ከእንግሊዝ መንግስታት እንዲሁም ከለጋሽ ድርጅቶች በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ ይህን አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል።አሁን ላይ የምእራባውያን ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እያደረጉት ያለው የገንዘብ ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መምጣቱን ዶክተር አበበ ተናግረው ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነው የእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት የሚከናወነው ከውጪ ሀገራት በሚገኝ ድጋፍ መሆኑን አስረድተዋል።

ይህ ድጋፍ በአሁኑ ወቅት በተመሳሳይ መልኩ እየቀነሰ መምጣቱን የጠቀሱት ካንትሪ ዳይሬክተሩ እንዲህ ያሉ አገልግሎቶችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ በኩል የሀብት ውስንነቶች እንዳሉ ጠቁመዋል።በዚህ ወቅት ተቋሙ ራሱን የሚያጠናክርበትን የቢዝነስ ሞዴል ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን ከመንግስት የጤና ተቋማት ከፍ ያለ፣ከግል የጤና ተቋማት ባነሰ ክፍያ አገልግሎትን እየሰጠ ይገኛል።

በዚህም የተነሳ በለጋሽ ድርጅቶች በኩል የሚስተዋለውን የገንዘብ ድጋፍ ስጋቶች መቀነስ መቻሉን የተናገረው ሜሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2025 በ70 በመቶ ያህል እራሱን ከውጪ ሀገራት ድጋፍ ጥገኝነት ማላቀቁን አስታውቋል።እንደዚሁም ተቋሙ 80 በመቶ የሚሆነውን አገልግሎቱን ከውጪ ድርጅቶች በሚያገኘው ድጋፍ በገጠሩ የኢትዮጵያ ቦታዎች ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በነፃ ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።

በቅድስት ደጀኔ

25/05/2026

🩸 በእርግዝና ጊዜ ደም ካየሽ — ዝም አትዪ!
እርጉዝ እያለሽ ደም ከታየሽ፣ ወዲያውኑ ወደ ጤና ተቋም ሂጂ። ❓ "ለምን?" ❓ "እንዴት?" ❓ "ምንድነው ችግሩ?" — የምትጠይቂው ጥያቄ ሕይወትሽን ሊታደግ ይችላል። 💛
👶 ጤናማ እናት = ጤናማ ልጅ 🏥 አትዘግዪ — ዛሬ ሂጂ!
ዛሬውኑ ወደ ማዕከላችን ብቅ ይበሉ! 📞 ለበለጠ መረጃ በነጻ መስመር 8044 ይደውሉልን። 📍 MSI ኢትዮጵያ- ጤናሽ፣ ምርጫሽ፣ ውበትሽ!

MSI Ethiopia Reproductive Choices has been awarded Health Excellence award at the Crown of Humanity AwardsMSI Ethiopia h...
25/05/2026

MSI Ethiopia Reproductive Choices has been awarded Health Excellence award at the Crown of Humanity Awards

MSI Ethiopia has received the Health Excellence Award at the second edition of the Crown of Humanity Awards, held at the Adwa Victory Memorial Museum, Addis Ababa. This recognition underscores MSIE’s unwavering commitment to enhancing maternal and child healthcare services across Ethiopia.

On the occassion, Dr. Abebe Shibru, Country Director of MSI Ethiopia, expressed heartfelt gratitude to the organizing committee for the honor. “This award is a testament to our dedicated team and our mission to provide Quality healthcare services to mothers and children in different parts of the country,” Dr. Shibru stated.

From 2020 to 2025, MSIE made significant strides in its healthcare outreach, serving over 6.1 million individuals through its network of five maternity centers and 15 sexual and reproductive health (SRH) centers. MSIE places a strong emphasis on client-centered care, ensuring an improved patient experience for all who seek their services. MSI Ethiopia continues to lead the way in reproductive healthcare, committed to making a lasting impact on the health and wellness of communities across the country.

