13/07/2026
💔 "ልጄ ሞቶብኝ... ምድር ጨልማብኝ። የማደርገው ጠፍቶብኝ ነበር። በዚያ ከባድ ሰዓት ነፃ የጀናዛ ትጥበት አገልግሎታችሁን ስላገኘሁ፣ በእውነት ወንድሞች እንዳሉኝ ተሰምቶኛል። አላህ ከፍ ያለ ምንዳ ይስጣችሁ።"
— የአፋቁል ዓለም ነፃ የጀናዛ ትጥበት ተጠቃሚ
🤲 በሀዘን ሰዓት ከቤተሰቦች ጎን መቆም ከታላላቅ መልካም ሥራዎች አንዱ ነው። የእርስዎ ድጋፍ ለሌላ ቤተሰብ በጭንቅ ጊዜ ተስፋ፣ እፎይታ እና ወንድማዊ እገዛ ይሆናል።
📲 የአፋቁል ዓለም ነፃ የጀናዛ ትጥበትና ተያያዥ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በቴሌብር በመደገፍ የዚህ ሰናይ ሥራ ተባባሪ ይሁኑ።
"መልካም ሥራ ላይ የሚያግዝ እንደ ፈጻሚው ምንዳ ያገኛል።"