kasma charity organization

kasma charity organization Ethiopia free from human trafficking!
ከህገወጥ የሰዎች ዝውውር የፀዳች ኢትዮጵያ

የችግኝ ተከላ     ዛሬ በቀን 30/11/2016 የካስማ በጎ አድራጎት ድርጅት ከኦሮሚያ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመሆን ከአዲስ አበባ ውጪ በዱከም በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የዱከ...
06/08/2024

የችግኝ ተከላ
ዛሬ በቀን 30/11/2016 የካስማ በጎ አድራጎት ድርጅት ከኦሮሚያ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመሆን ከአዲስ አበባ ውጪ በዱከም በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የዱከም ክ/ከተማ ኩማ ኢደኤ የህዝብ መፅሐፍት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ችግኞችን ተክለናል
➨TikTok
https://www.tiktok.com/.charity.org?_t=8ocUo4IpO0g&_r=1

➨facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=100090470217630&mibextid=ZbWKwL

ካስማዎች ነን ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ዘመናዊ ባርነት  እንዲሁም ደህንነቱ ያልተጠበቀ ፍልሰት ላይ እንሰራለን ።    አንድ ወቅት በተለያየ ምክንያት በሰው ሀገር አካላዊ, ስነ-ልቦናዊ ...
18/03/2024

ካስማዎች ነን ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ዘመናዊ ባርነት እንዲሁም ደህንነቱ ያልተጠበቀ ፍልሰት ላይ እንሰራለን ።
አንድ ወቅት በተለያየ ምክንያት በሰው ሀገር አካላዊ, ስነ-ልቦናዊ ፣አምሮአዊ ብሎም ሞራልን የሚጎዳ ነገር ገጥሞን ነበር ዛሬ ግን በሀገራችን ላይ እህት ወንድሞቻችን እኛ ያለፍንበትን መንገድ እንዳያልፉበት ድምፃችንን እናሰማለን ተሞክሮአችንን እናካፍላለን ፣መንግስት የፖሊስ ለዎጦችን ማሻሻልን እንዲያደርግ እንናገራለን ፣ማህበረሰቡ ለፍልሰት ተመላሾች ተገቢውን ትኩረትና እውቅና እንዲሰጥ እንጥራለን ፣ባለሃብቶች የተሻለ ስራንና ክፍያን ለሰራተኞቹ እንዲሰጥ እንወተውታለን …………
ሰዎች ሀገር ውስጥ እንዲሰሩና እንዲኖሩ እናበረታታለን ነገር ግን ፍልሰት መብት በመሆኑ ከቦታ ቦታ ሲቀሳቀሱ በመረጃ ላይ የተመሰረተ እንዲያደርጉ አደራ እንላለን ።
ካስማ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከህገወጥ የሰዎች ዝውውር የፀዳች ኢትዮጲያን ማየት ነው ዕራዩ ።
በተለያየ ሀገር የሚኖሩ ሴቶች የሀገር ባለውለታዎች ናቸው ።
ለዚህም ስራችን የህግ አካላት ኩራቶቻችንና አጋሮቻችን ናቸው እናመሰግናለን፡፡

በቢሮው በሰው መነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ።።።።።።።።።።።ግምገማው  የማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ...
09/02/2024

