Dejazmach Hailu Tesfaye Primary & Middle School

Dejazmach Hailu Tesfaye Primary & Middle School Educational Organization

"የምርጫዬ" መተግበሪያ አጠቃቀም …1.  “ምርጫዬ” የተሰኘውን የመራጮች መመዝገቢያ መተግበሪያ ከPlay Store / APP Store በማውረድ በስልክዎ ላይ ይጫኑ፣2.  በስልክዎ ላይ ከተጫኑ...
06/03/2026

"የምርጫዬ" መተግበሪያ አጠቃቀም …

1. “ምርጫዬ” የተሰኘውን የመራጮች መመዝገቢያ መተግበሪያ ከPlay Store / APP Store በማውረድ በስልክዎ ላይ ይጫኑ፣

2. በስልክዎ ላይ ከተጫኑ ዝርዝር መተግበሪያዎች ውስጥ “ምርጫዬ” የሚለውን መተግበሪያ ይክፈቱ፣

3. በመቀጠልም ከተከፈተው የ“ምርጫዬ” መተግበሪያ ላይ የሚጠቀሙበትን ቋንቋ ይምረጡ፣

4. ቋንቋ መርጠው ከገቡ በኋላ ከሚያገኟቸው ዝርዝሮች ውስጥ “የእርስዎን መገለጫ ይፍጠሩ” የሚለውን ይጫኑ፣

5. በመቀጠል “በፋይዳ አማካኝነት ወደ መለያ” የሚለውን አማራጭ ይጫኑ፣

6. የፋይዳ ገጹ ሲመጣልዎ ከፋይዳ መታወቂያዎት ላይ 16 አኅዝ ያለውን ቁጥር (FAN) ካስገቡ በኋላ በስልክዎ የሚላክልዎን ባለስድስት አኅዝ የአንድ ጊዜ ማረጋገጫ ቁጥር (OTP) ይሙሉ፣

7. መረጃዎን ከፋይዳ ሲያገኙ “ይቀጥሉ” የሚለውን በመጫን መተግበሪያው የሚጠይቅዎትን ቀሪ መረጃ በማስገባት መስማማትዎን በሳጥኑ ውስጥ ምልክት ያድርጉ፣

8. በመቀጠል ያስገቡትን መረጃ ወደ መተግበሪያው ለመላክ “አስገባ” የሚለውን በመጫን ከመተግበሪያው ቋሚ የመራጭነት መለያ ቁጥር ያገኛሉ፤ ይህ ሊይዙት የሚገባ ቋሚ የመራጭነት መለያ ቁጥርዎ ነው፣

9. ያስታውሱ! ቋሚ የመራጭነት መለያ ቁጥር አገኙ ማለት ምዝገባዎ ተጠናቋል ማለት አይደለም “ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ይመዝገቡ” የሚለውን መጫን ይኖርብዎታል፣

10. በመቀጠልም በአድራሻዎ መሠረት ቅርብ የሆነ የምርጫ ጣቢያ ለመምረጥ የምርጫ ጣቢያ ዝርዝር ያገኛሉ፣

11. ከሚያገኙት የምርጫ ጣቢያ ዝርዝሮች ውስጥ የሚቀርብዎን የምርጫ ጣቢያ በመምረጥ “ይመዝገቡ” የሚለውን ይጫናሉ፣

12. በመረጡት ምርጫ ክልል በኗሪነት ያልዎትን ቆይታ በዓመት እና በወር ያስገባሉ። ያስገቡትን መረጃ ትክክለኛነት በማረጋገጥ በሳጥኑ ላይ ምልክት በማድረግ ያረጋግጡ የሚለውን በመጫን ለምርጫው እራስዎን ይመዘግባሉ፣

13. በመቀጠል የመታወቂያዎን ዓይነት በመምረጥ የመረጡትን መታወቂያ ፊት እና ጀርባ ፎቶ ማንሣት እና ማያያዝ፣

14. መቀጠል ለምርጫ ቀን ይዘው የሚመጡት ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል የምርጫ ካርድ ከ48 ሰዓት በኋላ ከመተግበሪያው ያገኛሉ፣

15. ምርጫ ካርድዎን አትመው ለመያዝ “ወደ ዋና ገጽ ይመለሱ” የሚለውን አማራጭ በመጫን ዋና ገጽ ላይ የሚገኘውን “ያትሙ” የሚለውን አማራጭ መጫን ይኖርብዎታል።

21/02/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Ayele Kifle, Eyob Alemayehu Eyob Alemayehu, Muluken Derbe, Addisalem Zeleke, Tolasa Robele, Ferensay Fanta Wa, Marishet Gemechu

 #ህፃናት ላይ መስራት ሀገር ላይ መስራት ነው!!የአዲስ  ከተማ ክፍለ ከተማ  ወረዳ 03  አስተዳደር ደጃዝማች ኃይሉ ተስፋዬ ቅደመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ወላጅ፣ ተማሪ፣መምህራን  ህብረት  ...
19/02/2026

#ህፃናት ላይ መስራት ሀገር ላይ መስራት ነው!!

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ደጃዝማች ኃይሉ ተስፋዬ ቅደመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ወላጅ፣ ተማሪ፣መምህራን ህብረት (ወተመህ) እና ከህብረተሰቡ የተሰባሰቡ ለትምህርት ቤቱ መዋለ ህፃናት መጨዋቻ የሚሆን የትምህርት መማሪያ ቁሳቁሶችን እና መጫወቻ ዕቃዋችን ድጋፍ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራ እንደሚገኝ የተመህ ተወካይ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ አበዛ ገልጿል።

የቅደሜ 1ኛ ደረጃ አሰተባባሪ የሆኑት መ/ሪት ማረሸት ገመቹ እንዳሉት ህፃናት ላይ መስራት ሀገር ላይ መሆኑን በመገንዘብ ከህፃናት ጋር የተያያዙ በርካታ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፤ ከነዚህም ስራዎች መካከል የተለያዩ የትምህርት አጋዥ ቁሳቁሶች ለትምህርት ቤቱ አሰረክቧል። በወረዳው የሚገኙ ህፃናት አንድ ላይ በመሆን በተመቻቸላቸው የመጫወቻ ቦታ ላይ በአንድነት፣በፍቅርና በአብሮነት ሆነው ደስ የሚል ጊዜ እንዲያሳልፉ በማድረግ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸው እንዲዳበር እየተሰራ እንደሚገኝ ተነስቷል፤


የካቲት 12 /2018 ዓ.ም

የጥናትና ምርምር ፅብረቃ ሲካሄድ
10/02/2026

የጥናትና ምርምር ፅብረቃ ሲካሄድ

Address

Addis Ketema Infront Amanuel Hospital
Addis Ababa
00000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dejazmach Hailu Tesfaye Primary & Middle School posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share