ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን-Impact Makers Foundation

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን-Impact Makers Foundation Impact Makers Foundation (IMF) is an Ethiopian charity addressing gaps in education, capacity building, and research.

It empowers communities through training, workshops, and sustainable programs, aiming to drive social and economic transformation.

በነቀምቴ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን  ንቁ፣ ብቁ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪና ተምሳሌታዊ ዜጐችና ተቋማት በኢትዮጲያ እንዱፈጠሩ አበክሮ ...
21/02/2025

በነቀምቴ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን ንቁ፣ ብቁ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪና ተምሳሌታዊ ዜጐችና ተቋማት በኢትዮጲያ እንዱፈጠሩ አበክሮ የሚሠራ አገር በቀል የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡ ፋውንዴሽኑ ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ ተግባር ተኮርና ክህሎትን መሠረት ያደረጉ ስልጠናዎችን የሚሰጥ፣ ጥናትና ምርምሮችን የሚያካሄድና የማማከር አገልግሎቶችን የሚሰጥ ተቋም ነው፡፡

በዚሁ መሰረት ፋውንዴሽኑ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሴቶችና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትና ከሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ጋር በመተባበር በተመረጡ የአገራችን ከተሞች ለአራት ቀናት ወጣቶችን እያሰለጠነ ይገኛል ፡፡ ስልጠናው ከሚሰጥባቸው ከተሞች መካከል አንዷ ነቀምቴ ስትሆን በከተማው ሲሰጥ የነበረው ስልጠናም በዛረው ዕለት ተጠናቀዋል። ሰልጣኞች ከ 4ቱ የወለጋ ዞኖች(ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ) የተውጣጡ ሲሆን ስልጠናው በዋናነት በአመራር (leadership) እና በስራ ፈጠራ (entrepreneurship) ላይ ያተኮረ ነበር።

በጅማ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል፣ከየኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት እና ከኢምፓክት ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽ...
18/02/2025

በጅማ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል፣ከየኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት እና ከኢምፓክት ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን-Impact Makers Foundation ጋር በመተባበር በጅማ ከተማ ከጅማ ዞንና ከተማ፣ከቡኖ በደሌና ኢሊባቦር ዞን እና አከባቢው ከተሞች ለተውጣጡ ወጣቶች የአገልጋይ አመራርነትና የስራ ፈጠራን ፅንሰ ሃሳብ ትግበራ ላይ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ።

በባህር ዳር ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን  ንቁ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪና ተምሳሌታዊ ዜጐችና ተቋማት በኢትዮጲያ እንዲፈጠሩ አበክሮ የ...
10/02/2025

በባህር ዳር ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን ንቁ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪና ተምሳሌታዊ ዜጐችና ተቋማት በኢትዮጲያ እንዲፈጠሩ አበክሮ የሚሠራ አገር በቀል የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡ ፋውንዴሽኑ በጥራቱና በሥልጠና አቀራረቡ ልዮ የሆነ ተግባር ተኮርና ጥናትን መሠረት ያደረጉ ሥልጠናዎችን ይሰጣል፡፡

በዚሁ መሰረት ፋውንዴሽኑ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሴቶችና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትና ከኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ጋር በመተባበር ለ 4 ቀናት በባህር ዳር ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቀዋል። የስልጠናው ተሳታፊዎች ከተለያዩ የአማራ ከልል ከተሞች የተውጣጡ ሲሆን ስልጠናው በዋናነት በአመራር (leadership) እና በስራ ፈጠራ (entrepreneurship) ላይ ያተኮረ ነበር።

የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በእስልምና አሰተምህሮ ላይ በተመሰረተ መልካም ስነ ምግባር የታነፀ፣ በአምልኮ ተግባራት ንቁ የሆነ፥ ማንነቱንና እሴቱን የሚያከብር፣ ለህብረተሰብ ደህንነትና ለሀገር ልማት አሰተዋፅዖ የሚያደርግ በእምነት፣ በእውቀትና በአገልግሎት መሪ የሚሆን ወጣት ትውልድ ለማፍራት የሚሰራ ተቋም ነው።

ሥልጠናው ዛሬም በባህርዳር ቀጥሏል🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺''በእስልምና አሰተምህሮ ላይ በተመሰረተ መልካም ስነ ምግባር የታነፀ፣ በአምልኮ ተግባራት ንቁ የሆነ፥ ማንነትና እሴቱን የሚያከብር፣ ለህብረ...
08/02/2025

