Al-Hikma Islamic Organization አል-ሒክማ ኢስላማዊ ድርጅት

Al-Hikma Islamic Organization  አል-ሒክማ ኢስላማዊ ድርጅት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Al-Hikma Islamic Organization አል-ሒክማ ኢስላማዊ ድርጅት, Nonprofit Organization, Addis Ababa.

27/06/2025

🌙ቀኑ ጁሙአ ነው🌙
ከጁሙአ ቀን ሱናዎች መካከል
√ ገላን መታጠብ
√ ንፁህ ልብስ መልበስ
√ ሽቶ መቀባት
√ ሱረቱል ከህፍን መቅራት
√ ለ ጁሙአ ሶላት ቀደም ብሎ ወደ መስጅድ መሄድ ።

ተቀባይነት ያለው ጁሙአ ያድርግል።
አሚን

24/06/2025

ፓዌ ከተማ

የፓዌ ወረዳ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም ቤት ሙስሊሙን ማህበረሰብ በሚጠቅሙ ጉዳዮች እያደረጉት ያለው እንቅስቀሴ እጅግ የሚያኮራና የሚደንቅ ሁኖ እናገኘዋለን።

በአርቆ አሳቢነት፣ ለመጭው ትወልድ መቃናት፣ የእናቶች የሸሪአ እውቀት መማርን ታሳቢ በማድረግ አሁን ላይ ዘመናትን ተሻግሮ ሊሄድ የሚችልን ማዕከል እውን እንዲሆን በተግባርም፣ በአቃፊነት በአባትነትም ሁነው እውን ሁኖ ለማየት ከአሏህ ጋር ባለ ሙሉ ተስፋ ላይ ሁነው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

ይህ እውን እንዲሆን ከግለሰብ እስከ ተቋማት ያሉ
ሙስሊም ማህበረሰብ በወረዳ መጅሊሶች አማካኝነት በተከፈተው የሂሳብ አካዉንት ድገፋችሁን እንድታደርጉ በአሏህ ስም እንጠይቃለን።

የመጭው መፃኢ ሙስሊም ትውልድ መቃናት የአሁኑ ትውልድ የአንበሳው ድርሻ ይወስዳል።

√ 1000689210377
አል– ሒክማ ኢስላማዊ ማዕከል (ፓዌ)

✅እንዲሁም አል–ኢስላማዊ ድርጅት በስሩ ከ50 በላይ ኡለሞች በመርዳት ላይ ይገኛል በመሆኑም የእርስዎ ድጋፍ ዋናው የድርጅቱ ገቢ ምንጭ ነውና ታች ባሉት አካውንት የተቻላችሁን ድጋፍ በማድርግ የበኩሎውን ድርሻ ይወጡ እንላለን።

√ 1000571349748 ንግድ ባንክ
√ Al 75 ( 19951992) አቢሲኒያ
√ 0029741720101 ዘምዘም
√ 10005255520001 ሂጅራ

ድጋፍ ያደረጋችሁበት ደረሰኝ በውስጥ መስመር እንድትልኩልን ለማስታዎስ እንወዳለን።

🌙አል–ሒክማ ኢስላማዊ ድርጅት🌙

21/06/2025

√ 🌙ነገን🌙

የነገውን ታሪካዊ ፕሮግራም ከጠንካራ ሙስሊም ማህበረሰባችን ጋር ከጠዋቱ 3:00 በአቅሷ መስጅድ በመገኘት አል–ሒክማ ኢስላማዊ ማዕከል(ፓዌ) የወደፊቱን ኢስላማዊ ትውልድ የሚቀረፅበትን ስፍራ በጋራ ጅማሮው እናብስር።

