Ifada Islamic Organization

Ifada Islamic Organization በተያያዙ ክንዶች
በኢስላማዊ ቤተሰብነት

የተረሳውን ማስታወስ፣
የጎደለውን መሙላት፣
በልብ ለልብ ትስስር
ስለ እስልምና መተዋወስ፣

ሁሉንም በህብረት!

"በየቀኑ ጠዋት አላህን መቶ ጊዜ ምህረት እጠይቃለሁ"የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)    #ኢፋዳ
09/10/2026

"በየቀኑ ጠዋት አላህን መቶ ጊዜ ምህረት እጠይቃለሁ"
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)


#ኢፋዳ

08/10/2026

#ኢፋዳ

  ዛሬ በዙሪያህ ያሉት ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ የምትወዳቸው ሰዎች፣ ከጎንህ የሚቆሙ የሚመስሉህም አሉ። የገነባሃዉ ስም አለ፣ የምትመካበት ሀብት አለ፣ የምትደገፍባቸው ሰዎች አሉ....
05/10/2026


ዛሬ በዙሪያህ ያሉት ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ የምትወዳቸው ሰዎች፣ ከጎንህ የሚቆሙ የሚመስሉህም አሉ። የገነባሃዉ ስም አለ፣ የምትመካበት ሀብት አለ፣ የምትደገፍባቸው ሰዎች አሉ...ዱንያም እንደማትለቅህ አድርጋ ትታይሃለች።

ግን አንድ ቀን…

የሰው ሁሉ ድምፅ ይጠፋል፣ የምትጠራቸው ሰዎች ከጎንህ አይኖሩም፣ ሀብትህም አይከተልህም፣ የተሸከምከው ስምም አይጠቅምህም። ያኔ የዓለም ሁሉ ጫጫታ ተረጋግቶ፣ አንተ ብቻህን በጌታህ ፊት ትቆማለህ።
አላህም ይህን ክስተት እንዲህ ሲል ይነግረናንል፦

وَكُلُّهُمْ آتِيهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فَرْدًا
«ሁሉም በትንሣኤ ቀን ብቻውን ወደ እርሱ ይመጣል።»
(ሱረቱ መርየም — 95)

ነገ ከጌታህ ፊት ብቻህን እንደምትቆም አትርሳ...ምክንያቱም...የቂያም ቀን ሰው ከሰው ጋር የሚመጣበት ቀን አይደለም፤ ሰው ከራሱ ሥራ ጋር የሚመጣበት ቀን እንጂ...🕊️
#ኢፋዳ

ቅዳሜ ምሽትን ከኢፋድዮች ጋርየኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት የሚሰራቸውን ስራዎች ለማስተዋወቅ እና እናንተንም የስራው አካል ለማድረግ ልዩ ልዩ መሰናዶዎችን አዘጋጅቶ የፊታችንን ቅዳሜ ከምሽቱ 3:00...
02/10/2026

ቅዳሜ ምሽትን ከኢፋድዮች ጋር
የኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት የሚሰራቸውን ስራዎች ለማስተዋወቅ እና እናንተንም የስራው አካል ለማድረግ ልዩ ልዩ መሰናዶዎችን አዘጋጅቶ የፊታችንን ቅዳሜ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በድርጅቱ የቲክቶክ አካውንት ላይቭ ላይ ይጠብቃችኋል።


#ኢፋዳ

وَيَسِّرْ لِي أَمْرِي«ነገሬንም ለእኔ አግራልኝ፡፡»(ቁርአን 20:26)   #ኢፋዳ
02/10/2026

وَيَسِّرْ لِي أَمْرِي
«ነገሬንም ለእኔ አግራልኝ፡፡»
(ቁርአን 20:26)

#ኢፋዳ

 አንዳንዴ ሰው የሚጠብቀው ለውጥ ከሰማይ የሚወርድ መልስ ይመስለዋል፤ የተዘጋው በር በራሱ ይከፈት፣ የተጨነቀው ልብ በራሱ ይረጋ፣ የተዘበራረቀው ሕይወትም በአንድ ቀን ይስተካከል ይላል።ነገር ...
28/09/2026


አንዳንዴ ሰው የሚጠብቀው ለውጥ ከሰማይ የሚወርድ መልስ ይመስለዋል፤ የተዘጋው በር በራሱ ይከፈት፣ የተጨነቀው ልብ በራሱ ይረጋ፣ የተዘበራረቀው ሕይወትም በአንድ ቀን ይስተካከል ይላል።

ነገር ግን አላህ ለውጥን ከውጭ ከመጠበቅ በፊት ወደ ውስጣችን እንድንመለስ ያስተምረናል። ምክንያቱም የሕይወታችን መልክ ብዙ ጊዜ የልባችንን ሁኔታ ይከተላል።

የምትመኘው ነገር ካልተለወጠ፣ ምናልባት አንተ ራስህ እንድትለወጥ የሚጠብቅ ነገር አለ። የምትፈልገው መንገድ ካልተከፈተ፣ ምናልባት እርምጃህን ለመቀየር የመጣ ጊዜ ነው...እና በዚያ የውስጥ ለውጥ መነሻ ላይ፣ አንድ የአላህ ቃል እንደ ብርሃን አምድ ከፊት ይቆማል...🦋

إِنَّ اللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا مَا بِأَنْفُسِهِمْ
«አላህ አንድን ሕዝብ ያለበትን ሁኔታ እነርሱ በራሳቸው ውስጥ ያለውን እስኪለውጡ ድረስ አይለውጥም።»
(ሱረቱ አር-ረዕድ — 11)
ለውጥን ከውጭ አትጠብቅ፤
አንዳንድ ጊዜ የምትጠብቀው መልስ የሚጀምረው ከውስጥህ ነው።
#ኢፋዳ

إِنَّ اللَّهُ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُوا عَلَيْهِ وَسَلَّمُوا تسلي...
18/09/2026

إِنَّ اللَّهُ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُوا عَلَيْهِ وَسَلَّمُوا تسليما

#ኢፋዳ

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 05:00
Tuesday 08:30 - 05:00
Wednesday 08:30 - 05:00
Thursday 08:30 - 05:00
Saturday 08:30 - 05:00
Sunday 08:30 - 05:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ifada Islamic Organization posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share