Ethiopian Red Cross Society

Ethiopian Red Cross Society Our vision is to be the leading national society in Africa.

Welcome to the Ethiopian Red Cross Society The Ethiopian Red Cross Society(ERCS) is one of the 192 Red Cross and Red Crescent Societies around the world,was founded on July 8th,1935 by goverment Decree. We are a humanitarian Society, established by the Geneva Convention and its additional protocols; guided by the seven fundamental principles of the Red Cross Red Crescent Movement. We are auxiliary to the Ethiopian government in matters of humanitarian interventions; we work in partnership with the International Federation of the Red Cross and Red Crescent Societies (IFRC), the International Committee of the Red Cross (ICRC), partnering national societies, volunteers and our beneficiaries. Our mission is to prevent and alleviate human suffering through appropriate and timely humanitarian and develoment interventions, contribute to the well-being of humankind and prevalence of peace by mobilizing the public and partners in Ethiopia and around the world.

የስዊዘርላንድ የልማትና ትብብር ኤጀንሲ ቡድን በወላይታ ዞን የተከናወኑ የውሃና የስነ-ንጽህና  ተግባራትን ጎበኘ ከስዊዘርላንድ የልማትና ትብብር ኤጀንሲ(SDC) የተውጣጣ ቡድን  “የውሃና ስነ...
21/09/2026

የስዊዘርላንድ የልማትና ትብብር ኤጀንሲ ቡድን በወላይታ ዞን የተከናወኑ የውሃና የስነ-ንጽህና ተግባራትን ጎበኘ

ከስዊዘርላንድ የልማትና ትብብር ኤጀንሲ(SDC) የተውጣጣ ቡድን “የውሃና ስነ-ንጽህና እና ከአካባቢው ጋር ተስማሚ ትምህርት ቤቶች ፕሮጀክት"(WASH and Environmentally Friendly Schools Project) አማካይነት በወላይታ ዞን በቂሎ ሰኞ እና ደምባ ጋሌ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በኤጀንሲው የገንዘብ ድጋፍ የተከናወኑ ተግባራትን መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም የጎበኘ ሲሆን ከተማሪዎች፣ ከመምህራንና ከትምህርት ቤቱ ማኅበረሰብ ጋር ውይይት አድርጓል።

ፕሮጀክቱ እየተተገበረ ያለው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከስዊዘርላንድ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር እና ከስዊዘርላንድ የልማት እና የትብብር ኤጀንሲ (SDC) ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን የውሃና የስነ-ንጽህና (WASH) አገልግሎቶችን ለማጠናከር እና በጂማ እና ወላይታ ዞኖች በሚገኙ 14 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ የትምህርት ቤት መገልገያዎችን ለማስተዋወቅ እ.አ.አ.በሀምሌ 2024 የተጀመረ ሲሆን ፕሮጀክቱ በጅማና በወላይታ ዞኖች በሚገኙ 14 ትምህርት ቤቶች የውሃና ስነ-ንጽህና አገልግሎቶችን እያሻሻለ ይገኛል።

ፕሮጀክቱ በ14ቱም ትምህርት ቤቶች ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ መጸዳጃ ቤቶችንና የተሻሻሉ የእጅ መታጠቢያ ስፍራዎችን ያሟላ ሲሆን ለዘጠኝ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ተማሪዎች ደህንነቱ የተጠበቀና ክብርን በሚጠብቅ መልኩ የወር አበባ ንፅህናቸውን እንዲጠብቁ የሚያስችሉ ልዩ ክፍሎች (MHM rooms) ተዘጋጅተውላቸዋል።

በተጨማሪም የውሃ ቧንቧ መስመር ዝርጋታን በማስፋፋት በ11 ትምህርት ቤቶች የውሃ አቅርቦቱ እንዲሻሻል የተደረገ ሲሆን በወላይታ ዞን በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ደግሞ ተጨማሪ ጥልቀት የሌለው የውሃ ጉድጓድ ተቆፍሯል።

ዘላቂ አማራጭ የውሃ ምንጮችን ለማስተዋወቅም በዞኑ የሚገኙ ስድስት ትምህርት ቤቶች የዝናብ ውሃ ማጠራቀሚያ ስርዓቶችን እንዲያገኙ ተደርጓል።

ቡድኑ በውሃና ስነ-ንጽህና መገልገያዎችና በትምህርት ቤቶቹ አካባቢ ላይ የተደረጉትን ማሻሻያዎች ያደነቀ ሲሆን፣ በጉብኝቱ ወቅት የታየው ለውጥም አጥጋቢ እንደነበርም ተገልጿል።

እነዚህ ተግባራት ትምህርት ቤቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ጤናማ፣ ሁሉን አቀፍና ከአካባቢው ጋር ተስማሚ እንዲሆኑ እያደረጉ ሲሆን፣ በተመሳሳይም ለተማሪዎች፣ ለመምህራን እና ለሰፊው የትምህርት ቤት ማህበረሰብ አስፈላጊ የሆኑ የውሃና ስነ ንጽህና አገልግሎቶችን ተደራሽነትን እያሻሻሉ ይገኛሉ።

ለሰብዓዊነት እንኖራለን!
------------------------------
SDC Team Visits WASH Project Schools in Wolaita Zone to Assess Progress

A team from the Swiss Agency for Development and Cooperation (SDC) visited Beqilo Segno and Demba Galle Primary Schools in Wolaita on September 15, 2026, to observe the progress and achievements of the WASH and Environmentally Friendly Schools Project and engage with students, teachers, and school communities.

