ይፋት ወ መንዝ /Yifat & Menz

ይፋት ወ መንዝ /Yifat & Menz Giving latest information about Menz and Yifat

24/08/2025

የአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሐራ ገበያ እና የሐራ ገበያ - መቐለ የባቡር መስመሮች ግንባታ ሊጀምር ነው ተባለ

| 🚆 የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ በ2013 ዓ.ም በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ግጭት ምክንያት ግንባታቸው ተቋርጠው የነበሩትን የባቡር መንገዶች ግንባታ ለማስጀመር የሚያስችሉ ግምገማዎች ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

ማዕከላዊ ኢትዮጵያን ከሰሜን ጋር ለማገናኘት የተነደፉት የባቡር መስመሮቹ፦

🔶 የአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሐራ ገበያ 392 ኪሎ ሜትር፣
🔶 የሐራ ገበያ - መቀሌ 268 ኪሎ ሜትር ርዝመት አላቸው፡፡

ፕሮጀክቶቹ፣ የቻይና የፋይናንስ ተቋማትን ጨምሮ በአብዛኛው በውጭ ብድር የሚሠሩ መሆናቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

🛤 ኮርፖሬሽኑ በዓመቱ ውስጥ ከግንባታ ፕሮጀክቶች እና ከሌሎች የንግድ እንቅስቃሴዎች 710 ሚሊዮን ብር ገቢ ቢያገኝም፣ ከባቡር ሐዲድ ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በውጭ ዕዳ ጫና ውስጥ እንደሚገኝ ግምገማው ላይ ተጠቅሷል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡

19/08/2025
19/08/2025

Guassa Media

News Update | Ethiopia, Africa & World

🇪🇹 Ethiopia Headlines

Migrant Tragedy: A shipwreck off Yemen has left 132 migrants missing, many of them Ethiopians. Families mourn the dangers faced by youth forced to take risky routes for survival.

Civil Servant Salary Rise: The Federal Civil Service Commission confirmed that starting September, entry-level degree holders will earn 11,500 birr/month. A welcome boost for public workers during tough economic times.

Historic Fossil Discovery: In Ethiopia’s Afar region, scientists uncovered 2.6 million-year-old fossil teeth, proving that two different human ancestor species lived side by side. A groundbreaking insight into our shared past.

🌍 Africa News

⚖️ Sudan: The army is facing torture allegations, drawing international concern.

📺 Tanzania: The government bans live coverage of a high-profile treason trial, sparking debate about press freedom.

🕊 Burkina Faso: Authorities repatriate the body of activist Alino Faso, honoring his legacy in the country’s fight for justice.

🌎 World Highlights

🎬 Hollywood Loss: Veteran British actor Terence Stamp, famous for playing General Zod in the original Superman films, has passed away at the age of 87.

🌐 Global Outlook: Scientists, politicians, and activists continue to warn that climate change and migration crises remain the world’s top challenges of 2025.

Stay updated, stay inspired!

Media






https://www.facebook.com/profile.php?id=61579239118020

10/08/2025

https://www.facebook.com/profile.php?id=61579239118020

🌍 News | 🎭 Culture | 🎓 Education | 🎥 Entertainment | 💡Inspiration
Bringing you stories that inform, inspire, and empower.
Follow to stay connected to everything that matters.
📲 DM us to share your story or collaborate.

ከኤፍራታና ግድም ወረዳ ሠላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት የተሰጠ የሀዘን መግለጫ‼️ኤፌሶን፦ነሐሴ 03/2017ዓ/ም(ኤፍራታ ኮሙኒኬሽን) በኤፍራታና ግድም ወረዳ መስቀል በር ቀበሌ ገንጃት ጎጥ ንፉ...
09/08/2025

ከኤፍራታና ግድም ወረዳ ሠላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት የተሰጠ የሀዘን መግለጫ‼️

ኤፌሶን፦ነሐሴ 03/2017ዓ/ም(ኤፍራታ ኮሙኒኬሽን)

በኤፍራታና ግድም ወረዳ መስቀል በር ቀበሌ ገንጃት ጎጥ ንፉስ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ እና የመሬት መንሸራተት የ4 ሰዎች ሕይዎት ማለፍ እና የ2 ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን የኤፍራታና ግድም ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘውዱ ትለፍ ገልፀውልናል።

እንደ ሀላፊው ገለፃ በመስቀል በር ቀበሌ ገንጃት ጎጥ በቀን 02/12/2017ዓ.ም ለሊት ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ በተከሰተ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት የአንድ ቤተሰብ አቶ ተፈራ ክብረትን ጨምሮ 4ሰው በሞት 1ሴት ከባድ እና የ1ሰው ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ተናግረው በንብረት ላይ እና በተዘሩ ሰብል ከባድ ጉዳት መድረሱንም ተናግረዋል።

