Ethiopia A New Horizon of Hope

Ethiopia A New Horizon of Hope Striving to make Ethiopia a symbol of African prosperity

20/12/2025

ቃታ በመሳብ የሚመጣ ማህበራዊ ቀውስ እንጂ መፍትሔ የለም

15/12/2025

ከጊዜ ኋላ እንድንገኝ ያደረገን #ዐቢቹ

03/12/2025

በብሔራዊ ጥቅም ድርድር የለም #ኢትዮጵያ #ቀይባህር

*ለዓመታት ተኝተናል ፣ አሁን ግን ላንተኛ እንደሀገር ነቅተናል‼️* "በቦሌም በባሌም ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ትሆናለች። ከ10 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 200 ሚሊዮን ሊደርስ...
25/10/2025

*ለዓመታት ተኝተናል ፣ አሁን ግን ላንተኛ እንደሀገር ነቅተናል‼️*

"በቦሌም በባሌም ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ትሆናለች። ከ10 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 200 ሚሊዮን ሊደርስ ይችላል። 200 ሚሊዮን ሕዝብ በ2 ሚሊዮን ሕዝብ መታፈን የለበትም። ሀገራችን የተፈጥሮ ሀብቷን እንዳትጠቀም በውስጣዊ ግጭት እንድታተኩርና ለዘመናት በድህነትና ኋላቀርነት እንድትቆይ የሚፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ሴራ በጀግናው ሰራዊታችን ጀግንነት ፣ በመላ ህዝባችን ድጋፍና በመሪዎቻችን በሳል አመራር ሰጭነት በመበጣጠስ ወደ ሰላምና ልማት እየተሸጋገርን እንገኛለን። የተፈጥሮ ሀብታችንን ተጠቅመን እንዳንበለፅግ የሚሰሩ ታሪካዊ ጠላቶቻችንና የባዕዳን አቤት ባይ ሀይሎችን እኩይ ሴራ በማክሸፍ የልማት ፣ የሰላምና የመንሰራራት መንገዳችንን ጀምረናል። ላለፋት ሰላሳ ዓመታት ተኝተናል ፣ አሁን ግን ላንተኛ እንደሀገር ነቅተናል። የሀገራችን የህልውና ጥያቄ የሆነውን የሰላም ፣ የልማትና የባህር በር ተጠቃሚነት እናሳካለን "
- ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ዛሬ በ118ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን በዓል ላይ ከተናገሩት

ከሳርቤት - ጀርመን አደባባይ - ጋርመነት ፉሪ  የሚዘልቀው የኮሪደር ልማት ምን ይዟል? 👉 እስከ 60 ሜትር የሚሰፋ 16 ነጥብ 5 ኪ.ሜ አስፓልት መንገድ (በተጨማሪ 3 ነጥብ 5 ኪ. ሜ የው...
25/10/2025

ከሳርቤት - ጀርመን አደባባይ - ጋርመነት ፉሪ የሚዘልቀው የኮሪደር ልማት ምን ይዟል?

👉 እስከ 60 ሜትር የሚሰፋ 16 ነጥብ 5 ኪ.ሜ አስፓልት መንገድ (በተጨማሪ 3 ነጥብ 5 ኪ. ሜ የውስጥ ለውስጥ መንገድ) ያለው፣
👉 33 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ፣
👉 13 ነጥብ 3 ኪ.ሜ የሳይክል መንገድ፣
👉 21 የተለያዩ ፕላዛዎች፣
👉 ክረምት ከበጋ፣ በቀን እና በምሽት አገልግሎት የሚሰጡ 20 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣
👉 20 የልጆች መጫወቻ ቦታዎች፣
👉 5 ነጥብ 2 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የወንዝ ዳርቻ ልማት፣
👉 20 የመኪና ማቆሚያ ቦታና ተርሚናሎች፣ 1 የመኪና ቻርጂንግ ስቴሽን፣
👉 በግለሰቦች እና በመንግስት የተገነቡ 1 ሺህ 107 የንግድ ቤቶች፣
👉 50 ነጥብ 5 ሄክታር ስፋት ያላቸዉ አረንጓዴ ቦታዎች፣
👉 40 የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች፣
👉 38 የታክሲና አውቶቡስ ቤይ፣
👉 13 ካፌዎች እና 1 ሬስቶራንት እንዲሁም ከ1 ሄክታር በላይ የነርሰሪ ቦታን በዉስጡ አካትቷል።

የባህር በርን ጨምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ስብራቶችን ለመጠገን ከባለድርሻዎች ጋር በትጋት ይሰራል - ብልፅግና ፓርቲ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የባህር በርን ጨምሮ ቀሪ የኢትዮ...
25/10/2025

