15/08/2026
የቀጠናዊ ትስስር እና ልምድ ልውውጥ፡- አዲስ የእድገት ምዕራፍ❗️
🔰ባሳለፍነው ሳምንት በ National Care Leaver's Associations Coalition Ethiopia (NCLAC) አስተባባሪነት የ Somaliland Care Leavers Organisation (SOCLO) ከፍተኛ አመራሮች እና ተወካዮች በአዲስ አበባ ለ 4 ቀናት የአቅም ግንባታ እና የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አድርገዋል። በቆይታቸውም የኬር ሊቨርስ ማህበራትን፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን፣ የቤተሰብ መምሪያ ማህበርን እና የ Care Leavers ማህበራትን ገቢ ማስገኛ (IGAs) እንቅስቃሴዎች ጎብኝተዋል።
🔰ከነዚህ ተቋማት መካከል ማህበራችን የቀድሞ ኤስ .ኦ . ኤስ ወጣቶች ማህበር ኢትዮጲያ / SOS Almuni Youth Association Ethiopia አንዱ የነበረ ሲሆን፣ እንግዶቻችንን በዋና ቢሮአችን ሞቅ ባለ ሁኔታ ተቀብለን ጥሩ የልምድ ልውውጥ እና ውይይት ጊዜዎች አሳልፈናል ። በቢሮችን በነበራቸው ቆይታ የማህበራችንን ምስረታ ምን እንደሚመስል፣ የነበሩ ተሞክሮዎችን፣ የተከናወኑ አበይት ተግባራትን እና የአሁናዊ ስትራቴጂካዊ ትኩረት አቅጣጫዎችን ገለፃ አድርገናል። በመቀጠልም የማህበራችን ገቢ ማስገኛ ቢዝነስ ወደሆነው Vision Coffee House በማቅናት፣ ተቋሙ እንዴት እንደሚሰራ ገለፃ በማድረግ ከምርጥ ቡና ግብዣ ጋር ቀጣይነት ባላቸው ትስስሮች እና በኢኮኖሚያዊ አቅም ግንባታ ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።
🔰ይህ አይነቱ ቀጠናዊ ትስስር፣ በኬር ሊቨርስ ወጣቶች መካከል ያለውን የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት ግንኙነት ከማጠናከሩ ባለፈ፣ ድበር ተሻጋሪ እውቀትና ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ፣ ዘላቂ የገቢ ማስገኛ ስትራቴጂዎችን ለመቅረጽ እና በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ የወጣቶችን ድምፅ እና ስትራቴጂካዊ ውክልና ለማጎልበት አዲስ ትልልቅ በር የሚከፍት በመሆኑ ሊቀጥል እና ሊበረታታ ይገባል እንላለን ።
# # # # # # # # # # # # # #
: 👉A Milestone inCross-Border Care Leaver Empowerment!
🔰Last week, under the coordination of the National Care Leavers Association Coalition (NCLAC), executive leaders and representatives from the Somaliland Care Leavers Organization (SOCLO) completed a productive 4-day capacity-building and experience-sharing visit in Addis Ababa. Their itinerary included visits to care leavers' associations, government offices, the Family Guidance Association, and various Income-Generating Activities (IGAs) run by care leavers.
🔰As one of the host institutions, SOS Alumni Youth Association Ethiopia was honored to welcome the delegation to our head office. During our session, we shared the story of our association's establishment, key achievements, lessons learned, and current strategic directions.
Following our main office meeting, we visited our flagship IGA, Vision Coffee House. Over a cup of specialty coffee, we demonstrated the operational model of the business and held engaging discussions centered on economic empowerment and building sustainable, long-term partnerships.
✅️Regional engagements like this go beyond strengthening bonds among care leavers—they create vital opportunities for cross-border knowledge sharing, sustainable revenue strategy development, and amplification of youth voices across East Africa. We look forward to building on this momentum and encouraging further collaboration in the region.
SOS Children's Villages in Ethiopia SOS Children's Villages Eastern and Southern Africa SOS Børnebyerne SOS-Kinderdörfer weltweit African Union Embassy of Denmark in Ethiopia SOS Children's Villages International