Tiko Ethiopia

Tiko Ethiopia የቲኮ አባል ሲሆኑ የቤተሰብ እቅድ እና የምክር አገልግሎቶች በነጻ ያገኛሉ!
በቲኮ፣ መፍትሄ ለዉጥ ስኬት!

🌟 ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን 2026🌟በነሀሴ 15  እና 16 በሐዋሳ ከተማ የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ቲኮ አብሮ አክብርዋል 👏✨"የወጣቶች እውቀት ለጋራ ራዕይ" በሚለው መሪ ቃል፣ ቲኮ ኢት...
31/08/2026

🌟 ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን 2026🌟

በነሀሴ 15 እና 16 በሐዋሳ ከተማ የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ቲኮ አብሮ አክብርዋል 👏✨

"የወጣቶች እውቀት ለጋራ ራዕይ" በሚለው መሪ ቃል፣ ቲኮ ኢትዮጵያ ከሲዳማ ክልል ሴቶችህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ፣ ከሲዳማ ክልል ወጣቶች ማህበር፣ ከኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) እና ከአፍሪያን (AfriYAN) ኢትዮጵያ በተጨማሪም ከክልሉ አመራሮችና አጋሮች ጋር በመሆን ጠንካራ ተሳትፎ አድርጓል።

በዚህም ክብረ በዓል ፡
🌳 በችግኝ ተከላ እና ተሳትፈናል

🎭 በኪነ-ጥበብ ምሽት የወጣቶችን ፈጠራና ባህላዊ ችሎታ አክብረናል

🏥 የስነ-ተዋልዶ ጤና እና የአእምሮ ጤና ግንዛቤ በመፍጠር እንዲሁም በደም ልገሳ ላይ በግንባር ቀደምትነት ተሳትፈናል

🗣️ በወጣቶች ውሳኔ ሰጪነት እና በ"ሶስቱ ስጋቶች ዙሪያ ከክልል ዳይሬክተሮች ጋር ውይይት አድርገናል

መልካም የወጣቶች ወር! 🚀💜💪
#ወጣቶች #ቲኮ

✨ እንኳን ለ1501ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✨እንኳን  ለነቢዩ ሙሐመድ  የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረስዎ። ይህ  በዓል የፍቅር፣ የደስታ እና የበርካታ በረከቶች እን...
24/08/2026

✨ እንኳን ለ1501ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✨

እንኳን ለነቢዩ ሙሐመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረስዎ። ይህ በዓል የፍቅር፣ የደስታ እና የበርካታ በረከቶች እንዲሆንልዎ እንመኛለን።

መልካም በዓል ከቲኮ! 💚

#መውሊድ #መልካምበዓል #ቲኮ

🌸✨ እንኳን ለ2018 ዓ.ም የአሸንዳ፣ ሻደይ እና አሸንድዬ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✨🌸የሴቶች ውበት፣ ባህልና አንድነት በሚደምቅበት በዚህ ህብረ-ቀለማት በዓል፤ በየአካባቢው የሚገኙ እህቶ...
22/08/2026

🌸✨ እንኳን ለ2018 ዓ.ም የአሸንዳ፣ ሻደይ እና አሸንድዬ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✨🌸

የሴቶች ውበት፣ ባህልና አንድነት በሚደምቅበት በዚህ ህብረ-ቀለማት በዓል፤ በየአካባቢው የሚገኙ እህቶቻችንና እናቶቻችን በደስታና በፍቅር የናከርበት የሰላም፣ የጤና እና የደስታ በዓል እንዲሆንልዎ እንመኛለን! 🌺💛

🌼 መልካም የሴቶች በዓል! 🌼

💡 በቲኮ ለውጥ ✨ በቲኮ መፍትሔ 🔑 በቲኮ ስኬት 🎯 የተረጋገጠ ነው!

