መቄዶንያ-mekedonia

መቄዶንያ-mekedonia ሁሌም ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ በመቄዶንያ youtube live fundraising ላይ ይሳተፉ! ZELL OR CASHAPP 240,938,2992

የሁሉም ባንክ አካውት ቁጥራችን - 7979
call 8131/0979797979/0989898989
(7)

05/08/2026
05/08/2026
05/08/2026
05/08/2026
05/08/2026
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት  ለመቄዶንያ ድጋፍ አደረገ!!!​የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በየዓመቱ ሐምሌ 29 ቀን የሚያከብረውን የበጎ አድራጎት ቀን በማስመልከት ላለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት...
05/08/2026

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለመቄዶንያ ድጋፍ አደረገ!!!

​የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በየዓመቱ ሐምሌ 29 ቀን የሚያከብረውን የበጎ አድራጎት ቀን በማስመልከት ላለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት መቄዶንያ በመገኘት ለሦስተኛ ጊዜ በደመቀ ሁኔታ አከበረ።

​የመከላከያ ሚኒስቴር የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ሁሉሀገርሽ ድርስ በስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ ሠራዊቱ የሀገርን ህልውና በጽናት ከመጠበቅ ባሻገር፣ በማዕከሉ ተገኝቶ ፍቅሩን እና ሰብዓዊነቱን በማሳየት ለወገኑ ቀዳሚ ደራሽነቱን አስመስክሯል።

ዳይሬክተሯ አክለውም ሠራዊቱ ከማዕከሉ ጋር ጥብቅ ቤተሰባዊ ቁርኝት እንዳለው ገልጸው፣ ሀገርን በክብር ያገለገሉ አረጋውያንን በመደገፋቸው ኩራት እንደሚሰማቸው ገልፀው ያመጧቸውን ግምታቸው ከ600,000 ሺህ ብር በላይ የሆኑ የተለያዩ የምግብ ፍጆታዎችን፣ ዊልቸር፣ ዋከር፣ አልባሳት፣ የፅዳት ቁሳቁሶች አስረክበው ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ለአረጋውያንም ልዩ የምሳ ግብዥ በማድረግ እለቱ ሐምሌ 29ን አረጋውያኑ ልዩ ቀን አድርገው እንዲያስቡት አረጋግጠዋል

​የመቄዶንያ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ የክብር ዶክተር ብንያም በለጠ በበኩላቸው፤ ሠራዊቱ ሕይወቱን አሳልፎ ከመስጠት ባለፈ በማዕከሉ የሚገኙ ወገኖችን በፍቅር እና በርህራሄ በመጎብኘቱ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል። በማዕከሉ የሚገኙ የሀገር ባለውለታዎችም ለሠራዊቱ ያላቸውን ፍቅር በምርቃት ገልጸዋል።

በመጨረሻም የቀሩትን የግንባታ ስራዎች በፍጥነት ለማጠናቀቅ ኅብረተሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

05/08/2026
05/08/2026

Address

Hayat
Addis Ababa
4315

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መቄዶንያ-mekedonia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to መቄዶንያ-mekedonia:

Shortcuts

Share