Peace and justice. /PJW/

Peace and justice. /PJW/ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Peace and justice. /PJW/, Nonprofit Organization, Addis Ababa.

በዚህ ገጽ---
ለሀገራዊ ዘላቂ ሰላም ግንባታ፣ ለፍትህና የሕግ የበላይነትን መረጋገጥ፣ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት መጎልበት ለጋራ አላማ በጋራ እንተጋለን፡፡
ሰላምና ፍትህ ለህዝቦች ነፃነት!!
--------------------

01/06/2026

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-

• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

Uummanni Itoophiyaa dinqisiisaafi ajaa'ibsiisaadha! Uumaa malee uummata keenya guutummaan beekuufi gamaaggamuu kan danda'u eenyu? Aadaa gabbataa, uummata biyya jaallatuufi fedhiisaa waloo eeguu danda'u ta'uusaa filannoo baranaatiin irradeebiidhaan addunyaatti agarsiiseera. Guyyaa seena-qabeessa har'aatiin:
- Qorriifi dukkanni halkani kan isaani hin sodaachifne,
- Aduun saafaafi bokkaan tasaa kan isaan jilbeenfachiifne,
- Cidhi, gaddi, da'umsiifi taateewwan hawaasummaa kanbiroon kan isaan dhorkine,
- Hiriironni dhedheeroon kan isaan hin nuffisiifne,
- Qaama miidhamtummaan sagalee kennuuf kan isaan hin daangessine,
- Dhukkubniifi dullumni abdii biyyaa arguuf kan isaan hin dhowwine,
- Daa'imasaanii kichuu bor biyya dhaalu baatanii filuun kan isaan hin dadhabsiifne
- Hundumaa caalaa lammiilee iyyiifi sodaachiifni diinaa isaan hin dhaabsifne,
Ciminni bu'aa bayii hedduu keessatti agarsiiftan gatii diimokraasiifi jiraachuu biyyatiif kanfalame waan ta'eef galata guddaatu malaafi.

Uummata kana tajaajiluun carroomuu waan ta'eef filatamtoonni warra isin kabajan kabajjanii uummata sirna diimookraasiif gatii baase kana qulqullummadhaan tajaajiluuf isin haa gahu.

The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.

On this historic day:

* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;

The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.

It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን  እየመረጡ ነው፤**********🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹****7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የደምፅ አሰጣጥ ስነ- ሥርዓት ከማለደው 12:00 ጀምሮ  በሀገራችን በሁሉም ክልሎችና ከተማ አ...
01/06/2026

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን እየመረጡ ነው፤
**********🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹****
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የደምፅ አሰጣጥ ስነ- ሥርዓት ከማለደው 12:00 ጀምሮ በሀገራችን በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተጀመረ ሲሆን ከፍተኛ የሀገር መሪዎች በየምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምፅ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያውያን በማለዳ ለምርጫ ዝግጁ ሆነዋል;************🇪🇹🇪🇹🇪🇹*******,ዛሬ ግንቦት 24 ቀን በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ዜጎች የወደፊት እጣ ፈንታቸውን ለመወሰን ይህንን ...
01/06/2026

ኢትዮጵያውያን በማለዳ ለምርጫ ዝግጁ ሆነዋል;
************🇪🇹🇪🇹🇪🇹*******,
ዛሬ ግንቦት 24 ቀን በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ዜጎች የወደፊት እጣ ፈንታቸውን ለመወሰን ይህንን ታሪካዊ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድና የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታቸውን ለማፅናት በነቂስ ወጥተው ይገኛሉ።

31/05/2026

Let Ethiopians Decide: Electoral Legitimacy Must Be Judged by Voters, Not External Actors

+++++++++++++++++
: "Elections are not gifts bestowed by external actors; they are expressions of popular sovereignty."

As over 54 million Ethiopians prepare to head to the polls for the 7th National Election on June 1, 2026, a familiar wave of external criticism has begun. But who truly decides the legitimacy of an election? Is it foreign media and international policy institutes, or the sovereign will of the voters casting the ballots?

In his latest piece for Gazette Plus, Ermias Yemanebirhan (PhD) argues that while constructive, evidence-based criticism is essential for growth, predetermined narratives cannot substitute the voices of millions of Ethiopian citizens.

