18/04/2020
ዳዊትም በእግዚአብሄር በአምላኩ ልቡን አበረታ 1ሳሙ 30:6
በሰዎች ህይወት የተጠበቁና ያልተጠበቁ ብዙ ነገሮች ይደርሳሉ። ጥሩም መጥፎም ከባድና ቀላል አይነት።
በዳዊት ህይወት የደረሰው ግን ያልተጠበቀ ነው። ወደ ቤቱ እሱና አብረውት ያሉት ሲመለሱ የጠበቁትና የሆነባቸው ፈጽሞ የተለያዩ ነበሩ። ጉዳታቸው በማልቀስ ብቻ የሚያበቃ አልነበረምና ጨምረው ለማልቀስ ቢፈልጉ እንኳን አልቻሉም።
ዳዊት በዚህ መቀጠል እንደማያዋጣ ስላወቀ መፍትሄው ማልቀስ መቆጨት ሳይሆን ልብን ማበርታት እንደሆነ ገባው። ግን ልቡን የሚያበረታለት ሰው አልነበረም ይባስ ብለው የቅርብ የሚላቸው ከዱት።
ያለው አማራጭ በአምላኩ ልቡን ማበርታት ነበርና አበረታ። ወገኖች ሁኔታው ከባድ ሊሆን ይችላል መፍትሄው ስጋት ልቅሶና ፍርሃት ሳይሆን ልባችንን አበርትተን እንደ ዳዊት በሞት ጥላ መካከል እንኳን አንተ ከኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም ብለን መዘመር ነው።