The project is being implemented by the Ethiopian Red Cross Society (ERCS) in partnership with the Swiss Red Cross (SRC) and with funding from the Swiss Agency for Development and Cooperation (SDC) was launched in July 2024 to strengthen water, sanitation and hygiene (WASH) services and promote environmentally friendly school facilities in 14 schools across Jimma and Wolaita.

The project has delivered disability-inclusive latrines and improved handwashing facilities in all 14 schools, and nine schools now have dedicated Menstrual Hygiene Management (MHM) rooms to support safe, dignified menstrual hygiene for students.

Water access has also improved in 11 schools through pipeline extensions, and the team constructed an additional shallow well at one school in Wolaita. To promote sustainable alternative water sources, six Wolaita schools have received rainwater harvesting systems.

The SDC team welcomed the improvements made to the WASH facilities and learning environment and expressed their satisfaction with the progress observed during the field visit.

These interventions are contributing to safer, healthier, more inclusive and environmentally sustainable schools, while improving access to essential WASH services for students, teachers and the wider school community.

We Live for Humanity!


Embassy of Switzerland in Ethiopia Schweizerisches Rotes Kreuz Swiss Development & Cooperation
-----------
📌Website: https://redcrosseth.org/
📌Instagram፡ https://www.instagram.com/ercs1935/
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/ethiopian-red-cross-society/
📌YouTube: https://www.youtube.com/
📌X(Twitter): https://x.com/EthioRedCross
📌Telegram: https://t.me/ERCSHQ
📌 Tiktok: https://www.tiktok.com/
📌 Flickr፡- 137615657@N05/" rel="ugc" target="_blank">https://www.flickr.com/photos/137615657@N05/

ማኅበሩ በሰሜን ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከ350 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገበኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰሜን ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከ350 ሺ...
21/09/2026

ማኅበሩ በሰሜን ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከ350 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰሜን ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከ350 ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የትምህርት ቁሳቁሶችን ለሰሜን ወሎ፣ ለጉባላፍቶ እና ለወልዲያ ትምህርት መምሪያዎች ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰሜን ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መንግስቴ ባዬ ለየትምህርት መምሪያ ሀላፊዎቹ ያስረከቡ ሲሆን፣ ድጋፉ አቅም የሌላቸው ተማሪዎች በትምህርታቸው ገበታ ላይ እንዲቆዩና የትምህርት ቁሳቁስ እጥረት እንዳያጋጥማቸው ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ዘገባው የሰሜን ወሎ ዞን ኮምዩኒኬሽን ነው

ለሰብዓዊነት እንኖራለን!
---------------------------
ERCS North Wollo Zone Branch Donates Educational Materials Worth Over ETB 350,000

The Ethiopian Red Cross Society (ERCS) North Wollo Zone Branch has donated educational materials worth more than ETB 350,000 to the education departments of North Wollo, Gubalafto and Woldia.

Mr. Mengiste Baye, Head of the ERCS North Wollo Zone Branch, handed over the materials to the heads of the respective education departments. He noted that the donation will help students from disadvantaged backgrounds remain in school and reduce shortages of essential educational supplies.

Report by the North Wollo Zone Communication Office.

We Live for Humanity!


-----------
📌Website: https://redcrosseth.org/
📌Instagram፡ https://www.instagram.com/ercs1935/
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/ethiopian-red-cross-society/
📌YouTube: https://www.youtube.com/
📌X(Twitter): https://x.com/EthioRedCross
📌Telegram: https://t.me/ERCSHQ
📌 Tiktok: https://www.tiktok.com/
📌 Flickr፡- 137615657@N05" rel="ugc" target="_blank">https://www.flickr.com/photos/137615657@N05

በማኅበሩ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም .የስራ  አፈጻጸምን በመገምገም በ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት እቅዱ ላይ ተወያየበኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር  የኦሮሚያ ክልል ቅር...
18/09/2026

በማኅበሩ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም .የስራ አፈጻጸምን በመገምገም በ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት እቅዱ ላይ ተወያየ

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ብሔራዊ ጽ/ቤቱን በመወከል የማኅበሩ ምክትል ዋና ጸሐፊ፣ የክልል አመራሮች እንዲሁም የ21 የዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት የ2018 ዓ.ም. አፈጻጸምን በመገምገም ለ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት እቅዱ ላይ ያተኮረ ውይይት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ አካሒዷል።

በመድረኩ ላይ የቅርንጫፍ ጽ/ ቤቱ በ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት ያስመዘገባቸውን ዋና ዋና ውጤቶችና አፈጻጸሞች የገመገሙ ሲሆን፣ ተሳታፊዎችም በ2019 ዓ.ም. የሥራ ዕቅድ ላይ ዝርዝር ውይይት አድርገዋል።

መድረኩ በበጀት አመቱ የተገኙ ስኬቶችን ለመገምገም፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመለየትና በቀጣዩ በጀት ዓመት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ዕቅዶች ለማጠናከር ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ነበር።

ውይይቶቹ በዋና ዋና ውጤቶች፣ በአፈጻጸም ወቅት ባጋጠሙ ተግዳሮቶች፣ በተገኙ ትምህርቶች እና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ ተሳታፊዎቹ በአዲሱ በጀት ዓመት የታቀዱ ተግባራትን አፈጻጸም ለማጠናከር እና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመፈጸም የሚያስችሉ መንገዶችን በጋራ ለይተዋል።