No election is perfect, but the ultimate judgment belongs to the people. Let Ethiopians decide. 🇪🇹

Check the comment section to access the full story

ለኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊያን በክብር ቁመን፤ በድል እንመርጣለን !********************🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹*** 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ጥቅም እና የሉዓላዊነት ጉዳይ ብቻ...
31/05/2026

ለኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊያን በክብር ቁመን፤ በድል እንመርጣለን !
********************🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹***
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ጥቅም እና የሉዓላዊነት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ይህ ታሪካዊ ዕለት የዜግነት ግዴታችንን በክብር የምንወጣበት እና የነገዋን ኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ የምንወስንበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው።

አባቶቻችን "ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" ብለው በተረትና ምሳሌ እንዳስተማሩን፣ የ54 ሚሊዮን ዜጎች ድምፅ በአንድነት ሲዋሃድ የድህነትን፣ የመከፋፈልንና የኋላቀርነትን ጠንካራ ሰንሰለት በጥሶ መጣል የሚችል የማይበገር አገራዊ አቅም ይፈጥራል።

ዛሬ የምንመርጠው ተወዳዳሪን ወይም የፖለቲካ ፓርቲን ብቻ ሳይሆን፣ ለልጆቻችን በኩራት የምናስረክባትን ጽኑ እና የበለፀገች ሀገር መሠረት ጭምር መሆኑን መዘንጋት የለብንም።

ስለዚህ፣ ሁላችንም በማለዳ በነቂስ ወጥተን፣ በሰላምና በጨዋነት ድምፃችንን እንስጥ! ድምፃችን ዴሞክራሲያዊ መብታችን ብቻ ሳይሆን፣ መጻኢዋን ኢትዮጵያ የማነፅ ኃይላችን ነው።

ከምንም በላይ ለሀገራችንን እናስቀድም፤

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን በሰላም ወጥተው በስኬት ይመርጣሉ!!
31/05/2026

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን በሰላም ወጥተው በስኬት ይመርጣሉ!!

 #ኢትዮጵያ ትመርጣለች! የሉዓላዊነት እና የሀገረ-መንግሥት ግንባታ ሕያው ማሳያ፤ **********🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹***"ኢትዮጵያ ትመርጣለች!" የሚለው ይህ ሐረግ  የሉዓላዊነታችን እና የጽኑ ሀ...
30/05/2026

#ኢትዮጵያ ትመርጣለች! የሉዓላዊነት እና የሀገረ-መንግሥት ግንባታ ሕያው ማሳያ፤
**********🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹***
"ኢትዮጵያ ትመርጣለች!" የሚለው ይህ ሐረግ የሉዓላዊነታችን እና የጽኑ ሀገረ-መንግሥት ግንባታችን ሕያው ማሳያ ማህተም ነው።

የምርጫ ካርድን በሳጥን ውስጥ መጨመር፣ ኢትዮጵያ የራሷን እጣ ፈንታ በገዛ ልጆቿ ጥበብ እና እጅ የመወሰን የማያወላውል መብቷን ለዓለም በኩራት የምታውጅበት ታሪካዊ የክብር መድረክ ነው።

ይህ ሂደት የሀገራችንን የነገ አቅጣጫ በራሳችን ውሳኔ የምንቀርጽበት የማይናወጥ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነው። በዚህ ውብ የዴሞክራሲ ጉዞ፣
54 ሚሊዮን 57 ሺህ 861 ድምጻውያን ብሩህ ታሪክ ለመሥራት ተዘጋጅተዋል።

42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እንዲሁም 10 ሺህ 438 እጩዎች (80ዎቹን የግል እጩዎች ጨምሮ) የሕዝብን ድምፅ እና አደራ ለመቀበል በአደባባይ ቀርበዋል።

ይህ የነቃ እና ሰፊ ተሳትፎ ጠንካራ፣ አቃፊ እና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለንን ብሔራዊ ራዕይ በሚገባ ያንጸባርቃል።

የሂደቱን ግልጽነት እና ተዓማኒነት በተግባር ለማረጋገጥ 55 የሀገር ውስጥ ሲቪል ማኅበረሰብ ታዛቢዎች፣ 59 የአፍሪካ ኅብረት እና 26 የኢጋድ አባላት በስፍራው ተገኝተዋል።

68 የሚዲያ ተቋማት (56 ሀገር በቀል እና 12 የውጭ ሚዲያዎች) ይህንን የሉዓላዊነት ድል ለዓለም ይዘግባሉ።

እያንዳንዱ የምንሰጠው ድምፅ፣ የሀገራችንን ሉዓላዊነት የሚያጸና እና የተረጋጋች ኢትዮጵያን መሠረት የሚያጠነክር ቋሚ የሕዝብ ማኅተም ነው።

