10/03/2026
አምስት የሮተሪ ክለቦች ከሮተሪ ኢትዮጵያ እና Hohe Awards ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ልዩ የመፅሀፍ ውይይት እና የንባብ ምሽት በቅርቡ ሊካሄድ ነው። ይህ መድረክ የተዘጋጀው በመመለስ መፅሀፍ ዙሪያ ከመፅሀፉ ደራሲ ከብርቱካን ሚዴቅሳ ጋር በቀጥታ ለመወያየት እና የተለያዩ ልምዶችን፣ ሀሳቦችን እና ተሞክሮዎችን ለመወያየት ነው።
በመጪው አርብ መጋቢት 04፣ 2018 ዓ.ም. ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ በሴፍ ላይት ኢኒሼቲቭ አዳራሽ (ቦሌ ድልድይ ኬኬር ህንፃ ላይ) የሚካሄደው ይህ የመፅሀፍ ዳሰሳ መርሃ ግብር ከመፅሀፍ ዳሰሳ በላይ የሆነ ውይይት ይሆናል፤ ተሳታፊዎች የመፅሀፉን ይዘት በጥልቅ ለመወያየት፣ ከደራሲዋ ጋር በቀጥታ ለመገናኘት እና የራሳቸውን አስተያየቶች ለማጋራት ዕድል ያገኛሉ።
መፅሀፉን ሁለተኛው ፎቶ ላይ በተቀመጠው አድራሻ አሁንም በማዘዝ ከውይይቱ በፊት ማንበብ ይችላሉ፤ ይህም በውይይቱ ላይ በበለጠ ተሳትፎ ለማድረግ ያግዛችኋል። በእለቱ የመፅሀፍ ፊርማ ሥነ-ስርዓትም ይካሄዳል፤ በመሆኑም ተሳታፊዎች በደራሲዋ የተፈረመ መፅሀፍ በዳሰሳው ላይ ማግኘት ይችላሉ።
ይህ መድረክ የእንደራሴ ሮተሪ ክለብ የንባብ ባህልን ለማበረታታት፣ ሀሳቦችን ለማጋራት እና በመፅሀፍ ዙሪያ ጤናማ ውይይት ለመፍጠር የጀመረው ስራ አንዱ አካል ነው።
ኑ ስለ መመለስ እንወያይ፤ ኑ እናንብብ፤ ኑ ሀሳብ አስተያየታችንን እናጋራ።
ጠሪ አክባሪ ነው እና እንዳትቀሩ! 📚
ቦታ:- https://maps.app.goo.gl/B3MTs8d8eEdUhnto6
መግቢያ:- በነፃ
Rotary Ethiopia