Health, Development and Anti-Malaria Association - HDAMA

Health, Development and Anti-Malaria Association - HDAMA This page is intended to help promote HDAMA as an NGO, thereby endorse its activities and accomplishments.

የጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በባህር ዳር ተካሄደ ።ባህር ዳር — መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም.የጤና፣ ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባ...
12/10/2026

የጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በባህር ዳር ተካሄደ ።

ባህር ዳር — መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም.
የጤና፣ ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት (አብክመ) ጤና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ በድምቀት አካሄደ።
በጉባዔው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መልካሙ ጌትነት፣ ማኅበሩ በክልሉ የጤና፣ የልማትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

የማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶክተር አበረ ምሕረቴ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርቱ ተቋማዊ አቅም ግንባታን፣ አጋርነትን፣ አባላት ማበራከትን እና የገቢ ማጠናከር ሥራዎች በሰፊው ተዳሰዋል። በወባ መከላከልና ቁጥጥር፣ በስነ-ተዋልዶና ጾታዊ ጥቃት መከላከል፣ እንዲሁም በትንባሆ ቁጥጥር ላይ የተሠሩ ሥራዎች ተነስተዋል። በተለይም በክልሉ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት መድኃኒት ወደ ጤና ተቋማት ለማድረስ የተፈጠረውን እንቅፋት ለመቅረፍ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ለወረዳ ጤና ተቋማት የተደረገው የመድኃኒት አቅርቦት ድጋፍ እንደ ዋና ስኬት ተጠቅሷል።

የቀረቡት የ2018 በጀት ዓመት የክንውን ሪፖርት እና የሒሣብ ምርመራ (ኦዲት) ሪፖርት በጉባዔው አባላት በሙሉ ድምፅ ጸድቀዋል። በተጨማሪም የማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በሰፊው ተወያይተውበት በሙሉ ድምፅ ጸድቀዋል። በመጨረሻም የማኅበሩ የጋራ መዝሙር ለታዳሚው ቀርቦ ጸድቋል።

በስብሰባው ማጠናቀቂያ ላይ ለማኅበሩ ሥራዎች መቃናት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አጋር አካላት፣ ለወረዳ እና ለክላስተር አስተባባሪዎች የምስክር ወረቀትና እውቅና ተሰጧል። ከክላስተሮች መካከል ከፍተኛ አፈጻጸም በማሳየት ከ1ኛ እስከ 3ኛ የወጡት፡-
አቶ ግዛቸው ባይሌ — ደቡብ ጎንደር ክላስተር
አቶ አብጠው ከበደ — እነማይ ክላስተር
አቶ አገኘሁ ሙሉነህ — አዊ ክላስተር
እንዲሁም የክልል አስተባባሪ አቶ ጋሻው ድሌ የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል።
በተጨማሪም የማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር ላለፉት ዓመታት ላሳዩት ከፍተኛ ትጋት እና ድጋፍ ለማኅበሩ ሠራተኞች፣ ለአጋር አካላት እንዲሁም ለመላው የማኅበሩ አባላት የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ይህንን 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በአማራ ክልል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ እና በጸሐፊ ወ/ሮ አስካለ አድማሱ መሪነት የተካሔደ ሲሆን፤ በወረዳና በማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቶች በኩል 456,000 የማኅበሩን አባላት ወክለው የተገኙ በርካታ ተሳታፊዎች ታድመውበታል። ጉባዔው የማኅበሩን መዋቅራዊ አቅም ማጠናከር፣ ገጽታ ግንባታ እና ገቢን ማሳደግ ላይ ያተኮሩ ማጠቃለያዎችን በማስቀመጥ በስኬት ተጠናቋል።

የማቴዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ ወ/ማርያም በ72 ዓመታቸው፣ መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም. በሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ...
04/10/2026

የማቴዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ ወ/ማርያም በ72 ዓመታቸው፣ መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም. በሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር ከማቴዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን ጋር በትምባሆና ጤናማ ባልሆኑ ምግቦች ቁጥጥር ዙሪያ የሕዝብ ጤናን ለማሻሻል በጋራ ሲሠራ ቆይቷል። በዚህ የሥራ ትብብር ውስጥ አቶ ወንዱ ያበረከቱት አስተዋፅኦና የሰጡት ድጋፍ በክብር ይታወሳል።

የጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር አመራርና ሠራተኞች በአቶ ወንዱ በቀለ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለሥራ አጋሮቻቸው እና ለማቴዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን ሠራተኞች ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን።

የጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር በጃቢ ጠህናን ወረዳ ላበረከተው አስተዋጽኦ የምስጋናና የምስክር ወረቀት አገኘ።​የጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር በጃቢ ጠህናን ወረዳ ውስጥ ባከናወናቸው የልማ...
18/09/2026

የጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር በጃቢ ጠህናን ወረዳ ላበረከተው አስተዋጽኦ የምስጋናና የምስክር ወረቀት አገኘ።

​የጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር በጃቢ ጠህናን ወረዳ ውስጥ ባከናወናቸው የልማትና የጤና ሥራዎች ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የክብር የምስጋናና የምስክር ወረቀት ተበረከተለት ።

​ማኅበሩ በመንግሥት በጀት ብቻ ሊሸፈኑ ያልቻሉ የልማትና የሕዝብ አገልግሎት ክፍተቶችን በመለየት በግንባር ቀደምትነት ሲሠራ መቆየቱ ተገልጿል። በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተሰማርቶ ባከናወናቸው ተግባራት ለወረዳው ስኬትና ለአካባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ ጠቃሚነት ላላቸው ሥራዎች ውጤታማ ሚና መጫወቱም ተገልጿል ።
​
ይህንን የማኅበሩን አወንታዊ እንቅስቃሴና የላቀ አገልጋይነት ዕውቅና ለመስጠት፤ የጃቢ ጠህናን ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት እና የገንዘብ ጽሕፈት ቤት በጋራ በመሆን የምስጋናና የምስክር ወረቀቱን አበርክተዋል።

​በቀጣይም የማኅበሩ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ለሌሎች አካላትም አርዓያ የሚሆን አጋርነት መሆኑ ተጠቅሷል።

17/09/2026
10/09/2026

እንኳን ለ2019 ዓ.ም. ለዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ!

ለመላው የጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር ቤተሰቦች፣ አጋር ድርጅቶችና የማኅበረሰብ አባላት፣ እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!

ባለፈው ዓመት ማኅበራችን በተለያዩ አካባቢዎች የጤና አገልግሎቶችን በማጠናከር፣ ወባን በመከላከል፣ በምርመራና በሕክምና፣ የማኅበረሰብ ግንዛቤን በማሳደግ እና በተለይም ተንቀሳቃሽ ሠራተኞችንና ከፍተኛ የወባ ጫና ያለባቸውን ማኅበረሰቦች በመድረስ አስፈላጊ ሥራዎችን አከናውኗል።

በተጨማሪም፣ በአማራ ክልል ይልማና ዴንሳ ወረዳ በሚገኙ የፀበል ቦታዎች የኮሌራ በሽታን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የጤና፣ የአካባቢና የግል ንፅህና ተግባራትን በማጠናከር የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር ሰርቷል።

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በሚገኙ አምስት ወረዳዎች ከJSI ጋር በመተባበር የሚተገበረው Momentum Integrated Health Resilience (MIHR-E) ፕሮጀክትም፣ በግጭትና ተጋላጭነት ባለባቸው አካባቢዎች የእናቶችና የሕፃናት ጤናን፣ የተመጣጠነ ምግብን እና የጤና ሥርዓትን ለማጠናከር ሰፊ ተግባራትን አከናውኗል ።

