05/12/2024
ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር የህንፃ አዋጅን አስመልክቶ በአሀዱ ራዲዮ ስለተላለፈ የተሳሳተ ዘገባን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር በህንፃ አዋጅ ረቂቅ ላይ የተለያዩ ማዳበሪያ ሀሳቦችን ከማቅረቡም በላይ አቋም የያዘባቸውን ጉዳዮች እና ስጋቶቹን መግለጫ በማውጣት በግልፅ አሳውቋል።
በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በተለይ የባለሙያውን ሚና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ እና እንደ ስጋት የጠቀስናቸውን መሰረታዊ ጉዳዮች በሙሉ ምላሽ በማግኘታቸው ይህንን ድምፃችንን ሰምተው ተገቢውን ማስተካከያ ያደረጉ አካላትን በሙሉ ማህበሩ ማመስገን ይፈልጋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሀዱ ራዲዮ አዋጁ ከመፅደቁ በፊት በረቂቁ ላይ የተሰነዘረን ሃሳብ አዋጁ ከፀደቀ በዃላ እንደተሰጠ አስመስሎ ማቅረቡን በማየታችን እጅጉን አዝነናል። ይህንን አይነት ስህተት አሀዱን ከሚያህል ታላቅ የሚዲያ ተቋም የሚጠበቅ ባለመሆኑ ስህተቱን በአስቸኳይ እንዲያረም እያሳሰብን፤ ለተፈጠረውም ስህተት በግልፅ ይቅርታ ይጠይቅ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር
ስራ አስፈፃሚ