በቢሮው በሰው መነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ።
።።።።።።።።።።
ግምገማው የማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ኃላፊ እና ዐቃቢያነ ሕግ ፣ የክፍለ ከተማ እና የከተማ የትብብር ጥምረት አባላት እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ አጋርድር ድርጅቶች በተገኙበት በህይወት ኢትዮጵያ አስተባባሪነት በሳሬም ሆቴል ተካሂዷል።
በወቅቱ የማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ን ጨምሮ የግንዛቤ ፈጠራና የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ፣ተጎጂዎችን መልሶ ማቋቋም የስራ ቡድን፣ የህዝብ አደረጃጀት ተወካይ ከሴት መሀበር እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የግማሽ አመት አፈጻጸማቸውን አቅርበዋል።
የማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ታደሰ ፈይሳ በመክፈቻ ንግግራቸው የዕቅድ አፈጻጸምን ወቅቱን ጠብቆ መገምገም ስራዎች ምንደረጀ ላይ እንዳሉ ለመለየት እና ቅድሚያ የሚጠውን በመለየት ከቀሪ የስራ ወራቶች ጋር ማጣጣም ያስችል ዘንድ ነው ብለዋል።
የጽ/ቤት ሀላፊው አክለው በሰው መነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል እጅግ እየከፋ እና እየረቀቀ መምጣቱን በመግለጽ ጽ/ቤታቸው ሁሉም ባለድርሻ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።
የማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ በስድስት ወራት ውስጥ ካከናወናቸው ተግባራት መካከል የግንዛቤ ፈጠራ ስራ፣ ወንጀሉን ለመከላከል ከፖሊስ አካላት ጋር በመቀናጀት የወንጀል ምርመራውን በማገዝ ጥቆማዎችን በመስጠ ስራዎችን እርምጃዎችን የማስወሰድ ስራዎች መሰራታቸውን ፣ ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም እና ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ የማስተባበር ስራዎች መሰራታቸውን እና የትብብር ጥምረት አደረጃጀት የማጠናከር ስራ መሰራቱ የማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ዐቃቤ ሕግ አቶ ነብዩ በቀለ በሪፖርቱ አቅርበዋል።
በወቅቱ ከተሳታፊው የተሰጠው አስተያየት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ እቅዶችንም ሆነ አፈጻጸሞችን ትኩረት በመስጠት በወቅቱ በመገምገም አስፈላጊና ጊዜውን የዋጀ የስራ አቅጣጫ መስጠቱ እጅግ የሚያስመሰግነው እና ለሌሎችም አስተማሪ የሚሆን ነው በማለት ከተጠሪ ተቋማት እና ባለድርሻ አካላትም ጋር ያለው አሳታፊነት ጥብቅ መሆኑ ጽ/ቤቱ ለስራው የሰጠውን ትኩረት ያመላክታል ብለዋል።
በመጨረሻም ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ የ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወር የተከለሰ ዕቅዱን በማቅረብ አወያይቷል።

ካስማ የበጎ አድራጎት ድርጅት የገናን በዓልን ከተለያዩ በተመላሽ ፍልሰተኞች የተመሰረቱ ድርጅቶች እና በፍልሰት ዙሪያ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር አክብረን ነበር    ሀንቴድ ስቱደዲ...
25/01/2024

ካስማ የበጎ አድራጎት ድርጅት የገናን በዓልን ከተለያዩ በተመላሽ ፍልሰተኞች የተመሰረቱ ድርጅቶች እና በፍልሰት ዙሪያ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር አክብረን ነበር
ሀንቴድ ስቱደዲዪ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በመተባበር በጥሩ ሁኔታ ከሽኖት ፕሮግራሙ ቀርቦ ነበር

በ28/3/2016 Intranational  Migerants day 2023  ለ18ጊዜ  ቦሌ ኦሎምፕያበግሪክ ክለብ በIom አዘጋጅነት  በተደረገው  ባዛር ላይ ተመላሾች ስለምሠራቸው ሥራዎች  ገለ...
08/12/2023

በ28/3/2016 Intranational Migerants day 2023 ለ18ጊዜ ቦሌ ኦሎምፕያበግሪክ ክለብ በIom አዘጋጅነት በተደረገው ባዛር ላይ ተመላሾች ስለምሠራቸው ሥራዎች ገለፃ ያደረጉ አና ምርቶቻቸውን የሸጡበት ዝግጅት ነበር ።
ዋና ዓላማው ; ተመላሾች በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንድችሉ ለሌሎችም ተመላሾች ዓርአያ መሆናቸውን ማሳያ ነው።
በዚሁ ዝግጅት ላይ የተለያዬ የውጭ ዜጎች ተገኝተው አድናቆታቸውን ገልፀዋል ።
በካስማ በኩል የቀረበውም ምርት በመግዛት ትብብራቸውን ገልፀውልናል

ካስማ በጎ አድርጎት ድሮጅት ባገኘው ዕድል ራሱን ያስተዋወቀበት መድረክ ሲሆን ለቀጣይ ሥራዎቹ መልካም ዕድል እንደሆነለት ያምናል።
መልካም የሥራ ዘመን ተመኘን!!!!