በግምገማ መድረኩ ላይ በማኅበሩ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች፣ ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን መድረኩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በበጀት ዓመቱ ስላስመዘገበው እድገት በጥልቀት ለመወያየት፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና ለቀጣዩ ዓመት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለመለየት ለማቀናጀት እድል የፈጠረ ነበር።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ምርጥ አፈጻጸም ላሳዩ የዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እውቅና የተሰጠ ሲሆን በአጠቃላይ አፈጻጸማቸው መሠረትም የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አንደኛ፣ የምዕራብ ሸዋ ዞን ሁለተኛና የምዕራብ ወለጋ ዞን ሦስተኛ ደረጃን ሲይዙ በሀብት ማሰባሰብ፣ በውስጥ አቅም ፕሮጀክቶችን በመተግበር፣ ለአደጋ ምላሽ በመስጠት እና በላቀ ተነሳሽነት ዘርፎች የአርሲ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አንደኛ፣ የሸገር ከተማ ሁለተኛ ና የምዕራብ አርሲ ዞን ሦስተኛ ደረጃን አግኝተዋል።

ማስተባበሪያ የዞን ቅርንጫፎችን በተመለከተ፣ የቄለም ወለጋ ማስተባበሪያ ጽ/ቤተ አንደኛ ደረጃን በማግኘቱ እውቅና ተሰጥቶታል።

ማኅበረሰቡን ለማገልገልና ሰብዓዊ ተልዕኳችንን ለማሳካት በጋራ መስራታችንን እንቀጥላለን።

ለሰብዓዊነት እንኖራለን!
------------------------
ERCS Oromia Branch Reviews 2018 E.C. Performance and Plans for 2019 E.C.

The Ethiopian Red Cross Society (ERCS) Oromia Regional Branch held its 2018 Ethiopian Calendar (EC) Budget-Year Performance Review and discussed the 2019 FY Plan with the presence of the Deputy Secretary General from the National Headquarters, regional management, and the heads of 21 zonal branches in Waliso Town, Southwest Shewa Zone.

The meeting reviewed the branch’s performance and key achievements during the 2018 budget year, while participants also held detailed discussions on the 2019 EC Budget Year work plan.
The meeting provided an opportunity to review achievements, identify challenges, and strengthen the branch’s plans for the coming fiscal year.

The discussions further focused on key achievements, implementation challenges, lessons learned, and future priorities. Participants are jointly identifying ways to strengthen implementation and ensure effective delivery of planned activities during the new budget year.

The review allowed ERCS Oromia Regional Branch leadership, staff, and relevant stakeholders to reflect on progress, address challenges, and align priorities for the year ahead.

At the end of the meeting, we recognized the best-performing zonal branch and based on their overall performance, the South West Shewa Zonal Branch secured first place, followed by the West Shewa Zonal Branch in second place and the West Wellega Zonal Branch in third place.

In the areas of resource mobilization, implementation of projects using internal resources, emergency response, and outstanding initiatives, the Arsi Zonal Branch ranked first, Shagar City Administration Branch second, and West Arsi Zonal Branch third. Among coordinating zonal branches, Qeellam Wellega Coordinating Branch was recognized for securing first place.

Together, we continue to serve communities and advance our mission.

We Live for Humanity!


------------
📌Website: https://redcrosseth.org/
📌Instagram፡ https://www.instagram.com/ercs1935/
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/ethiopian-red-cross-society/
📌YouTube: https://www.youtube.com/
📌X(Twitter): https://x.com/EthioRedCross
📌Telegram: https://t.me/ERCSHQ
📌 Tiktok: https://www.tiktok.com/
📌 Flickr፡- 137615657@N05/" rel="ugc" target="_blank">https://www.flickr.com/photos/137615657@N05/

በማኅበሩ የጉራጌ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገየጉራጌ ዞን ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ወጪ የ...
18/09/2026

በማኅበሩ የጉራጌ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

የጉራጌ ዞን ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ወጪ የተዘጋጁ የመማሪያ ቁሳቁሶችንና የሚኒ ሚዲያ ማጠናከሪያ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ለጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ድጋፍ አድርጓል።

‎በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም ማኅበሩ ከሚሰራቸው ሰብዓዊና የበጎ ፈቃድ ተግባራት አንዱ የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች በየዓመቱ የሚያደርገው ድጋፍ መሆኑን ጠቅሰው፤ ድጋፉ የተማሪዎችን የትምህርት ቁሳቁሶች እጥረት በመቅረፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

‎በዕለቱ ርክክብ የተደረገው ከ6 ሺህ በላይ ደብተሮችና የሚኒ ሚዲያ ማጠናከሪያ ግብዓቶች መሆናቸውን ያነሱት አቶ መብራቴ፤ ‎በዞኑ የሚገኙ ሁሉም ተማሪዎች የቀይ መስቀል አባል በመሆን የበጎ አድራጎት ባህልን ማዳበር እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል፡፡

‎በማኅበሩ የጉራጌ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አሰፋ አካሉ በበኩላቸው፤ ማኅበሩ ከአደጋ ጊዜ እርዳታና መጠለያ ድጋፍ ባሻገር ህጻናት ከልጅነታቸው ጀምሮ የመረዳዳትና የበጎነት አስተሳሰብ ይዘው እንዲያድጉ በትምህርት ቤቶች የሚደረገውን እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

‎በዕለቱም ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ወጪ የተዘጋጁ ከ6 ሺህ በላይ የመማሪያ ቁሳቁሶችንና ለተመረጡ 3 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ለሚኒሚዲያ ማጠናከሪያ የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ለዞኑ ትምህርት መምሪያ መበርከታቸውን አቶ አሰፋ አስታውቀዋል።