ሥልጠናው ዛሬም በባህርዳር ቀጥሏል
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
''በእስልምና አሰተምህሮ ላይ በተመሰረተ መልካም ስነ ምግባር የታነፀ፣ በአምልኮ ተግባራት ንቁ የሆነ፥ ማንነትና እሴቱን የሚያከብር፣ ለህብረተሰብ ደህንነትና ለሀገር ልማት አሰተዋፅዖ የሚያደርግ በእምነት፣ በእውቀትና በአገልግሎት መሪ የሚሆን ወጣት ትውልድ ማፍራት" ን ርዕዩ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል
ከኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ ጋር በመተባበር በተለያዩ ቦታዎች ሲያካሂደው የነበረውን የአመራር እና ሥራ ፈጠራ ስልጠና መስጠቱን ቀጥሏል።

በዛሬው ዕለትም በአማራ ክልል፡ በባህርዳር ከተማ ከተለያዩ የክልሉ ከተማዎች ለተውጣጡ ወጣቶች የሚሰጠውን የስልጠና ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ አስጀምሯል:: በተጨማሪም ከክልሉና ከዞኑ የመጅሊስ አመራሮች ጋር ውጤታማ ውይይት አካሄዷል ::ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሸንም እንደከዚህ ቀደሞቹ ሥልጠናዎች በባህርደሩ ሥልጠናም አሰልጣኞችን በማቅረብና በማሰልጠን ተሳትፏል።ባለፉት ሳምንታት በወራቤ፣በሀዋሳ፣በሻሸመኔ፣ በአርባምንጭና በሌሎች ከተሞች ሥልጠናው መሰጠቱ ይታወሳል።

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን በአርባ ምንጭ ከተማ ለአራት ተከታታይ  ቀናት ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ዛሬ  አጠናቀቀ፡፡💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን  ንቁ ተጽዕኖ ፈጣሪና...
27/01/2025

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን በአርባ ምንጭ ከተማ ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ዛሬ አጠናቀቀ፡፡
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን ንቁ ተጽዕኖ ፈጣሪና ተምሳሌታዊ ዜጐችና ተቋማትን በኢትዮጲያ እንዱፈጠር አበክሮ የሚሠራ አገር በቀል የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡ ፋውንዴሽኑ በጥራቱና በሥልጠና አቀራረቡ ልዮ የሆነ: ተግባር ተኮርና ጥናትን መሠረት ያደረጉ ሥልጠናዎችን በመስጠት ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሰረት ፋውንዴሽኑ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሴቶችና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትና ከሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ጋር በመተባበር በተመረጡ የአገራችን ከተሞች ለአራት ቀናት ወጣቶችን እያሰለጠነ ይገኛል ፡፡ ስልጠናው ከሚሰጥባቸው ከተሞች መካከል አንዷ አርባ ምንጭ ስትሆን በከተማው ሲሰጥ የነበረው ስልጠናም በዛረው ዕለት ተጠናቀዋል። ስልጠናው በዋናነት በአመራር (leadership) እና በስራ ፈጠራ (entrepreneurship) ላይ ያተኮረ ነበር።

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን በሐዋሳ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ፡፡💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥ፋውንዴሽኑ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሴቶችና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይ...
25/01/2025

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን በሐዋሳ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ፡፡
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

ፋውንዴሽኑ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሴቶችና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትና ከሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ጋር በመተባበር በተመረጡ የአገራችን ከተሞች ለአራት ቀናት ወጣቶችን እያሰለጠነ ይገኛል ፡፡ ስልጠናው ከሚሰጥባቸው ከተሞች መካከል አንዷ ሀዋሳ ከተማ ሲሆን በከተማው ሲሰጥ የነበረው ስልጠናም በዛሬው ዕለት ተጠናቋል። ስልጠናው በዋናነት በአመራር (leadership) እና በስራ ፈጠራ (entrepreneurship) ላይ ያተኮረ ነበር።

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን በሻሸመኔ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን  ንቁ ተጽዕኖ ፈጣሪና ተምሳሌታዊ ዜጐችና ተቋማትን በኢትዮጵ...
24/01/2025