የባህር በርን ጨምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ስብራቶችን ለመጠገን ከባለድርሻዎች ጋር በትጋት ይሰራል - ብልፅግና ፓርቲ

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የባህር በርን ጨምሮ ቀሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ስብራቶችን ለመጠገን ከባለድርሻ አካላት ጋር በትጋት ይሰራል አለ።

የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ እንዳሉት፤ የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮችና የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ መክሮ አቅጣጫ አስቀምጧል።

የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና የማረጋገጥ ራዕይን ሰንቆ ወደ ተግባር የገባው ፓርቲው ባለፉት ዓመታት ለህዝብ ቃል የገባውን በውጤታማነት እየፈጸመ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያን ቀሪ ስብራቶች ለመጠገን ከባለድርሻ አካላት ጋር በትጋት እንደሚሰራ ተናግረው፤ ብሔራዊ ጥቅምን ማዕከል ያደረጉ የተሟላ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንደሚወጣ ገልፀዋል።

ባለፉት ዓመታት በተሠሩ የልማት ስራዎች ኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ውጤት መምጣቱን ገልጸው፤ ለአብነትም ባለፈው ዓመት የ9 ነጥብ 2 በመቶ እድገት መመዝገቡን ተናግረዋል።

የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር እየተረጋገጠ መሆኑን ሥራ አስፈጻሚው መገምገሙን ጠቅሰው፤ በዚህም ኢኮኖሚው ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪና ዘመናዊ አገልግሎት እየተሸጋገረ ይገኛል ብለዋል።

በገቢ ማሰባሰብ፣ በወጪ ንግድ እና በተኪ ምርት አመርቂ ውጤት መመዝገቡን በማንሳት አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገቱ ፈጣን ብቻ ሳይሆን አካታች፣ ጥራት ያለውና የህዝቡን ኑሮ በተጨባጭ እያሻሻለ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን በተጀመሩ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸው፤ በሰው ተኮር ስራዎችም በርካታ አቅመ ደካማ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በቀጣይም ተረጂነትን የማስወገድ፣ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለማሟላት በቂ ፈንድ የመያዝ እንዲሁም ብሔራዊ የመጠባበቂያ ክምችትን በራስ አቅም የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሰላም እና የፖለቲካ ጉዳዮችን መገምገሙን በማንሳት ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካት የበኩሉን ሚና ለመወጣት ቁርጠኛ መሆኑን ማረጋገጡን ጠቅሰዋል።

መጪው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ተአማኒ፣ ግልጽና አሳታፊ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ ፓርቲው የድርሻውን እንደሚወጣም ገልጸዋል።

ውስን የሰላምና ፀጥታ ችግር የነበረባቸውን አካባቢዎችን ለማረጋጋት መንግስትና ህዝብ በጋራ በሰሩት ስራ ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል።

የፖለቲካ ጥያቄ ያለው ማንኛውም አካል ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ምህዳር መፈጠሩን ገልጸው፤ ፓርቲውና የሚመራው መንግስት ሁልጊዜም በራቸው ለሰላም ክፍት ነው ብለዋል።

በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ስብሰባ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ ለማድረግ የተቀመጠው አቅጣጫ ወደ ተጨባጭ ተግባር መግባቱን ተገምግሟል ነው ያሉት።

በዚህም የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የማስፋትና የዲጂታላይዜሽን ስራዎች እየተከናወነ መሆኑን አመልክተው፤ እስካሁንም 16 ማዕከላት ተገንብተው አገልግሎት እየሠጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በመሶብ ማዕከላት የህዝቡ እርካታ ወደ 95 መቶ መድረሱን ገልጸው፤ ማዕከላቱን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ 100 ለማድረስ እንዲሰራ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አቅጣጫ ማስቀመጡን ተናግረዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ጠንካራ መንግስትና ሀገር ለመገንባት የያዘውን ግብ ለማሳካት የአመራርና አባላቱን አቅም የሚያጎለብቱ የተለያዩ ተግባራትን እንዳከናወነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አመራርና አባላቱ በተሠጣቸው ተልዕኮ ልክ በየደረጃው የመገምገም ስራ ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰው፤ በምዘናው መሠረት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡት እውቅና መሰጠቱን ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል የተሰጣቸውን ሀገራዊና የፓርቲ ተልዕኮ በአግባቡ ባልተወጡ አመራሮች ላይ የተለያዩ ርምጃዎችን መወሰዱን ተናግረው፤ ፓርቲው ህዝብና ሀገርን ተጠቃሚ ለማድረግ የጀመራችውን ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