የትምባሆ ጉዳትን በመከላከልም የማኅበረሰብ ግንዛቤን በማሳደግ፣ የትምባሆ ቁጥጥር ሕግ እንዲተገበርና ሕዝብ ከትምባሆ ጭስ እንዲጠበቅ በሚዲያና በአድቮኬሲ ሥራዎች አስተዋጽኦ አድርጓል።

እንዲሁም በግጭትና በፀጥታ ችግር ምክንያት ተደራሽ ባልሆኑ አካባቢዎች ለሚገኙ የጤና ተቋማት ሕይወት አድን መድኃኒቶችንና የሕክምና ግብዓቶችን በማጓጓዝና በማሰራጨት በርካታ ዜጎች አስፈላጊውን የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓል።

በ2019 ዓ.ም. ም ይህንን የጋራ ጥረት በማጠናከር የበለጠ የህበረተሰብ ክፍል የጤናና የልማት ተጠቃሚ እንዲሆን አብረን እንስራ። የማኅበሩ ራዕይና ተልዕኮ እንዲሳካ አባል በመሆን፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በማበርከት፣ በማኅበሩ የጤናና የልማት ሥራዎች በንቃት በመሳተፍ የጋራ ተልዕኳችንን እንድናሳካ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

⭐️ መልካም አዲስ ዓመት!⭐️

ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር (HDAMA)

02/09/2026

ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር በ“ሰናይ” ፕሮጀክት አማካኝነት በወባ በሽታ ለተጋለጡ ጊዜያዊና ተንቀሳቃሽ ሠራተኞች የወባ መከላከል፣ ምርመራና ሕክምና አገልግሎቶችን ተደራሽ እያደረገ ነው።

ፕሮጀክቱ በአማራ ክልል በአምስት ወረዳዎች በሚገኙ ሰፋፊ እርሻዎችና የልማት ቀጠናዎች ላይ በማተኮር፣ በእነዚህ የሥራ ቦታዎች ለሚገኙ የወባ በሽታ ተጋላጭ ሠራተኞች የጤና አገልግሎትን በቀጥታ ወደ ሥራ ቦታዎች እያደረሰ ይገኛል።

ነሐሴ 22፣ 2018 ዓ.ም. በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ እርግብ ቀበሮ ቀበሌ በሚገኙ የሥራ ቦታዎች ላይ የወባ ምርመራና ሕክምና አገልግሎት ተሰጥቷል።
የምርመራና ሕክምና ሥራው የወባ በሽታን በፍጥነት ለመለየት፣ ተገቢውን ሕክምና በወቅቱ ለመስጠት እና በሥራ ቦታዎች የወባ ስርጭትን ለመቀነስ የሚያግዝ ነው።

“ሰናይ” ፕሮጀክት የተንቀሳቃሽና ጊዜያዊ ሠራተኞች የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ያላቸውን ችግሮች በመቅረፍ፣ የወባ በሽታን በተጋላጭ ማኅበረሰቦች መካከል ለመቆጣጠር እና የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ የሚያግዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር ለትንባሆ ቁጥጥር ላበረከተው አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጠውአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2018 ዓ.ም. —ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር  በኢትዮጵያ የትንባሆ ቁጥጥር ሥራን ለ...
31/08/2026

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር ለትንባሆ ቁጥጥር ላበረከተው አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጠው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2018 ዓ.ም. —
ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር በኢትዮጵያ የትንባሆ ቁጥጥር ሥራን ለማጠናከር ላበረከተው አስተዋጽኦ ከኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን (EFDA) የምስጋናና የእውቅና ምስክር ወረቀት ተቀበለ።

እውቅናው የተሰጠው ማኅበሩ በትንባሆ ቁጥጥር ዘርፍ የሚከናወኑ ሥራዎችን በመደገፍ፣ የትንባሆ ቁጥጥር ጉዳይ በተገቢው ትኩረት እንዲያገኝ በመሥራት እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በትብብር እንዲሠሩ በማበረታታት ላበረከተው ሚና ነው።