‎በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻሚል ስቴሮ እና የወልቂጤ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ስሜነሽ ግርማ እንዳሉት፤ ድጋፉ አቅመ-ደካማ ተማሪዎች በቁሳቁስ እጦት ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ የሚታደግ መሆኑን ገልጸው፤ የቅስቀሳና የአባልነት ምዝገባው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።

‎ተማሪዎች የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አባል በመሆን የበጎ አድራጎት ባህልን እንዲያዳብሩና የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ህጻናት ከትምህርት ገበታ እንዳይስተጓጎሉ ባለድርሻ አካላት እንዲረባረቡም ጥሪ አቅርቧል።

መረጃው የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ነው

ለሰብዓዊነት እንኖራለን!
--------------------------------
ERCS Gurage Zonal Branch Donates Educational Materials Worth Over ETB 1 Million

The Ethiopian Red Cross Society (ERCS) Gurage Zonal Branch has donated educational materials and electronic equipment worth more than ETB 1 million to the Gurage Zone Education Department to support students and strengthen school-based mini-media programs.

Speaking at the handover ceremony, Ato Mebrate Woldemariam, Head of the Gurage Zone Education Department, said the annual support provided to students facing economic hardship is among the Society’s important humanitarian and voluntary initiatives. He noted that the assistance contributes significantly to addressing shortages of educational materials among disadvantaged students.

Ato Mebrate said the donated items include more than 6,000 notebooks and materials to support mini-media activities. He also encouraged students across the zone to become ERCS members and develop a culture of volunteerism and mutual support.

Ato Assefa Akalu, Chairperson of the ERCS Gurage Zone Branch Board, said the Society is committed not only to providing emergency assistance and shelter but also to strengthening school-based activities that promote mutual support and volunteerism among children from an early age.

He announced that the branch had donated more than 6,000 educational items valued at over ETB 1 million, along with electronic equipment to strengthen mini-media facilities in three selected schools.

Mr. Shamil Stero, Head of the Programme Sector at the branch, and Ms. Simenesh Girma, Head of the Wolkite City Education Office, noted that the support can help prevent students from disadvantaged families from dropping out of school due to a lack of educational supplies. They also emphasized the importance of strengthening awareness and ERCS membership registration efforts.

Stakeholders called for continued collaboration to encourage students to join the Ethiopian Red Cross Society, promote a culture of volunteerism, and help ensure that children facing economic hardship can continue their education.

Source: South Radio and TV Agency

We Live for Humanity!


---------------
📌Website: https://redcrosseth.org/
📌Instagram፡ https://www.instagram.com/ercs1935/
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/ethiopian-red-cross-society/
📌YouTube: https://www.youtube.com/
📌X(Twitter): https://x.com/EthioRedCross
📌Telegram: https://t.me/ERCSHQ
📌 Tiktok: https://www.tiktok.com/
📌 Flickr፡- 137615657@N05/" rel="ugc" target="_blank">https://www.flickr.com/photos/137615657@N05/

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለበጎ ፈቃደኞችና ለአምቡላንስ አሽከርካሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ዕርዳታ ሥልጠና ሰጠበኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር  የትግራይ ምስራቅ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዴንማርክ...
18/09/2026

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለበጎ ፈቃደኞችና ለአምቡላንስ አሽከርካሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ዕርዳታ ሥልጠና ሰጠ

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የትግራይ ምስራቅ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዴንማርክ ቀይ መስቀል በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለበጎ ፈቃደኞችና ለአምቡላንስ አሽከርካሪዎች የአምስት ቀናት የመጀመሪያ ድረጃ የህክምና ዕርዳታ ሥልጠና በዓዲግራት ከተማ ሰጥቷል።

ሥልጠናው በዓዲግራት ከተማና በጋንታ አፈሹም የሚገኙ በጎ ፈቃደኞችና የአምቡላንስ አሽከርካሪዎችን የአደጋ ጊዜ ሁኔታዎችን በትክክል የመለየት፣ በፍጥነትና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ምላሽ የመስጠት እና የተጎዱ ሰዎችን የመርዳት አቅማቸውን ለማጠናከር ያለመ ነው።

ሥልጠናው የሕይወት አድን ተግባራትን፣ በአደጋ ወቅት በልብና በመተንፈሻ አካላት ላይ የሚደርስን የተግባር መስተጓጎል ወደ በነረበት እንዲመለስ የማድረግ (CPR/Resuscitation) ፣ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን እና የታካሚዎችን ደህንነቱን በጠበቀ መልኩ ወደ ተገቢው የጤና ተቋም የማስተላለፍ ክህሎቶችን ያካተተ ተግባራዊ ሥልጠና ነው።

ይህም በማኅበረሰብ ደረጃ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትና ምላሽን ለማጠናከር እንዲሁም የቀይ መስቀልን የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሥራዎች ለመደገፍ ያግዛል።

በሥልጠናው ከዓዲግራት ከተማና ከጋንታ አፈሹም ወረዳ የተውጣጡ 100 የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የትግራይ ምስራቅ ዞን ቅርንጫፍ በጎ ፈቃደኞችና የአምቡላንስ አሽከርካሪዎች ተሳትፈዋል።

መረጃው: የክልሉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኮሙኒኬሽን ክፍል

ለሰብዓዊነት እንኖራለን!
-----------------------------
ERCS Tigray Branch Office Provides First Aid Training for Volunteers and Ambulance Drivers

The Ethiopian Red Cross Society (ERCS), Tigray Eastern Zone Branch, with financial support from the Danish Red Cross (DRC), successfully hosted a five-day intensive first aid training session for volunteers and ambulance drivers in Adigrat Town.