ቀን 21/03/2016 ዓ.ም ካስማ፤ፍኖት፤ብሩህ አዲስ እና ምሳሌ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ከኢትዮጲያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡    የበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ ስደተኞችን...
07/12/2023

ቀን 21/03/2016 ዓ.ም
ካስማ፤ፍኖት፤ብሩህ አዲስ እና ምሳሌ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ከኢትዮጲያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡
የበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ ስደተኞችን እና ከስደት ተመላሾችን በተመለከተ የተለያዩ ስራዎችን የሚሰሩ ሲሆን ሁሉም ድርጅቶች ከስደት ተመላሽ በሆኑ ዜጎች የተቋቋሙ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በመንግስት የተቋቋመ ገለልተኛ ተቋም ሲሆን የኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን ለማቋቋም በወጣ አዋጅ ቁጥር 210/2000 እና በማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1224/2020 የተቋቋመ ለሰብአዊ መብቶች መከበር የሚሰራ ተቋም ነው፡፡ በኮሚሽኑ የስደተኞች፤ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ፍልሰተኞች የስራ ክፍል (Department) ባልደረባ የሆኑ የኮሚሽኑ ሰራተኞች በካስማ የበጎ አድራጎት ድርጅት ቢሮ ተገኝተው የአራቱ በጎ አድራጎት ድርጅት ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ጠቃሚ ውይይት አከናውነዋል፡፡ ተቋሙ ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል የተለያዩ ሰብአዊ መብቶችን ተፈፃሚነት በሚመለከት የተለያዩ ምርመራዎችን በማከናወን ሪፖርቶችን በማዘጋጀት የሚመለከታቸው አካላት የማስተካከያ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ምክረ ሃሳቦችን ማቅረብ ይገኝበታል፡፡
ውይይቱ ያተኮረው ድርጅቶቹ ስለሚሰሩዋቸው ስራዎች፤ ህገ ወጥ የሰዎች ስደትን እና የውጪ ሀገር የስራ ስምሪትን በተመለከተ በሚሰሩ ስራዎች ላይ ስለሚስተዋሉ ተግዳሮቶች ላይ ነበር፡፡
የውጪ ሀገር የስራ ስምሪትን በተመለከተ ተሳታፊዎቹ የሚከተሉትን ሃሳቦች አንስተዋል፡፡
 የኢትዮጲያ የውጪ ሀገር የስራ ስምሪትን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ዜጎች ወደ ውጪ ሀገራት ለቤት ውስጥ ስራ ለመሄድ በሚቀጠሩበት የስራ መስክ ስልጠና ወስደው አግባብ ካላው የምዘና ማእከል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ሊኖራቸው እንደሚገባ ያመለክታል፡፡ ነገር ግን አሁን በስራ ላይ ባለው የሙያ ስልጠና የተለያዩ ችግሮች እየተስተዋሉ መሆኑ ተነስቷል፡፡ ለአብነት ያህልም የሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት በተለይም ራቅ ባሉ የሀገራችን ክፍሎች ለሚገኙ ሄጎች ተደራሽ አለመሆን፤በአስፈላጊው ግብአት አለመሟለት እና የሙያ ማረጋገጫ ማስረጃው ለዜጎች አግባብ ባልሆነ መንገድ ወይንም ስልጠናውን ሳይወስዱ የሚሰጥበት ሁኔታ መኖሩ ተጠቃሽ ነው፡፡ ይህ አይነቱ አሰራር በትምህርት ማስረጃዎች ላይም የሚስተዋል መሆኑ በመድረኩ ተነስቷል፡፡
 ሌላው ከውጪ ሀገር የስራ ስምሪት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ችግር ወደ ውጪ ሀገር ለሚሄዱ ዜጎች ስለሚሄዱበት ሀገር አኗኗር፤ባህል እና ስለአጠቃላይ ሁኔታው የሚሰጠው መግለጫ በቂ አለመሆን ነው፡፡ አንደሚታወቀው ዜጎች ወደ ውጪ ሀገራት ለስራ በሚሄዱበት ወቅት ከሚወስዱት የሙያ ስልጠና በተጨማሪ ስለመዳረሻ ሀገራቱ ነባራዊ ሁኔታ እና ስራ ላይ ሊያጋጥሙዋቸው ስለሚችሉ ጉዳዮች በቂ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ ለዜጎች የሚሰጠው ስልጠና በዚህ ረገድ በቂ የሚባል አይደለም፡፡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ ከስደት ተመላሽ በሆኑ ዜጎች የተቋቋሙ መሆናቸው እንደዚህ አይነት ስልጠናዎችን እንዲሰጡ በመንግስት በኩል እድሉ ቢመቻች በተሻለ ሁኔታና ሄጎችን በሚጠቅም መልኩ ስልጠናውን መስጠት እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡

 በአጠቃላይ የውጪ ሀገር የስራ ስምሪትን በተመለከተ ምንም እንኳን የህግ ማእቀፍ የወጣለት ቢሆንም ከአፈፃፀም አንፃር ብዙ ክፍተቶች የሚስተዋሉ ሲሆን በቀጣይ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ለተፈፃሚነቱ በአትኩሮት መሰራት እንደሚገባው አንስተዋል
ህገ-ወጥ የሰዎች ስደትን በተመለከተ

 መንግስት ለህገ-ወጥ ስደት መነሻ የሆኑ ገፊ ምክንያቶች ላይ ትኩረት በመስጠት መስራት እንደሚገባው ተመላክቷል፡፡

 ህገ-ወጥ የሰዎች ስደትን በተመለከተ ድርጊቱ ተፈፅሞ ከተገኘ ቡሃላ አጥፊዎች ላይ አርምጃዎችን ከመውሰድ ይልቅ አንደዚህ አይነት ወንጀሎች ከመፈፀማቸው በፊት የመከላከሉ ተግባር ቅድሚያ ቢሰጠው የሚል ሃሳብ ተንፀባርቋል፡፡
ከስደት ተመላሽ ዜጎችን በተመለከተ
 ከስደት ተመላሽ ዜጎችን በተመለከተ የሚሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑ በተሳታፊዎች ተነስቷል፡፡ በተለይም ከአረብ ሀገር ተመላሽ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሰጠው ድጋፍ እጅጉን አናሳ የሚባል ሲሆን አነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች ለቤተሰቦቻቸው ብሎም ለሀገር ካበረከቱት በጎ አስተዋፅኦ አንፃር ከስደት ተመላሽ ሆነው በሚቀርቡበት ወቅት በማህበረሰቡም ሆነ በመንግስት የሚሰጣቸው ቦታ እጅጉን የሚያሳዝን መሆኑ ተመላክቷል፡፡

 በተለይም ለተለያየ አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት ተጋልጠው ከስደት በተለይም ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚመለሱ ስደተኞችን በማቆያዎች ከማስቀመጥ ይልቅ የተለያዩ ሙያዎችን እንዲያገኙ እና ድጋፍ ተደርጎላቸው ራሳቸውን በሚችሉበት የስራ ዘርፍ እንዲሰማሩ የሚያስችላቸውን ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተነስቷል፡፡
በአጠቃላይ ዜጎች በሀገራቸው ሰርተው የሚለወጡበት እድል ቢመቻች የተሸለ እንደሆነ እና ይህ ባልሆነበት ግን ዜጎች ወደ ውጪ ሀገራት ወደ ስራ በሚሄዱበት ወቅት በቂ የሆነ ስልጠና ሊሰጣቸው አንደሚገባ ተሳታፊዎቹ ሃሳባቸውን ገልፃዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በሀገራችን ኤጀንሲዎች ተመልምለው በተለያዩ ድርጅቶች ተቀጥረው በሚገኙ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ ከፍ ያለ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ እነዚህ ሰራተኞች ማግኘት ከሚገባቸው ክፍያ ከሃምሳ ፐርሰንት በላይ ሚሆነው በኤጀንሲዎቹ ለተለያዩ ወጪዎች በሚል የሚቆረጥባቸው መሆኑ ሰራተኞ ለሚሰሩት ስራ ተገቢውን ክፍያ እንዳያገኙ እያደረገ መሆኑ ተነስቷል፡፡