20/06/2025

ዛሬ ጁሙአ ነው
√ የጁሙአ ሱናዎችን በመትግበር የጁሙአን ሶላት በጀመአ እንሰገድ።

ሳምንት ከሳምንት ወንጀላቸው ከሚማርላቸው ሰዎች ያድረገን። አሚን

19/06/2025
17/06/2025

🌙 ታላቅ የብስራት ዜና🌙
ለመላው ሙስሊም ማህበረሰባችን በሙሉ አል–ሒክማ ኢስላማዊ ድርጅት ታላቅ ብስራት ይዞ የፊታችን እሁድ ሰኔ 15 / 2017 በአቅሷ መስጅድ
ሸይኽ ሰኢድ አህመድ ሙስጦፍ ፣ ሸይኽ አብዱረህማን አደም እንዲሁም ሸይኽ ሙሃመድ አወል በተገኙበት አል– ሒክማ ኢስላማዊ ማዕከል(ፓዌ) ለወራት ኢንጅነሮችና አርክቴክቸሮች የተጠበቡት ውብ ሁለተናዊ ኢስላማዊ አገልግሎት የሚሰጠው ማዕከል በታላቅ ድምቀት ለአባላቶች ይፋዊ የዲዛይን እይታ ይደረጋል።

ሁላችንም በእዚህ ታሪካዊ ፕሮግራም በመገኘት
የፕሮግራሙ ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

አሏሁ አክበር
♻️አል–ሒክማ ኢስላማዊ ድርጅት♻️

15/06/2025

አል–ሒክማ
ኢስላማዊ ማዕከል ( ፓዌ)

አል–ሒክማ ኢስላማዊ ድርጅት ኡለሞችንና ዱአቶችን ከማገዝ በተጨማሪ
በሚገኙባቸው አካባቢዎች ኢስላማዊ ማዕከላትን በመመስረት ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ሁለተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰራ ነው ።
♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️
እንደ አል–ሒክማ ይህን የቦታ ሁኔታዎች ለማመቻቸት እገዛውን በጀመርንባቸው አካባቢዎች ቦታ በማፈላለግ ላይ የቆየን ሲሆን በመጨረሻም በመተከል ዞን ፓዌ ወረዳ በፓዊ ከተማ እንብርት ቦታ 10,000 ካሬ ቦታ ማግኘት ተችሏል።
🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙

ይህን ቦታ ቀደም ብለን ሰፍራው ድረስ በመገኘት ከፓዌ ወረዳ መጅሊሶች ጋር ውይይት ምክክር እንደዚሁም የመስክ ጉበኝት ያካሄድ ሲሆን ለአዊ ለጎጃምና ጎንደር ዞኖችማዕከላዊ የሆነ ቦታ ከመሆኑ ጋር ሰላሟ እንዲሁ አስተማማኝ በሚባል ደረጃ መገኘቱ ጥንታዊ ባለ ታሪክ ከተማ የሚያስብሏት ብዙ መስህቦች መኗሯም ተመራጭ እንዲሆን አድርጎታል።
♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️
በእዚህም መሰረት አል – ሒክማ ኢስላማዊ ድርጅት በውስጡ አል– ሒክማ ኢስላማዊ ማዕከል በሚል ስያሜውን በማድረግ ከወረዳ መጅሊሱ ጋር በጋራ ለማልማት ስራውን ህዝቡን ታች ድረስ ልኡካንን በመላክ በማስተባበር እንዲሁም ተጨባጭ ስራዎችን ሀ ብሎ በመጀመር ማበሰራችንን በተከታታይ ፓስታችን ማሳወቃችን የሚታወቅ ነወ።
♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️

በአል–ሒክማ ኢስላማዊ ድርጅት የስራ አቅጣጫ መሰረት የ ፓዌ ወረዳ መጅሊሶች አሏህ ስራቸውን ይውደድላቸውና ቀን ለሊት ሳይሉ በአጭር ጊዚያት በዙሪያቸው የሚገኙ ከ20 በላይ ቀበሌዎችን በማስተባበር የቦታውን ይዞታ በልዩ ሁኔታ በማጠር ቦታዉን በልዩ ሁኔታ የተጠበቀ እንዲሆን ማድርግ ተችሏል።
♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️
ከእዘህ በመቀጠል ቦታውን ኢስላማዊ ማዕከል እንዲሰራበት ከወረዳ መጅሊሱ ይሁንታ ከተቀበልንበት እለት ጀምሮ በአርክቴክቸር ዲዛይን (archtecture design) ኢንጅነሮች አማካኝነት ሙሉ የግንባታ ፕላኑን እያሰራን ሲሆን ሳምንት ባልፈጀ ጊዜ ተጠናቆ እንደምንረከብ ልንገልፅላችሁ እንወዳለን።
♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️