ግንቦት 14/2018 በኢትዮጵያ ከ35 ዓመታት በፊት ጀምሮ የስነ ተዋለዶ፣የ እናቶችና ህጻናት ጤና አግልጎሎቶችን ሲሰጥ የቆየው የኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ (   ) ከፍተኛ ቁጥር የነበረውን የእ...
23/05/2026

ግንቦት 14/2018

በኢትዮጵያ ከ35 ዓመታት በፊት ጀምሮ የስነ ተዋለዶ፣የ እናቶችና ህጻናት ጤና አግልጎሎቶችን ሲሰጥ የቆየው የኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ( ) ከፍተኛ ቁጥር የነበረውን የእናቶችና ጨቅላ ህፃናት ሞት እንዲቀንስ ከፍተኛ አስተዋፆ ማድረጉን ተናገረ፡፡

ድርጅቱ ባለፉት 10 ዓመታት በተለይ በዓመት በአማካይ ለ2 ሚሊዮን ሰዎች አገልግሎቱን ሲሰጥ መቆየቱን ጠቅሷል፡፡

በሰጣቸው የስነ ተዋለዶ፣ የእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎቶች የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር አንዲያድግ አንዲሁም የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ሞት አንዲቀንስ ከፍተኛ አስተዋጾ ማበርከቱን የኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተሩ አበበ ሽብሩ (ዶ/ር) ነግረውናል፡፡

በዚህም ለምሳሌ ባለፈው ዓመት ብቻ ከወሊድ ጋር በተያያዘ 1000 እናቶችን ከሞት ታድገናል ብለዋል፡፡

30 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ብዙ እናቶች ከሚሞቱባቸው 4 ሀገሮች ውስጥ እንደነበረችና የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ተደራሽ አለመሆን በተለይ አገልግሎት ምቹ የሆነ ፖሊሲ ያልነበረው መሆኑ ችግሮች ነበሩ ሲሉ ሃላፊው አስረድተዋል፡፡

የእናቶችን ሞት ቁጥር ለመቀነስ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ብዙ ከወሊድ አገልግሎቶች ጋር በተገናኘ የሚሞቱ እናቶችና ህፃናት ቁጥር መቀነስ እንዲሁም የስነ ተዋልዶ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ወጣቶችን ማገዝ ላይ የተከወኑ ስራዎች ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን አበበ (ዶ/ር) ይናገራሉ፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ከዓመታት በፊት ከ 100,000 እናቶች 1,000 ያህሉ ከወሊድ ጋር በተገናኙ የጤና ችግሮች ምክንያት ይሞቱ እንደነበር ያነሱት አበበ (ዶ/ር) አሁን ይህ ምጣኔ ወደ 160 መቀነሱን ተናግረዋል፡፡

ይህ ለውጥ የመጣውም በመንግስት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት፣ የሲቪክ ማህበረሰብ የሙያ ማህበራት ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት ነው ብለዋል፡፡

ነገር ግን ከቅርብ አመታት ወዲህ የአምአቀፍ ለጋሾዎች ድጋፍ መቀነስ በስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ላይ ተጽእኖ እያሳደረ በመሆኑ ስራዎቹ በሀገር ውስጥ ምንጭ ላይ መመስረት እንዳለባቸው አስገድዶናል ሲሉም አስረድተዋል፡፡

የኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያም በራሱ ሃብት መፍጠር ላይ ለመስራት ከ5 ዓመታት በፊት በመወሰን ወደ ስራ ገብቷል ተብሏል፡፡