ለ3ቀናት የቆየ ስልጠና በቤስት ዌስት ፕላዛ ሆቴል ከ28/9/2015__30/92015 ድረስ;   ።Azdadi kenya  ከሕገወጥ የሠዎች ዝውውር በሕይወት በተረፉ ሰዎች የተመሠረተ ድርጅት በኬ...
23/11/2023

ለ3ቀናት የቆየ ስልጠና በቤስት ዌስት ፕላዛ ሆቴል ከ28/9/2015__30/92015 ድረስ;
።Azdadi kenya ከሕገወጥ የሠዎች ዝውውር በሕይወት በተረፉ ሰዎች የተመሠረተ ድርጅት በኬኒያ ውስጥ ይሠራል ።
የስልጠናው ዓላማ በሁለት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር
1::የካስማ በጎ አድራጎት ድርጅት ሥራ አስፈፃምዎችን የተለያዩ ስልጠናዎች መስጠት
2 ; እድገት ፕሮጄክትን በተመለከተ ካስማ ስለምሠራው ሥራ ነው
እድገት ፕሮጄክት ከተለያዩ አረብ ሀገራት የተመለሱና በሀገራቸው 3አመትና ከዛ በላይ ለቆዩ ተመላሾች ትኩረት ተ ሰጥቶ የምሠራበት ፕሮጄክት ነው።

የጋራ ውይይት አደረግን 10/6/2023        ካስማ የበጎ አድራጎት ድርጅት, ከፍኖት የበጎ አድራጎት ማህበር ,  ምሳሌ የበጎ አድራጎት ማህበር  እና ብሩህ አዲስ የበጎ አድራጎት ማህበር...
22/11/2023

የጋራ ውይይት አደረግን 10/6/2023
ካስማ የበጎ አድራጎት ድርጅት, ከፍኖት የበጎ አድራጎት ማህበር , ምሳሌ የበጎ አድራጎት ማህበር እና ብሩህ አዲስ የበጎ አድራጎት ማህበር በፍሪደም ፈንድ ቢሮ ተገኝተው ስለ መመስረታቸው እና ወደ ስራ መግባታቸውን የሚገልፅ የማስተዋወቅ ፕሮግራም እንዲሁም ፈንዶችን በማፈላለግ ዙርያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል
https://t.me/KasmaEt

16/02/2016 ዓ.ም በምስራቅ አፍሪካ የበጎ አድራጎት ህብረት (East African Philanthropy network) እና በሌሎች አጋር አካላት አዘጋጅነት የኢትዮጲያን የበጎ አድራጎት ህ...
30/10/2023

16/02/2016 ዓ.ም በምስራቅ አፍሪካ የበጎ አድራጎት ህብረት (East African Philanthropy network) እና በሌሎች አጋር አካላት አዘጋጅነት የኢትዮጲያን የበጎ አድራጎት ህብረት መመስረትን ማብሰሪያ ፕሮግራም ቦሌ በሚገኘው ቤስት ዌስተርን ፕላስ ሆቴል ተከናወነ

ካስማ የበጎ አድራጎት ድርጅትን በመወከል ወ/ሮ የኔነሽ ጥላሁን ( Manager) እና አቶ ምስጋናው ደለለኝ (program coordinator) ተገኝተው በቆይታቸው ከመድረኩ ተገቢውን ልምድ ቀስመዋል፡፡

የዚህ መድረክ አስፈላጊነት በዋነኝነት በኢትዮጲያ የበጎ አድራጎት ህብረት መመስረትን ለማብሰር ሲሆን ፕሮግራሙ በዋንኝነት ያዘጋጀው የምስራቅ አፍሪካ የበጎ አድራጎት ህብረት ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር ነው፡፡

