የሀላባ ወጣቶች ማህበር አድስ አበባ-Halaba Youth Association Addis Ababa

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የሀላባ ወጣቶች ማህበር አድስ አበባ-Halaba Youth Association Addis Ababa

የሀላባ ወጣቶች ማህበር አድስ አበባ-Halaba Youth Association Addis Ababa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የሀላባ ወጣቶች ማህበር አድስ አበባ-Halaba Youth Association Addis Ababa, Nonprofit Organization, Addis Ababa.

30/05/2026

የትም ተወለድ ሀላባ ላይ እደግ ብሏል ወንድማችን❤

በሀላባ ዞን በቁሊቶ ከተማ 1447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓት በድምቀት ተከበረግንቦት 18/2018 ‎በሀላባ ዞን በቁሊቶ ከተማ 1447ኛው የኢድ አል...
27/05/2026

በሀላባ ዞን በቁሊቶ ከተማ 1447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓት በድምቀት ተከበረ

ግንቦት 18/2018 ‎በሀላባ ዞን በቁሊቶ ከተማ 1447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓት በድምቀት ተከብረዋል።

በበዓሉ ወቅት የሀላባ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የአረፋ በዓልን ስናከብር አቅመ ደካሞችን በማሰብና በመደገፍ ሊሆን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል ልዩ የሚያደርገው ሙስሊሙ ማህበረሰብ በአንድነት ቆሞ ከሚያከብራቸው በዓላት አንዱ የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል መሆኑን ገልጸዋል።

ዕለቱ ሁሉም የእምነቱ ተከታዮች እንደየአቅማቸው እርድ በመፈፀም ያለው ለሌለው በማካፈል እኩል ተደስቶ እንዲውል የሚደረግበት ታላቅ በዓል እንደሆነም ጠቁመዋል።

እኛም በዓሉን ስናከብር የእምነቱ አስተምህሮ በሚያዘው መሰረት አቅመ ደካሞችን በማሰብና ያለው ለሌለው በማካፈል በጋራ ልናከብር ይገባል ብለዋል።

አረፋ የእርድ በዓል እንደመሆኑ መጠን ካረድነው አንድ ሦስተኛውን ለተቸገሩ ወገኖች በማካፈልና አብሮ በመብላት በዓሉን በጋራ ለማሳለፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በበዓሉ ወቅትም የእርስ በርስ ትስስርና አንድነትን የሚያጠናክሩ እሴቶቻችንን አጉልተን በማሳየት በደስታ ልናሳልፍ ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በበዓል አከባበሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር መሀመድ ኑሪዬ፣ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴንን ጨምረው ሌሎች የክልል እና የዞኑ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና የእስልምና እምነት ተከታዮች ተገኝተው ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶችን በመከናወን ተከብሯል።

የሀላባ ወጣቶች ማህበር አድስ አበባ-Halaba Youth Association Addis Ababa የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

በዛሬው የጀግኖቹ የሀላባ ከተማ እግር ኳስ ሉዑከን ቡድኑ አቀባበል ላይ የሀላባ ዞን አስተዳደር አቶ ሙህዲን ሁሴን ያስተላለፉት መልዕክት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇ሁለት እየተፈላለጉ ነገር ግን ...
10/05/2026

በዛሬው የጀግኖቹ የሀላባ ከተማ እግር ኳስ ሉዑከን ቡድኑ አቀባበል ላይ የሀላባ ዞን አስተዳደር አቶ ሙህዲን ሁሴን ያስተላለፉት መልዕክት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ሁለት እየተፈላለጉ ነገር ግን ሳይገናኙ ለረጅም አመታት በናፍቆት እየተንገበገቡ ሲጠባበቁ የነበሩ ስሜቶች አንድ ላይ ሆነው የደስታ እንባ ሲያነቡ ከማየት በላይ ደስታ ከየት ይገኛል? የዚህ ታሪክ ተጋሪ ለመሆን ጉብዝና ብቻውን በቂ አይደለም እድለኛ መሆንንም ጭምር ይጠይቃል።
የሀላባ እግር ኳስ ጀግኖች በጀግናው የሀላባ ህዝብ አቀባበል ሲደረግላቸው ያየነው ይህንን ለረጅም አመታት በጽናት የቆየውን የሀላባ ህዝብ የእግር ኳስ ፍቅርና የእግር ኳስ ድል አንድ ላይ የፈጠሩትን በቃላት ከመግለጽ በላይ የሆነ ልዩ ስሜት ነው።

እነዚያን የመከራና የፈተና ጊዜያት በጽናትና በትጋት በማለፍ ዛሬ የሀላባ ከተማ እግር ኳስ ለእግር ኳስ ድል ውለታ ተገቢን ምላሽ በሚሰጥ የሀላባ ህዝብ ዘንድ ማረፊያውን አድርጓል ።

ለዚህን ድል እንድንበቃ በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በሀሳብ ከጎናችን የነበራችሁ የሀላባ እግር ኳስ ወዳጆች፣ ደጋፊዎችና ቤተሰቦች እንዲሁም መላው የሀላባ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ! ደስ አለን !!!