13/08/2026

ቲኮ የልቤ ቁም ነገር 🤍
ዛሬ አለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ነዉ፣
እንኳን አደረሳችሁ 🎉

የእንቺ ድምጽ፣ የእንቺ ምርጫ፣ የእንቺ ኃይል 💪🏽

ዛሬ፣ በአለም ዙሪያ ያሉ ወጣቶችን በየቦታው እናከብራለን - ጥንካሬሽን፣ ድምጽሽን እና ደህንነሽን የተጠበቀ፣ የበለጠ ፍትሃዊ አለም በመፍጠር እናከብራለን። 🌍

በቲኮ፣ ከወጣቶች ጋር ለመቆም ቆርጠናል በተለይም ከ15-24 ዓመት የሆኑ አፍላ ወጣቶችን - የሚከተሉትን አገልግሎቶች በማቅረብ እንገኛለን፤
✅ ነፃ፣ ለወጣቶች ተስማሚ የሆነ የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶት
✅ በስነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ ባለሞያዋችን ለማናገር እና ለመመካከር ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ
✅ የአቻ ለአቻ ድጋፍ እና ጏደኝነት
✅ ስርዐተ ጽታ ጥቃት ለደረሰባቸው ሚስጥራዊ የጤና አገልግሎት ድጋፍ እና የምክር አገልግሎት

በዚህ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን፣ ከጥቃት ነፃ የመኖር መብትሽን እና ምርጫሽ የተሚከበርበትን አለም ፣ በክብር፣ በደህንነት እና በድጋፍ እናከብራለን።

ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች ደውሉልን! +251979796400 +251903242570 +251979796200 ወይንም ቴሌግራም ላይ መልእክት ያስቀምጡልን 💌

መልካም አለም አቀፍ የወጣቶች ቀን!

#ወጣት #ቲኮ

በሰኔ 30/2018 ዓ.ም ቲኮ ኢትዮጵያ የአምስት ዓመት በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ወጣቶችና አፍላ ወጣቶች የሥነ ተዋልዶና ተያያዥ የጤና መረጃና አገልግሎቶችን በቀላሉ፣ በተደራሽነትና በሚስጥራ...
09/07/2026

በሰኔ 30/2018 ዓ.ም ቲኮ ኢትዮጵያ የአምስት ዓመት በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ወጣቶችና አፍላ ወጣቶች የሥነ ተዋልዶና ተያያዥ የጤና መረጃና አገልግሎቶችን በቀላሉ፣ በተደራሽነትና በሚስጥራዊነት እንዲያገኙ ያለመ የሥነ ተዋልዶ ጤና፣ ኤች አይ ቪ እና ጾታዊ ጥቃት አገልገሎት የሚሰጥበትን ፕሮጀክት በይፋ አስጀመረ።

ለበለጠ መረጃ ቻናሎችንን ይቀላቀሉ 👇

ፌስቡክ- https://www.facebook.com/share/1Hbn296K9D/?mibextid=wwXIfr

ቴሌግራም- https://t.me/tikoethiopia

ቲክ-ቶክ- https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZS-95SEWrEKcK4

💡 በቲኮ ለውጥ ✨ በቲኮ መፍትሔ 🔑 በቲኮ ስኬት 🎯 የተረጋገጠ ነው!

ይህንን ታውቁ ኖርዋል? 🤔በኢትዮጵያ ከ15 እስከ 49 ዓመት የሆናቸው 35% ሴቶች አካላዊ ጥቃት ሲደርስባቸው 17% የሚሆኑት ጾታዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል። 💔የቲኮ አጋር ጤና ጣቢያዎች፣ ጾታዊ ጥ...
24/06/2026

ይህንን ታውቁ ኖርዋል? 🤔

በኢትዮጵያ ከ15 እስከ 49 ዓመት የሆናቸው 35% ሴቶች አካላዊ ጥቃት ሲደርስባቸው 17% የሚሆኑት ጾታዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል። 💔

የቲኮ አጋር ጤና ጣቢያዎች፣ ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን 15-24 እዲሜ የሆኑ ወጣቶችን የህክምና እንክብካቤን እና የምክር አገልግሎትን ድጋፍ የሚያገኙበትን ሁኔታ አመቻችተናል።

በጋራ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰቦችን እንገንባ። 💪🏽💙 እኛ ለእርስዎ እዚህ ነን!💡

ከመጀመሪያው ዕርዳታ ጀምሮ፤ የሥነ ልቦናዊ ምክር አገልግሎት እና የኤችአይቪ እና ሙሉ ምርመራ በማካተት ፣ ለእርስዎ ተገቢውን እንክብካቤ ለመስጠት ከጎኖት ነን። 🩺✨

