KASMA Ethiopia

KASMA Ethiopia We are Ethiopia's first survivor led organization based in Addis Ababa. It is the first survivor-led organization in Ethiopia.

Our mission aims to use returnees as change agents to MOBILIZE resources, ADVOCATE for system change, and EMPOWER women to lead in the frontlines to end modern slavery. KASMA Charity Organization is a non-profit, nonpartisan, and nongovernmental local organization based in Addis Ababa, Ethiopia. It was established in November 2021 by fourteen founding members who returned from the Middle East. KASMA exists to contribute to the efforts of the government and anti-trafficking organizations in Ethiopia by advocating for stronger anti-trafficking policies and laws, providing services and support for survivors of trafficking, and developing long-term strategies to end human trafficking in Ethiopia.

06/10/2026

"በሳምንት ውስጥ አረብ ሀገር እንልካለን!" — ከዚህ የማታለያ ወጥመድ እራስዎን ይጠብቁ! 🛑⚠️

ደላሎች "በፍጥነት እና በቀላሉ ህይወታችሁን ትለውጣላችሁ" እያሉ የብዙ ወጣቶችን ህይወት ለቁማር ይዳርጋሉ። እውነታው ግን ህገ-ወጥ ፍልሰት ለሰው በላ ደላሎች ትርፍ እንጂ፣ ለተጓዡ ወጣት ውርደትን፣ ስቃይንና ሞትን ነው የሚያተርፈው።

በካስማ በጎ አድራጎት ድርጅት (በስደት ውስጥ ባለፉ ባለታሪኮች የተመሰረተ ተቋም)፣ መልዕክታችን ግልጽ ነው፦
✅ ህጋዊ የፍልሰት መንገዶችን ለዩ!
✅ እውቀትና ሙያ ሳይኖራችሁ አትነሱ!
✅ በሀገራችሁም ሰርቶ የመለወጥ በርካታ አማራጮች እንዳሉ እወቁ!

ህይወት አንድ ናት፤ ለደላላ የውሸት ተስፋ አትስጧት። ይህንን ወሳኝ መልዕክት ለቤተሰብዎ እና ለወዳጅዎ SHARE በማድረግ የሰው ህይወት ይታደጉ! 🙏🏾

"We will send you abroad in a week!" Don't fall into the broker's trap! 🛑⚠️

Illegal brokers prey on desperation with quick promises of visas and wealth. But irregular migration only enriches traffickers while costing our youth their safety, dignity, and lives.

Learn the truth from lived experience. Kasma Charity Organization urges everyone to choose legal pathways and explore local livelihood opportunities.

Protect your life and your future. Please SHARE this video to save a life today! 🇪🇹✨

#የስራእድል #ፍልሰት

03/10/2026

ህገ-ወጥ ፍልሰት ብቸኛው አማራጭ ነው ያለው ማነው? ❌

26/09/2026

"የማይታይ ቁስል ከሚታየው በላይ ያማል።" 🩹

ስደት የሚተወው ጠባሳ በቆዳ ላይ ብቻ አይደለም፤ በነፍስ፣ በሐሳብ እና በስሜት ላይ የሚያርፈው ስብራት ይበልጥ የከፋ ነው።

ብዙ ወገኖቻችን ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ቤተሰብ እና ማህበረሰብ የሚጠብቀው ቁሳዊ ስኬትን ብቻ ነው። ነገር ግን በውስጣቸው
የተሸከሙትን የጭንቀት፣ የፍርሃት እና የድካም ሸክም የሚያስተውልላቸው ጥቂት ነው።

ካስማ Organizational Charity ዘንድ ስትመጡ ትልቁ ተልዕኳችን ስራ ማስተማር ብቻ አይደለም፤ መጀመሪያ የተሰበረውን
ልብ ማዳመጥ እና መፈወስ ነው።

እባካችሁ ዝም አትበሉ፤ ማውራት፣ ስሜትን ማጋራት እና ህክምና ማግኘት ድክመት አይደለም። ራስን ከአእምሮ ስብራት ማዳን ከሁሉ የላቀ
ጀግንነት ነው።

