Women and Girls Support-Ethiopia (WGS-E)

Call Website Contact the organization

Women and Girls Support-Ethiopia (WGS-E) Women and Girls Support Ethiopia-(WGS-E)


The project directly targeted 2500 high school girls from low income families select None government organization

ዉድ ኢትዩዸያዉያን ወገኖቼ እንኳን ለአዲሱ ዓመት ፳፻፲፱ ዓ.ም  በሰላም አደረሰን:በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት እና የአብሮነት ይሁንልን።
10/09/2026

ዉድ ኢትዩዸያዉያን ወገኖቼ እንኳን ለአዲሱ ዓመት ፳፻፲፱ ዓ.ም በሰላም አደረሰን:

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት እና የአብሮነት ይሁንልን።

11/07/2026
Every girl knows that moment.Your period comes without warning. You ask your friend, she doesn't have one either. You le...
26/06/2026

Every girl knows that moment.
Your period comes without warning. You ask your friend, she doesn't have one either.
You leave class quietly, hoping nothing has leaked through.
That moment costs girls their confidence, their focus, and sometimes their education.
UNFPA Ethiopia with the support of The Embassy of Canada to Ethiopia and Royal Norwegian Embassy in Addis Ababa is taking the first steps to change that, by installing menstrual pad dispensing machines in schools.
This solution works. Now it needs to reach every school.
Every girl deserves to stay in the room. 🔴


UN in Ethiopia UNFPA East and Southern Africa Regional Office UNFPA Sk Kouame
Women and girls support Ethiopia

https://www.instagram.com/reel/DZCTWGWsxk_/?igsh=cGkwbG0ybGR6Y2R4

26/06/2026
ታላቅ የምረቃና የድጋፍ ፕሮግራም፦ የ"እምዬ" ዲጂታል ማሽን በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተመረቀች!ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. — የክብር እንግዳው ክቡር ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ (የጤና ሚኒስቴር...
26/06/2026

ታላቅ የምረቃና የድጋፍ ፕሮግራም፦ የ"እምዬ" ዲጂታል ማሽን በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተመረቀች!

ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. — የክብር እንግዳው ክቡር ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ (የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ) በተገኙበት፣ አጋር አካላት በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በመሰብሰብ ዓለም አቀፍ የወር አበባ ንፅህና ቀንን በታላቅ ድምቀት በጋራ አክብረዋል።

በዕለቱ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ባስተላለፉት መልዕክት፦ "ትምህርት የአንድ ሀገር ልማት መሠረት ነው። ሴት ልጆችን ማስተማር ደግሞ ሀገርን ሙሉ በሙሉ መለወጥ ነው" በማለት የዘርፉን ወሳኝነት አፅንኦት ሰጥተውታል።

ይህ ታላቅ ፕሮግራም በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ተራድኦ ድርጅት (UN in Ethiopia)፣ በUNFPA ምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጠናዊ ቢሮ፣ በUNFPA እና በኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ትብብር የተዘጋጀ ነው።

"እምዬ" (EMMYE) የዲጂታል ማከፋፈያ ማሽን ምንድን ናት?
የወር አበባ ንፅህና አጠባበቅ ተደራሽነትን ይበልጥ ለማቃለልና ለማረጋገጥ፣ ከሴቶችና ልጃገረዶች ድጋፍ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር "እምዬ" (EMMYE) የተሰኘችው ዘመናዊ የዲጂታል የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ አገልግሎት መስጫ ማሽን በይፋ ተመርቃ ሥራ ጀምራለች። UNFPA እና DSW የዚህ ዘላቂ መፍትሄ አካል በመሆናቸው ታላቅ ኩራት ይሰማቸዋል።
በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሚገኙ ሴቶችና ሴት ልጃገረዶች የተደረገው ድጋፍ፦
✅ 1,000 የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ (Sanitary Pads) በነፃ ተደግፏል።
✅ ዘላቂና ቀጣይነት ያለው አቅርቦትን ለማረጋገጥ የሚያስችል 1 የሞዴስ ማከፋፈያ ማሽን (Dispensing Machine) በይፋ ተመርቋል።

"ማንኛዋም ሴት በየትኛውም ቦታና በማንኛውም ጊዜ የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ምርቶችን በክብር የማግኘት ሙሉ መብት አላት።"

የማሽኑ ዋና ዋና ጥቅሞችና አስፈላጊነት ከትምህርት ገበታ መስተጓጎልን ማስቀረት፦ ማሽኑ ሴት ልጆች በወር አበባ ወቅት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩና ትምህርታቸውን ያለ ምንም እንቅፋት እንዲከታተሉ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያበረክታል ክብርንና ግላዊነትን መጠበቅ፦ ብዙ ልጃገረዶች መምህራንን ወይም እኩዮቻቸውን ሞዴስ ለመጠየቅ ያፍራሉ ወይም ይጨነቃሉ። በትምህርት ቤታቸውና በተለያዩ ተቋማት የሚቀመጡት እነዚህ ማከፋፈያ ማሽኖች ክብራቸውን በጠበቀ መልኩ ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያገለግሉ የሚያስችል ድብቅና አስተማማኝ መፍትሔ ይሰጣሉ።
ለድንገተኛ ሁኔታ ዝግጁ መሆን፦ የወር አበባ አንዳንድ ጊዜ ባልተጠበቀ ሰዓት ሊመጣ ይችላል። ይህ ማሽን በቅርበት መገኘቱ ልጃገረዶች እንዳይደናገጡና እንዳይጨነቁ፣ እንዲሁም ትምህርታቸውን ወይም ሥራቸውን አቋርጠው ወደ ቤት የመሄድ ፍላጎትን ሙሉ በሙሉ ያስቀራል።