ይሁን እንጂ ተቋሙ ከተመሠረተበት ዓላማ አንጻር ለአገልግሎት ክፍያ መጠየቁ የንግድ ተቋም አያደርገውም ወይም አንዳንዴ ቅሬታ ሲቀርብበት ይታያል ያልናቸው ዳይሬክተሩ፤ ድርጅቱ ራሱን እንዲችልና ከውጭ ድርጅቶች ድጋፍ ሙሉ በሙሉ ጥገኝነቱ እንዲቀንስ ነው፤ አገልግሎት እንዳይቋረጥ በውጪ ድርጅቶች ያለን ጥገኝነት ለመላቀቅና ከአገልግሎት የሚገኘው ገቢ በመሰብሰብ መልሶ ለማህበረሰቡ ማዋል የሚያስችል አሰራር ነው የፈጠርነው ይህም በጤና ሚኒስቴር ጭምር ዕውቅና ተሰጥቶታል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. https://tinyurl.com/yb2c3u53

ምህረት ስዩም

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7

22/05/2026

https://www.tiktok.com//video/7642728086261304598?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7616024211966264853

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እናቶች የመረጡን በምክንያት ነው።
ምን እናቀርባለን?
✅ በስፔሻሊስት ሀኪሞች የሚሰጥ የቅድመ ወሊድ፣ ማዋለድ እና ድህረ ወሊድ አገልግሎት
✅ እጅግ ዘመናዊ የ 4D አልትራሳውንድ አገልግሎት
✅ ግላዊ መብትን የሚጠብቁ ዘመናዊ የምጥ እና ማዋለጃ ክፍሎች
✅ የቤተሰብ ፍቅር የሚሰጡ ባለሙያዎች
እናት የአለም ምርጡ ይገባታል። ዛሬውኑ ወደ ማዕከላችን ብቅ ይበሉ!
📞 ለበለጠ መረጃ በነጻ መስመር 8044 ይደውሉልን።
📍 MSI ኢትዮጵያ- ጤናሽ፣ ምርጫሽ፣ ውበትሽ!

20/05/2026

https://www.tiktok.com//video/7641995630671416598?is_from_webapp=1&sender_device=pc

በእርግዝናሽ ወቅት የደም ግፊት መጨመር ቸል አይባልም! ⚠️
​በእርግዝና ወቅት የሚከሰት ከፍተኛ የደም ግፊት ፈጣን የህክምና ክትትል ካልተደረገለት የአንቺንም ሆነ የጽንሱን ህይወት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል። የተሟላ የቅድመ ወሊድ ክትትል በወቅቱ በማድረግ ልጅሽን በጤና ለመውለድ ዛሬውኑ ትክክለኛውን ውሳኔ ውሰጂ። 🩺❤️
​👇 ለተሟላ የቅድመ ወሊድ ክትትል፦
📞 በነጻ ይደውሉ: 8044
📍 አድራሻ: አዳማ፣ ከፓን አፍሪክ ሆቴል 300 ሜትር ገባ ብሎ
MSI ኢትዮጵያ

18/05/2026

https://www.tiktok.com//video/7641221527945399574?is_from_webapp=1&sender_device=pc

ለቤታችሁ አዲስ ተስፋ! ✨
የልጅ ናፍቆት እና የዘመድ ጥያቄ በልባችሁ ውስጥ የሚፈጥረውን ጫና እንረዳለን። ብዙ ጊዜ መፍትሄው እጃችሁ ላይ ሆኖ ሳለ፣ ወደ ትክክለኛው ባለሙያ አለመሄድ ብቻ ጊዜ እና ገንዘባችሁን ሊያባክን ይችላል።
አሁን ሩቅ መሄድ ሳያስፈልጋችሁ፣ በኤም.ኤስ.አይ (MSI) ሀና ማሪያም ማዕከል ልዩ የፈርቲሊቲ ህክምና ጀምረናል።
ለምን ወደ እኛ ትመጣላችሁ?
ልዩ ባለሙያ፦ የወንድም ሆነ የሴት የመውለድ ችግሮችን በጥልቀት የሚከታተሉ የፈርቲሊቲ ሰብ-ስፔሻሊስት (Sub-specialist) ሐኪም አዘጋጅተናል።
ዘመናዊ ቴክኖሎጂ፦ በዘመናዊ የሆርሞን መመርመሪያ ማሽን የታገዘ ትክክለኛ ምርመራ እናደርጋለን።
ምስጢራዊነት፦ ከባለሙያዎቻችን ጋር በምስጢር እና በነጻነት የመመካከር እድል ታገኛላችሁ።
📍 አድራሻችን፡- ከሀና ፀበል ወደ ሀና ቀለበት ብረት ድልድይ ጋር 50 ሜትር ገባ ብሎ
☎ ቀጠሮ ለማስያዝ ወይም ለባለሙያ ምክር በነፃ የስልክ መስመር 8044 ደውይልን!