ከቀጣይ ሰኔ 15 ማዕከሉን የምናስተዋውቅበት የመጀመሪያ መርሃ ግብር የአል–ሒክማ አባላትና የአካባቢው ተወላጆች እንዲሁም ሸህ ሰኢድን ጨምሮ አንጋፋ ኡለሞች በተገኙበት በደማቅ ለማካሄድ ዝግጅት ጨርሰን ሰኔ 15 በመጠበቅ ላይ እንገኛለን።
♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️
የመምጣት ችሎታ ያገኝን በሙሉ ለሰኔ 15 / 2017 አ,ል በአቀሷ አፍንጮበር መስጅድ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

አካባበቢያችንን በኢስላም ብርሃን በማስዋብ በሀገራችን ፈርቀዳች የሆነ ማዕከልን በመገንባት ህዝበ ሙስሊሙን
ተጠቃሚ ሊያደርጉ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ በአንድ ሁነን እውን ማድረግ ይገባናል።


አል– ሒክማ ኢስላማዊ ድርጅት

7 / 10/2017
መግለጫ

✅ ቢልአም ኢብኑ ባዑራ ♻️የአለክላኪ ውሻ አምሳያ የተሰጠዉ የመጥፎው ኡለሞች ምሳሌ  የሆነው የከነአኑ አዋቂ የነበረ ሰው በሱረቱል አዕራፍ 176 እንዲህ ተገልፆ ይገኛል።وَلَوْ شِئْنَ...
12/06/2025

✅ ቢልአም ኢብኑ ባዑራ

♻️የአለክላኪ ውሻ አምሳያ የተሰጠዉ የመጥፎው ኡለሞች ምሳሌ የሆነው የከነአኑ አዋቂ የነበረ ሰው በሱረቱል አዕራፍ 176 እንዲህ ተገልፆ ይገኛል።

وَلَوْ شِئْنَا لَرَفَعْنَٰهُ بِهَا وَلَٰكِنَّهُۥٓ أَخْلَدَ إِلَى ٱلْأَرْضِ وَٱتَّبَعَ هَوَىٰهُ فَمَثَلُهُۥ كَمَثَلِ ٱلْكَلْبِ إِن تَحْمِلْ عَلَيْهِ يَلْهَثْ أَوْ تَتْرُكْهُ يَلْهَث ذَّٰلِكَ مَثَلُ ٱلْقَوْمِ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا فَٱقْصُصِ ٱلْقَصَصَ لَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ

በሻንም ኖሮ በእርሷ ከፍ ባደረግነው ነበር፡፡ እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ፡፡ ፍላጎቱንም ተከተለ፡፡ ብጤውም ብታባርረው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ ወይም ብትተወው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ እንደ ኾነ ውሻ ነው፡፡ ይህ የእነዚያ በአንቀጾቻችን ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ነው፡፡ ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው፡፡
ይህ አዋቂ የነበረ ሰው ሙሳ አለይሂ ሰላም ከመላካቸው በፊት የነበረ አቢድ እና ኡለማ ነበር
በእዚሁም ምክንያት አሏህን በሚለምን ጊዜ ዱአው ሁሉ መቅቡል ( ተቀባይንት) ይኖረው ነበር።
በሚኖርበት አካባቢ ማንኛውም ሰው ችግርና
መከራ ሲገጥማቸው ወደ እዚህ ሰው ዘንድ በመሄድ ዱዐ ያሰደርጉ ነበር የሚፈልጉትም ነገር ተሰክቶላቸው ይመለሳሉ።
በአካባቢው ላይ ታዋቂ ኡለማና አሏህ ፈሬ በመሆን እውቅናን አተረፈ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሙሳ አለይሂሰላም ወደዚህ ምድር ነብይ ሁነው ወደ ፊርአዉን ( በኒ እስራኢል ህዝቦች)ተላኩ ፊርአዉን ተወግዶ እሳቸው የአካባቢ መሪ ሁነው በሚያስተዳድሩበት ጊዜ
ከአሏህ በኩል በሆነ ትዕዛዝ ዲነል ኢስላምን ወደ አጎራባች ከተሞች እንዲያስፋፉ ትዕዛዝ ተሰጣቸው።
በእዚህ ጊዜ ነበር ሙሳ ያ አዋቂ ወደ ነበረት ከነአን
ኢስላምን እንዲቀበሉ ካልሆነ ግብር እንዲከፍሉ አሻፈረኝ ካሉ ግን እንደሚዘምቱባቸው መልዕክት
ይልኩላቸዋል ።