ውድ ተመላሾች፣ ብቸኝነት በፍጹም አይሰማችሁ። እኛ ካስማዎች ሁሌም ከጎናችሁ አለንላችሁ።

📞 እርዳታ፣ ማማከር ወይም መጽናናት የምትፈልጉ ወገኖች በሙሉ በውስጥ መስመራችን አሊያም በቢሮአችን በኩል በነፃነት
እንድታናግሩን ጥሪያችንን እናቀርባለን። ይሄ መልዕክት እንዲደርሳቸው ለምትፈልጓቸው ወገኖች ሼር በማድረግ የፈውስ አካል ይሁኑ።

በሀገራዊ የፍልሰት ፖሊሲ ላይ የባለታሪኮችን ድምፅ ማስተጋባት! 🇪🇹🌍መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም (September 17, 2026)፣ የካስማ በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች እና ዋና ስራ አስ...
23/09/2026

በሀገራዊ የፍልሰት ፖሊሲ ላይ የባለታሪኮችን ድምፅ ማስተጋባት! 🇪🇹🌍

መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም (September 17, 2026)፣ የካስማ በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ የኔነሽ ጥላሁን በብሔራዊ የትብብር ጥምረት (NPC) እና በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM Ethiopia) በተዘጋጀው የመጀመሪያው ረቂቅ የዓለም አቀፉ የስደት ስምምነት (GCM) ብሔራዊ አፈፃፀም ዕቅድ (2026–2029) የምክክር መድረክ ላይ ተሳትፈዋል።
በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ የተካሄደው ይህ ከፍተኛ መድረክ፤ መንግስታዊ ተቋማትን፣ የሲቪል ማህበራትንና ባለድርሻ አካላትን በማሰባሰብ በቀጣዮቹ 4 ዓመታት የኢትዮጵያን የስደት አስተዳደር በሚመሩ 5 ዋና ዋና የትኩረት መስኮች ላይ መክሯል።
ካስማ በባለታሪኮች የሚመራ ድርጅት እንደመሆኑ፤ ማንኛውም ሀገራዊ የስደት ፖሊሲና አሰራር በስደት ውስጥ ያለፉ ወገኖችን ድምፅና እውነተኛ ተሞክሮ ማካተት እንዳለበት በጽኑ ያምናል። የባለታሪኮች ተሳትፎ ሲኖር ህጎች ተግባራዊ፣ ተቋማት ተደራሽ፣ የተመላሾች ማቋቋም ስራም ዘላቂ ይሆናል!
ለዚህ ሁሉን አቀፍ ውይይት ለብሔራዊ የትብብር ጥምረት፣ ለ IOM Ethiopia እና ለአውሮፓ ህብረት ምስጋናችንን እናቀርባለን።

Shaping Inclusive Migration Governance in Ethiopia! 🇪🇹🌍

On 17 September 2026, Kasma Charity Organization's Executive Director, Yenenesh Tilahun, participated in the high-level consultation on Ethiopia’s first draft Global Compact for Migration (GCM) National Implementation Plan (2026–2029), presented by the National Partnership Coalition (NPC) in collaboration with IOM Ethiopia and funded by the European Union.
As a survivor-led organization, Kasma emphasizes that genuine migration governance must place the lived experiences of returnees and survivors at the heart of policy design.
We thank the NPC, IOM Ethiopia, and the EU for ensuring broad civil society participation in shaping the country's migration agenda!

#ፍልሰት #ካስማ #ኢትዮጵያ

መንገድ ከመውጣት በፊት (Before the Journey)"ጉዞዎች ሁሌም ቢሆን በእግር አይጀመሩም። አንዳንዱ በሃሳብ፣ በተስፋ... ነገ እቀየራለሁ በማለት፣ በቤተሰብ ግፊት ይጀመራል... ግን ...
17/09/2026

መንገድ ከመውጣት በፊት (Before the Journey)