The training aims to strengthen the capacity of volunteers and ambulance drivers in Adigrat and Gantaafeshum to effectively recognize, respond to, and manage emergencies through a practical workshop covering lifesaving skills, including CPR/resuscitation, emergency preparedness, and safe patient referral skills, thereby enhancing community-level emergency response and supporting Red Cross emergency operations.

The training brought together 100 ERCS Tigray Eastern Zone branch volunteers and ambulance drivers from Adigrat town and Gantaafeshum woreda.

Source: ERCS Tigray Regional Branch Communication Department

We Live for Humanity!

#𝐓𝐢𝐠𝐫𝐚𝐲
Røde Kors
-------------
📌Website: https://redcrosseth.org/
📌Instagram፡ https://www.instagram.com/ercs1935/
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/ethiopian-red-cross-society/
📌YouTube: https://www.youtube.com/
📌X(Twitter): https://x.com/EthioRedCross
📌Telegram: https://t.me/ERCSHQ
📌 Tiktok: https://www.tiktok.com/
📌 Flickr፡- 137615657@N05/" rel="ugc" target="_blank">https://www.flickr.com/photos/137615657@N05/

በማኅበሩ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በክረምት ስፖርታዊ ውድድሮች አማካኝነት ማኅበራዊ ትስስርን እያጠናከረ ነው በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር  የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዴንማርክ...
17/09/2026

በማኅበሩ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በክረምት ስፖርታዊ ውድድሮች አማካኝነት ማኅበራዊ ትስስርን እያጠናከረ ነው

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዴንማርክ ቀይ መስቀልና በአውሮፓ ህብረት በጋራ በሚደገፈው የማኅበራዊ ትስስር ፕሮጀክት አማካይነት በክልሉ በተላላክ እና ጭፍራ ወረዳዎች የክረምት ስፖርታዊ ውድድሮችን ሲያካሂድ ቆይቷል ።

ከስፖርታዊ እንቅስቃሴዎቹ ጎን ለጎን የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና እርዳታ፣ የአእምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ፣ በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን መከላከልና ማኅበራዊ ትስስር ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ክፍለ ጊዜዎች የተካሄዱ ሲሆን ህብረተሰቡ የተቋቋሙትን የማኅበረሰብ ማዕከላት በተሻለ ሁኔታ እንዲጠቀም ለማበረታታት የማኅበረሰብ ተሳትፎ እንቅስቃሴዎችም ተካሂደዋል።

ኩነቱ ግንዛቤን ለማሳደግ፣ ማኅበራዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከርና ማኅበረሰብ ላይ የተመሰረቱ የድጋፍ አገልግሎቶችን ለመጠቀም የሚያስችሉ እድሎችን በመፍጠር ማኅበረሰቦችን በስፖርታዊ ውድድሮች በአንድ ላይ ያሰባሰበ ነበር።

ለሰብዓዊነት እንኖራለን!
----------------------------
ERCS Afar Regional Branch Promotes Social Cohesion Through Summer Sports

The Ethiopian Red Cross Society (ERCS) Afar Regional Branch organized summer sports competitions in Telalak and Chifra Woredas as part of a social cohesion project jointly supported by the Danish Red Cross and the European Union.

Alongside the sporting activities, awareness-raising sessions were conducted on first aid, mental health and psychosocial support, the prevention of gender-based violence, and social cohesion. Community outreach activities were also carried out to encourage residents to make greater use of the established community centers.

The activities brought communities together through sports while creating opportunities to promote awareness, strengthen social connections, and encourage the use of community-based support services.

We Live for Humanity!


Røde Kors European Union in Ethiopia
------------
📌Website: https://redcrosseth.org/
📌Instagram፡ https://www.instagram.com/ercs1935/
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/ethiopian-red-cross-society/
📌YouTube: https://www.youtube.com/
📌X(Twitter): https://x.com/EthioRedCross
📌Telegram: https://t.me/ERCSHQ
📌 Tiktok: https://www.tiktok.com/
📌 Flickr፡- 137615657@N05/" rel="ugc" target="_blank">https://www.flickr.com/photos/137615657@N05/

በማኅበሩ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከ1.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ለአቅመ ደካሞች አደረገበኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደሩ ሥር ለሚገኙ...
17/09/2026

በማኅበሩ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከ1.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ለአቅመ ደካሞች አደረገ

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደሩ ሥር ለሚገኙ ከሁለት ቀበሌዎች ለተውጣጡ ነዋሪዎች ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምግብና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ የተደረገው በዝናብ እጥረት ምክንያት የምግብ ዋስትና ችግር ለገጠማቸው ለላጎዳ ሚርጋ እና ላጋዲኒ ቀበሌዎች ነዋሪዎች ነው።

በዚሁ የድጋፍ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር፤ ማኅበሩ ያደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ ሊበረታታ የሚገባው መሆኑን ገልጸው፣ ለአቅመ ደካማ ወገኖች የሚደረጉ መሰል ድጋፎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በአሁኑ ወቅት በአካባቢው በተከሰተው የዝናብ እጥረት ምክንያት ማኅበረሰቡ እንዳይጎዳ አስተዳደሩ በትኩረት እየሠራ መሆኑን የጠቆሙት ከንቲባው፣ ሕዝቡም እርስ በርሱ የመረዳዳትና የመተጋገዝ ባህሉን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።

ማኅበሩ ያደረገው ይህ ድጋፍ በሁለቱ ቀበሌዎች የሚገኙ 482 አባወራዎችንና እማወራዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን፣ ለቤተሰቦቹ የምግብ እህልና የምግብ ዘይት የተከፋፈለ ሲሆን ድጋፍ ከተደረገላቸው ቤተሰቦች የተውጣጡ 150 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

