Mekdim Ethiopia National Association/MENA

Mekdim Ethiopia National Association/MENA MENA is a pioneer non governmental organization working on the HIV AIDS and related social problems.

Mekdim Ethiopia National Association is a pioneer local Non government organization working on HIV epidemic control over two decades in Ethiopia.

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮችእንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ( ዐረፋ) በዓል አደረሳችሁ #ኢድ ሙባረክመቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽንMekdim Ethiopia National Ass...
26/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ( ዐረፋ) በዓል አደረሳችሁ

#ኢድ ሙባረክ

መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን

Mekdim Ethiopia National Association/MENA
Mekdim Ethiopia National Association-Jimma Branch

በመቅድም ኢትዮጵያ  ሁልጊዜም እንደምናምነው፥ የኤች.አይ.ቪ (HIV) ምርመራ ውጤት የህይወት ማብቂያ ሳይሆን ወደ ጥንካሬ፣ ራስን ወደ መቀበል እና ወደ አዲስ እድገት የሚመራ የጉዞ መጀመሪያ ...
25/05/2026

በመቅድም ኢትዮጵያ ሁልጊዜም እንደምናምነው፥ የኤች.አይ.ቪ (HIV) ምርመራ ውጤት የህይወት ማብቂያ ሳይሆን ወደ ጥንካሬ፣ ራስን ወደ መቀበል እና ወደ አዲስ እድገት የሚመራ የጉዞ መጀመሪያ ነው። 💙

የጥንካሬ እና የአገልግሎት ታሪኮቻችንን ማጋራት፤ መግለልና መድሎን ለመስበር፣ ፍርሃትን ለማስወገድ እና ማንኛውም ሰው ሙሉ እና ደስተኛ ህይወት መኖር እንደሚችል ለሌሎች ለማስታወስ ትልቁ መሣሪያችን ነው።

ታሪክዎን በኩራት ይኑሩት፣ የህይወት ጉዞዎን ያጋሩ፣ እናም መገለልን በጋራ እናስቅር። የእርስዎ ድምፅ ለብዙዎች ብርሃን ነው! 🌟

#መቅድምኢትዮጵያ #የጥንካሬታሪኮች #መገለልንና መድሎን ማስቀረት

At Mekdim Ethiopia National Association (MENA), we believe a positive HIV diagnosis is not the end—it can mark the beginning of a journey toward strength, self-acceptance, and personal growth. 💙

Sharing our stories of resilience and empowerment is our greatest tool to break the silence, shatter stigma, and remind everyone that it is possible to live a full, vibrant life.

Own your story, share your journey, and let’s end stigma together. Your voice matters!🌟

መቅድም ኢትዮጵያ እና የጤና ሚኒስቴር የሀገሪቱን የጤና ሥርዓት ዘላቂነት ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ _________________________መቅድም ኢትዮጵ...
22/05/2026

መቅድም ኢትዮጵያ እና የጤና ሚኒስቴር የሀገሪቱን የጤና ሥርዓት ዘላቂነት ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ
_________________________
መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ከፌዴራል ጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የተሳካ ስትራቴጂካዊ የምክክር መድረክ ማካሄዱን በደስታ ይገልጻል። በጤና ሚኒስቴር በኩል የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ እና የዘርፍ ብዙ ምላሽ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ያደታ የተገኙበት ይህ መድረክ፤ መቅድም ኢትዮጵያ ወደፊት የሚያከናውናቸውን ስትራቴጂካዊ የሥራ መርሐ-ግብሮች በሀገሪቱ እየተተገበሩ ካሉ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ ማሻሻያዎች ጋር ለማቀናጀትና ዘላቂነታቸውን ለማረጋገጥ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

