24/09/2026
EWLA in Action: Empowering grassroots Legal Advocates in Dessie for Survivor-Centered Support!
From September 22-24, 2026, Ethiopian Women Lawyers’ Association (EWLA), in partnership with Ethiopia, provided capacity-building training on: survivor centered paralegal service for paralegal committees in Dessie.
Bringing together 25 paralegals and Bureau of Justice focal persons from Woldia, Kemise, Mersa and Dessie, the session focused on strengthening legal aid services at the grassroots level. Participants enhanced their skills in local grievance handling, legal assistance, survivor-centered emotional support, and community referral pathways. By promoting cross-zonal learning across Amhara’s zonal committees, this initiative directly empowers local advocates to deliver accessible, compassionate, and effective justice to their communities.
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ከ #ኢንጀንደር ኸልዝ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በአማራ ክልል ደሴ ለሚገኙ የኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ በጎ ፈቃደኛ ኮሚቴዎችና ከፍትሕ ቢሮ ለተውጣጡ ተወካዮች ተጎጂዎችን ባማከለ መሰረታዊ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከመስከረም 12-14 ቀን 2019 ዓ.ም. የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።
ከወልዲያ፣ ከኬሚሴ፣ ከመርሳ እና ከደሴ የተውጣጡ 25 የኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ በጎ ፈቃደኛ ኮሚቴዎች እና የፍትህ ቢሮ ተወካዮች የተሳተፉበት ይህ ስልጠና በማህበረሰብ ደረጃ የሚሰጡ የሕግ ድጋፍ አገልግሎቶችን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር። ተሳታፊዎች ከስልጠናው በአካባቢው የሚተገበሩ የቅሬታ አፈታት፣ የጥቃት ተጎጂዎችን ስሜት ያማከለ
የሕግ ድጋፍ አገልግሎት አሰጣጥ እና የሪፈራል/የቅብብሎሽ ዘዴዎች ላይ ያላቸውን ክህሎት አሻሽለዋል። በአጠቃላይ ስልጠናው በአማራ ክልል ዞኖች በሚገኙ ኮሚቴዎች መካከል ያለውን የልምድ ልውውጥ ከማስተዋወቅ ባሻገር የአካባቢው ሻምፒዮኖች ለማህበረሰቦቻቸው ተደራሽ እና ውጤታማ ፍትህ እንዲያገኙ ለመርዳት የሚያስችል ግንዛቤ ፈጥሯል።