Ethiopian Nurses Association

Ethiopian Nurses Association Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Nurses Association, Community Organization, Megenagna , Amare Abrham building, 11th floor, Addis Ababa.

Ethiopian Nurses Association is a not-for-profit which exists to represent the profession of nursing in Ethiopia, to promote excellence in the nursing practice and protect the public as well as the rights of nurses. The Ethiopian Nurses Association (ENA) was established in1952 and is legally recognized professional association that represents nurses in Ethiopia, striving to standardize, and promot

e quality nursing services to the society through research, education, leadership and good governance. ENA is a not-for-profit which exists to represent the profession of nursing in Ethiopia, to promote excellence in the nursing practice and protect the public as well as the rights of nurses. The Ethiopian Nurses Association (ENA) strives to provide and promote quality nursing services to the society through quality service, research, advocacy and leadership by standing for the rights of nurses. Vision
The ENA envisions attaining excellence in leadership, advocacy, quality service and to be innovative, translational and influential professional association in Africa by the year 2025

Mission
ENA strives to support system for provision and promotion of quality nursing services to the society through empowering nurses, research, improving quality of education, advocacy, leadership and by standing for the rights of nurses

ዜና ዕረፍት____________በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የጤና ባለሙያ የነበሩት ሲ/ር ካሳዬ ሀጎስ በገጠማቸው የጤና እክል ምክንያት በማስተማሪያ ሆስፒታሉ በህክምና ሲረዱ ቆ...
09/08/2026

ዜና ዕረፍት
____________
በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የጤና ባለሙያ የነበሩት ሲ/ር ካሳዬ ሀጎስ በገጠማቸው የጤና እክል ምክንያት በማስተማሪያ ሆስፒታሉ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሀሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ አለም ድካም አርፈዋል።

መላው የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሲ/ር ካሳዬ ሀጎስ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ፈጣሪ ለመላው ቤተሰባቸውና የስራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን እንዲሰጣቸው ይመኛል ።

የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ

ነፍስ ይማር !

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማራችሁ ፣ የተማሩትን የቀጠራችሁ እና ሌሎችም ።ይህችን መጠይቅ ሙሉልን ተብላችሗል ።
08/08/2026

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማራችሁ ፣ የተማሩትን የቀጠራችሁ እና ሌሎችም ።

ይህችን መጠይቅ ሙሉልን ተብላችሗል ።

This survey, developed by Addis Ababa University, invites stakeholders of the MSc in Advanced Nursing Program, including faculty, administrators, students, clinical partners, employers, and other invested parties, to share their perspectives on the program’s quality and relevance. You will be aske...

የሐዘን መግለጫ‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጤና ባለሙያ የነበሩት ኮማንደር ሲስተር የትምወርቅ አለሙ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።‎‎ኮማንደር ሲ/ር የትምወርቅ አለሙ ከአባታቸው ከአቶ በየነ ታፈሰ...
05/08/2026

የሐዘን መግለጫ

‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጤና ባለሙያ የነበሩት ኮማንደር ሲስተር የትምወርቅ አለሙ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

‎ኮማንደር ሲ/ር የትምወርቅ አለሙ ከአባታቸው ከአቶ በየነ ታፈሰ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብርቄ ባዩ በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጨለንቆ በተባለ ቦታ በ1957 ዓ.ም. ተወለዱ።

‎ኮማንደር ሲ/ር የትምወርቅ ያደጉት በአያታቸው በአቶ አለሙ ጨነቀው ዘንድ ሲሆን ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጨለንቆ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በአዲስ አበባ በቀድሞው ኮከበ ጽባሕ ትምህርት ቤት ተምረው አጠናቀቁ።

‎በ1977 ዓ.ም. ሀገርን በፖሊስነት ሙያ ለማገልገል ካላቸው ጥልቅ ፍቅር የተነሳ ተቋሙን ተቀላቅለው በመስራት ላይ እያሉ በተቋሙ በተመቻቸላቸው የትምህርት ዕድል በ1979 ዓ.ም የጤና ረዳትነት ሙያ ተምረው ተቋሙን በታታሪነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

‎መኮንኗ በክሊኒካል ነርሲንግ ዲፕሎማ ተመርቀው ሠራዊቱን ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን ሙያቸውን በትምህርት ለማሳደግ ካላቸው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ በነርሲንግ የመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብለው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በጤና ሙያተኝነት እስከ ቲም አመራርነት አገልግለዋል።