የቲኮ አባል ዛሬዉኑ ይሁኑ! ከእርሷ የሚጠበቀዉ በቲኮ ሲስተም ላይ ለመመዝገብ እንዲረዳዎ የሰለጠኑ አስተባባሪዎቻችንን ያግኙ። ወይም አጭር የጽሁፍ መልክት KODE ብለዉ ወደ 6428 ይላኩ

ለበለጠ መረጃ እባክዎን በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች ይደውሉ! 📞+251979796400 +251903242570 +251979796200

ሁልጊዜም በቲኮ – ለውጥ! 🔄 በቲኮ – መፍትሔ! 🔓 በቲኮ – ስኬት! 🏅

✨ ዒድ ሙባረክ ከቲኮ! 🌙ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን  ለ1,447ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ እያልን፣ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እንዲሁም የመደጋገፍ ...
26/05/2026

✨ ዒድ ሙባረክ ከቲኮ! 🌙

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1,447ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ እያልን፣ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እንዲሁም የመደጋገፍ ይሆንልዎ ዘንድ እንመኛለን።
ቤታችሁ በሰላም፣ ልባችሁ በምስጋና፣ ሕይወታችሁም በበረከት የተሞላ ይሁን።

እንካን ለኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

Check out Tiko’s video.

ይህ ታውቁ ኖሯል ?ደካማ የአእምሮ ጤና 🧠 ከሰነፍነት ወይም ድክመት ጋር የተያያዘ አይደለም፡፡ ሁሉም የምታውቁት ሰው 👥 የተወሰነ ጊዜ ላይ የአእምሮው ጤናው ረገድ ይቸገራል፡፡ እንዲሁም ለማገ...
14/05/2026

ይህ ታውቁ ኖሯል ?

ደካማ የአእምሮ ጤና 🧠 ከሰነፍነት ወይም ድክመት ጋር የተያያዘ አይደለም፡፡ ሁሉም የምታውቁት ሰው 👥 የተወሰነ ጊዜ ላይ የአእምሮው ጤናው ረገድ ይቸገራል፡፡ እንዲሁም ለማገገም እርዳታ 🤝 ያሻዋል፡፡ በርካታ ሁኔታዎች ለአእምሮ ጤና ሁኔታዎች አስተዋጽኦ ያበረክታሉ፡፡ የእኛ የአእምሮ ጤና በየቀኑ 🗓 የምንከባከበው ነገር ነው፣ ልክ እንደ አካላዊ ጤናችን 🏥 ማለት ነው፡፡

ሁሉም ነገር የሚጀምረው በእናንተ ነው ✨፤ እራሳችሁን ካልተንከባከባችሁ ሌሎችን ለመንከባከብ መቼም ቢሆን ጉልበት አይኖራችሁም 💔። እላዩ ላይ ትንሽ ቀዳዳ እንዳለው ጆክ ማለት ነው፡፡ በውሃ 💧 ልንሞላው እንችላለን፣ ነገር ግን ቀዳዳዋ እስካልተደፈነች 🕳 ድረስ ሁል ጊዜም ውስጣችን መሟጠጡ ይቀጥላል፡፡

የአእምሮ ጤና ❤️ ችግሮች በጣም የተለመዱ ናቸው, እና በሁላችንም ዕድሜዎች ላይ የሚከሰቱ ናቸው። የአእምሮ ጤና ችግር መኖሩ አሳፋሪ አይደለም። በቅደም ተከተል ከእናንተ አውታረ መረብ 🌐 እና ከቅርብ ጓደኞችሁ 👯‍♀️፣ ከማህበረሰባችሁ 🏘 ወይም የአእምሮ ጤና እንክብካቤ አቅራቢዎች ድጋፍ 🤗 ማግኘት ትችላላችሁ።

ሁልጊዜም በቲኮ – ለውጥ! 🔄 በቲኮ – መፍትሔ! 🔓 በቲኮ – ስኬት! 🏅

ሴቶች በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መዋቅር ውስጥ ያበረከቱት አስተዋፅዖ የእውነተኛ ፅናታቸው 💪 ምስክር ነው። ለወጣት ሴቶች 👩🏽‍🎓 ደግሞ ይህንን ሊያሳኩበት የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠ...
06/05/2026

