Bole 04 communicatiion

Bole 04 communicatiion ለአንድ ተቋም መረጃ ሀብት ነው፡፡

15/09/2026
15/09/2026
ትውልድ በዕውቀት የሚገነባበት የ2019 የትምህርት ዘመን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ።በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የ2019 የትምህርት ዘመን በዛሬው ዕለት በወረዳው በሚ...
15/09/2026

ትውልድ በዕውቀት የሚገነባበት የ2019 የትምህርት ዘመን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ።

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የ2019 የትምህርት ዘመን በዛሬው ዕለት በወረዳው በሚገኙ ሁሉም የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች በይፋ ተጀምሯል።

አዲስ መንፈስ እና ከፍተኛ ተነሳሽነት በተንጸባረቀበት የዛሬው የትምህርት አጀማመር፤ ተማሪዎችና መምህራን በታላቅ ደስታ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል።

የዛሬው የ2019 የትምህርት ዘመን የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ትኩረቱን ሙሉ በሙሉ በትውልድ ግንባታ፣ በሕብረተሰቡ ሰፊ ርብርብ እና በትምህርት ጥራት ማሻሻያ ላይ ያደረገ ሲሆን፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች ለዘንድሮው ከፍታ እንደ መሠረት መሆናቸው ተመላክቷል።

ትምህርት ቤቶች በሮቻቸውን ለነባር እና ለአዳዲስ ተማሪዎች ክፍት ሲያደርጉ፤ ዋናው ግብ የነገን ሀገር ተረካቢ ህጻናትን በሥነ-ምግባር፣ በዕውቀት እና በብቃት ማነጽ መሆኑ በግልጽ ታይቷል።

በማስጀመሪያው የተገኙት የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት እንደገለጹት፤ ትምህርትን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ እና ጥራቱን ለማረጋገጥ የተጀመረው ርብርብ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ወላጆች፣ መምህራን እና መላው የወረዳው ማህበረሰብ ለተማሪዎች ስኬት የተለመደውን አጋርነት እንዲያጠናክሩም ጥሪ አቅረበዋል።

ይህ በዛሬው ዕለት በሁሉም የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች የተጀመረው የትምህርት ዘመን፤ የቦሌ ክፍለ ከተማን የትውልድ ግንባታ እና የትምህርት ጥራት ግቦች ከምንጊዜውም በላይ እውን የሚያደርግ፣ ታላቅና የላቀ ውጤት የሚመዘገብበት ታሪካዊ ጅምር ሆኗል።

መስከረም 5/2019
ቦሌ ወረዳ 04 ኮምኒኬሽን

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት የሀገራችን ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊትን ጠብቀው እንዲከበሩ በጋራ መስራት ይገባናል ።በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር በዚህ ወር በታላቅ ድምቀት ...
15/09/2026

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት የሀገራችን ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊትን ጠብቀው እንዲከበሩ በጋራ መስራት ይገባናል ።

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር በዚህ ወር በታላቅ ድምቀት የሚከበሩት የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበሩ ለማስቻል በተዘጋጀው ሰነድ ዙሪያ ከወረዳው ሰራተኞች ጋር የፓናል ውይይት ተካሄደ ።

የወረዳው የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሀላፊ አቶ ዋሲሁን አለማየሁ የዘንድሮውን የበዓል አከባበር ከሌላው ጊዜ ለየት የሚያደርገው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫን በስኬት ፣ በሀገራዊ ምክክር ነባር ችግሮቻችንን በጋራ ለመፍታት በምንተጋበት ማግስት ፤ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ደምቆ የታወጀበት ወቅት ፣ የዲፕሎማሲ አቅማችን ከፍታ ለአለም የታየበት በመሆኑ በዓሉን ልዩ እንደሚያደርገው ገልጸው ፤ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ኢትዮጵያ በማይዳሰስ ቅርስነት UNESCO ላይ ካስመዘገበቻቸው ቅርሶቻችን መካከል ተጠቃሽ መሆኑን አፅንኦት ጠቁመው ፤ ወንድማማችነት ፣ እህትማማችነት እና አብሮነትን በማጠናከር ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ሃብቶቻችን ይዘታቸውን ሳይለቁ እና የኩራታችን ምንጭ ብቻ ሳይሆኑ የቱሪዝም እና የገቢ ምንጮች ሆነው እንዲያገለግሉ ሰላማዊነታቸውን ማስጠበቅ የሁሉም ህብረተሰብ ክፍል ሀላፊነት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አያይዘውም የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት የአደባባይ በዓላት እንደመሆናቸው መጠን የሀገራችን ባህልና ትውፊት ጠበቀው ሲከበሩ ለአብሮነታችን የሚያስተላልፉት መልዕክት የጎላ ከመሆኑ ባሻገር በዓላቱ ለከተማችን ጠቀሜታው ዘርፈ ብዙ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