‎ኮማንደር ሲ/ር የትምወርቅ ለሠላሳ ሰባት ዓመት ከዘጠኝ ወራት በከፍተኛ ሙያዊ ዲሲፕሊንና ታታሪነት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጤና አገልግሎት ዋና መምሪያ ሲያገለግሉ ቆይተው ዕድሜያቸው ለጡረታ ሲደርስ በ2015 ዓ.ም ከተቋሙ በክብር በጡረታ ተሰናብተዋል።

‎መኮንኗ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በክብር በጡረታ ከተለዩ በኋላ በለገሀር ጠቅላላ ሆስፒታል ተቀጥረው በሙያቸው እያገለገሉ በነበረበት ወቅት ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በተወለዱ በ61 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

‎ኮማንደር ሲ/ር የትምወርቅ አለሙ ታታሪ፣ ሰው አክባሪና በመልካም ምግባራቸው የሚታወቁ፤ ለተቋሙና ለሕክምና ሙያቸው ጥልቅ ፍቅርና ክብር ያላቸው ከፍተኛ መኮንን ነበሩ።

‎የኮማንደር ሲ/ር የትምወርቅ አለሙ የቀብር ሥነ ሥርዓት ፈረንሳይ ጉራራ መካነ ኢየሱስ ቤተሰቦቻቸው፣ የሥራ ባልደረቦቻቸውና ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ማለትም ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በክብር ተፈፅሟል።

‎ኮማንደር ሲ/ር የትምወርቅ አለሙ ባለትዳርና የሁለት ወንድ ልጆች እና የአንድ ሴት ልጅ እናት ነበሩ።

‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በኮማንደር ሲ/ር የትምወርቅ አለሙ ሕልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ

A Tribute to a Pioneer: Mourning the Passing of Sister Birkenesh KebedeDate: July 31, 2026To: The Family of the Late Sis...
31/07/2026

A Tribute to a Pioneer: Mourning the Passing of Sister Birkenesh Kebede
Date: July 31, 2026

To: The Family of the Late Sister Birkenesh Kebede, the Ethiopian Nursing Community, and the General Public.

It is with profound sorrow and a deep sense of loss that the Ethiopian Nurses Association (ENA) announces the passing of one of our profession's most distinguished pioneers, Sister Birkenesh Kebede.

She passed away on ሀምሌ 23, 2018 E.C. (July 30, 2026 G.C.) at the age of 96.

Sister Birkenesh was a cornerstone of the Ethiopian nursing profession. As one of the first nine graduates of the Ethiopian Red Cross School of Nursing in 1949, she was part of a generation that laid the very foundation of modern nursing in our nation.

Her career was not merely a job; it was a lifelong mission of courage, compassion, and unwavering service to humanity.

Her legacy is forever intertwined with moments of global significance.

Following her graduation, she and her colleague, Sister Aster Ayana, were selected to serve with the 3rd Kagnew Battalion of the United Nations Peacekeeping Force in Korea from 1953 to 1954. As one of the first two Ethiopian nurses to serve in an international conflict zone, she provided critical medical care to wounded peacekeepers and served as a translator, demonstrating extraordinary bravery and professionalism. This service set a powerful precedent for future generations of Ethiopian nurses.

Upon her return, she continued her dedicated service in Ethiopia, working at St. Paul's Hospital and other health institutions across the country. Her contributions were recognized on the world stage when she received the prestigious Nightingale Medal, the highest international distinction a nurse can achieve. This honor is a testament to her "exceptional courage and devotion" to the wounded, sick, and vulnerable, and it places her in a select group of African women to have received this recognition.

Sister Birkenesh's life exemplified the very values that the Nurses strives to uphold: excellence in practice, advocacy for the health of the public, and the promotion of the nursing profession. She was a role model, a trailblazer, and an inspiration to the thousands of nurses we present today.

Her legacy will continue to inspire us as we work to improve the health and well-being of our society. She will be forever remembered as a symbol of mercy, heroism, and unparalleled national service. The Ethiopian Nurses Association remains committed to carrying forward the torch of excellence she so brilliantly lit for all of us.

May her soul rest in eternal peace.