የክረምት ወቅት እንደመሆኑ መጠን ማህበረሰቡ ጥንቃቄ ከሚያስፈልጋቸው አንዱ የጎርፍ መፋሰሻ የሆኑ መሬቶችን በማፅዳት እና ከጎርፍ ማፋሰሻ ቦታዎች ላይ በመነሳት እራሳቸውን ከአደጋ እንዲጠብቁ አሳስበው ለሟች ቤተሰብ እና ለወረዳችን ህዝብ መፅናናትን ተመኝተውዋል።

"ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን" እንመኛለን፡፡

የክልል ከተሞችን ከአዲስ አበባ ጋር የሚያስተሳስሩ የፍጥነት መንገዶች! ~~~~~~~   አዲስ አበባ ከተማን ከተለያዩ የክልል ከተሞች ጋር የሚያስተሳስሩ 4 አዳዲስ የፍጥነት መንገዶችን ለመገን...
05/07/2025

የክልል ከተሞችን ከአዲስ አበባ ጋር የሚያስተሳስሩ የፍጥነት መንገዶች!
~~~~~~~
አዲስ አበባ ከተማን ከተለያዩ የክልል ከተሞች ጋር የሚያስተሳስሩ 4 አዳዲስ የፍጥነት መንገዶችን ለመገንባት የአዋጭነት ጥናት መጠናቀቁ ተገልጿል።

የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክቶቹ 2 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ናቸው።

👉ከእነዚህም መካከል፦

❶ አዲስ አበባ=> ደብረብርሃን=> ኮምቦልቻ=> ደሴ 352 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት፣

❷ አዲስአበባ=> ፍቼ=> ደብረ ማርቆስ 317 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገዶች ይገኙበታል።

ቀሪ ሁለት የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክቶች ደግሞ፦ አዲስ አበባ=> ወልቂጤ=> ጅማ እንዲሁም ከአዲስ አበባ=> ነቀምቴ ድረስ የሚገኘቡ ናቸው።

ለፍጥነት መንገድ ፕሮጀክቶቹ ግንባታ የሚያስፈልገው 10 ቢሊየን ዶላር ገደማ በመንግሥት፣ በግል አጋርነት እንዲሁም በዓለም አቀፍ የጨረታ ውድድር የሚሸፈን ይሆናል።

Beautifull Nature
19/06/2025

Beautifull Nature

አቶ መሸሻ ዘወልዴ ማናቸው?     በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ በመሐል ሜዳ ከተማ ደቦ የእርዳታ ማህበር የሚባል የትኩረት መስኩን የተማሪዎች አቅም ግንባታ ላይ ያደረገ መታሰቢያነቱ ለአቶ መሸሻ ...
19/06/2025

አቶ መሸሻ ዘወልዴ ማናቸው?
በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ በመሐል ሜዳ ከተማ ደቦ የእርዳታ ማህበር የሚባል የትኩረት መስኩን የተማሪዎች አቅም ግንባታ ላይ ያደረገ መታሰቢያነቱ ለአቶ መሸሻ ዘወልዴ የሆነ ደቦ የእርዳታ ማህበር የሚባል አንድ ድርጅት አለ፡፡ የዚህ ድርጅት ባለቤትና መስራች ዶ/ር አያልነሽ የፊታውራሪ መሸሻ ዘወልዴ የልጅ ልጅ የዶ/ር በለጠ መሸሻ ልጅ ናቸው፡፡
አቶ መሸሻ ዘወልዴ ትውልድ አገራቸው በድሮ አጠራር በመንዝና ግሼ አውራጃ ጌራ ምድር ወረዳ አፍተነት ቀበሌ ልዩ ስሙ ጨርጨር የሚባል ቦታ ሲሆን በጣሊያን ወረራ ወቅት መንዝ ካፈራቻቸው አርበኞች መካከል አንዱና ጣሊያንን ሲዋጉ ተማርክው ጣሊያን ሞቃድሾ ወስዶ አስሯቸው የነበሩ አርበኛ ነበሩ፤ ጣሊያን ከሞቃድሾ ለራሱ የውስጥ አርበኛ እንዲሆኑ ቢለቃቸውም እሳቸው ግን አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ጣሊያንን ከድተው በተጉለትና ቡልጋ ካሉ የሸዋ አርበኞች ጋር ተቀላቅለው ጣሊያንን በአርበኝነት ተዋግተዋል፡፡በመጨረሻም ጣሊያን ተሸንፎ ካገር ሲወጣ የፊታውራሪነት ማዕረግ ተሰጥቷቸው በድሮ አጠራር የይፋትና ጥሙጋ አውራጃን እስከ አፋር ድረስ አስተዳድረዋል በአውራጃ አስተዳዳሪነት ዘመናቸው ወደ ትውልድ አገራቸው መንዝ ሲመጡ በጦርነቱ ምክንያት የመንዝ ህዝብ የቤት እስሳውን በመዘረፉና እንስሳው ስለሞተበት የቤት እንስሳት አልባ ሆኖ ስላገኙት የይፋትና የአፋር ህዝብን በማወያየት የቤት እንስሳትን በማሰባሰብ በርካታ ከብቶች ፣በግና ፍየል አስመጥተው አከፋፍለዋል፡፡