በውይይቱም ማህበረሰብ-ተኮር የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው እና ሀገራዊ የጤና ዋስትናን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የአገር በቀል ድርጅቶች ሊጫወቱ በሚገባቸው ሚናዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በምክክር መድረኩ ላይ ክቡር ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ መቅድም ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ግንባር ቀደምና መሪ በመሆን ላበረከተው ታሪካዊ አስተዋፅኦ እና በተለይም ኤች አይቪ ኤድስን ለመከላከል በተደረገው ሀገር አቀፍ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ከመነሻው ጀምሮ ለነበረው ጉልህ የመሪነት ሚና እና አሁንም እያደረገ ላለው የማይተካ አበርክቶት ምስጋና እና ዕውቅና የሰጡ ሲሆን፤ በተለይም ላለፉት 30 አመታት በላይ ያካበተውን ተግባራዊ ልምድና ሰፊ የመፈጸም አቅም ታሳቢ ባደረገ መልኩ ብሎም የኤች አይቪ ኤድስ በደማቸው የሚገኝባቸውን ወገኖች ቀጥተኛ የአባላት ውክልና እንዳለው ሀገር በቀል ማህበር ፤ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ማህበሩን በአገር አቀፍም ሆነ በክልል ደረጃ በሚደደረጉ የኤች አይቪን የመከላከል እና የድጋፍ አገልግሎቶች ና በሌሎችም የጤና ዕድሎችና መድረኮች ላይ ለማሳተፍና ለመደገፍ ሙሉ ቁርጠኝነት እንዳለው አረጋግጠዋል።

መቅድም ኢትዮጵያም በበኩሉ አሁን ከሚያከናውናቸው የኤች አይቪ ተኮር አገልግሎቶች በተጨማሪም የተቀናጀ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ አገልግሎትን ይበልጥ ለማጠናከር፣ የአገር ውስጥ አቅምን ለመገንባት እና የጤና አገልግሎት ፍትሃዊነትን በማረጋገጥ ሩቅና ተደራሽ ላልሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ጭምር አገልግሎቱን ለማስፋፋት የጀመረውን ዝግጅት እና ስትራቴጂካዊ ሽግግር አብራርቷል።
ይህ ስትራቴጂካዊ አጋርነት በቀጣይ የአገር ውስጥ ሀብት ማሰባሰብ አቅምን ማሳደግ፤ በኤች አይቪ እና ሌሎች የ ማህበረሰብ-ተኮር የጤና አገልግሎቶችን ዘላቂ ማድረግ ላይ በትኩረት የሚሰራ ይሆናል። መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ላሳዩት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ፣ ጠቃሚ ምክር እና አጋርነት ያለውን ጥልቅ ምስጋና እያቀረበ፤ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን አስተማማኝና ጠንካራ የጤና ሥርዓት ለመገንባት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለመገለጽ ይወዳል ፡፡

“ኤች አይ ቪ በደማቸዉ የሚገኝባቸዉንና በኤድስ ምክንያት ችግር ያጋጠማቸዉን ወገኖች እናፍቅር! እንርዳ! እንንከባከብ"

ከመቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ጋር አብረው ይስሩ፤ ለተጨማሪ መረጃዎች ገጻችንን ይከታተሉ።

Mekdim Ethiopia National Association/MENA

በመደበኛነት የጤና ምርመራ ማድረግ  ስለ ሙሉ ጤንነትዎ ማሰብ ነው! 🩺ዘወትር የሚደረግ የጤና ምርመራ የኤች.አይ.ቪ (HIV) ሁኔታን ለመከታተል ብቻ ሳይሆን፥ ማንኛውንም የጤና እክል አስቀድሞ...
18/05/2026

በመደበኛነት የጤና ምርመራ ማድረግ ስለ ሙሉ ጤንነትዎ ማሰብ ነው! 🩺

ዘወትር የሚደረግ የጤና ምርመራ የኤች.አይ.ቪ (HIV) ሁኔታን ለመከታተል ብቻ ሳይሆን፥ ማንኛውንም የጤና እክል አስቀድሞ ለመለየት፣ የህክምናዎን ውጤታማነት ለመጨመር እና አጠቃላይ ደህንነትዎን ለመጠበቅ ይረዳል።

ዛሬ ለጤናዎ ቅድሚያ ይስጡ፤ የወደፊት ማንነትዎ ነገ ያመሰግንዎታል!

