Mary Joy Ethiopia

Mary Joy Ethiopia Mary Joy Ethiopia charity that works to empower vulnerable and underserved community groups through integrated development programs.

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ለመላው ኢትዮጵያዊያን በሙሉ እንኳን ለቡሄ (ደብረ ታቦር) በዓል አደረሳችሁ!መልካም በዓል!                                                   ...
19/08/2026

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ለመላው ኢትዮጵያዊያን በሙሉ እንኳን ለቡሄ (ደብረ ታቦር) በዓል አደረሳችሁ!
መልካም በዓል! ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ
“ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን”
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ  ማኔጅመንት አባላት እና ሙሉ ሠራተኞች የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት ጤና አባልነት ፕሮግራምን  ተቀላቀሉ።************************************...
17/08/2026

የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ማኔጅመንት አባላት እና ሙሉ ሠራተኞች የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት ጤና አባልነት ፕሮግራምን ተቀላቀሉ።
***********************************************
‎
‎ነሐሴ11/2018 ዓ.ም
‎ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
‎ሀዋሳ
‎
‎የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ማኔጅመንት አባላት እና ሙሉ ሠራተኞች ከደመወዛቸው ሁለት መቶ ብር በየወሩ በመቁረጥ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት ጤና አባልነት ፕሮግራም አባል ሆነዋል።
‎
‎የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሌ ሀርሲሳ በንግግራቸው ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል የኩላሊት ሕመም ታካሚዎች በከፍተኛ የሕክምና ወጪ እና በተወሰነ የአገልግሎት አቅርቦት ምክንያት ሕይወታቸው እዳያልፍ እየሰጠ ያለው አገልገሎት ተስፋ ሰጪ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
‎
‎የቢሮዉ ኃላፊ አክለውም በሀገራችን የኩላሊት ህክምና ብዙ ወጪ የሚጠይቅና ፈታኝ በመሆኑ ይህንን ለማቅለል ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ስለሚገኝ ሁሉችንም በጎ ተግባራትን በመደገፍ እና በመረዳዳት የበኩላችንን ኃላፊነት መወጣት አለበን ብለዋል።
‎
‎በኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት የደቡብ ኢትዮጵያ ክላስተር አስተባባሪና የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት አምባሳደር የሆኑት አቶ ዘመን ለገሰ በንግግራቸው ማዕከሉ ለግለሰቦች፣ ለቤተሰቦች እና ለማህበረሰቡ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው የኩላሊት ዕጥበት አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን እየሰራ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።
‎
‎እንዲሁም የአባልነት ፕሮግራሙን በመቀላቀል አባላት የራሳቸውን እና የቤተሰባቸውን ጤና ከመጠበቅ ባሻገር፣ አቅም ለሌላቸው ወገኖች ሕይወት አዳኝ ድጋፍ በማድረግ የተሻለ እና ጤናማ ማህበረሰብ ለመገንባት ያስችላሉ ብለዋል።
‎
‎በመጨረሻም የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች እና ሥራስካጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ማኔጅመንት አባላት እና ሠራተኞች ለማዕከሉ ያደረጉትን የበጎ ድጋፍ በማዕከሉ ስም አመስግነዋል።

17/08/2026
አንድ ትንሽ ድጋፍ ለአንድ ህጻን ወይም ለአንድ አረጋዊ ትልቅ ተስፋ ነው።  በቻሉት አቅም በመነሳት ዛሬ ድጋፍዎን ያድርጉ፤ ፍቅርዎን፣ ርህራሄዎን እና አጋርነትዎን ያሳዩ። አብረን እንደግፍ፣ ...
17/08/2026

አንድ ትንሽ ድጋፍ ለአንድ ህጻን ወይም ለአንድ አረጋዊ ትልቅ ተስፋ ነው። በቻሉት አቅም በመነሳት ዛሬ ድጋፍዎን ያድርጉ፤ ፍቅርዎን፣ ርህራሄዎን እና አጋርነትዎን ያሳዩ።
አብረን እንደግፍ፣ አብረን ተስፋ እንስጥ!
#ህጻናትንእናአረጋዊያንንእንደግፍ
#ስፖንሰርያድርጉ
#የሰውነትፍቅር

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ዲላ ኩላሊት እጥበት ማዕከል የግንባታ መሰረት ድንጋይ ተጣለ።
16/08/2026

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ዲላ ኩላሊት እጥበት ማዕከል የግንባታ መሰረት ድንጋይ ተጣለ።

“አንድ ልጅን መደገፍ የነገን ተስፋ ማብራት ነው።” ዶ/ር መሳይ ገብረ ማርያም በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ “ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን” በሚለው መርህ በመነሳት፣ ድጋፍ የሚሹ ህፃናትን በስፖንሰር...
14/08/2026

“አንድ ልጅን መደገፍ የነገን ተስፋ ማብራት ነው።”

ዶ/ር መሳይ ገብረ ማርያም በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ “ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን” በሚለው መርህ በመነሳት፣ ድጋፍ የሚሹ ህፃናትን በስፖንሰርሺፕ በቋሚነት ደግፈዋል።
የዛሬ ድጋፍ ለአንድ ህፃን ተስፋ ነው፤
የዛሬ ስፖንሰርሺፕ ለነገ የተሻለ ሕይወት መሠረት ነው።

🙏 ዶ/ር መሳይ ገብረ ማርያም ለህፃናቱ ተስፋ በመሆን ላደረጉት ደግነትና ድጋፍ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ለህፃናት ዛሬ እንደግፍ፤ ነገን አብረን እንገንባ!