"ጉዞዎች ሁሌም ቢሆን በእግር አይጀመሩም። አንዳንዱ በሃሳብ፣ በተስፋ... ነገ እቀየራለሁ በማለት፣ በቤተሰብ ግፊት ይጀመራል... ግን ከመሄዳችን በፊት ማን ስለ መንገዱ ይነግረናል?" 💔

በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ተሸላሚ የሆነው አጭር ዶክመንተሪ ፊልማችን!
⚠️ ከመወሰናችን በፊት ማወቅ ያለብን መራራ እውነቶች ምንድን ናቸው?
🔴 ሙሉውን ቪዲዮ አሁኑኑ በ YouTube ቻናላችን (KASMA ETHIOPIA) ይመልከቱ!

https://youtu.be/FiYn9RpbB0w

"ጉዞዎች ሁሌም ቢሆን በእግር አይጀመሩም። አንዳንዱ በሃሳብ፣ በተስፋ... ነገ እቀየራለሁ በማለት፣ በቤተሰ...

እንኳን ለ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! 🌼✨ክረምቱ ተሰናብቶ በምድራችን ላይ ቢጫው የአደይ አበባ ሲፈካ፣ በካስማ በጎ አድራጎት ድርጅት (Kasma Ch...
11/09/2026

እንኳን ለ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! 🌼✨

ክረምቱ ተሰናብቶ በምድራችን ላይ ቢጫው የአደይ አበባ ሲፈካ፣ በካስማ በጎ አድራጎት ድርጅት (Kasma Charity Organization) አዲስ ተስፋንና አዲስ ራዕይን ሰንቀን አዲሱን ዓመት እንቀበላለን።
በ14 ከስደትና ፍልሰት ተመላሽ ባለታሪኮች የተመሰረተው ተቋማችን፣ አዲሱ ዓመት ለተመላሽ እህትና ወንድሞቻችን የፈውስ፣ የክብር እና የታደሰ ህይወት እንዲሆንላቸው ከልብ ይመኛል!
ባለፈው ዓመት ከጎናችን ለነበራችሁ ውድ አጋሮቻችን፣ ለጋሾች፣ እና መላው የካስማ ቤተሰቦች ምስጋናችን የላቀ ነው።

አዲሱ 2019 ዓ.ም፦
🌼 የሰላም እና የፍቅር፣
🌼 የተሰበረው የሚጠገንበት፣
🌼 በሀገራችን ሰርተን የምንለወጥበት የተባረከ ዘመን ይሁንልን!

መልካም አዲስ ዓመት! 💚💛❤️

#እንቁጣጣሽ #አዲስዓመት #ካስማ #ኢትዮጵያ #ተስፋ

08/09/2026

አዲስ ምዕራፍ፣ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ ጅምር! 🌼✨

ያለፈው ዓመት ያስተማረን ትልቁ እውነት ቢኖር፤ በአንድነት ስንቆም የማይሻገሩት ፈተና፣ የማይጠገን ስብራት እንደሌለ ነው።

ካስማ በጎ አድራጎት ድርጅት (Kasma Charity Organization) በባለታሪኮች የተመሰረተ ተቋም እንደመሆኑ፤ በአዲሱ ዓመትም ከስደትና ፍልሰት ተመላሽ የሆኑ እህትና ወንድሞቻችንን በስነ-ልቦና፣ በክህሎት እና በኢኮኖሚ በማብቃት ለተሻለ ህይወት የሚያደርጉትን ጥረት በቁርጠኝነት ይደግፋል።

ባለፈው ዓመት ከጎናችን ለነበራችሁ አጋሮቻችን፣ ለጋሾች፣ በጎ ፈቃደኞች እና መላው ቤተሰቦቻችን ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳችሁ! አብሮነታችን ለብዙዎች የተስፋ ካስማ (ምሰሶ) ሆኖ ቀጥሏል።

አዲሱ ዓመት፦
🌼 የሰላም እና የፍቅር፣
🌼 የተሰበረው የሚጠገንበትና ህልሞች እውን የሚሆኑበት፣
🌼 በሀገራችን ሰርተን የምንለወጥበት የተባረከ ዘመን ይሁንልን!