በማኅበሩ የድሬዳዋ ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱሰላም አህመድ በበኩላቸው፤ የከተማ አስተዳደሩ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በየዓመቱ የ10 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግና የሰብዓዊ ተግባሩ ዋነኛ ደጋፊ መሆኑን ገልጸው፤ ለተጎዱ ወገኖች የተደረገው የሰብዓዊ ድጋፍም ከዚሁ ከከተማ አስተዳደሩ በተገኘው በጀት መሸፈኑን በመጠቆም ለክቡር ከንቲባውና ለከተማ አስተዳደሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የማኅበሩ የቦርድ አባል ወ/ሮ ሐያት አህመድ በበኩላቸው፤ ለድጋፉ የሚሆን ትክክለኛ መረጃ ከአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ባለሥልጣን መገኘቱን ገልጸው፤ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለነፍሰ ጡርና አጥቢ እናቶች እንዲሁም ከዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች ለተውጣጡ ተማሪዎች ቅድሚያ መሰጠቱን አብራርተዋል።

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ በሐር አደም ማኅበሩ ከሕዝብ የሚሰበስበውን ሀብት ችግረኞችን ለመደገፍ እያዋለ መሆኑን ገልጸው፣ የድሬዳዋ ማኅበረሰብ የማኅበሩ አባል በመሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጠይቀዋል።

መረጃው የድሬ ቴሌቭዥን ነው

ለሰብዓዊነት እንኖራለን!
---------------------------
ERCS Dire Dawa Branch Provides Aid Worth Over 1.4 Million Birr to Vulnerable Residents

The Ethiopian Red Cross Society (ERCS) Dire Dawa Branch provided food and educational materials worth more than 1.4 million Birr to vulnerable residents of Lagoda Mirga and Lagadini Kebeles in Dire Dawa City Administration, where communities are facing food insecurity due to inadequate rainfall.

The assistance benefited 482 households across the two Kebeles, with food grains and cooking oil distributed to affected families. In addition, 150 students from beneficiary households received educational materials.

Speaking at the handover ceremony, Dire Dawa City Administration Mayor Kadir Juhar commended the humanitarian support provided by ERCS and called for continued efforts to strengthen assistance to vulnerable community members. He also urged the public to further strengthen the culture of mutual support and cooperation as the city administration works to mitigate the impact of the rainfall shortage.

Mr. Abdusalam Ahmed, Board Chairperson of the ERCS Dire Dawa Branch, noted that the city administration has been a key supporter of the branch’s humanitarian activities, providing an annual financial grant of 10 million Birr. He expressed his appreciation to the Mayor and the administration, noting that the assistance was funded through this grant.

Ms. Hayat Ahmed, a branch board member, explained that beneficiary data was obtained from the Disaster Risk Management Authority, with priority given to persons with disabilities, pregnant and lactating women, and students from low-income families.

Ms. Bahar Adem, Head of ERCS Dire Dawa Branch Office, said the Society is using resources mobilized from the public to support people in need and called on the Dire Dawa community to contribute to humanitarian action by becoming ERCS members.

Source: Dire Televisio

We Live for Humanity!



------
📌Website: https://redcrosseth.org/
📌Instagram፡ https://www.instagram.com/ercs1935/
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/ethiopian-red-cross-society/
📌YouTube: https://www.youtube.com/
📌X(Twitter): https://x.com/EthioRedCross
📌Telegram: https://t.me/ERCSHQ
📌 Tiktok: https://www.tiktok.com/
📌 Flickr፡- 137615657@N05/" rel="ugc" target="_blank">https://www.flickr.com/photos/137615657@N05/

በማኅበሩ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት አመራሮች  በሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኝት የልምድ ልውውጥ አደረጉየኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት አመራር ...
16/09/2026

በማኅበሩ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት አመራሮች በሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኝት የልምድ ልውውጥ አደረጉ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት አመራር አባላት በሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኝት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ እያከናወናቸው በሚገኙ የገቢ ማሰባሰቢያ ተግባራት ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡

የልምድ ልውውጡ በዋናነት ያተኮረው የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ማስወገድና በህንጻ ግንባታ ዙሪያ በስፋት እያከናወነ ስላለው የገቢ ማሰባሰብ ተግባር ውይይትና የመስክ ጉብኝት በማድረግ ላይ ሲሆን የሶማሌ ክልል አመራር አባላትም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በዚህ ረገድ ያለውን ልምድ በዚሁ መድረክ ላይ አካፍለዋል፡፡

የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ አስፋው ሰንበቶ ለተደረገላቸው ቤተሰባዊ አቀባበል ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ከሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽ ቤት ያገኙትን ልምድ በቅርንጫፍ ጽ/ቤታቸው በስራ ላይ ለማዋል ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል፡፡

በማኅበሩ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀሰን አደን በበኩላቸው የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ልምድ ለመቅሰም በክልሉ ለተገኘው የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት አመራር አባላት ምስጋና አቅርበው፤ እንዲህ አይነቱ የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ መድረክ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ የጋራ እድገት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለሰብዓዊነት እንኖራለን!
---------------------
ERCS Harari Regional Branch Leaders Exchange Experiences with Somali Regional Branch

Leadership of the Ethiopian Red Cross Society (ERCS) Harari Regional Branch visited the Somali Regional Branch to exchange experiences and learn from its ongoing resource mobilization initiatives.