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን በሻሸመኔ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን ንቁ ተጽዕኖ ፈጣሪና ተምሳሌታዊ ዜጐችና ተቋማትን በኢትዮጵያ እንዲፈጠር አበክሮ የሚሠራ አገር በቀል የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡ ፋውንዴሽኑ በጥራቱና በሥልጠና አቀራረቡ ልዩ የሆነ: ተግባር ተኮርና ጥናትን መሠረት ያደረገ ሥልጠናዎችን በመስጠት ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሰረት ፋውንዴሽኑ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሴቶችና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትና ከሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ጋር በመተባበር በተመረጡ የአገራችን ከተሞች ለአራት ቀናት ወጣቶችን እያሰለጠነ ይገኛል ፡፡ ስልጠናው ከሚሰጥባቸው ከተሞች መካከል አንዷ ሻሸመኔ ከተማ ስትሆን በከተማው ሲሰጥ የነበረው ስልጠናም በዛሬው ዕለት ተጠናቋል። ስልጠናው በዋናነት በአመራር (leadership) እና በስራ ፈጠራ (entrepreneurship) ላይ ያተኮረ ነበር።

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን ከኢትዮጵያ ወጣት ሙስሊሞች ካውንስል ጋር በመተባበር ስልጠና ሰጠ፡፡💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን  ንቁ ተጽዕኖ ፈጣሪና ተምሳሌታዊ ዜጐችና ተ...
23/01/2025

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን ከኢትዮጵያ ወጣት ሙስሊሞች ካውንስል ጋር በመተባበር ስልጠና ሰጠ፡፡
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን ንቁ ተጽዕኖ ፈጣሪና ተምሳሌታዊ ዜጐችና ተቋማትን በኢትዮጲያ እንዲፈጠር አበክሮ የሚሠራ አገር በቀል የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡ ፋውንዴሽኑ በጥራቱና በሥልጠና አቀራረቡ ልዮ የሆነ: ተግባር ተኮርና ጥናትን መሠረት ያደረገ ሥልጠናዎችን በመስጠት ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሰረት ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት የሴቶችና የወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት: የሙስሊሞች ወጣቶች ካውንስል ጋር በመተባበር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በወራቤ ከተማ ለአራት ቀናት ወጣቶችን ስያሰለጥን ቆይቷል፡፡ ስልጠናው በዋናነት በአመራር (leadership) እና በስራ ፈጠራ (entrepreneurship) ላይ ያተኮረ ሲሆን መሰረታዊ የአመራር ጽንስ ሀሳብ(fundamentals of leadership), በአገልጋይ አመራር(Servant Leadership)፣ በስሜት ብልህነት (emotional intelligence) እና የቡድን ግንባታ(team building) ላይ ያተኮረ ነው፡፡
በተጨማሪ መሰረታዊ የስራ ፈጠራ ጽንሰ ሀሳብ (basic concept of entrepreneurship), የስራ ፈጠራ አመለካከት (Entrepreneurial mindset), ሀሳብ የማፍለቅ ክህሎት(idea generation)፣ የቢዚነስ እቅድ ዝግጅት (business plan development) እና የገበያ ስትራቴጂ (marketing strategy) በስልጠናው በጥልቀት የተዳሰሱ ርዕሶች ናቸው፡፡

ስልጠናው ወጣቶች ራሳቸውንም ሆነ ተቋማትና ማህበረሰብን ከመምራት አኳያ የነበራቸውን ግንዛቤ ያሻሻለና ስራን በመፍጠር፣ በማዳበር፣ በማስፋፋትና ውጤታማ የቢዝነስ አንቀሳቃሽ ለመሆን የሚያስችላቸውን መሰረታዊ እውቀትና ክህሎት እንዲይዙ አድርጓል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎችም በስልጠናው የተካተቱ ርዕሰ ጉዳዮች ወሳኝና አስፈላጊ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን የስልጠና አሰጣጥ ዘዴውም የተለየና ተግባርና ክህሎትን መሠረት ያደረገ በመሆኑ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው በሌሎች የአገራችን አካባቢዎችም በቀጣይነት የሚሰጥ ሲሆን የሰለጠኑ ወጣቶች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችላቸው ክትትልና ድጋፍ በቀጣይ የሚደረግላቸው ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፥  በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ከመጅሊስ የተለያዩ መዋቅር አደረጃጀቶች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የምክክር ፕሮግራም ከትናንት በ...
21/01/2025

የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፥ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ከመጅሊስ የተለያዩ መዋቅር አደረጃጀቶች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የምክክር ፕሮግራም ከትናንት በስቲያ ያካሄደ ሲሆን በትናንትናው እለትም በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ አዘጋጅነትና በካውንስሉ አስተባባሪነት የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ የወጣቶች የስራ አመራርና ስራ ፈጠራ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽንም አሰልጣኞችን በማቅረብና በማሰልጠን እየተሳተፈ ይገኛል።

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን ለአዲስ አበባ ከተማ የመጅሊስ አመራሮች ስልጠና ሰጠ::🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺ኢምፓክት ሜክርስ ፋውንዴሽን በአቅም ግንባታ፣ በጥናትና ምርምር እና በማማከር አገል...
10/01/2025

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን ለአዲስ አበባ ከተማ የመጅሊስ አመራሮች ስልጠና ሰጠ::
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺

ኢምፓክት ሜክርስ ፋውንዴሽን በአቅም ግንባታ፣ በጥናትና ምርምር እና በማማከር አገልግሎት ላይ የተሰማራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን በዚህም ብቁ፣ ንቁና ተምሳሌታዊ ዜጎችንና ተቋማትን በመፍጠር በሀገሪቷ ብቃት ያለው ምርታማ የሰው ሀይል ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩሉን አስተዋጻኦ ለማበርከት እየሰራ ይገኛል።

በዚሁ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከከተማ እስከ ወረዳ ላሉ የም/ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት፣ ለማማከር አገልግሎትና፣ ጥናትና ምርምር በጋራ ለማካሄድ የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ስምምነት በፋውንዴሽኑና በከፍተኛ ም/ቤቱ መካከል መፈረሙ ይታወሳል።

በስምምነቱ መሰረት ፋዉንዴሽኑ የመጀመሪያ የሆነውን የአቅም ግንባታ ስልጠና ለከተማው፣ ለክፍለ ከተሞች እና ለወረዳ የመጅሊስ አመራሮች ሰጥተዋል። ስልጠናው በዋናነት በውጤታማ አመራር ላይ ያተኮረ ሲሆን ለሰልጣኞች የተሻለ ግንዛቤና የስራ ውጤታማነት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

በስልጠናው ላይ የከፍተኛ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ክቡር ዶ/ር ሼህ ሱልጣን አማንና ሌሎች የምክር ቤቱ የአመራር አባላት ተገኘተዋል። በቀጣይም በተመረጡ ወሳኝ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከከተማ እስከ ወረዳ ላሉ የም/ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎች ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል።

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽንና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና  የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የከፍተኛ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ክቡር ዶ/ር ሼህ...
08/01/2025

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽንና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የከፍተኛ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ክቡር ዶ/ር ሼህ ሱልጣን አማንና የም/ቤቱ አመራር አባላት የተገኙ ሲሆን በኢምፓክት ሜከርስ ፋውንሽን በኩል የፋውንዴሽኑ መሥራችና የቦርድ ሰብሳቢ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል እና የፋውንዴሽኑ ዋና ዳይሬክተር ሺሃቡዲን ሼህ ኑራ ተገኝተዋል።
ስምምነቱ በዋናነት የአቅም ግንባታ ስልጠና፣ ጥናትና ምርምር እና የማማከር አግልግሎትን መሰረት ያደረገ ሲሆን በዚህመ፦
 የከፍተኛ /ም/ቤቱን የባለሙያና የአመራር አቅም ለመገንባት፣
 ለዕቅድ ግብዓት የሚሆኑና የማህበረሰቡን መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ሊፈቱ የሚያስችሉ ጥናትና ምርምሮችን ለማካሄድ
 የአሰራር ማኑዋሎችን፣ የተለያዩ መመሪያዎችን፣ የስታንዳርድ ሰነዶችን ለማዘጋጀትና
 ተቋማዊ ለውጦችን/ሪፎርሞችን ለማሳካት የሚያስችሉ የምክር አገልግሎቶችን መስጠትና በመሳሰሉት ጉዳዮች ዙሪያ ነው ።
የም/ቤቲ ፕሬዝደንቱ ክቡር ዶ/ር ሼህ ሱልጣን አማን በወቅቱ እንደ ገለጹት የከተማችን የመጅልስ መዋቅር እስከ ወረዳ ድረስ የተዘረጋ ሲሆን ለመዋቅሩ አመራሮችና ሠራተኞች የስራ ላይ ስልጠና በመስጠትና አቅማቸውንና ብቃታቸውን ማጎልበት ያስፈልጋል ብለዋል። በመሆኑም ስምምነቱን በከፍተኛ ሁኔታ በመከታተል ለውጤታማነቱ የሚጠበቅብንን ኃላፊነት ሁሉ እንወጣለን በለዋል ።
የፋውንዴሽኑ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል በበኩላቸው ፋውንዴሽኑ ከተቋቋመ ሁለት ዓመት ገደማ ያስቀጠረ መሆኑን ገልጸው በዚህ ጊዜ ዉጤታማ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን የቅድመ ዝግጅት ስራ ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል። የፋውንዴሽኑ ዋና ዳይሬክተር ሺሃቡዲን ሼህኑራ በበኩላቸው ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን ራዕይ ንቁ: ተፅዕኖ ፈጣሪና ተምሣሌታዊ ዜጉችና ተቋማት ተፈጥሮ ማየት መሆኑን ጠቅሶ ይህ ስምምነት በጋራ ሕዝባችንን የሚመጥን ተቋም ለመገንባት የመጀመሪያ እርምጃ ነው ብሏል::
ሁለቱም ተቋማት ለስምምነቱ ትግበራ ዉጤታማነት ቁርጠኛ መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን ለቀጣይ ተግባራዊ ስራ በጋራና በቅርበት ለመስራት ተስማምተዋል።

