Egziabher Abe Maheber

Egziabher Abe Maheber 1ኛ ቆሮ 16:13 -14 ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ። በእና?

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፡፡...ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን.... ያዕ 4፡15
20/02/2018

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፡፡...ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን....
ያዕ 4፡15

16/06/2017

ትን. ዕንባቆም 2፡3
እርሱም አይዋሽም፤ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው፤ እርሱ አይዘገይም፡፡

ጳግሜ 3+++ እንኳን ለሊቀ መላእክ ቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ +++ይህ ቀን ርኀወ ሰማይ ማለት በእግዚአብሔር አምላክ ቸርነት በቅዱስ ሩፋኤል አማካኝነት ለ24 ሰዓት ...
08/09/2016

ጳግሜ 3
+++ እንኳን ለሊቀ መላእክ ቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ +++

ይህ ቀን ርኀወ ሰማይ ማለት በእግዚአብሔር አምላክ ቸርነት በቅዱስ ሩፋኤል አማካኝነት ለ24 ሰዓት ገነት የሚከፈትበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ማለት ሰማይ መከፈት መዘጋት ኖሮበት ሳይሆን የአምላክ የቸርነቱ ምስጢር ተገልፆ የሚታየበት ዕለት ነው ለማለት ነው፡፡
ጳግሜ 3 ቀን ቅዱስ ሩፋኤል ለሰው ልጀች ቋሚ አገልጋይ በሁሉም ነገር ረዳት በመሆን የተሾመበት የሰማይን የምህረት በር ለመክፈትና ለመዝጋት ሙሉ ሥልጣን ያገኘበትና ለሰው ልጅ ምህረት ከፈጣሪ የሚሰጥበት ቀነ ስለሆነ ዕለተ ምርያ የምህረት የደስታ፣ የይቅርታ፣ የሰላም ዕለት ትባላለች፡፡

በዚህ ዕለት ማንኛውም ሰው የሚዘንበውን ዝናብ በፀበልነቱ አምኖ ቢጠጣና ቢጠመቅ ከተለያየ በሽታ ይፈወሳል፡፡ ዝናቡ የምህረት የሚወርደውም ጠል ለምድር በረከት ለሰው የሰላም የፍቅር የጤና የበረከት ማግኛ ይሆናል፡፡

እንዲሁም ከፍጡራን ወገን በሰማይ በምድርም የሚተከከለው የሌለ የሳሌም ንጉሥና ነቢይ እናትና አባት እንዳለው የማይታወቅ ሙቶ ተቀበረ የማይባል ንፁህ ክቡር የካህኑ መልከ ጼዴቅ በዓልም የሚከበረው በዚሁ ዕለት ነው፡፡

የእግዚአብሔር አብ የእግዚአብሔር ወልድ የእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ቸርነት ይደረግልን፡፡ የካህኑ መልከ ጼዴቅ በረከት የቅዱስ ሩፋኤል በረከተ ቃል ኪዳን በእኛ እና በሀገራችን ሁሉ ላይ ይሁን፡፡ እግዚአብሔር አብ ኢትዮጵያ ሀገራችንን እና ህዝቧን ሠላም ያድርግልን፡፡
መልካም በዓል!!

እንኳን ለደብረታቦር እና እግዚአብሔር አብ በዓል በሰላም አደረሳችሁየደብረ ታቦር /ቡሄ/ በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ደቀ መዛሙርት ማለትም ጴጥሮስ፣ ዮሐንስንና ያዕቆብ...
19/08/2016

እንኳን ለደብረታቦር እና እግዚአብሔር አብ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
የደብረ ታቦር /ቡሄ/ በዓል
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ደቀ መዛሙርት ማለትም ጴጥሮስ፣ ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ ክርስቶስ ባይሞት እንዴት ያለ ክብር እንደሚቀርባቸው ያሳያቸው ዘንድ ምስክርም እንዲሆኑ እነዚህን ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ይዞ ወጣ፡፡ በዚያም እንደ ዮርዳኖስ ወንዝ መድኃኔዓለም ክብረ መንግሥቱን፣ ብርሃነ መለኮቱን ገልጠላቸው፡፡ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን ቤተ ክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ዘጠኙ ዐበይት የጌታ በዓላት አንዱ የሆነው በዓለ ደብረታቦር የዚህ ታሪክ መታሰቢያ ነው ፡፡ በዚህ ዕለት ሕፃናት ጅራፋቸውን ገምደው እያስጮኹ ይጨፍራሉ፡፡ ይኸውም ጅራፍ ሲጮህ እንደሚያስደነግጥ ሁሉ ከጌታ ጋር የነበሩት ሦስቱ ደቀ መዛሙርትም አብ በደመና ሆኖ ሲናገር መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን የሚያስታውስ ነው፡፡