The exchange focused particularly on the Somali Regional Branch’s resource mobilization activities through city sewerage services and building construction. The visiting team held discussions with branch leaders and conducted field visits to gain practical insights into the branch’s experience and approaches in these areas.

Mr. Asfaw Senbeto, Head of ERCS Harari Regional Branch, expressed his appreciation for the warm and family-like welcome extended to the delegation. He said the branch would work to apply the lessons and experiences gained from the visit to strengthen its own operations.

Mr. Hassan Aden, Head of the ERCS Somali Regional Branch, also expressed appreciation to the Harari Regional Branch leadership for visiting and learning from the branch’s experience. He emphasized that such experience-sharing platforms are important for strengthening the capacity and collective growth of ERCS branches.

We Live for Humanity!


---------------------------------
📌Website: https://redcrosseth.org/
📌Instagram፡ https://www.instagram.com/ercs1935/
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/ethiopian-red-cross-society/
📌YouTube: https://www.youtube.com/
📌X(Twitter): https://x.com/EthioRedCross
📌Telegram: https://t.me/ERCSHQ
📌 Tiktok: https://www.tiktok.com/
📌 Flickr፡- 137615657@N05/" rel="ugc" target="_blank">https://www.flickr.com/photos/137615657@N05/

16/09/2026

“የስልክ ቻርጅ አገልግሎት ከዘመዶቻችን እና ከጓደኞቻችን ጋር ለመገናኘት ጠቅሞናል። ከዚህም ባለፈ ለማንበብ፣ ለመማር እና ማኅበራዊ ሚዲያዎችን ለመጠቀምና ለመሳሰሉት ረድቶናል።” ተማሪ ነጃ አብዲ፣ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ

ለሰብዓዊነት እንኖራለን!
---------------------------
“I have benefited from the phone charging service in terms of connecting with our relatives and friends. It has also helped us with reading, learning, using social media platforms, and so on.”

Nejah Abdi, Student-beneficiary.

We Live for Humanity!


# International Committee of the Red Cross Ethiopia
------------
📌Website: https://redcrosseth.org/
📌Instagram፡ https://www.instagram.com/ercs1935/
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/ethiopian-red-cross-society/
📌YouTube: https://www.youtube.com/
📌X(Twitter): https://x.com/EthioRedCross
📌Telegram: https://t.me/ERCSHQ
📌 Tiktok: https://www.tiktok.com/
📌 Flickr፡- 137615657@N05/" rel="ugc" target="_blank">https://www.flickr.com/photos/137615657@N05/

Internal /External Vacancy AnnouncementThe Ethiopian Red Cross Society (ERCS) wants to recruit employees in the followin...
15/09/2026

Internal /External Vacancy Announcement

The Ethiopian Red Cross Society (ERCS) wants to recruit employees in the following vacant positions the details of which are mentioned below.

About the Ethiopian Red Cross Society

The Ethiopian Red Cross Society (ERCS) was established in 1935 and is one of the oldest and largest humanitarian organizations in Ethiopia. ERCS provides services to communities affected by natural and manmade disasters through the provision of emergency responses, ambulance and first aid, family reunification, essential drugs, water and sanitation, and other humanitarian services. ERCS also runs disaster risk reduction programs with the aim of creating resilience households and communities. Currently the ERCS has a structure consisting of 15 Regional Offices, Zonal Branches and District/Woreda Branches, Woreda Red Cross Committee and Kebele Red Cross committees.

ERCS also runs disaster risk reduction programs relating to food security, climate change adaptation, livelihood diversification, and institutional capacity building interventions, with the aim of creating resilience households and communities. ERCS works in partnership with the Ethiopian Government, International Federation of the Red Cross and Red Crescent (IFRC), International Committee of the Red Cross (ICRC), partnering National Societies, members, volunteers and the communities we serve.

I.Details of the vacant position

Job Title: ERCS-DRC Migration Project Coordinator (contract)
Work Unit: Disaster Risk Reduction Department
Reports to: Migration and Restoring Family Links Division Manager
Terms of employment: Contract
Place of Work: Addis Ababa
Salary: As per the organizations salary scale

II Job Summary
Job Summary
The Ethiopian Red Cross Society (ERCS) is one of the country's leading humanitarian organizations, dedicated to preventing and alleviating human suffering through humanitarian assistance, disaster response, health, and community resilience programmes. As part of its humanitarian mandate, ERCS implements migration programs that protect and assist migrants, returnees, internally displaced persons (IDPs), refugees, and vulnerable host communities. The Migration and Returnee/Reintegration Program Coordinator is responsible for the overall planning, coordination, implementation, monitoring, and reporting of migration and reintegration programs. Reporting to the Manager, Migration and Restoring Family Links (MRFL) Division, the position provides technical and operational leadership to ensure the effective delivery of humanitarian assistance, protection, Mental Health and Psychosocial Support (MHPSS), livelihoods, social cohesion, and community resilience interventions that promote the safe, dignified, and sustainable reintegration of returnees and other vulnerable populations. The Program Coordinator ensures that all program activities are implemented through established ERCS structures and comply with ERCS policies and procedures, donor requirements, humanitarian standards, and the Fundamental Principles of the Red Cross and Red Crescent Movement. The position also provides technical guidance and support to project staff and volunteers, coordinates with government and humanitarian partners, and ensures timely delivery of quality programmes that strengthen the resilience and self-reliance of affected communities.

Key performance area

Project Planning and Implementation

•Lead the planning, implementation, and coordination of migration projects in accordance with approved project documents, work plans, budgets, and donor requirements.

•Develop annual, quarterly, monthly, and activity implementation plans.

•Ensure timely and quality implementation of project activities across all target branches.