👉 የጤና ምርመራ ቀጠሮዎን ያስታወሱ !

#መልካም የጤና ሳምንት ይሁንልዎ

#የቅድመመከላከልህክምና #የጤናምርመራ #ደህንነት #ከኤችአይቪጋርበደስታመኖር #ጤናማአኗኗር #መቅድም ክሊኒክ

መቅድም ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ ፡፡___________________________________________መቅድም...
15/05/2026

መቅድም ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ ፡፡
___________________________________________

መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለበርካታ ዓመታት የቆየውን የጋራ ትብብር ወደ ተጠናከረ ዘርፈ-ብዙ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሸጋገር ያለመ ከፍተኛ የሥራ መሪዎች የምክክር መድረክ አካሂደዋል።
በጤናው ዘርፍ ያለውን የቴክኒክ ልምድ እና የሃይማኖት ተቋማትን መንፈሳዊ መሪነት ማቀናጀት ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ በጋራ በመተግበር ላይ ከሚገኙት ፕሮግራሞች በተጨማሪ፤ ሁለቱም ተቋማት አዲስ ስትራቴጂካዊ መርሐ-ግብር ነድፈው ለመንቀሳቀስ ተስማምተዋል። ይህ ስምምነት ተቋማዊ ዘላቂነትን በማረጋገጥ የጤና ና የማህበራዊ አገልግሎቶችን ተደራሽነት ይበልጥ ለማስፋት እንዲሁም ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ባለፈ ሰፊ የሕዝብ ጤና እና ማህበራዊ ድጋፍ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው።
ይህም በሃይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት የሚተገበሩ ማህበረሰብ-ተኮር የጤና አገልግሎቶች በኢትዮጵያ ብሔራዊ የጤና ሥርዓት ውስጥ ግንባር ቀደም የድጋፍ ምሰሶ ሆኖ እንዲቀጥል ያስችላል።
“ ኤች አይ ቪ በደማቸዉ የሚገኝባቸዉንና በኤድስ ምክንያት ችግር ያጋጠማቸዉን ወገኖች እናፍቅር! እንርዳ! እንንከባከብ|

ከመቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ጋር አብረው ይስሩ፤ ለተጨማሪ መረጃዎች ገጻችንን ይከታተሉ።

𝗠𝗘𝗡𝗔 𝗮𝗻𝗱 𝗜𝗥𝗖𝗘 𝗘𝗹𝗲𝘃𝗮𝘁𝗲 𝗦𝘁𝗿𝗮𝘁𝗲𝗴𝗶𝗰 𝗣𝗮𝗿𝘁𝗻𝗲𝗿𝘀𝗵𝗶𝗽 𝗳𝗼𝗿 𝗛𝗲𝗮𝗹𝘁𝗵 𝗦𝘂𝘀𝘁𝗮𝗶𝗻𝗮𝗯𝗶𝗹𝗶𝘁𝘆

Mekdim Ethiopia National Association (MENA) and the Inter-Religious Council of Ethiopia (IRCE) have concluded a high-level strategic meeting to transition their long-standing collaboration into a formalized, multi-sectoral alliance.

Recognizing the vital synergy between technical healthcare and spiritual leadership, both institutions have committed to a new roadmap and strengthened partnership focused on institutional sustainability and expanded health services and other community supports to address broader public health priorities beyond HIV/AIDS.
This collaboration ensures that faith-supported community health remains a pillar of Ethiopia’s national health system.

“𝙇𝙀𝙏 𝙐𝙎 𝙇𝙊𝙑𝙀 𝙎𝙐𝙋𝙋𝙊𝙍𝙏 𝘼𝙉𝘿 𝘾𝘼𝙍𝙀 𝙁𝙊𝙍 𝘼𝙄𝘿𝙎 𝙊𝙍𝙋𝙃𝘼𝙎 𝘼𝙉𝘿 𝙑𝙄𝘾𝙏𝙄𝙈𝙎 !!!”