የመድረኩ አላማም በሀገራችን የሚገኙ የሲቪል ማህበራት፤ ለጋሽ አካላት(Donors) እና በመሀል የሚገኙ አካላት(intermediaries) የኢትየጲያ የበጎ አድራጎት ህብረትን አንዲቀላቀሉ እና አልፎም በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ የተቋቋመውን የምስራቅ አፍሪካ የበጎ አድራጎት ህብረት አባል እንዲሆኑ ግንዛቤ መስጠት እና አስቸኳይ ሁኔታዎችን መፍጠር ነው፡፡ እነዚህ ህብረቶች በሀገር ደረጃ እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በሚመለከት በተናበበ መልኩ ስራዎችን ለመስራት እና ከፍ ያለ ተሰሚነትን በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚና ይኖራቸዋል፡፡ በሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማለትም በኬንያ ፤ ሩዋነዳ፤ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ በሀገራቱ የበጎ አድራጎት ህብረቶች ተቋቁመው አመታትን ያስቆጠሩ ሲሆን በዚህም ከፍተኛ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይተዋል፡፡

ከዚህም በመነሳት ለረዥም ጊዜ ጥረቶች ሲከናወኑ ቆይተው ጥረቶቹ ፍሬ በማፍራታቸው የኢትዮጲያን የበጎ አድራጎት ህብረት በዚሁ ዕለት ማለትም በቀን 16/02/2016 ዓ.ም በይፋ ተመስርቷል፡፡ በመድረኩ የተገኙ የተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህብረቱን ለመቀላቀል ሙሉ ፍቃደኝነታቸውን ገልፀዋል፡፡ ካስማም በመድረኩ የህብረቱ አባል ለመሆን ዝግጁ መሆናቸውን ከገለፁ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው፡፡
በመድረኩ የተነሱ አበይት ጉዳዮች

➫የመድረኩን አስፈላጊነት በተመለከተ የምስራቅ አፍሪካ የበጎ አድራጎት ህብረትን በመወከል ንግግር ያደረጉት የህብረቱ ዳይሬክተር ሲሆኑ በዚህም የህብረቱ መመስረት በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ የሚከተሉትን አላማዎች ለማሳካት ይረዳል ብለዋል
➫የበጎ አድራጎት ስራዎችን እና በአጠቃላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ስራ በተመለከተ ያሉ የመረጃ ክፍቶችን በመሙላት የተናበበ እና ድግግሞሽን በማስቀረት የተባበረ ስራዎችን ለመስራት ያስችላል
➫በ 2018 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና ከተሰጣቸው የዘላቂ እድገት ግቦች መካከል የሆነውን እና ማንንም ከኋላ አለማስቀረትን ያነገበውን (Leave no one behind) ግብ ለማሳካት ጠቃሚ መሆኑን እንዲሁም
➫ለበጎ አድራጎት ስራዎች አመቺ የሆነ አካባቢን ከመፍጠር አንፃር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በማብራራት የመድረኩ ተሳታፊዎች አባል እንዲሆኑ ግብዣ ካቀረቡ ቡሃላ የኢትዮጲያን የበጎ አድራጎት ህብረት መመስረትን በይፋ አብስረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ ግለሰቦች በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በዋነኝነት በሚከተሉት አንኳር ጉዳዮች ላይ ሃሳባቸውን አካፍለዋል፡፡
1. የሲቪል ማህደራትን በተመለከተ በኢትዮጲያ ስላለው ገዢ የህግ ማዕቀፍ እና የተስተዋሉ እድገቶች
2. በጎ አድራጎትን በተመለከት በኢትዮጲያ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎች
3. የመረጃ (data) አስፈላጊነት ከበጎ አድራጎት ስራዎች አንፃር እንዲሁም
4. የበጎ አድራጎት ስራዎችን በተመለከተ ወቅቱን ያገናዘቡ የፓራዳይም (paradigm) ለውጦችን
ከላይ የተጠቀሱትን ሃሳቦች በተመለከተ የተለያዩ ግለሰቦች ንግግር ካደረጉ ቡሃላ ከመድረኩ ተሳታፊዎች የተለያዩ ሃሳቦች እና ጥያቄዎች ተነስተው ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
_______________//_______________