የወረዳው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ማስተባበርያ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ አሸብር አበበ የመስቀል ደመራ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ብሎም የዓለም አቀፍ ህዝብ ቅርስነት ደረጃ የደረሰ በመሆኑ ለሀገራችን ገፅታ ግንባታ አስተዋፅኦ ያለው ነው፤ ሁሉም በአንድነት ሊያከብረው ይገባል ብለዋል። በተመሳሳይ የኢሬቻ በዓል ወንድማማችነትና ፍቅር፣ ለምስጋናና ለይቅርታ እንዲሁም ለአንድነት የሚከበር በመሆኑ በጋራ ሀገራዊ ስሜት ማክበር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

5/1/2019 ዓ.ም
ቦሌ ወረዳ 04 ኮምኒኬሽን

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት የሀገራችን ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊትን ጠብቀው እንዲከበሩ በጋራ መስራት ይገባናል ።በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር በዚህ ወር በታላቅ ድምቀት ...
14/09/2026

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት የሀገራችን ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊትን ጠብቀው እንዲከበሩ በጋራ መስራት ይገባናል ።

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር በዚህ ወር በታላቅ ድምቀት የሚከበሩት የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበሩ ለማስቻል በተዘጋጀው ሰነድ ዙሪያ ከወረዳው ሰራተኞች ጋር የፓናል ውይይት ተካሄደ ።

የወረዳው የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሀላፊ አቶ ዋሲሁን አለማየሁ የዘንድሮውን የበዓል አከባበር ከሌላው ጊዜ ለየት የሚያደርገው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫን በስኬት ፣ በሀገራዊ ምክክር ነባር ችግሮቻችንን በጋራ ለመፍታት በምንተጋበት ማግስት ፤ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ደምቆ የታወጀበት ወቅት ፣ የዲፕሎማሲ አቅማችን ከፍታ ለአለም የታየበት በመሆኑ በዓሉን ልዩ እንደሚያደርገው ገልጸው ፤ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ኢትዮጵያ በማይዳሰስ ቅርስነት UNESCO ላይ ካስመዘገበቻቸው ቅርሶቻችን መካከል ተጠቃሽ መሆኑን አፅንኦት ጠቁመው ፤ ወንድማማችነት ፣ እህትማማችነት እና አብሮነትን በማጠናከር ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ሃብቶቻችን ይዘታቸውን ሳይለቁ እና የኩራታችን ምንጭ ብቻ ሳይሆኑ የቱሪዝም እና የገቢ ምንጮች ሆነው እንዲያገለግሉ ሰላማዊነታቸውን ማስጠበቅ የሁሉም ህብረተሰብ ክፍል ሀላፊነት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አያይዘውም የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት የአደባባይ በዓላት እንደመሆናቸው መጠን የሀገራችን ባህልና ትውፊት ጠበቀው ሲከበሩ ለአብሮነታችን የሚያስተላልፉት መልዕክት የጎላ ከመሆኑ ባሻገር በዓላቱ ለከተማችን ጠቀሜታው ዘርፈ ብዙ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

የወረዳው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ማስተባበርያ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ አሸብር አበበ የመስቀል ደመራ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ብሎም የዓለም አቀፍ ህዝብ ቅርስነት ደረጃ የደረሰ በመሆኑ ለሀገራችን ገፅታ ግንባታ አስተዋፅኦ ያለው ነው፤ ሁሉም በአንድነት ሊያከብረው ይገባል ብለዋል። በተመሳሳይ የኢሬቻ በዓል ወንድማማችነትና ፍቅር፣ ለምስጋናና ለይቅርታ እንዲሁም ለአንድነት የሚከበር በመሆኑ በጋራ ሀገራዊ ስሜት ማክበር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

Address

Behind To Plaza Hotel
Addis Ababa
251

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bole 04 communicatiion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Bole 04 communicatiion:

Shortcuts

Share