Follow and partner with Ethiopia National Association - The Pioneer.
Stay tuned for more updates.

Mekdim Ethiopia National Association-Jimma Branche

Inter Religious Council of Ethiopia

በሁሉም ቦታ በሁሉም የስራ መስክ ያላችሁ ላብአደሮች  በሙሉ መልካም የላብ አደሮች ቀን ይሁንላችሁ !በስራችን እና በአገልግሎታችን  ሁሉ ኤች አይ ቪ በደማቸዉ የሚገኝባቸዉንና በኤድስ ምክንያት...
01/05/2026

በሁሉም ቦታ በሁሉም የስራ መስክ ያላችሁ ላብአደሮች በሙሉ መልካም የላብ አደሮች ቀን ይሁንላችሁ !

በስራችን እና በአገልግሎታችን ሁሉ ኤች አይ ቪ በደማቸዉ የሚገኝባቸዉንና በኤድስ ምክንያት ችግር ያጋጠማቸዉን ወገኖች እናፍቅር! እንርዳ! እንንከባከብ!

#መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን
#የላብ አደሮች ቀን
#2018

🎗️ 𝗦𝘁𝗿𝗲𝗻𝗴𝘁𝗵𝗲𝗻𝗶𝗻𝗴 𝗜𝗺𝗽𝗮𝗰𝘁 𝗧𝗵𝗿𝗼𝘂𝗴𝗵 𝗣𝗮𝗿𝘁𝗻𝗲𝗿𝘀𝗵𝗶𝗽: 𝗦𝗶𝘁𝗲 𝗩𝗶𝘀𝗶𝘁 𝘄𝗶𝘁𝗵 𝗣𝗿𝗼𝗷𝗲𝗰𝘁 𝗛𝗢𝗣𝗘We were pleased to conduct a productive site vi...
17/04/2026

🎗️ 𝗦𝘁𝗿𝗲𝗻𝗴𝘁𝗵𝗲𝗻𝗶𝗻𝗴 𝗜𝗺𝗽𝗮𝗰𝘁 𝗧𝗵𝗿𝗼𝘂𝗴𝗵 𝗣𝗮𝗿𝘁𝗻𝗲𝗿𝘀𝗵𝗶𝗽: 𝗦𝗶𝘁𝗲 𝗩𝗶𝘀𝗶𝘁 𝘄𝗶𝘁𝗵 𝗣𝗿𝗼𝗷𝗲𝗰𝘁 𝗛𝗢𝗣𝗘

We were pleased to conduct a productive site visit at our Maedot, Addis Ketema SDP, hosting guests from the Project HOPE Head Office. This visit is part of the ongoing USG Family-Focused HIV Prevention, Care, and Treatment Activity in Addis Ababa.

During the visit, our team presented a comprehensive overview of:

• Project Scope of Work and strategic implementation.

• Best Practices and key lessons learned from the field.

• Implementation Challenges and our collaborative solutions.

• The continuity of life-saving services for the families we serve.

𝘛𝘩𝘦 𝘧𝘦𝘦𝘥𝘣𝘢𝘤𝘬 𝘧𝘳𝘰𝘮 𝘰𝘶𝘳 𝘱𝘢𝘳𝘵𝘯𝘦𝘳𝘴 𝘸𝘢𝘴 𝘪𝘯𝘤𝘳𝘦𝘥𝘪𝘣𝘭𝘺 𝘦𝘯𝘤𝘰𝘶𝘳𝘢𝘨𝘪𝘯𝘨. 𝘞𝘦 𝘳𝘦𝘮𝘢𝘪𝘯 𝘤𝘰𝘮𝘮𝘪𝘵𝘵𝘦𝘥 𝘵𝘰 𝘰𝘶𝘳 𝘶𝘯𝘸𝘢𝘷𝘦𝘳𝘪𝘯𝘨 𝘦𝘧𝘧𝘰𝘳𝘵𝘴 𝘪𝘯 𝘥𝘦𝘭𝘪𝘷𝘦𝘳𝘪𝘯𝘨 𝘩𝘪𝘨𝘩-𝘲𝘶𝘢𝘭𝘪𝘵𝘺, 𝘧𝘢𝘮𝘪𝘭𝘺-𝘤𝘦𝘯𝘵𝘦𝘳𝘦𝘥 𝘤𝘢𝘳𝘦. 🤝