ሐምሌ 19 ቀን ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በሰማ እትነት መከራ የተቀበሉበት እለት ነው።የእግዚአብሔር መልአክ ሃያሉ ቅዱስ ገብርኤልእግዚአብሔርን የሚያመለኩና የሚገዙ እንዲሁም ለእርሱ ከብር...
26/07/2016

ሐምሌ 19 ቀን ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በሰማ እትነት መከራ የተቀበሉበት እለት ነው።
የእግዚአብሔር መልአክ ሃያሉ ቅዱስ ገብርኤል
እግዚአብሔርን የሚያመለኩና የሚገዙ እንዲሁም ለእርሱ ከብርን በመስጠት ያሉ ሁሉ ከነገር እንኳን አንዳች እንደማይጎድላቸው በዘመናት መካከል ተመልክተናል፡፡ ይህም ደግሞ እውነት ነው፡፡ ደግሞም እግዚአብሔር ለሚወዱት የሚሆን ጠባቂ በዙሪያቸው ያቆማል፡፡
ቅዱስ ቂርቆስ እድሜው የሦስት አመት ሳለ እናቱ ቅድስት እየሉጣ ከሮሜ ወደ ሌላ ሃገር ሸሽታ ይዛው ሄደች በዚያም የሸሸችውን መኮንኑን አገኘችው። የሚያውቋትም ሰዎች ሸሽታ እንደመጣች ስለተረዱ ለመኮንኑ ነገር ሰሩባት። መኮንኑም ወደ እርሱ አስጠራትና ስለ አምልኮ ጠየቃት። ቅድስት እየሉጣም መኮንን ሆይ፡ እድሜው ሦስት አመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው። ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ወደ አለበት ጭፍራውን ልኮ ወደ እርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው። ሕጻን አዱስ ቂርቆስም መለሰለት እንዲህም አለው። አዎ እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ ደስታየም ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኅዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው መጽሐፍ ቅዱስም ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና አለው። እግዚአብሔር አምላክ ኃይልንና ንግግርን ሰጥቶታልና በዚያ ለተሰበሰቡት ሰዎች እስኪደነግጡ ድረስ ብዙ ተናገረ። ሕፃን ቅዱስ ቂርቆስም ንጉሱን መኳንንቱንና ጣኦታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ። መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ስቃይ፡ ታላላቆች አንኳ የማይችሉትን ታላቅ አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው። እናቱ ቅድስት እየሉጣንም ከ እርሱ ጋር እንደ እርሱ በጣሙን አሰ ቃያት። እግዚአሔብሔር ግን ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር።
ብዙዎች አህዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት አምነው በሰማእትነት ሞቱ የሰማእትነትንም አክሊል ተቀበሉ። በሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት። ታላላቅ ድንቅ ተአምራቶችንም ያደርግ ነበር። ብዙዎች በሽተኞችንም ያድናቸው ይፈውሳቸው ነበር። ይህንን ያየ መኮንን በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውሃ ጨምረው በ እሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ። የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ሆነ ድምጹም በጣም ያስተጋባ ነበር። ይህን ያየችና የሰማች እናት ቅድስት እየሉጣም ፍርሃትና የሃይማኖት ጉድለት ታየባት። ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናቱ ቅድስት እየሉጣን ሁኔታዋን አይቶ ወደ አምላኩ እግዚአብሔር ጸለየ። ያን ጊዜ ልዑል እግዚአብሔር ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አሳያት። ቅድስት እየሉጣም እንደገና በሃይማኖቷ ጸናች። እግዚአብሔር አምላኳንም አመሰገነችው። ልጇን ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስንም ልጄ ሆይ አንተ ከ እንግዲህ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ አለችው። ቅድስት እየሉጣም ለልጇ ያች የተወለድክባት እለት ቀኗ የተባረከችና የተቀደሰች ናት አለችው። የመኳንንቱ ጭፍሮችም እሳት ወደ አለበት ጋኖች ውስጥ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት እየሉጣን በጨመሯቸው ጊዜ የውሃው ፍላት ወደያውኑን ቀዘቀዘ። ከ እግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የ እሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና። ይህን ያየ መኮንን ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው አንዲጎትቷቸው አዘዘ። ከ እግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸው። መኮንኑም በታላቅ ስቃይ ያሰቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው። በዚህን ጊዜ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስን አረጋጋው አጽናናው። ስሙን ጠርተው መታሰቢያ ለሚያደርጉለትም በረከትን እንደሚያገኝ ቃል ኪዳን ሰጠው ። እግዚአብሔር አምላካችን የሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት እየሉጣን በረከታቸውንና ረድኤታቸውን ያድለን አሜን።
(አትሮንስ ከዲያቆን ንጋቱ አበበ ገፅ ላይ የተወሰደ)
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ!!!