መልዕክቱ የደረሳቸው ወገኖች ተሰባስበዉ ወደ ቢልዐም አብኑ ባዑር ቤት ሄዱ ሙሳ እና ወታደሮቹን
አሏህ እንዲያጠፋላቸው ዱአ እንዲያደርጉላቸው
ይለምናቸዋል።
በጊዜው ዱአ ለማድረግ ከእነሱ ገለል አሉ ዱአም አደረጉ አሏህም ሙሳ ነብይ እንደሆነ ያሳውቀዋል።
ወደ ህዝቦቹ ተመልሰው ጌታ ከልክሎኛል ብሎ መለሰላቸው በመበሳጨት ወደ የቤታቸው ተመለሱ
ተመካክረው ገንዘብ በማሰባሰብ ድጋሚ ወደ አዋቂ ሰው ቤት ይሄዳሉ።
አዋቂውም ሰውየ ገንዘቡን በተመለከተ ጊዜ ልቡ ወደ ዱንያ አዘነበለ የጌታውን ትዕዛዝ ወደ ጎን በማለት አህያውን ይዞ ለድጋሚ ዱአ አህያውን ይዞ
ወደ ከፍታ ተራራ ይወጣል።
ከተራራው ወደ ታች ሲመለከት ሙሳንና ወታደሮቹን
ይመለከታል። ተራራዉም ላይ ወገኖቹ በዙሪያው እንዲሰበሰቡ አደረገ እሱ ዱአ ሲያደርግ አሚን እንዲሉ ይነግራቸዋል። ዱአ ማድረግ ጀመረ ማለት የፈለገው ሙሳና ህዝቦችን አጥፋ ከነአኖችን እርዳታ የሚል ነበር ምላሱ ግን እንዲህ አለ ጌታ ሆይ ሙሳና ህዝቦቹን እርዳ ከንአንዮችን አጥፋ ይላል በእዚህ ጊዜ እንዴ ምንሁነህ እረገምከን አሉት የምላስ ወለምታ ነው አለና ድጋሚ አሁንም ሙሳናህዝቦችን እርዳ ከንአንዮች አጥፋ አለ።
በመጨራሻም ምላሱ እንደ አበደ ውሻ ተግተልትሎ ወረደ አናንተ ዱንያየንም አኺራየን አበላሻችሁብኝ ኢማኔም ጠፋ ከእዚህ በሆላ ተራና የተዋረድኩ ሰው ሁኛለው በሎ እያለቀሰ ወደ መሬት ወደቀ።
ይህ ታሪክ ብዙ ኡለሞች እውቀታቸውን በዱንያ ቀይረው ሃቅን ከመናገር ወደ ኃላ ያሉበት ጊዜ ላይ ደርሰናል በመሆኑም ዱአቸውና ተቅዋቸው እንደ አበደ ውሻ ምላስ ወርዶ ብጣሽ ለመለቅም አቀርቀረው አሏህ ከፍ ያደረገባቸውን የዲን እውቀት
አስተባብለው እየኖሩ ይገኛ።
ከእነዚህና መሰል መጥፎ ኡለሞች አሏህ ይጠብቀን።
አሚን
https://t.me/anwarmereja