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ
“ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን”
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
#እንደግፍ #ህፃናትንእንደግፍ

አንድ ቤተሰብ፣ አሥር ልጆች፣ ብዙ ተስፋ! “ለሌላ ሰው የምንዘረጋው እጅ፣ የተስፋ መንገድ ይሆናል።”የአቶ ሙሉጌታ ገዌ ቤተሰብ በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ “ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን” በሚለው መ...
14/08/2026

አንድ ቤተሰብ፣ አሥር ልጆች፣ ብዙ ተስፋ!

“ለሌላ ሰው የምንዘረጋው እጅ፣ የተስፋ መንገድ ይሆናል።”
የአቶ ሙሉጌታ ገዌ ቤተሰብ በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ “ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን” በሚለው መርህ በመነሳት፣ ድጋፍ ለሚሹ 10 ህፃናት ቤተሰቦችን በወርሃዊ ስፖንሰርሺፕ በቋሚነት ለመደገፍ ዛሬ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

ይህ ድጋፍ የዛሬን ፍላጎት ብቻ የሚያሟላ ሳይሆን፣ ለህፃናቱ የተሻለ ነገ እንዲኖር የሚያስችል ቀጣይነት ያለው ተስፋ ነው።

🙏 ለአቶ ሙሉጌታ ገዌ ቤተሰብ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
አንድ ድጋፍ አንድን ህፃን ሊያበረታታ ይችላል፤ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ግን የአንድን ቤተሰብ ሕይወት ሊለውጥ ይችላል።
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ
“ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን”
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
#ወርሃዊስፖንሰርሺፕ #እንደግፍ

ነሐሴ7/2018 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ  ማኔጅመንት አባላት የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ሀዋሳ የኩላሊት ዕጥበት ህክምና ማዕከልን ጎበኙ።      ***************************...
13/08/2026

ነሐሴ7/2018 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ማኔጅመንት አባላት የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ሀዋሳ የኩላሊት ዕጥበት ህክምና ማዕከልን ጎበኙ።
****************************

‎የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ማኔጅመንት አባላት የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ሀዋሳ የኩላሊት እጥበት ማዕከልን ጎብኝተው አምስት ሚሊዮን ብር የሚገመት ጄኔሬተር ድጋፍ አድርገዋል።
‎
‎በጉብኝቱ ወቅት የማዕከሉን አገልግሎት፣ የወደፊት ዕቅዶች እና የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት ጤና አባልነት ፕሮግራምን በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል።
‎
‎የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሌ ሀርሲሳ በንግግራቸው ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል የኩላሊት ሕመም ታካሚዎች በከፍተኛ የሕክምና ወጪ እና በተወሰነ የአገልግሎት አቅርቦት ምክንያት ሕይወታቸው እዳያልፍ እየሰጠ ያለውን ጠቃሚ አገልግሎት በማድነቅ፣ በቀጣይ አገልግሎቱን ለመደገፍና ከማዕከሉ ጋር በጋራ ለመስራት ፍቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
‎
‎አክለውም የኩላሊት ጤና አባልነት ፕሮግራም በስፋት እንዲጠናከር የሚጠበቅባቸውን ተቋማዊ ትብብር ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
‎
‎በኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት የደቡብ ኢትዮጵያ ክላስተር አስተባባሪና የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት አምባሳደር የሆኑት አቶ ዘመን ለገሰ በጉብኝቱ ወቅት ባስተላለፋት መልዕክት የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት ጤና አባልነት ፕሮግራም በስፋት እንዲጠናከር እና ተጨማሪ ዜጎች በፕሮግራሙ እንዲሳተፉ ከተቋማት እና ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
‎
‎በመጨረሻም ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ሀዋሳ የኩላሊት ዕጥበት ህክምና ማዕከል ከሲዳማ ክልሉ ገንዘብ ቢሮ ለተደረገው የጄኔሬተር ድጋፍ እና ጉብኝት በማዕከሉ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ወይዘሮ የሻረግ በየነ አበበ ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ሐዋሳ የኩላሊት እጥበት ማዕከል የሕክምና መሳሪያዎችን በመለገስ ለኩላሊት ሕመምተኞች የሚሰጠውን የሕክምና አገልግሎት ለማጠናከር የላቀ አስተዋፅ...
13/08/2026

ወይዘሮ የሻረግ በየነ አበበ ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ሐዋሳ የኩላሊት እጥበት ማዕከል የሕክምና መሳሪያዎችን በመለገስ ለኩላሊት ሕመምተኞች የሚሰጠውን የሕክምና አገልግሎት ለማጠናከር የላቀ አስተዋፅኦ አድርገዋል።

ወይዘሮ የሻረግ በየነ አበበ ለማዕከሉ ያደረጉትን የሕክምና መሳሪያዎች ልገሳ በእናታቸው መታሰቢያነት ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ያበረከቱ ሲሆን፣ ለተደረገልን የላቀ ድጋፍ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ለእናታቸው ፈጣሪ የዘላለም ዕረፍትን እንዲሰጣቸው እየተመኘን፣ ለመታሰቢያቸው የተደረገው ይህ በጎ ተግባር ለብዙ የኩላሊት ሕመምተኞች ሕይወትን ለማገዝ እና ተስፋን ለማጠናከር የሚያገለግል ዘላቂ መታሰቢያ ይሁን።

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

08/08/2026

❤️ Sponsor a child or support an elder for just $10/month.

Click the link, choose your child or elder, and start making a difference today. 🤝

https://share.google/n5fxLYaso4FWT5LpK

Address

ፒያሳ ገዳም ስፍር 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ፊት ለፊት ኣራዳ ወረዳ 5 ግቢ
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mary Joy Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Mary Joy Ethiopia:

Shortcuts

Share