18/09/2026
የቅማንት ልማት ማህበር 14ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ
==================++++++++++++++++
መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም. ቅማንት ልማት ማህበር 13ኛ ዓመት 14ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በጎንደር ከተማ በሃይሌ ሪዞርት አካሂዷል።
በጉባኤው የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ኪዴ በኩል በዝርዝር ቀርቦ የተገምግሞ ሲሆን፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ እንዲሁ በዝርዝር ቀርቦ ተገምግሞ ጸድቋል፣ የቀጣይ የማህበሩ የሥራ አቅጣጫዎችም በግልጽ የተቀመጠበት ሲሆን የማህበሩ አመታዊ የአባላት ክፍያ መጠንም እዲሻሻል ተደርጓል።
የ2019 ዓ.ም. ዋና ዋና ዕቅዶች
=====================
🔹 በጭልጋ ወረዳ የጤና ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክት ማስጀመር።
🔹 በላይ አርማጭሆ ወረዳ የትምህርት ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ማስጀመር።
🔹 የቅማንትን ህዝብ ባህልና ቋንቋ ለመጠበቅ፣ ለማሳደግና ለማስተዋወቅ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት።
🔹 በጭልጋ ወረዳ በዝጅብል ምርት ላይ የምርምርና ጥናት ሥራ ማካሄድ።
🔹 በጭልጋና በላይ አርማጭሆ ወረዳዎች ለሚገኙ አዳሪ ተማሪዎች የሚደረገውን ድጋፍ ማጠናከርና ማስቀጠል።
🔹 የሰብዓዊ ድጋፍና ርዳታ ሥራዎችን ማጠናከርና ማስቀጠል።
🔹 ከእነዚህ በተጨማሪ የማህበሩን ዓላማዎች ለማሳካት የሚያስችሉ ሌሎች የልማትና የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎችን ማከናወን።
የአባላትና የማህበረሰቡ ተሳትፎ ለእነዚህ ዕቅዶች ተግባራዊነት ሚናው የላቀ ሲሆን፣ ቅልማ ከአባላቱ 33.2 ሚሊዮን ብር በመሰብሰብ፣ ማህበረሰቡም በጉልበት፣ በቁሳቁስ እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ 9.5 ሚሊዮን ብር በማበርከት እነዚህን የልማትና የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎች በተግባር ለማሳካት ታቅዷል።
በጉባኤው ላይ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አወቀ አሰፋሬ ተገኝተው፣ ቅልማን በቁርጠኝነት እንደሚደግፉና ከዛሬ ጀምሮ የማህበሩ አባል ሆነው አመታዊ የአባላት ክፍያ የከፈሉ ሲሆን የጉባኤውን ትርጉም የበለጠ አጉልቶታል።
ያለፈውን በመገምገም፣ ዛሬን በማጠናከር፣ ነገን በጋራ በማቀድ—ለልማታችን በቁርጠኝነት እንስራ!
#ልማታችን የጋራ ራዕያችን ነው‼️
ቅልማን በመደገፍ ለልማት እንሰለፍ! 🤝