01/06/2026
🌙 የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የእርድ ስጋ እና የአስቤዛ እደላ ተደረገ ።
እንኳን ለ1447ኛው (2018 ዓ.ሂ / 2026) የዒድ አል-አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በመተዛዘን በጎ አድራጎት ድርጅት (Metazazen Charity Organization) አዘጋጅነት የተዘጋጀው የዒድ አል-አድሃ የአስቤዛ፣ የምግብ ዘይት ፣ሩዝ እና ዱቄት እንዲሁም የእርድ ስጋ ድጋፍ ለተጠቃሚዎች በስኬት ተደራሽ ተደርጓል።
የብዙ እህት ወንድሞቻችንን የበዓል ማዕድ ላደመቁት ውድ ደጋፊዎቻችን ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡-
✨ በተለየ ልዩ ምስጋና ለሚገባቸው ለ፦
👉አብዱሰላም በድሩ (ከኳታር)
👉ሚካኤል ዘውገ እና የለንደን ጀማዓዎች
👉አብድልጀሊል ከድር ሼህ እና የኳታር ጀማዓዎች
#አሸናፊ ታምሩ
የእናንተ ልግስና እና ደግነት ዛሬ የብዙዎችን ቤት አስደስቷል። አሏህ በጎ ስራችሁን ይቀበላችሁ፤ በነበራችሁ ላይ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይተካላችሁ
መተዛዘንን ለመርዳት
1000680446869 መተዛዘን በጎ አድራጎት
0948338585/ 0974434344/0911562020/