About the Ethiopian Nurses Association (ENA)

Established in 1952, ENA is the first professional association in Ethiopia, legally recognized to represent the nursing profession. We are dedicated to standardizing and promoting quality nursing services through research, education, and leadership.

Contact
Ethiopian Nurses Association
Addis Ababa, Ethiopia
[email protected]

ሌላዋን ለማዳን የተሰዋች ነብስ!እውነተኛ ጀግንነት ሁልጊዜ በጦር ሜዳ አይገለጥም፤ አንዳንድ ጊዜ በሆስፒታል ክፍል፣ በጤና ጣቢያ እና በአምቡላንስ ውስጥ ይፃፋል። ይህም Midwife ነርሷ ህይ...
27/07/2026

ሌላዋን ለማዳን የተሰዋች ነብስ!

እውነተኛ ጀግንነት ሁልጊዜ በጦር ሜዳ አይገለጥም፤ አንዳንድ ጊዜ በሆስፒታል ክፍል፣ በጤና ጣቢያ እና በአምቡላንስ ውስጥ ይፃፋል። ይህም Midwife ነርሷ ህይወት ታሪክ ነው።

ህይወት በሲዳማ ክልል አለታ ወንዶ ወረዳ በአንድ ጤና ጣቢያ የምታገለግል ታታሪ አዋላጅ ነርስ ነበረች። አንድ ምሽት በከባድ ምጥ የተያዘች እናት ወደ ጤና ጣቢያው መጣች። ህይወት እናቷን በሰላም ለማዋለድ የቻለችውን ሁሉ አደረገች፤ ነገር ግን ሁኔታው ከአቅሟ በላይ ሆኖ በመገኘቱ ወደ አቅራቢያው ሆስፒታል እንድትላክ ሪፈራል ጻፈች።

ነገር ግን በሪፈራል ወረቀት ብቻ አልቆመችም። ታካሚዋን ብቻዋን መላክ አልፈለገችም፤ በአምቡላንሱ አብራት ተሳፈረች፣ እስከ ሆስፒታሉ ድረስ ከጎኗ ሆና ተጓዘች።

ሆስፒታሉ እንደደረሱ እናቷ በሰላም ተገላገለች፤ አንድ ሕይወት ተረፈ፣ አንድ ቤተሰብም ደስታን አገኘ።

ነገር ግን ይህ ደስታ ለህይወት በከፍተኛ ዋጋ ተከፈለ። እርሷም ነፍሰ ጡር ነበረች። በአምቡላንሱ ጉዞ ውስጥ በተፈጠረው መናጥ ፅንሷ በከባድ ሁኔታ ተጎዳ፤ በኋላም እርሷ ራሷ ሕይወቷን አጣች።

ይህ ታሪክ ሙያን ከሥራ በላይ እንደ ጥሪ የተቀበለች ሴት ታሪክ ነው። ሌላ እናት እንድትኖር፣ ሌላ ሕፃን በሰላም ወደ ዓለም እንዲመጣ የራሷን ሕይወት በመስዋዕትነት የከፈለች ጀግና ነበረች።

ህይወት በስሟ ብቻ ሳይሆን በተግባሯም "ህይወት" ነበረች። ታሪኳ የሙያ ታማኝነት፣ የሰብአዊነት እና የፍቅር ዘላለማዊ ምስክር ሆኖ ይኖራል።

ለሌላዋ ሕይወት የተከፈለ የነፍስ ዋጋ ፈጽሞ አይረሳም።

Via Muluken Birhanu

ጉርሻ page

Advanced Nursing የስራ መደብ በሆስፒታሎች እና በሌሎች የጤና ተቋማት ዘንድ !
21/07/2026

Advanced Nursing የስራ መደብ በሆስፒታሎች እና በሌሎች የጤና ተቋማት ዘንድ !