🌟 Empowering Leaders, Transforming Communities 🌟From December 25-29, 2024, Impact Makers Foundation successfully hosted ...
31/12/2024

🌟 Empowering Leaders, Transforming Communities 🌟

From December 25-29, 2024, Impact Makers Foundation successfully hosted a transformative training workshop, "Empowering Non-Profit Leaders in Challenging Environments," at the African Leadership Development Excellence Center in Addis Ababa.

🎓 Topics Covered:
✅ Emotional Intelligence
✅ Problem Solving & Creative Thinking
✅ Change Management
✅ Strategic Thinking
✅ System Thinking
✅ Influencing Skills

This immersive program brought together passionate leaders from various non-profit organizations, equipping them with the tools and skills to thrive amidst challenges and drive impactful change in their communities.

✨ Highlights:

Inspiring discussions on navigating uncertainty.
Practical sessions fostering innovative solutions.
Building resilience and enhancing leadership influence.
Together, we are building a future of excellence, empowerment, and impactful leadership. 🌍

🌟 መሪዎችን ማብቃት፣ ማህበረሰቦችን መለወጥ 🌟

ከታህሳስ 16 እስከ 21 ቀን 2017 ኢምፓክት ሰሪዎች ፋውንዴሽን በሱሉልታ በሚገኘው የአፍሪካ አመራር ልህቀት ማዕከል "ለትርፍ ያልተቋቋሙ ተቋማት መሪዎችን ማብቃት" የተሰኘ የለውጥ ስልጠና አውደ ጥናት በተሳካ ሁኔታ አዘጋጅቷል።

🎓 የተሸፈኑ ርዕሶች፡-
✅ ስሜታዊ ብልህነት
✅ ችግር መፍታት እና የፈጠራ አስተሳሰብ
✅ ለውጥ አስተዳደር
✅ ስልታዊ አስተሳሰብ
✅ የስርዓት አስተሳሰብ
✅ ተፅእኖ የመፍጠር ክህሎት

ይህ መሳጭ ፕሮግራም ከተለያዩ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች መሪዎችን ሰብስቧል፣ በችግሮች መካከል እንዲበለፅጉ እና በማህበረሰባቸው ውስጥ ጠቃሚ ለውጥ ለማምጣት መሳሪያዎችን እና ችሎታዎችን በማስታጠቅ ተጠናቋል::

✨ ዋና ዋና ነጥቦች፡-

- ኢ- እርግጠኛ ሁኔታዎችን በማሰስ ላይ አነቃቂ ውይይቶች።
- አዳዲስ መፍትሄዎችን የሚያበረታቱ ተግባራዊ ክፍለ ጊዜዎች።
- የመቋቋም ችሎታ መገንባት እና የአመራር ተፅእኖን ማሳደግ.

በጋራ፣ ወደፊት የላቀ ብቃት፣ ንቃት እና ተፅእኖ ያለው አመራር እየገነባን ነው። 🌍

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን-Impact Makers Foundation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share