24/08/2026
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሄርን ያመስግን!
መልካም ሰዎች ድሮም ነበሩ ዛሬም አሉ ወደፊትም ይኖራሉ።
መልካሞች የጊዜና የሁኔታ ባሪያ አይደሉም። ከፍታና ዝቅታ የመልካምነታቸው በር መክፈቻ እጄታ አይደለም።
ሁሌም ያካፍላሉ።
ከሀገር ውጪ የሚኖሩ የድርጅታችን የረጅም ጊዜ ደጋፊዎች ናቸው በየዓመቱ ደግሞ የልደት በዓላቸውን ምክንያት በማድረግ ያካፍላሉ።
በየዓመቱ እንደሚያደርጉት ነሀሴ 17/2018 ዓ.ም የአይናለምና የዘኒ ልደት በዓል በወጣት ሳሚ ተወካይነት የምሳ ግብዣና ህፃናትን በደስታ የሚያስቦርቀው የኬክ ቆረሳና የጣፋጭ ግብዣ በማድረግ እናቶችን ከነልጆቻቸውን እንዲህ ደስስስስ አሰኝተዋል።
መልካም ልደት! እንኳን ተወለዳችሁልን!!!
የምድሩንም የሰማዩንም ፀጋ በረከት ያብዛላችሁ! ሁሌ ስጡ!!!
ልዩ ምስጋናችን:-
ለቀድሞ የመሠረት በጎ አድራጎት ድርጅት ሠራተኞች:-
ሲ/ር ሌሊሴ እና ትቅደም