Alfejir Islamic Association አልፈጅር እስላማዊ ድርጅት

Alfejir Islamic Association  አልፈጅር እስላማዊ ድርጅት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Alfejir Islamic Association አልፈጅር እስላማዊ ድርጅት, Non-Governmental Organization (NGO), Addis Ababa.

22/06/2026
09/05/2026
09/05/2026
ፈጅር ኢስላማዊ ድርጅትአልሐምዱ ሊላህበዛሬው ቀን  በደቡብ ወሎ  ለጋንቦ ወረዳ  በፊጣ ቀበሌ ፈጅር ኢስላማዊ ድርጅ በአዲስ አበባ ከተለያዩ  መስጂዶች ፣ከአካባቢው ማህበረሰብ እና አንድ አህለ...
20/12/2025

ፈጅር ኢስላማዊ ድርጅት
አልሐምዱ ሊላህ
በዛሬው ቀን በደቡብ ወሎ ለጋንቦ ወረዳ በፊጣ ቀበሌ ፈጅር ኢስላማዊ ድርጅ በአዲስ አበባ ከተለያዩ መስጂዶች ፣ከአካባቢው ማህበረሰብ እና አንድ አህለል ኸይር ጋር በመተባበር ያስገነባውን መስጂድ እና መድረሳ በዛሬው እለት አስመረቀ ። በዚህ ምርቃት ሼህ ሐሰን ሃሚዲን : ከዞኑ መጅሊስ ስራ አስፈፃሚዎች የአልፈጅር ድርጅት የስራ አመራሮች : ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የአከባቢው መህበረሰብ በተገኘበት ደማቅ የደዕዋ ፕሮግራም ተካሂዶል ። አልሀምዱ ሊላሂ ረቢልዓለሚን ።

አልፈጅር ኢስላማዊ ድርጅት ከዚህ ኪታብ 40 ገዝቶ ለደረሶች አበርክቷል ።የእውቀት ቅብብሎሽ እና የሰለፎች መንገድ አስፈላጊነትቀን: ታህሳስ 05, 2018 ዓ.ም.ቦታ: አዲስ አበባ፣ አወሊያ መ...
15/12/2025

አልፈጅር ኢስላማዊ ድርጅት ከዚህ ኪታብ 40 ገዝቶ ለደረሶች አበርክቷል ።

የእውቀት ቅብብሎሽ እና የሰለፎች መንገድ አስፈላጊነት
ቀን: ታህሳስ 05, 2018 ዓ.ም.
ቦታ: አዲስ አበባ፣ አወሊያ መመረቂያ አዳራሽ

በሸይኽ ሰዒድ አራጌ "አውኑ ረሕማን" መጽሐፍ ምርቃት ላይ የቀረቡ ወሳኝ ምክሮች
በአወሊያ መመረቂያ አዳራሽ የተካሄደው የሸይኽ ሰዒድ አራጌ "አውኑ ረሕማን" መጽሐፍ ምርቃት ዝግጅት፣ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪካዊ ፈተናዎች እና የዒልም (የእውቀት) ቅብብሎሽ ወሳኝ ሚና ላይ ትኩረት አድርጎ ተካሂዷል። ዝግጅቱ በዋነኝነት የታሪካዊ ውዥንብሮችን (እንደ አህባሽ አጀንዳ ያሉትን) ለመመከት እና የእምነትን ንጽህና ለመጠበቅ የፅሑፍ ሥራዎች እና ኢስናድ (የሰነድ ሰንሰለት) ያላቸውን ወሳኝ ሚና አጉልቷል።

ፕሮግርሙ ላይ የተለያዩ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ የነበሩት ሸይኽ ሙሀመድ ዘይን ዘህረዲንም በንግግራቸው፣ ዑለማዎች የቀደመውን የእውቀት ውርስ ለመቀጠል እና ለትውልድ ለማሻገር፣ በሀገር ቋንቋ የተለያዩ መጻሕፍትን በማዘጋጀት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አደራ አሳስበዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የታደሙት ሸይኽ ኤልያስ አህመድም በመረጃ እና በሰነድ የተደገፈ እውቀት አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል። "ኢስናድ የዲን አካል ነው፤ ኢስናድ ባይኖር ሁሉም ሰው የሻውን ይናገር ነበር" የሚለውን የአብደላህ ኢብኑ ሙባረክን ንግግር ጠቅሰው፣ በመረጃና በሰነድ የተደገፈ እውቀት ብቻ ከውሸቶች እና የተዛቡ አመለካከቶች (የእምነት ርዕሶችን የኺላፍ ርዕስ አድርጎ ከማቅረብ) እንደሚከላከል አብራርተዋል።

ኡስታዝ አህመዲን ጀበልም በሰጡት አስተያየት፣ በሰለፎች አኗኗር (ሀያት) ላይ ብቻ ከማተኮር ጎን ለጎን፣ መሰረታዊ የሆነውን እምነታቸውን (አቂዳቸውን) ለመጠበቅ እና ትኩረት ለመስጠት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

በመጨረሻም፣ ዝግጅቱ ሁሉም ሙስሊሞች በተለይም ደግሞ ዑለማዎች የሰለፎችን ንጹሕ አቂዳ በመረጃ (ኢስናድ) ላይ ተመስርቶ እንዲያሰራጩና ለቀጣዩ ትውልድ በሀገር ቋንቋ የተሟላ የእውቀት ቅብብሎሽ አሻራ እንዲያስቀምጡ አሳስቦ ተጠናቋል።

አልሀምዱ ሊላህ አልፈጅር ኢስላማዊ ድርጅት በአዊ ዞን በጓንጓ ወረዳ በይማሌ ቀበሌ  ከአንድ አህለል ኸይር ጋር በመተባበር  5 ክላስ መድረሳ አስገንብቶ ለማህረሰቡ በዛሬው ዕለት አስረክቧል። ...
15/12/2025

አልሀምዱ ሊላህ
አልፈጅር ኢስላማዊ ድርጅት በአዊ ዞን በጓንጓ ወረዳ በይማሌ ቀበሌ ከአንድ አህለል ኸይር ጋር በመተባበር 5 ክላስ መድረሳ አስገንብቶ ለማህረሰቡ በዛሬው ዕለት አስረክቧል። 05/04/2018

21/05/2025
21/05/2025

አንጋፋው አፍሪካ ቲቪ ዳግም ለብዙሃን ለመድረስ

በቅርብ ቀን በኢትዮ ሳት !



21/05/2025

Address

Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alfejir Islamic Association አልፈጅር እስላማዊ ድርጅት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share