አቶ መሸሻ ዘወልዴ እስከ ህይወታቸው ፍፃሜ አዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ ይኖሩ የነበረ ሲሆን የህይወታቸው ፍፃሜ ሲቃረብ ለልጆቻቸውና ለልጅ ልጆቻቸው መንዝ አፍተነት ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን ወስደው እንዲቀብሯቸው ባሳለፉት የኑዛዜ ቃል መሰረት ካረፉ በኋላ መንዝ አፍተነት ቂርቆስ ቤተክርስቲያን መጥተው እንዲቀበሩ ተደርጓል፤ የቀብራቸውን ስነስርአት ለማስጸም ከመሃል ሜዳ ወደ አፍትነት ቂርቆስ ቤተ ክርሰቲያን በሚደረገው ጉዞ የመንዝና ግሼ ህዝብ የት ቀረህ ሳይባል ከመሃል ሜዳ ሳይነቅል አፍተነት ቂርቆስ ድረስ ማለትም በትንሹ 10 ኪሎ ሜትር የገታ የህዝብ ቁጥር የጀግናውንና የባለ ውለታውን የአቶ መሸሻ ዘወልዴን አሰከሬን ለመሸኘት በአገሬው ባህልና ወግ መሰረት ወንዱና አርበኛው ሰልፉን እያሳመረ እየሸለለና እየፎከረ ሴቱ ለምደኛውን ስፍቶ እሟሽሸና እያዘነ ስርአተ ቀብሩን አስፈጽሟል በወቅቱ በሙሾ ከተባለላቸው ለመጥቀስ ያክል በ1885ዓ.ም ብርሃን ወረደ መሸሻ ዘወልዴ ጨርጨር ተወለደ፤ የሚለው ይገኝበታል፡፡
አቶ መሸሻ ዘወልዴ ስርአተ ቀብራቸው ትውልድ ቀዬአቸው እንዲሆን ያደረጉበት ምክንያት ለመንዝ ህዝብ ያላቸውን ፍቅር እና አክብሮት ለመግለጽና ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ከመንዝ ህዝብ እዳይነጠሉ በህይወት ዘመናቸው የነበራቸውን ፍላጎትና ህልም እውን ለማድረግ እንደሆነ የቅርብ ወዳጆቻቸው ያስረዳሉ፡፡ይህም ህልማቸውና ፍላጎታቸው እውን ሆኖ በልጅ ልጃቸው በዶ/ር አያልነሽ በለጠ መስራችና አስተባባሪነት ዛሬ በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ መሐል ሜዳ ከተማ ደቦ እርዳታ ማህበር ትኩረቱን በተማሪዎች አቅም ግንባታ ላይ ያተኮረ ማዕከል ተቋቁሞ ለአካባቢው ወጣቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
መንዝ ከእኝህ ታላቅ አርበኛ በተጨማሪ በርካታ አርበኞችን ያፈራች አገር ናት በቀጣይ ሌሎች የመንዝ አርበኞች ታሪክን ይዘንላችሁ እንቀርባለን ይህን ታሪክ ያወጉንን የዘወትር የታሪክ ምንጭ በመሆን እያገለገሉን ያሉትን የቀድሞውን የመሃል ሜዳ ከተማ ከንቲባ አቶ ተሰማን ከበደና የቀድሞ የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳምጠው ልዑል ሰገድን ከልብ እናመሰግናለን አዲሱ ትውልድም በተሰለፈበት የስራና የሙያ ዘርፍ የአቶ መሸሻ ዘወልዴን ታሪክ አንዲደግም ጥሪያችንን እያስተላለፍን በዚህ አጭር ታሪክ ላይ አስተያየትና እርማት ካላቸሁ ለመቀበልና ለማረም ዝግጁ ነን፡፡ ከወደዳችሁት ሼርና ላይክ አድረጉት አዘጋጅ ጌትነት አጎናፍር
የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

20/05/2025

መሐል ሜዳ ከተማ ላይ 250 ካሬ በሊዝ የተሸነፈ ባዶ ቦታ አለ
አስቸኳይ በጣም በርካሽ ዋጋ ቀርቧል።
ቀበሌ 4 ጤና ጣቢያ
የለማ ሰፈር ላይ ያለ
0941895265
ይደዉሉ

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ይፋት ወ መንዝ /Yifat & Menz posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share