ማኅበሩ በተለይም በአዋጅ 1112/2011 የተደነገጉ የትንባሆ ቁጥጥር አላማዎችን ለማሳካት የሚደረጉ ጥረቶች እንዲጠናከሩ በተለያዩ ሥራዎች ላይ በመሳተፍ የበኩሉን ሚና ሲወጣ ቆይቷል።
የትንባሆ ቁጥጥር ሥራ የሕዝብ ጤናን ከትንባሆ ጉዳት ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ፣ ማኅበሩ በዘርፉ የሚደረጉ የጋራ ጥረቶች እንዲጠናከሩ ከመንግሥት ተቋማትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ሲሠራ ቆይቷል።

ከEFDA የተሰጠው ይህ የእውቅና ምስክር ወረቀትም ማኅበሩ በትንባሆ ቁጥጥር ዘርፍ እያከናወነ ላለው ሥራ እውቅና ከመስጠት ባለፈ፣ በቀጣይ የሚያከናውናቸውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ለማጠናከር አዲስ ማበረታቻ ይሆናል።

ማኅበሩ በቀጣይም ትንባሆን በመቆጣጠር የሕዝብ ጤናን ለመጠበቅ ከሚሠሩ የመንግሥትና የሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማት ጋር በመተባበር የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያጠናክር ተገልጿል

የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር 28ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በአዲስ አበባና በባህር ዳር ሊያከበር ነውአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15 ቀን 2018  የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር 28ኛ ዓመት የምስ...
21/08/2026

የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር 28ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በአዲስ አበባና በባህር ዳር ሊያከበር ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15 ቀን 2018
የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር 28ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በአዲስ አበባ እና በክልል ቅርንጫፉ በባህር ዳር በተለያዩ መርሃ ግብሮች ሊያከብር መሆኑ ተገለጸ።

በዓሉ በመጪው እሁድ፣ ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚከበር ሲሆን፣ ማኅበሩ በጤና ልማትና በሰብዓዊ ምላሽ ዘርፎች ባለፉት 28 ዓመታት ያከናወናቸውን ሥራዎችና ያስመዘገባቸውን ስኬቶች የሚዘከርበት መድረክ ይሆናል።

ማኅበሩ ከሚያከናውናቸው ዋና ዋና የሥራ መስኮች መካከል ወባንና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን መከላከልና መቆጣጠር፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከልና መቆጣጠር ይገኙበታል።

በተጨማሪም በአፍላ ዕድሜ ያሉ ወጣቶችን የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት መስጠት፣ ለወጣቶችና ለሴቶች የመተዳደሪያ አማራጮችን ማስፋፋትና የሥራ ዕድሎችን ማመቻቸት፣ እንዲሁም የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትና ሰብዓዊ ምላሽ መስጠት ይገኙበታል ።

በአዲስ አበባ በሚካሄደው በዓል ላይ የማኅበሩ የቦርድ አመራር አባላት፣ ሰራተኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው ልዩ ልዮ እንግዶች የሚገኙ ሲሆን፤ ዕለቱን የሚያጎሉ ዝግጅቶች ተደርገዋል።

ይህ የ28ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማኅበሩን የብዙ ዘመናት የስኬት ጉዞ ለመዘከር፣ ያጋጠሙ ፈተናዎችን አልፎ የተገኙ ውጤቶችን ለሕዝብ ለማጋራት፣ እንዲሁም በቀጣይ የሚከናወኑ የጤና ልማት፣ የበሽታ መከላከልና የሰብዓዊ ምላሽ ሥራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተገልጿል።

Address

Yeka Sub-city, Woreda-6, Located On The Right Bend Of Megenagna Road, Situated Between Women's Square And Adwa Bridge
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Health, Development and Anti-Malaria Association - HDAMA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Health, Development and Anti-Malaria Association - HDAMA:

Shortcuts

Share