መልካም አዲስ ዓመት! 💚💛❤️

A New Chapter of Hope & Resilience! 🌼✨

As we welcome the Ethiopian New Year, we reflect on a simple yet powerful truth: when we stand united, no hardship is insurmountable.

At Kasma Charity Organization, our survivor-led mission remains stronger than ever. In this New Year, we reaffirm our commitment to empowering returnees through psychosocial support, market-ready skills, and dignified employment.

To our incredible partners, donors, volunteers, and community: thank you for being the pillar of hope alongside us.

May this New Year bring lasting peace, renewed hope, and prosperity to Ethiopia and all our communities!

Melkam Enkutatash! 🇪🇹

#ካስማ #አዲስዓመት #እንቁጣጣሽ #ተስፋ #ፍልሰት #ኢትዮጵያ

02/09/2026

"ከመፍረድ በፊት ያሳለፈችውን ስቃይ እወቁ!" 🛑 ለዓመታት የሰውን ጫና ተሸክመው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ፍቅር እና እረፍት ለሚፈልጉ እህቶቻችን ከለላ እንሁን።

29/08/2026

"ስልጠና ብቻውን በቂ አይደለም፤ አእምሮም መገንባት አለበት!" 🧠✨

የካስማ በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች ወ/ሮ የኔነሽ፣ "Thrive" በተባለው ፕሮጀክት ላይ ካስማ ከ 'HOPE Enterprise' ጋር በመሆን እንዴት ከስደት ተመላሾችን እያገዘ እንደሆነ ታስረዳለች።

የእኛ ትልቁ ስራ የሙያ ስልጠናውን ከ የአቻ ለአቻ ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ (Peer Support) ጋር ማስተሳሰር ነው። ምክንያቱም እኛ ራሳችን ያንን ህመም ስላሳለፍነው፣ እንዴት ማለፍ እንዳለባቸው ጠንቅቀን እናውቃለን!
ተስፋን በጋራ እንገንባ! 🤝🇪🇹

ከሙያ ስልጠና ባሻገር፡ የውስጥ ጥንካሬን መገንባት! 🛠️❤️ከስደት ለተመለሱ እህትና ወንድሞቻችን የሙያ ስልጠና መስጠት ወሳኝ ነው፤ ነገር ግን ስኬታማ እና ዘላቂ እንዲሆን የስነ-ልቦና ድጋፍ ...
25/08/2026

ከሙያ ስልጠና ባሻገር፡ የውስጥ ጥንካሬን መገንባት! 🛠️❤️

ከስደት ለተመለሱ እህትና ወንድሞቻችን የሙያ ስልጠና መስጠት ወሳኝ ነው፤ ነገር ግን ስኬታማ እና ዘላቂ እንዲሆን የስነ-ልቦና ድጋፍ አይነተኛ ሚና ይጫወታል።

በቅርቡ ከተስፋ ድርጅት (HOPE Enterprise) ጋር በመተባበር ባስመረቅናቸው ተማሪዎች ጀርባ ያለው ትልቁ ሚስጥር የካስማ የአቻ ለአቻ ድጋፍ (Peer Support) ፕሮግራም ነው።

በነዚህ ስልጠናዎች ላይ፣ ተመላሾች፡
✅ ያሳለፉትን ጫና ያለፍርሃት ይጋራሉ
✅ አንዱ ለሌላው የጥንካሬ ምንጭ ይሆናል
✅ ወደ ስራ አለም ለመግባት የሚያስፈልጋቸውን በራስ መተማመን ይገነባሉ

እኛ በካስማ (በባለታሪኮች የምንመራ ድርጅት)፣ ይህንን ስልጠና የምንሰጠው ከተሞክሮ በመነሳት ነው። ምክንያቱም ህመሙን የሚያውቅ፣ ፈውሱንም ያውቃል! ✨

#ካስማ #የስነልቦናድጋፍ

Address

Bole Sub-city, Wereda 05, Ras Lulseged Street Near Ministry Of Revenue, Bawdutch Building, 2nd Floo
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when KASMA Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to KASMA Ethiopia:

Shortcuts

Share