12/06/2025

بسم الله الرحمن الرحيم

♻️የተዘነጋው የሸሪአ እውቀትና ደረጃው

አሏህ በተለያዩ የቁርአን አንቀፆች ለሸሪአ እውቀት ከፍ ያለ ደረጃ ሰጦ እናገኘዋለን።
ነቢያችንም صلى الله عليه وسلم በሀዲሳቸው ሰፊ በሆነ መልኩ ስለ አሊሞችና ሙተአሊሞች( ደረሶች) ልዩ ቦታ ሰጥተው ገስፀው አስተምረዋል።

ይህንን የተረዶ ትውልዶች ለልጆቻቸውን የሸሪአ እውቀት ይቀስሙ ዘንድ ትልቅ ፍላጎት ከመኖራቸው የተነሳ ገና በለጋነት እድሜ ልጆቻቸውን ወደ ኢልም ማዕከላት ይልኩ ነበር።

በተለይ በሀገራችን ኢትዮጲያ አባትና እናት ልጅ ከመውለዳቸው በፊት አሏህ ከሚሰጣቸው ልጆች መካከል ግማሹን ደረሳና አሊም እንዲሆንላቸው ይፈልጉ እንደነበርና ፍላጎታቸውንም ለማሟላት ወደ ዛውያዎችና የኢልም ሰፈሮች ይልኩ እንደነበር የሚታወቅ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ያ በሸሪአ እውቀት ትምህርት ጊዚያት ወስዶ ተምሮ የተመለሰው ደረሳ / አሊም ለቀሪ ወንድምና እህቶች ኢስላማዊ ማንነትን እንዲሰርፅባቸው በማድረግ ቤተሰቡን ብሎም አካባቢውን በኢስላም ብርሃን እንዲሞላ ያደርጋል።

በእዚህም ምክንያት በዙሪያው ያሉ ወጣት ትውልድ በመጥፎ ምግባራት እንዳይሰማሩ በማድረግ አይነተኛ ሚናው ይጫወታል።

ለእዚህም ነው አሏህ በቁርአኑ እንዲህ ብሎ የገለፃቸው

{يرفع الله الذين آمنوا منكم والذين أوتوا العلم درجات}
አሏህ ከእናንተ ውስጥ እነዚያ ያመኑትንና እንዚያንም እውቀት የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋቸዋል።

{شهد الله أنه لا إله إلا هو والملائكة وأولوا العلم قائما بالقسط لا إله إلا هو العزيز الحكيم}
አሏህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ይመሰክራል። መላኢካዎችና የእውቀት ባለቤቶች ፍትህን ይሰጣሉ። ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም። አሸናፊ ጥበበኛም ነው።

ይማም ቁርጡቢ እንዲህ ብለዋል:
ይህ አንቀፅ ለአሊሞች ክብር ደረጃ የሰጠበት ማስረጃ ነው ከአሊሞች የበለጠ ክብር ያለው ሰው ቢኖር የነበር ከስሙና ከመላኢኮቹ ስም አብሮ ይጠቅሳቸው ነበረ።

አሁንም ያለው ኡማ ለእዚህ ጉዳይ ሰፊ ትኩረት ማድረግ ይገባዋል ።
ማድረግ ካልተቻለ ግን በመጥፎ ትውልዶች መጥፎ ባህሪ ሙስሊም ትውልዶች ለእነዚህ መጥፎ እሳቢዎች ተጠማቂዎች ይሆናሉ።

በብዙ ሙስሊም ቤቶች ውስጥ የሚገኝ ትልቁ ችግር የሸሪአ እውቀት መጥፋትና ልጆች በሱሳሱስ መጠመዳቸው ነው።

አሁንም ቢሆን የቀሩትን የሸሪአ እውቀት ማዕከሎቻችንና ኡለሞች ከጎን ሁነን በመገዝ አዳዲስ ማዕከላትን በመክፈት ሰፊ ስራዎችን መስራት ይገባናል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Al-Hikma Islamic Organization አል-ሒክማ ኢስላማዊ ድርጅት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share