Muhidin Ibn Hussen

09/05/2026

የሀላባ ወጣቶች አአ የድል ስሜታቸውን በአደባባይ ስገልፁ❤

የውሃ እስፖንሰራችን ወንድማችን ሳዲቅ ጀማል ከልብ እናመሰግናለን🙏

With Halaba Tv – I just got recognised as one of their top fans! 🎉
08/05/2026

With Halaba Tv – I just got recognised as one of their top fans! 🎉

የከፍተኛ ሊጉ የአሸናፊዎች አሸናፊ የሀላባ ከነማ የምሳ ግብዣ ተደረገለት።ሚያዚያ 30/ 2018 ሀላባ ቲቪ------------------በትናንትናው ዕለት የ2018 የከፍተኛ ሊጉን ዋንጫ በማንሳ...
08/05/2026

የከፍተኛ ሊጉ የአሸናፊዎች አሸናፊ የሀላባ ከነማ የምሳ ግብዣ ተደረገለት።
ሚያዚያ 30/ 2018 ሀላባ ቲቪ
------------------
በትናንትናው ዕለት የ2018 የከፍተኛ ሊጉን ዋንጫ በማንሳት የሀላባ ህዝብ ከዳር እስከዳር ያስደሰቱት የሀላባ ከነማ ተጨዋቾች በዛሬው ዕለት የምሳ ግብዣ ተደርጎላቸዋል።

በምሳ ግብዣው ላይ የሀላባ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና ቢሮ ሀላፊ እንዲሁም የከነማው ምክትል ፕረዚዳንት የሆኑት አቶ ሃጂ ኑርዬ የሀላባ ህዝብ የብዙ ዓመታት ምኞቱ የሆነውን ፕሮሚየር ሊግ የመግባት ራዕይ በመሳካቱ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ደስታ መፍጠሩን ተናግረዋል።

በተለይም በትናንትናው ዕለት ስኬታችን በዋንጫ ድል በመደገሙ ደስታውን እጥፍ ድርብ እንዳደረገው ገልፀው ከነማው የተሰጠውን የህዝብ አደራ ከስኬት በማድረሱ ለመላው የከነማው ተጨዋቾች፣ አሰልጣኞችና ለክለቡ አመራሮች ትልቅ ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።

ሀላባና እግር ኳስ የረጅም ጊዜ ታሪክ እንዳላቸው የጠቆሙት አቶ ሃጂ ኑርዬ የሀላባ ህዝብ ለስፖርቱ ዘርፍ ዕድገት ካለው ብረቱ ፍላጎት የተነሳ በራሱ አቅም ዓለም አቀፍ ስታዲየም እየገነባ የሚገኝ ህዝብ መሆኑን አብራርተዋል።

የአንድነት ፓርኮች ኮርፖሬሽን የሀብት አስተዳደርና ልማት ምክትል ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ነጃት ግርማ የሀላባ ህዝብ በሠላምና ፍቅር እንዲሁም አቃፊነትና ልማታዊነት መገለጫው የሆነ ህዝብ እንደሆነ ገልፀዋል።

በትናንትናው ዕለት የተገኘው አኩሪ ድል ወደር የለሽ ደስታን የሚያጎናጽፍ አጋጣሚ እንደነበር አስታውሰዋል።

የሀላባ ከነማ ዋና አሰልጣኝ በሺር አብደላ በበኩላቸው የዞኑ መንግስትና ህዝብ ከክለቡ ጎን በመሆን ለዚህ ድርብ ድል በቅተናል ያሉ ሲሆን ለዚህም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የሀላባ ከነማ ስራ አስኪያጅ አቶ ወዳጆ ገራድ ሙንድኖ በበኩላቸው የከነማ ተጨዋቾች በጥሩ ድስፕሊናቸው የሚታወቁ መሆናቸውን ገልፀው በቀጣይም ይህንኑ ድስፕሊናቸውን አስጠብቀው እንደሚቀጡ መሆኑን ተናግረዋል።

በመጨረሻም የሀላባ ቀሊቶ ከተማ ምክትል ከንቲባና የገቢዎች ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዲልቃድር ኢማም ሎላሶ የምሳ ግብዣውን ላዘጋጁት ባለሀብቶች የከተማ አስተዳደሩ ምስጋናውን እንደሚያቀርብ ገልጿል።