29/30/7/2015 ዓ /ም            በሰው መነገድ ፣ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ለስራ ወደ ውጭ ሃገርመላክ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣ...
25/10/2023

29/30/7/2015 ዓ /ም
በሰው መነገድ ፣ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ለስራ ወደ ውጭ ሃገርመላክ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ ስትራቴጂ ሰነድ አደረጃጀት ላይ የ"ኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ ፍትህ ቢሮ" ያዘጋጀው እረቂቅ አዋጅ ላይ ከ iom እና ilo በመተባበር በአዳማ ከተማ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ ላይ በመገኘት ።
በመድረኩ ላይ የተለያዩ የፌደራል የፍትህ አካላትና የክልል ፍትህ ቢሮ ተወካዮችና ከተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅት የተገኙ አካላት ተገኝተው እረቂቅ ሰነዱን ለተከታታይ ሁለት ቀናት መርምረው የግብአት ሃሳብ አቅርበዋል ሰነዱ ላይ ካስማ የበጎ አድራጎት ድርጅት ቢጨመር ያላቸውን ሃሳቦች በቡድን ከሌሎች ሰዎች ጋር አቅርቧል
ለምሳሌ 1:- ዜጎች ወደ ሃገራቸው ሲገቡ በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ከቁሳቁስ ድጋፍ በተጨማሪ የደረሰባቸውን የህግ ጥሰት የሚያስረዱበት ሁኔታ ቢመቻች ።
2 :- ወንጀሉ ከመፈፀሙ በፊት መከላከሉ ላይ በቀጥታ ጉዳቱን የሚያደርሱ ሰዎች ላይ አፋጣኝ እርምጃ ቢወሰድባቸው
3 :-ተጋላጭ ድንበሮችን በተመለከተ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ቢደረግ
4:- እንዲሁም መልሶ ማቋቋም ለስደት ተመላሾች የሚሰጥ ስልጠናና ክህሎት ላይ በራሳቸው በስደት ተመላሾች ቢሰጥ ለዚም ደሞ ካስማ እራሳቸውን የለወጡና አርያ ተደርገው የሚወሰዱ ሴቶች አሉት -----------የሚልና ሌሎች ሃሳቦችን አንስተናል ።
ቆይታችን ጥሩና ጠቃሚ ነበር በቀጣይም ቢሰሩና ቢተገበሩ ብለን ያሰብናቸውን ሃሳብ አቅርበናል ካስማ በጎ አድራጎት ቀጣይ ሰነዱ ተደራጅቶ ለስራ በመቅረቡ አሻራውን በማሳረፉ ደስታ ይሰማዋል ።
ተሳታፊ የኔነሽ ጥላሁን

በቤይሩት/ሊባኖስ/ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስል ጄኔራል የሆኑት ክቡር አምባሳደር ተመስገን ዑመር ከFreedom Fund- (FF) የሥራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ።    በቤይሩት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስል ጄ...
15/03/2023