ሴቶች በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መዋቅር ውስጥ ያበረከቱት አስተዋፅዖ የእውነተኛ ፅናታቸው 💪 ምስክር ነው። ለወጣት ሴቶች 👩🏽‍🎓 ደግሞ ይህንን ሊያሳኩበት የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር መቀጠል አስፈላጊ ነው።
ቲኮ በማህበረሰባችን ውስጥ የሴቶችን እሴት በመገንዘብ 🌟 ወጣት ሴቶች እራሳቸውን የሚለውጡበት እና አቅማቸውን የሚገንቡበት ሲስተም አዘግጅቶ እየሰራ ይገኛል።

ለመላው ሴቶች መልካም የአርበኞች ቀን 🎉 የድል በአል 🏆 እንዲሆንላችሁ ቲኮ ይመኛል።

ዛሬውኑ የቲኮ አባል ሁኚ 💙! ከእንቺ የሚጠበቀዉ በቲኮ ሲስተም ላይ ለመመዝገብ እንዲረዳሽ የሰለጠኑ አስተባባሪዎቻችንን ማግኘት ነው☎️ ወይም አጭር የጽሁፍ መልክት ✉️ KODE ብለሽ ወደ 6428 መላክ ነው📲።

ለበለጠ መረጃ ℹ️ እባክዎን በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች ደውይልን!
📞 +251979796400
📞 +251903242570
📞 +251979796200
ሁልጊዜም በቲኮ – ለውጥ! 🔄 በቲኮ – መፍትሔ! 🔓 በቲኮ – ስኬት! 🏅

🌟 ዛሬ ሚያዝያ 23 ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀንን በማስመልከት፣ የቲኮ ራዕይን አብራችሁን እያሳካችሁ ስላላችሁ ባለሞያዎቻችን በሙሉ፤ በአንድነት እና በጋራ ኃላፊነታችሁን በመወጣት የስኬታችን ...
01/05/2026

🌟 ዛሬ ሚያዝያ 23 ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀንን በማስመልከት፣ የቲኮ ራዕይን አብራችሁን እያሳካችሁ ስላላችሁ ባለሞያዎቻችን በሙሉ፤ በአንድነት እና በጋራ ኃላፊነታችሁን በመወጣት የስኬታችን ምንጭ ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን። 💖

🔹ለቲኮ ሰራተኞቻችን 👩‍💼👨‍💼: በየቀኑ በጽኑ ኃላፊነት፣ በፈጠራ እና ወጣት ሴቶችን ለማብቃት ያለማቋረጥ በምታደርጉት ጥረታችሁ የምትፈጥሩት ተጽዕኖ የላቀ ነው! 💪
🔹ለቲኮ አስተባባሪዎቻችን 🤝: በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን ግንኙነት በማጠናከር እና የቲኮ ተፅእኖ እንዲሰፋ በማድረግ የምታደርጉት አገልግሎት ከፍተኛ እውቅና ይገባዋል! 🏆
🔹ለጤና አጋሮቻችን🩺💊: የአፍላ ወጣቶችን ጤና እና ደህንነት በማስጠበቅ የምትሰጡት አገልግሎት ህይወታቸውን እየለወጡ እና የወደፊት ህልሞቻቸውን እያሳኩበት ነው! ✨
🔹ለቲኮ አጋር ባለሱቆቻችን 💼: ደንበኞቻችንን በትህትና እና በትእግስት በማስተናገድ አስተዳደራዊ አስተዋፅዖዎቻችሁ የላቀ ነው። 🚀

👏🏼 ተባብረን በመስራታችንም የ365,836 ወጣት ሴቶች ህይወት በመቀየር የተሻለ ህይወት እንዲኖራቸው አድርገናል ✅ ወደፊትም በብዙ መተማመን፣ ብርታት እና አብሮ በመስራት የበለጠ ስኬት እንፈጥራለን! 💪🏾

🎊እናኳን ለዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን አደረሳችሁ! 🎊
🎉ሁላችሁንም እናመሰግናለን!🎉

ስለ ቲኮ አገልግሎት የበለጠ መረጃ ለማግኘት እባክዎን ከታች ባሉት ስልክ ቁጥሮች ይደውሉ ☎️
+251979796400 +251903242570 +251979796200

💡 በቲኮ ለውጥ ✨ በቲኮ መፍትሔ 🔑 በቲኮ ስኬት 🎯 የተረጋገጠ ነው!

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251993950396

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tiko Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Tiko Ethiopia:

Shortcuts

Share