በመሐመድ ሞክሼ
Halaba Tv

አሚን ሆስፒታል በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል ለመገንባት መሠረተ-ድንጋይ ተጣለ።ሚያዚያ 24/2018 ሀላባ ቲቪ በመርሐግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በምክትል ርዕሰ መ...
02/05/2026

አሚን ሆስፒታል በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል ለመገንባት መሠረተ-ድንጋይ ተጣለ።
ሚያዚያ 24/2018 ሀላባ ቲቪ

በመርሐግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር መሐመድ ኑርዬ፣ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባዔ ክብርት መነቴ ሙንድኖ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙዔል ዳርጌ፣ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን፣ የአሚን ሆስፒታል መስራች ዶ/ር መሐመድ ሹኩር፣ የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሙበራ ከማል፣ ሌሎች የክልል፣ የዞን፣ የወረዳዎችና የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሐይማኖት መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

Halaba Tv
Amin General Hospital 🙏🙏

👌👌👌👌👌
09/04/2026

👌👌👌👌👌

25/03/2026

🙏🙏🙏🙏

በሻምበል በድሩ ሀሰን የተዘጋጀው  ሀላቢሳ-አማርኛ መዝገበ-ቃላት የሞባይል መተግበሪያ የማስጀመሪያ መርሐግብር ተካሄደ።ጥር 5/2018 ሀላባ ቲቪ---------------------------የሞባ...
14/01/2026

በሻምበል በድሩ ሀሰን የተዘጋጀው ሀላቢሳ-አማርኛ መዝገበ-ቃላት የሞባይል መተግበሪያ የማስጀመሪያ መርሐግብር ተካሄደ።
ጥር 5/2018 ሀላባ ቲቪ
---------------------------
የሞባይል መተግበሪያውን በይፋ ያስጀመሩት የሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ኤፍሬም ዘለቀ ዘመኑ የዲጂታል ዘመን በመሆኑ መፅሓፎችን በዚህ መልኩ ወደሞባይል መተግበሪያ በመቀየር ማዘጋጀት የረጅም ጊዜ የህዝቡ ፍላጎት እንደሆነ ገልፀዋል።

በሻምበል በድሩ ሀሰን የተዘጋጀው ይህ ሀላቢሳ-አማርኛ የሞባይል መተግበሪያ በቀላሉ ለበርካታ አንባቢያን መድረስ የሚችል በመሆኑና ለአጠቃቀም ምቹ በመሆኑ ለየት እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

በመሆኑም መሰል የሀላቢሳ የሞባይል መተግበሪያዎች በቀጣይም እንዲስፋፉ ዘርፉን መደገፍ እንደሚገባ አስረድተዋል።

የመዝገበ-ቃላቱ አዘጋጅ የሆኑት ሻምበል በድሩ ሀሰን በበኩላቸው ከአምስት ዓመት በፊት "Sayichchu"/ብርሃን/ በሚል ርዕስ ያዘጋጁት ይህ መዝገበ-ቃላት ወደሞባይል መተግበሪያ እንዲቀየር በግላቸው ከፍተኛ መስዋዕትነት መክፈላቸውን ገልፀው ስራው ተጠናቆ ለዚህ በመብቃቱ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አያይዘውም የሞባይል መተግበሪያው ለብዙዎች እንዲደርስና በአጠቃቀሙ ዙሪያ አንዳችን ለአንዳችን በማሳየት መረጃ መለዋወጥ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

በሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቶ ጀማል አኒቻ በበኩላቸው የሀላቢሳ ትምህርት እዚህ ደረጃ እንዲደርስ በፊደል ቀረፃው ሂደት፣በመማሪያና ማስተማሪያ መፃሕፍት ዝግጅትና አርትዖት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ሲያበረክቱ መቆየታቸውን አስረድተዋል።

በመሆኑም ሻምበል በድሩ ሀሰንን ጨምሮ በዘርፉ የሚንቀሳቀሱ ፀሐፊዎችን ማገዝና ማበረታታት የሁላችንም ሀላፊነት መሆን አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

በመርሐግብሩ ላይ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ለሻምበል በድሩ ሀሰን የእውቅና ሠርተፊኬትና የማበረታቻ ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

የሞባይል መተግበሪያው ሊንክ
https://halabasit.gov.et/pages/halabisa_app.html

Halaba Tv
Halaba Media Network-ሀላባ ሚዲያ ኔትወርክ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ወጣቶች ማህበር አድስ አበባ-Halaba Youth Association Addis Ababa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share