15/05/2026

https://www.tiktok.com//video/7640124776740146454?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7616024211966264853

ሆድሽ እስኪገፋ ወይም ህመም እስኪሰማሽ መጠበቅ የለብሽም! 🤰 ቅድመ ወሊድ ክትትል ማድረግሽ ማንኛውንም አይነት የጤና ስጋት አስቀድሞ ለመለየት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የወሊድ ጊዜ እንዲኖርሽ ይረዳል።
ለምን MSI ሀና ማሪያምን ትመርጫለሽ?
ቅርበት፦ ሀና ማሪያም፣ ኃይለ ጋርመንት፣ ሰፈራ፣ ሳሪስ፣ ጀሞ፣ ለቡ እና አካባቢው ለምትገኙ ነፍሰ ጡር እናቶች እዚሁ ሰፈራችሁ እንገኛለን።
ዘመናዊ 4D አልትራሳውንድ፦ የልጅሽን የፊት ገጽታ እና እንቅስቃሴ በግልጽ ማየት የምትችይበት የ 4D አልትራሳውንድ ምርመራ አገልግሎት አለን።
ምቾት፦ ያለ ምንም ቀጠሮ በፈለግሽው ሰዓት ብቅ ብለሽ መታየት ትችያለሽ።
ባለሙያ፦ በዘርፉ የላቀ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎቻችን በሰላምና በክብር ትስተናገጃለሽ።
📍 አድራሻችን፡- ከሀና ፀበል ወደ ሀና ቀለበት ብረት ድልድይ ጋር 50 ሜትር ገባ ብሎ ☎ ቀጠሮ ለማስያዝ ወይም ለባለሙያ ምክር በነፃ የስልክ መስመር 8044 ደውይልን

OSSHD Explores MSI Ethiopia’s Successful Social Business ModelOrganization for Social Services, Health and Development (...
13/05/2026

OSSHD Explores MSI Ethiopia’s Successful Social Business Model

Organization for Social Services, Health and Development (OSSHD) held an experience-sharing session with MSI Ethiopia to learn from the organization’s successful social business model and explore opportunities for adaptation within its own operational context.

During the opening session, Mr. Chala Zecharias, Social business Department Director, reflects on the challenges faced during the early stages of establishing the social business model. He emphasized that building strong human capital has been one of the key pillars behind the success and sustainability of MSI Ethiopia’s social business model.

The experience-sharing meeting, held in MSI Ethiopia’s support office, brought together senior leadership members and technical experts from both organizations. Senior experts from the Social Business Department presented practical experiences and insights gained through implementing and scaling MSIE’s social business model over the years.

Speaking during the session, Abatiye highlighted leadership commitment as another critical factor contributing to the success of the social business model. He also noted that institutional dedication and strategic guidance have played a significant role in ensuring effective implementation and long-term impact.

The OSSHD senior leadership team expressed appreciation for MSI Ethiopia’s practical experience and valuable lessons. The participants acknowledged the relevance of the model and indicated their interest in adapting key approaches within their own organizational context to strengthen sustainable social service delivery.

Organization for Social Services, Health and Development previously known as OSSA, is a pioneer organization in the fight against HIV and AIDS in Ethiopia.

Address

Kirkos Sub City, Woreda 02, House No. 174
Addis Ababa
5775

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MSI Ethiopia Reproductive Choices posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to MSI Ethiopia Reproductive Choices:

Share