የምርጫ ወረቀት የማይሰጠውና ጣቱን የድምፅ ሰጪነት ቀለም የማይቀባው ማን ነው?******🇪🇹🇪🇹🇪🇹*******1. ማንኛውም ምርጫ ጣቢያ የተገኘ መራጭ የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርዱን እና የ...
29/05/2026

የምርጫ ወረቀት የማይሰጠውና ጣቱን የድምፅ ሰጪነት ቀለም የማይቀባው ማን ነው?
******🇪🇹🇪🇹🇪🇹*******
1. ማንኛውም ምርጫ ጣቢያ የተገኘ መራጭ የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርዱን እና የማንነት ማረጋገጫ ሰነድ ለተመዘገበበት ምርጫ ጣቢያ የመዝገብ ሹም በማቅረብ ስሙ በመዝገቡ ላይ እንዲታይለት ይጠይቃል።

2. የመዝገብ ሹሙም፡-
ሀ) የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርዱ በምርጫ ጣቢያው የተሰጠ መሆኑን፣

ለ) የመራጩን ማንነት የሚያረጋግጥ መታወቂያ ወይም መለያ ወረቀት አብሮ የቀረበ መሆኑን፣

ሐ) በካርዱ ላይ በተመዘገበው የመዝገብ ገጽ እና ተራ ቁጥር እንዲሁም የመራጭ መለያ ቁጥር መሰረት ሙሉ ስሙ በመዝገቡ ላይ በትክክል የሰፈረ መሆኑና፣

መ) የድምጽ ሰጪነት ቀለም ያልተቀባ መሆኑን ያጣራል፡፡

3. የምርጫ ጣቢያው የመዝገብ ሹሙ መራጭ ድምጽ የሰጠ መሆኑን ለማመልከት ከድምፅ መስጫ ወረቀት አዳዩ ድምፅ መስጫ ወረቀት ከመቀበሉ አስቀድሞ በግራ እጅ አውራጣቱ ጥፍር ግርጌ፣ የግራ አውራጣት ከሌለው በሌላ ማናቸውም የግራ እጅ ጣት፥ ማናቸውም የግራ እጅ ጣት ከሌለው በቀኝ አውራጣት ግርጌ ይህም ከሌለ በማናቸውም ሌሎች የቀኝ እጅ ጣት ጥፍር ግርጌ ላይ የማይለቅ ቀለም ይቀባል፡፡

4. መራጩ የእጅ ጣት የሌለው ከሆነ የመዝገብ ሹሙ አለመምረጡን ካረጋገጠ በኋላ ከመራጩ ጋር በመስማማት በቀላሉ የሚታይ ቦታ ላይ የማይለቅ ቀለም ይቀባና እንዲመርጥ ያደርጋል፡፡

5. መራጩ የማይለቅ ቀለም ከተቀባ በኋላ የምርጫ አስፈጻሚው በመራጭ መዝገብ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀው አምድ ላይ መራጩ እንዲፈርም ያደርጋል።

6. የእጆቹን ጣቶች ለምርጫ አስፈፃሚው ለማሳየት ወይም ቀለም ለመቀባት ፈቃደኛ ያልሆነ መራጭ የድምፅ መስጫ ወረቀት አይሰጠውም፣ መምረጥም አይችልም።

7. ድጋፍ ለሚፈልጉ መራጮች ድጋፍ ለመስጠት አብረው የመጡ ሰዎች ድምፅ የሚሰጡ ካልሆነ በስተቀር
ጣታቸውን ቀለም አይቀቡም።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 1447ኛው የዒድ አል-አድሃ(አረፋ) በዓል አደረሳችሁ።!!
27/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 1447ኛው የዒድ አል-አድሃ(አረፋ) በዓል አደረሳችሁ።!!

ኢትዮጵያን የአፍሪካ ብልጽግና ምሳሌ ለማድረግ ራዕይ አስቀምጠናል።************የኢትዮጵያ ብሔራዊ ራዕይ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው። ከትናንት ወራትን በመቁጠር ዛሬን በትጋትና በጥበብ በመ...
26/05/2026

ኢትዮጵያን የአፍሪካ ብልጽግና ምሳሌ ለማድረግ ራዕይ አስቀምጠናል።
************
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ራዕይ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው። ከትናንት ወራትን በመቁጠር ዛሬን በትጋትና በጥበብ በመስራት የበለፀገች ሀገርን ለትውልድ የማሸጋገር ራዕይ አለን። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ራዕያችንን እንዲጋሩ እንፈልጋለን።

Address

Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Peace and justice. /PJW/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share