Lukashenko: Belarus seeks to strengthen cooperation with Ethiopiaየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ከቤላሩሱ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሽንኮ ጋር ...
29/07/2025

Lukashenko: Belarus seeks to strengthen cooperation with Ethiopia

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ከቤላሩሱ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሽንኮ ጋር በሀገሪቱ ዋና ከተማ Minsk ተገኝተው ውይይት አድርገዋል።

የሀገሪቱ የዜና ምንጭ ቤልታ እንደዘገበው ሁለቱ ሀገራት ኢትዮጵያ ውስጥ በሽርክና የትራክተር ፋብሪካ የመገንባት ውጥን ያላቸው ሲሆን ሉካሽንኮ የኢትዮጵያ መንግስትን ቤላሩስ የብሪክስ አባል ትሆን ዘንድ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ፋብሪካውን በጋራ እንገነባለን ፣ የኢንጅነሪንግ ባለሙያዎቻችሁንም ለማሰልጠን ከጎናችሁ ነን ነው ያሉት የቤላሩሱ ፕሬዝዳንት ።

🤙 🤙 🤙

ሀገርም እንደ ሰው በምርጫው ነው ነገውን የሚያቀናው ። ወይ ውጊያና ግጭት መርጠህ እንደ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ተዝቆ የማያልቅ ሀብት ላይ ተቀምጠህ በድህነት ትኖራለህ አልያም እንደ ቦትስዋና ጦርነት የፋራ ነው ብለህ በዝምታ ኢኮኖሚህን ታስመነድጋለህ the choice is yours !

ሊንኩ comment መስጫው ላይ ተቀመጧል።

Egypt Independent  በትናንትናው ዕትሙ ~ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ገንብታ ለምረቃ ዝግጁ ያደረገችው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በወንዙ ላይ የገነባችው የመጀመሪያ እንጂ የመጨ...
25/07/2025

Egypt Independent በትናንትናው ዕትሙ ~ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ገንብታ ለምረቃ ዝግጁ ያደረገችው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በወንዙ ላይ የገነባችው የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ ግድብ አይደለም፤ ገና ብዙ ተጨማሪ ግድቦች በወንዛችን ላይ እንገነባለን ~ ሲሉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተናገሩ የሚል ሰፊ ሀተታ አስነብቦ ወደረኞቻችንን ድንኳን ጥሎ እያላቀሳ'ቸው ይገኛል — ምንም ማድረግ አይቻልም❗️❗️❗️🤙 🤙 🤙 💪
👉 👉 👉
በድምሩ 11,071 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል የሚያመነጩ የሦስት ከፍተኛ ግድቦች ማለትም የካራዶቢ፣ የማቢል እና የመንዳያ ግድቦች ግንባታ በመጪው አምስት አመት ውስጥ ይጠናቀቃሉ።
👊 👊 👊
‟ገና ገና ገና ምን አይተሽ
ልሂድ ትያለሽ”
እንዲል ከያኒው ገና ምኑ ግድብ ታየና ነው ዋይታውና ሙሾው? ሰከን በሉ 👉❗️❗️❗️
👌 👌 👌

Abiy Ahmed Ali ነው ሰውዬው 🙏💖🙏 የአባቶቹ ልጅ❗️❗️❗️
#ህዳሴ #ኢትዮጵያ #ግድብ #አባይ
Getnet Almaw Tiruneh Prosperity Party - ብልፅግና

𝐂𝐥𝐚𝐫𝐢𝐟𝐲𝐢𝐧𝐠 𝐭𝐡𝐞 𝐅𝐚𝐜𝐭𝐬: 𝐆𝐄𝐑𝐃 𝐈𝐬 𝐚𝐧 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚𝐧 𝐀𝐜𝐡𝐢𝐞𝐯𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭, 𝐁𝐮𝐢𝐥𝐭 𝐛𝐲 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚𝐧𝐬Recent comments by U.S. President Donald Trum...
16/07/2025

𝐂𝐥𝐚𝐫𝐢𝐟𝐲𝐢𝐧𝐠 𝐭𝐡𝐞 𝐅𝐚𝐜𝐭𝐬: 𝐆𝐄𝐑𝐃 𝐈𝐬 𝐚𝐧 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚𝐧 𝐀𝐜𝐡𝐢𝐞𝐯𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭, 𝐁𝐮𝐢𝐥𝐭 𝐛𝐲 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚𝐧𝐬

Recent comments by U.S. President Donald Trump regarding Ethiopia’s Grand Renaissance Dam (GERD) have again raised concerns due to misunderstanding about the project's source of funding. This is now the second time such incorrect claims have been made, and it is important to respond with clarity, respect, and truth.