•Coordinate project start-up, implementation, review, and closure processes.

•Monitor implementation progress and recommend corrective actions where necessary.

•Ensure that all interventions comply with ERCS operational procedures and donor requirements.

Project Management and Coordination

•Coordinate project implementation among ERCS headquarters, regional and branch offices, and partner organizations.

•Ensure effective communication and coordination between project teams and technical departments.

•Facilitate coordination meetings, review meetings, workshops, and planning sessions.

•Strengthen collaboration with government institutions, IFRC, ICRC, National Societies, UN agencies, NGOs, and other migration stakeholders.

•Represent ERCS in migration coordination forums and technical working groups.

Technical Leadership

• Provide technical guidance on migration programming, including:

•Humanitarian assistance to migrants and returnees

•Mental Health and Psychosocial Support (MHPSS)

•Livelihoods and Economic Inclusion

•Social Cohesion

•Community-Based Protection

•Restoring Family Links (RFL)

•Protection, Gender and Inclusion (PGI)

•Accountability to Affected Populations (AAP)

•Prevention of Sexual Exploitation and Abuse (PSEA)

•Ensure quality programming and adherence to humanitarian standards.

Monitoring, Evaluation, Accountability and Learning (MEAL)

•Monitor project performance against approved indicators and work plans.

•Conduct regular field monitoring and supportive supervision visits.

•Ensure quality data collection, verification, analysis, and documentation.

•Support baseline, midline, end-line, and operational assessments.

•Document lessons learned, best practices, case studies, and success stories.

•Promote evidence-based programming and continuous learning.
Reporting

•Prepare and submit high-quality weekly, monthly, quarterly, annual, and donor reports.

•Review reports submitted by branch teams and ensure quality and consistency.

•Coordinate financial and narrative reporting with finance, PMER, and technical departments.

•Maintain proper project documentation and filing systems.
Budget and Financial Management

•Prepare annual and quarterly budgets and cash forecasts.

•Monitor budget utilization and expenditure against approved budgets.

•Review Budget Versus Actual (BVA) reports regularly.

•Ensure compliance with ERCS financial procedures and donor regulations.
•Coordinate closely with finance staff to ensure sound financial management.

Capacity Building

•Identify capacity gaps among project staff and volunteers.

•Organize and facilitate trainings, coaching, mentoring, and technical support.

•Strengthen branch capacity in project management, reporting, MEAL, safeguarding, and financial compliance.

Partnership, Representation and Resource Mobilization

•Build and maintain strong partnerships with donors, government institutions, UN agencies, NGOs, and Movement partners.

•Participate in coordination meetings and technical forums.

•Support proposal development, concept notes, assessments, and fundraising initiatives.

•Contribute to the development of migration strategies, policies, and operational guidelines.

Risk Management and Compliance

•Identify operational, financial, and programmatic risks and recommend mitigation measures.

•Ensure compliance with ERCS policies, donor agreements, safeguarding standards, PGI, PSEA, fraud prevention, and accountability requirements.

•Promote ethical conduct and adherence to the Red Cross Code of Conduct.
Supervision
• Supervise project officers, consultants, volunteers, and implementing teams.

•Conduct regular performance reviews and provide technical support.

•Promote teamwork, accountability, and staff development.

Qualification Requirements:

Second/First in: Migration Studies, Development Studies, Social Work, Sociology, Psychology, Community Development, International Relations, Economics, Public Health, Disaster Risk Management, Peace and Conflict Studies and Other Related Social Science disciplines.

Experience

•Minimum 7/9 years related work experience.

•progressively responsible experience in humanitarian or development programming.

•At least 5 years of project management experience.

•Proven experience managing donor-funded migration or displacement projects.

•Experience working with migrants, refugees, returnees, IDPs, and host communities.

•Experience in staff supervision, coordination, and partnership management.

Technical Competencies

•Project Cycle Management

•Results-Based Management

•MEAL

•Budget and financial management

•Proposal development

•Humanitarian standards and principles

•Protection mainstreaming

•MHPSS programming

•Livelihoods programming

•Community engagement

•Risk management

•Report writing

•Microsoft Office Suite and project management tools

Core Competencies

•Leadership and team management

•Strategic planning

•Excellent communication and presentation skills

•Strong analytical and problem-solving skills

•Stakeholder engagement and negotiation

•Cultural sensitivity and interpersonal skills

•Ability to work under pressure and manage multiple priorities

•Commitment to humanitarian values and the Fundamental Principles of the Red Cross and Red Crescent Movement

Languages

•Excellent written and spoken English.

•Fluency in Amharic.

•Knowledge of additional local languages is an advantage.
Working Conditions

•Based in Addis Ababa with frequent travel to project locations.

•May require work outside normal office hours during emergencies or critical project periods.

How to Apply

We invite candidates meeting the required qualifications to fill out online employment application form With the indicated link https://erp.redcrosseth.org/job-opening?opening=ercs-drc-migration-project-coordinator-contract and https://ee.ifrc.org/x/fqTf4qqW before the closing date of this announcement on September 22, 2026.

We Live for Humanity!
--------------
📌Website: https://redcrosseth.org/
📌Instagram፡ https://www.instagram.com/ercs1935/
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/ethiopian-red-cross-society/
📌YouTube: https://www.youtube.com/
📌X(Twitter): https://x.com/EthioRedCross
📌Telegram: https://t.me/ERCSHQ
📌 Tiktok: https://www.tiktok.com/
📌 Flickr፡- 137615657@N05/" rel="ugc" target="_blank">https://www.flickr.com/photos/137615657@N05/

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Red Cross Society posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Red Cross Society:

Shortcuts

Share