ማሽኑ ማየት ለተሳናቸው ተማሪዎች በድምፅ (Voice-guided) የታገዘ መመሪያ የሚሰጥ ሲሆን፣ የአካል ጉዳተኛ ሴት ተማሪዎችንም ፍላጎት በልዩ ሁኔታ ታሳቢ አድርጎና ምቹ ሆኖ የተቀረጸ ነው።

# women and girls support Ethiopia

🤝 ለአዲስ ምዕራፍ የሚሆን የትብብር ስምምነት ተፈረመ!የሴቶች እና ሴት ልጆች ድጋፍ ኢትዮጵያ (WGSE) ከ FI-LMI Design and Garment ጋር በመሆን የሴቶችን ሁለንተናዊ አቅም ለ...
16/06/2026

🤝 ለአዲስ ምዕራፍ የሚሆን የትብብር ስምምነት ተፈረመ!
የሴቶች እና ሴት ልጆች ድጋፍ ኢትዮጵያ (WGSE) ከ FI-LMI Design and Garment ጋር በመሆን የሴቶችን ሁለንተናዊ አቅም ለማሳደግ፣ የክህሎት ልማትን ለማስፋፋት እና በስራ ፈጠራ ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ የሚያስችለውን ታሪካዊ የመግባቢያ ስምምነት (MoU) በይፋ ተፈራርመዋል።

It is indeed a great source of pride and wonderful news for our country. The selection of H.E. Dr. Ergogie Tesfaye as th...
10/05/2026

It is indeed a great source of pride and wonderful news for our country. The selection of H.E. Dr. Ergogie Tesfaye as the "Best Performing Minister in Africa" at the Thamani Africa Awards 2026 for her exemplary work is a testament to the global recognition of the effective efforts being made by her Ministry and Ethiopia in the sectors of women’s empowerment and social development.
This award will serve as a great inspiration to other female leaders and social advocates across the continent. I would like to extend my heartfelt congratulations to the Honorable Minister and the entire staff of the Ministry.

09/05/2026
ባህላችን ውበታችን፣ አንድነታችን ጥንካሬያችን! 🇪🇹✨ለመላው የኢትዮጵያ ወገኖቼ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን።ይህ በዓል የሰላም፣ የፍቅር እና የመረዳዳት ይሁንል...
19/03/2026

ባህላችን ውበታችን፣ አንድነታችን ጥንካሬያችን! 🇪🇹✨

ለመላው የኢትዮጵያ ወገኖቼ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን።
ይህ በዓል የሰላም፣ የፍቅር እና የመረዳዳት ይሁንልን።

ኢድ ሙባረክ! 🌙✨

🌹 እንኳን ለአለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 😎 በሰላም አደረሳችሁ! 🌹ሴት ልጅ የቤት ምሶሶ፣ የሀገር ብርሃን ናት!" 🌹“የሴት ልጅን ክብር ላወቀበት እና ላመነበት፤ ሴት ልጅ እናት ናት! እ...
07/03/2026

🌹 እንኳን ለአለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 😎 በሰላም አደረሳችሁ! 🌹

ሴት ልጅ የቤት ምሶሶ፣ የሀገር ብርሃን ናት!" 🌹

“የሴት ልጅን ክብር ላወቀበት እና ላመነበት፤ ሴት ልጅ እናት ናት! እህት ናት! ሚስት ናት! ነገ ደግሞ የአንተ ተተኪ ልጅህ ናት!”
ሴት ልጅ የሰው ዘር ፍሬ፣ የህይወት ምንጭ እና የቤተሰብ ዋልታ ናት። የሴት ልጅ ጥቅም ተዘርዝሮ አያልቅም፤ እርሷ ሰላም ስትሆን ነው ሀገር ሰላም የሚሆነው።
ዛሬ የምናስተምራት ሴት ልጅ፣ ነገ የምትገነባው ጠንካራ ሀገር አለ!
ጤናማ ትውልድ፣ የተረጋጋ ህብረተሰብ እና የበለፀገች ሀገር እንዲኖረን ሴት ልጆቻችንን መንከባከብ፣ ማክበር እና በትምህርት ማብቃት አማራጭ የሌለው ተግባራችን ሊሆን ይገባል።
ለእናንተ ለኢትዮጵያ እንቁዎች፣ ለጽናታችን ምንጮች እና ለቤታችን ብርሃኖች በሙሉ፦

መልካም የሴቶች ቀን ይሁንላችሁ! 🇪🇹🌼

Address

Arat Kilo
Addis Ababa
150040

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Women and Girls Support-Ethiopia (WGS-E) posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Women and Girls Support-Ethiopia (WGS-E):

Shortcuts

Share