በቤይሩት/ሊባኖስ/ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስል ጄኔራል የሆኑት ክቡር አምባሳደር ተመስገን ዑመር ከFreedom Fund- (FF) የሥራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ።
በቤይሩት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስል ጄኔራል የሆኑት ክቡር አምባሳደር ተመስገን ዑመር የFreedom Fund ፕሮግራም ማነጄር ከሆኑት Ms Sonia Martins እና የድርጅቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ከሆኑት አቶ ዳንኤል መለሰ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ ያተኮረው በሊባኖስ ችግር ላይ የወደቁ ኢትዮጵያውያን ያሉበትን ሁኔታ፣ ከዚህ ቀደም ወደ አገር ቤት በመመለስ ረገድ ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋርና ከድርጅቱ ጋር በመቀናጀት ስለተከናወነው BETE Project አፈጻጸም፣ የተገኙ ውጤቶችና ያጋጠሙ ችግሮች፣ እንዲሁም አሁንም በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎቻችን የሚፈልጓቸው ድጋፎች በተመለከተ ነበር፡፡
በመድረኩ ክቡር አምባሳደር ተመስገን ዑመር ባለፉት ሁለት ዓመታት በሊባኖስ ሲኖሩ የነበሩና ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ዜጎቻችን ችግር ከመፍታት አኳያ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያከናወናቸው ዋና ዋና ሥራዎችንና አሁንም ያልተፈቱና Freedom Fundን ጨምሮ ሌሎች አጋር አካላት ድጋፍ የሚሹ ጉዳዮችን በዝርዝር (Power Point) የታገዘ ገለጻ አቅርበዋል፡፡ Freedom Fund-Ethiopia ከ2021 ጀምሮ ከ590 በላይ ዜጎችን መብታቸውና ክብራቸው በተጠበቀ ሁኔታ አገር ቤት ሲመለሱ ማረፊያና የሥራ ዕድል ሁኔታ በማመቻቸት ላደረጋቸው ውጤታማ ቅንጅት አመስግነው አሁንም ችግሩ የቀጠለ በመሆኑ ድርጅቱ ራሱም ሆነ ከሌሎች ጋር በመቀናጀት ድጋፉን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ከበጎ አድራጎት ድርጅቱ ኃላፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶችም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የFreedom Fund ኃላፊዎችም በበኩላቸው ለተደረገላቸው ዝርዝር ገለጻ አመስግነው ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ የዜጎችን ችግር ለመፍታት አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር ለሰራቸው ውጤታማ ሥራዎችም አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡
ከዚህ በመቀጠል ኃላፊዎቹ በሊባኖስ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር አመራሮች ጋር ማኅበሩ ያሉት አባላት ብዛት፣ በችግር ላይ ለወደቁ ዜጎች የሚሰጣቸውን ድጋፎች እና በአጠቃላይ የማኅበሩ መዋቅራዊ አደረጃጀትና አሠራር ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ካደረጉ በኃላ ማህበሩ በሚያስተዳድረው መጠለያ ውስጥ የሚገኙ 45 ዜጎቻችንን ሁኔታ ጎብኝተዋል፡፡ ለወደፊትም ማህበሩ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች አጠናክሮ በሚሄድበትና ድጋፍ ሊደረግ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ለመተባበር ዝግጁነታቸውን ገልፀው ውይይት ተጠናቋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ዴሌጌሽኑ በቤይሩት ቆይታው ከተለያዩ የኢትዮጵያ አደረጃጀቶች/ጉሩፖችች/ ተወካዮች ጋር ውጤታማ ውይይቶች አካሄዷል።

https://t.me/KasmaEt

የውይይት መድረክ  ዛሬ መጋቢት 4/2015 ዕለተ ሰኞ ከጠዋቱ 4:00—6:00 ድረስ በሊባኖስ/ቤይሩት/ የሚገኝው የመስዋዕት በጎ አድራጎት ማዕበር ጋር ሰፊ ወይይት አድርገን ነበር    የማህበ...
13/03/2023

የውይይት መድረክ
ዛሬ መጋቢት 4/2015 ዕለተ ሰኞ ከጠዋቱ 4:00—6:00 ድረስ በሊባኖስ/ቤይሩት/ የሚገኝው የመስዋዕት በጎ አድራጎት ማዕበር ጋር ሰፊ ወይይት አድርገን ነበር
የማህበሩ መስራችና ስራ አስኪያጅ ሳሙኤል ተስፋዬ ጋር የልምድ ልውውጥ በስደተኛው ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል
በመጨረሻም ወደፊት አብረን በጋራ ልንሰራቸው ስለምንችል ጉዳዮችና የጋራ መድረኮችን ለማድረግ ተነጋግረናል
ካስማ በጎ አድራጎት ድርጅት
4/7/2015
mar 13/2023
Telegram
Ngo
https://t.me/KasmaEt

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251953867494

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when kasma charity organization posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to kasma charity organization:

Share