01/07/2016

ወዳጄ ሆይ የምትናገረው ነገር ሁሉ ያነጋገር ፍፃሜ እንዲሆንልህ አስበህ ከያንዳንዱ ሰው ጋራ በፍቅርና በርህራሄ ተነጋገር ቁጣ ቆይቶ ቢያስቡት ያሳዝናል፡፡ ወዳጆች ሆይ ሌላውን ሳትጐዱ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፡፡ ወንድምህ ቢቆጣ ክፉ ቢናገርህ አንዳች እንዳትመልስ፡፡ በወንድሙ ላይ በከንቱ የተቆጣ በፍርድ ይፈረድበታል፡፡ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ የሰው ቁጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያሠራምና ከእናንተ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርና ለቁጣ የዘገየ ይሁን፡፡
እግዚአብሔርአብ ማህበር መልካም ፆም

24/06/2016

በፍርድ ቀን ከአለም ሀብትና ንብረት ውጭ በእግዚአብሔር ፊት ትቆማለህ፡፡ መልካምም ይሁን ክፉ የሰራኸው ስራ እንጂ የአለም ቁሳዊ ነገር አይከተልህም፡፡ ስለዚህ ምኞትህንና ተስፋህን በአለም ላይ በማድረግ መታወክ ለአንተ ጥሩ አይደለም ይህች ምድር እሾህና አሜኬላ እንዳበቀለችልህ ትዘነጋለህ?
ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

20/06/2016

እንኳን ለእግዚአብሔርአብ ወርሀዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ♥ †
ሥላሴ ማለት ምን ማለት ነው?
ሥላሴ የሚለው ቃል ሠለሰ ሦስት አደረገ ከሚለው የግእዝ የተገኘ ሲሆን ፍቺውም ሦስት ማለት ነው፡፡ በአጠቃላይ ምሥጢረ ሥላሴ ማለት የሦስትነት ምሥጢር ማለት ነው፡፡
ሥላሴን በሴት አንቀፅ ቅድስት ማለታችን ለምንድን ነው?
ሥላሴን በሴት አንቀፅ ቅድስት ማለታችን እግዚአብሔር እንደእናት ርህሩህ እንደሆነ ለመግለፅ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ቅድስት ሥላሴ ማለት ልዩ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ እንዲሁም አንድነቱን ለመግለፅ ቅዱስ እግዚአብሔር እንላለን፡፡ በወንድ አንቀፅ ቅዱስ ማለታችን እንደ አባትነት ይንከባከበናል ያስብልናል እና ነው፡፡ በሌላ በኩል ቅዱስ እግዚአብሔር ማለት ልዩ አንድነት ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት ልዩ የተባለበት ምክንያት ከፍጡራን ውስጥ በባህርይ አንድ በአካል ሦስት የሆነ ፍጡር ስለማይገኝ ነው፡፡

02/05/2016

ሰላም ለእናንተ ይሁን ብሎ ሰላሙን ትቶልን ወደ አባቱና ወደ አባታችን አርጓል፡፡ እንግዲህ ፀንተን እንቁም እንደገናም በባርነት ቀንበር እንዳንያዝ ተጠንቅቀን እንኑር፡፡
He is Risen!!

28/04/2016

የዮሐንስ ወንጌል 1፡-15
1 ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው።
2 እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው አሳብ ካገባ በኋላ፥
3 ኢየሱስ አብ ሁሉን በልጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥
4 ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤
5 በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።
6 ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱም። ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው።
7 ኢየሱስም መልሶ። እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው።
8 ጴጥሮስም። የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም አለው። ኢየሱስም። ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም ብሎ መለሰለት።
9 ስምዖን ጴጥሮስም። ጌታ ሆይ፥ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም አለው።
10 ኢየሱስም። የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ግን ንጹሕ ነው፤ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፥ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም አለው።
11 አሳልፎ የሚሰጠውን ያውቅ ነበርና፤ ስለዚህ። ሁላችሁ ንጹሐን አይደላችሁም አለው።
12 እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ፥ እንዲህም አላቸው። ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?
13 እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።
14 እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል።
15 እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Egziabher Abe Maheber posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share