Visit our impact : www.mekdimethiopia.org
Work with us !



Project HOPE

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የአብሮነት እንዲሆንልን ከልብ እንመኛለን።መልካም የትንሣኤ በዓል!...
11/04/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የአብሮነት እንዲሆንልን ከልብ እንመኛለን።

መልካም የትንሣኤ በዓል!

#መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለስቅለት በዓል አደረሳችሁ!መልካም በአል #መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽንMekdim Ethiopia National Association/MENA Mek...
10/04/2026

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለስቅለት በዓል አደረሳችሁ!
መልካም በአል
#መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን
Mekdim Ethiopia National Association/MENA
Mekdim Ethiopia National Association-Jimma Branch
Ministry of Health,Ethiopia

የመቅድም ኢትዮጵያ ሠራተኞች ለማህበራችን አባላት የበአል ድጋፍን አደረጉ !_____________________መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ፣ የመቅድም ኢትዮጵያ ሠራተኞች ለአባላቶቻ...
08/04/2026

የመቅድም ኢትዮጵያ ሠራተኞች ለማህበራችን አባላት የበአል ድጋፍን አደረጉ !
_____________________

መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ፣ የመቅድም ኢትዮጵያ ሠራተኞች ለአባላቶቻችን የበዓል ድጋፍ አድርገዋል። ይህም ሰራተኞች ከደሞዛቸው በማዋጣት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን አባላት ለማገዝና ቤተሰባዊ መተሳሰብን በተግባር መግለጽን ታሳቢ ያደረገ ነው ፡፡

ይህ የበዓል ድጋፍ መርሃ-ግብር የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የሠራተኞች ተወካዮች በተገኙበት የተከናወነ ሲሆን፣ ድርጅቱ ከምስረታው ጀምሮ ለአባላቱና ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ያለውን ጽኑ አብሮነትና ወገናዊነት በድጋሚ ያረጋገጠበት ሆኗል።

የድጋፉ ተጠቃሚ የሆኑ የማሀብራችን አባላት በተደረገላቸው የበዓል ድጋፍ መደሰታቸውን ገልጸው፣ መቅድም ኢትዮጵያ ሁልጊዜም እንደ ቤተሰብ ከጎናቸው መቆሙ ትልቅ ብርታት እንደሚሆናቸው ገልጽው ለሠራተኞቹና ለድርጅቱ አመራር ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም በጋራ የምናደርገው ጥረት የብዙዎችን ጤና እና ሕይወት ለመለወጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለው የተነሳ ሲሆን በተለይ አባላት በመቅድም ክሊኒክ በነጻ የሚሰጡ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎቶችን ይበልጥ እንዲጠቀሙና ሌሎችም አገልግሎቱን እንዲያገኙም የድርሻቸውን እንዲወጡም መልእክት ተላልፏል፡፡
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፦ መልካም የስቅለትና ትንሳኤ በዓል እንዲሆንላችሁ ከወዲሁም ከልብ እንመኛለን!

#ዓላማችን ማገልገል፣ ደስታችን አብሮነት ነው !
#መልካም በአል
#አብረውን ይዝለቁ

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251111232408

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mekdim Ethiopia National Association/MENA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Mekdim Ethiopia National Association/MENA:

Share