ነፍስ ይማር !https://www.facebook.com/share/1EEzPDLqza/?mibextid=wwXIfr
11/07/2026

ነፍስ ይማር !

https://www.facebook.com/share/1EEzPDLqza/?mibextid=wwXIfr

የህክምና ባለሙያው ተክሌ ተስፋዬ ከዚህ አለም ድካም አርፏል

የአቶ ተክሌ አጭር የሕይወት ታሪክ

አቶ ተክሌ ተስፋዬ ኩማሎ ከአባታቸው አቶ ተስፋዬ ኩማሎ እና ከእናታቸው ወ/ሮ አዲሴ ጁቤ በ1985 ዓ.ም በወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋጫና ቀበሌ ተወለደ። አቶ ተክሌ ተስፋዬ ዕድሜው ለትምህርት እንዴ ደረሴ ትምህርቱን የመጀመሪያ ደረጃ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ባዴ ሐሙስ ተከታትለዋል።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ከ9ኛ እስከ 10ኛ ክፍል በበሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሁም ከ11ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ደግሞ በወላይታ ሶዶ ቀለምና መሰናዶ ትምህርት ቤት ሲማሩም፣ የላቀ ውጤትና ምሳሌ የሚሆን ሥነ ምግባር በማሳየት አጠናቁዋል።

አቶ ተክሌ ተስፋዬ በትምህርት ቆይታቸው ሁሉ በትምህርት ውጤታቸውም ሆነ በሥነ ምግባራቸው በትምህርት ቤት ሆነ በክላስተር ተማሪዎች መካከል ቀዳሚ በመሆን አጠናቀቁ። የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናም ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በመቀላቀል የመጀመሪያ ዲግሪያውን በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በአዋላጅ ነርሲንግ ትምህርት ክፍል ተምረው በከፍተኛ ውጤት ተመርቀዋል።

ከምረቃቸው በኋላ በ2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ በጤና ዘርፍ በመቀጠር ለሶስት ዓመታት በኦሴ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በባለሙያነት እና በኃላፊነት ፣ በታማኝነትና በትጋት ሕዝባቸውን አገልግለዋል።

በ2016 ዓ.ም ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ወደ ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ተዛውረው፣ እስከ 2017 ዓ.ም. ድረስ በሀናዜ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በጤና ባለሙያነትና በጤና ጣቢያ ኃላፊነት ሕዝብን በቅንነት አገልግለዋል።

ከሕዳር 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሕይወታቸው የመጨረሻ ቀን ድረስ በሶርቶ ማዘጋጃ ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ለማህበረሰባቸው በታማኝነት ሲያገለግሉ ኖረዋል።

አቶ ተክሌ ተስፋዬ ባለ ትዳር እና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ። በሕይወታቸው ሁሉ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ሰውን የሚያከብሩ፣ ትጉ፣ቅን፣ጨዋ፣ታጋሽና ታማኝ ሰው ነበሩ።

አቶ ተክሌ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ሥራ ቦታቸው በመሄድ ላይ ሳሉ በደረሰባቸው አስከፊ ድንገተኛ አደጋ ክፉኛ ተጎድተው በወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቆይተው፣ በሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም የሚወዷቸውን ቤተሰቦቻቸውን፣ ወዳጆቻቸውንና መላውን ሕዝብ በእጅጉ በሚያሳዝን ሁኔታ በሞት ተለዩ።

ይህ ድንገተኛ ህልፈት ለቤተሰባቸው ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ለማህበረሰቡ የማይረሳ ሐዘን አስቀርቷል። ሰው ለማገልገል የኖረ ልባቸው ቢቆምም ፣ መልካም ሥራቸው ፣ ቅንነታቸውና የፍቅር አሻራቸው በሰዎች ልብ ለዘላለም ይኖራል።

"ሰው ይሞታል ፤ መልካም ሥራው ግን አይሞትም። ወንድማችን ተክሌ ተስፋዬ በአካል ከእኛ ቢለይም ፣ በትዝታው ፣ በመልካም ሥራው እና በተወዳጅነቱ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር ሲታወስ ይኖራል።

ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ዘመዶቹ ለሥራ ባልደረቦቹ እና ለጓደኞቹ እግዚአብሔር ፍፁም መጽናናትን ይስጥ።

- ፍሬው ተፈሪ

Jimma University has secured accreditation for its undergraduate programs among them, the BSc in Nursing. The Ethiopian ...
09/07/2026

Jimma University has secured accreditation for its undergraduate programs among them, the BSc in Nursing.

The Ethiopian Nurses Association proudly stands behind this achievement, having served as a cornerstone stakeholder during the accreditation process.

https://www.facebook.com/share/p/18yQEDHaN7/?mibextid=wwXIfr

Address

Megenagna , Amare Abrham Building, 11th Floor
Addis Ababa
467

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30
Saturday 08:30 - 00:30

Telephone

+251114655436

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Nurses Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Nurses Association:

Shortcuts

Share