To begin with: The GERD has never been financed by the United States or any external party. The dam was built entirely by Ethiopians, funded through public contributions, diaspora support, and domestic resources. No loans. No donor money. This decision was intentional, reflecting Ethiopia’s desire to uphold national sovereignty and self-reliant development. GERD stands as a powerful example of what Ethiopians can achieve when united by purpose.

Geographically, the dam is located in northwestern Ethiopia, near the Sudanese border. Ethiopia and Egypt do not share a land border; they are linked by the Nile River, over 85% of its flow originates from Ethiopia. It is Ethiopia’s long-held position that this shared river should be a source of cooperation, not division.
The characterization that the dam as “closing up water going to the Nile”, is a misconception. GERD is a run-of-the-river project designed to regulate water flow, reduce flooding, and minimize evaporation losses, not to withhold water. A 2013 International Panel of Experts, which included representatives from Ethiopia, Egypt and Sudan, affirmed that GERD complies with international standards and would not cause significant harm downstream.

Most importantly, a number of Egyptian scholars and water experts have also acknowledged GERD’s benefits. Dr. Alaa el-Zawahri, a former negotiator, and Dr. Nader Noureddin, a well-respected hydrologist, have both emphasized the dam’s potential to contribute to regional stability and water management, if framed within a spirit of collaboration.

International media, including Reuters, The Guardian, and Al Jazeera, have recognized GERD as a symbol of African progress, regional integration, and clean energy potential for millions across East Africa.

In conclusion, the GERD is a symbol of Ethiopian self-reliance and its right to development. Misrepresenting it undermines both truth and regional trust. We call on all external actors to support respectful, fact-based dialogue. Ethiopia remains committed to using the Nile responsibly, guided by principles of equitable and reasonable utility of the water.
of &

Bara baajataa 2017 xumurameen galii birrii biliyoona 233 sassaabuun hojiiwwan misooma magaalaa keenyaa sadarkaa olaanaan...
15/07/2025

Bara baajataa 2017 xumurameen galii birrii biliyoona 233 sassaabuun hojiiwwan misooma magaalaa keenyaa sadarkaa olaanaan akka raawwatamu kan nu dandeessisan hojjettoota waajjira galiiwwaniif sagantaa beekamtii fi galateeffannaa gaggeessineerra.

Waaqni Itoophiyaa fi Uummata Ishee Haa Eebbisu.

በተጠናቀቀው የ2017 በጀት አመት 233 ቢሊዬን ብር ገቢ በመሰብሰብ የከተማችንን የልማት ስራዎች በላቀ ደረጃ እንድንፈፅም ላስቻሉን የገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች የእዉቅና እና የምስጋና መርሃግብር አካሄደናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ Mayor Office of Addis Ababa

ምሥጋና ለብሄረተኞች 🙏❤🙏© ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይ ጠላት ናቸው አሉን - እሺም አልናቸው። © ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማራ ጠላት ናቸው አሉን - እሺም አልናቸው። © ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦሮሞ...
15/07/2025

ምሥጋና ለብሄረተኞች 🙏❤🙏

© ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይ ጠላት ናቸው አሉን - እሺም አልናቸው።

© ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማራ ጠላት ናቸው አሉን - እሺም አልናቸው።

© ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦሮሞ ጠላት ናቸው አሉን - እሺም አልናቸው ።

የሶስቱ ብሄሮች ጽንፍ ፖለቲከኞች በኢትዮጵያዊነትና የብሄር ብሄረተኝነት መሀከል ግራ የተጋቡትን በርካታ ኢትዮጵያውያን "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያንተን/ያንቺን ብሄር ይጠላል" ሲሉ አሳምነው ወደ ብሄር ፖለቲካቸው ወሰዱልን።

መሀከለኛውን መንገድ center politics የምንደግፈው ኢትዮጵያውያን ብሄር ሳንለይ የጠቅላይ ሚኒስትሩን Abiy Ahmed Ali ኢትዮጵያን የማጽናት ፖሊሲ በነጻነት ለመደገፍ አስችሎናል። ለዚህም የብሄር ፖለቲካ መሪዎችን እናመሰግናለን ልንል ግድ ነው።

አማካዩ መንገድ center politics አሸናፊ ነው !
ኢትዮጵያ አዲሲቷ የተስፋ አድማስ❗️❗️❗️

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia A New Horizon of Hope posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share