13/03/2025
የቡና ጣዕም፣ የጥራት ምርመራ እና የቡና ገበያ ግብይት
3ተኛ ዙር ምዝገባ ተጀምሯል!!
የኢትዮጵያ ቡና ማህበር የአገራችንን ቡና ጥራት በዓለም ላይ በማስዋወቅ እና ተወዳዳሪነቱን በመሪነት እንዲይዝ እያደረገ ያለውን ስራውን በማጠናከር የአባሎቹንና በቡናው ዘርፍ ላይ ፍላጐት ያላቸውን ዜጐችም ስለ ቡና ጥራት እና የዓለም አቀፍ ቡና ገበያ ግብይት መገንዘብ የሚያስችል ስልጠና እየሰጠ ያለ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚህ መሰረት የቡና ጣዕም፣ የጥራት ምርመራ እና የቡና ገበያ ግብይት (Coffee Cupping, Raw Analysis and Coffee Marketing) ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን በደስታ እንገልጻለን፡፡
ለስልጠናው የሚያስፈልጉ መሟላት ያለባቸው፡-
- ስልጠናው የሚውስደው ጊዜ፡- 45 ቀናት
- የስልጠናው ቀን ከሰኞ እስከ አርብ በቀን ለ4፡ዐዐ ሰዓታት
- ስልጠናው የሚጀመርበት ቀን፡- መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ. ም.
- የስልጠናው ክፍያ በአንድ ሰልጣኝ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/
- ስልጠናውን ለመመዝገብ የኢትዮጵያ ቡና ማህበር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂ/ቁጥር 1000001847175 ገቢ አድርጋችሁ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ እና የትምህርት ዝግጅት ሰርተፊኬት ማቅረብ ይጠበቅባችኋል
- የስልጠናው ቦታ ጦር ኃይሎች በተለምዶ 3 ቁጥር አውቶቡስ ማዞሪያ አካባቢ
- ለበለጠ መረጃ፡- አቶ ኃይሉ ረጋሳ
የማርኬቲንግ መምሪያ ኃላፊ 0911 753582
Send a message to learn more