Addis Ababa Hotel Owners Association

Addis Ababa Hotel Owners Association Addis Ababa Hotel Owners Association (AHA) was established in 1997 as a non-profit employers association.
(1)

17/04/2026

History is in the making! Tomorrow, the first-ever Addis Ababa Grand Prix roars to life, transforming the heart of Ethiopia into a high-speed stage for global sport

​When: Tomorrow!
​Where: Addis Ababa – the rising hub of Africa.
​The Vibe: Thrilling competition meets world-class tourism

​Get ready for the adrenaline. Witness the city’s transformation.

የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር መልካም የትንሳኤ በዓል እንዲሆን ምኞቱን ይገልጻል!The Addis Ababa Hotel Owners Association wishes everyone a Happy...
11/04/2026

የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር መልካም የትንሳኤ በዓል እንዲሆን ምኞቱን ይገልጻል!

The Addis Ababa Hotel Owners Association wishes everyone a Happy and Blessed Easter!

#አዲስአበባ

22/03/2026
የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው ኢድ አል-ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።​ኢድ ሙባረክ!​The Addi...
19/03/2026

የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው ኢድ አል-ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
​ኢድ ሙባረክ!

​The Addis Ababa Hotel Owners Association wishes a peaceful and blessed 1447th Eid al-fitr.

Eid Mubarak!

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር በምርምር፣ የስራ ላይ ልምድ ልውውጥ እና የትብብር ስልጠና አብሮ ለመስራት የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡  መጋቢት 04/2...
13/03/2026

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር በምርምር፣ የስራ ላይ ልምድ ልውውጥ እና የትብብር ስልጠና አብሮ ለመስራት የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

መጋቢት 04/2018 ዓ.ም

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ መጋቢት 03/2018 ዓ.ም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ባካሄው ሀገር አቀፍ የካሪኩለም ክለሳ አውደ ጥናት ጎን ለጎን ከአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር ጋር በምርምር፣ የስራ ላይ ልምድ ልውውጥ እና የትብብር ስልጠና አብሮ ለመስራት የማህበሩ ፕሬዝዳንት አስቴር ሰለሞን እና የዩኒቨርሲቲው ቢዝነስ ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ጌታነህ ምህረት የጋራ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ዩኒቨርሲቲ እያስተማረ ከሚገኙት የትምህርት መርሐ ግብሮች መካከል የቱሪዝም እና ሆቴል ማኔጅመንት አንዱ ሲሆን በዚህ ዘርፍ የሚሰጠውን ትምህርት በተግባር የተደገፈና የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ እንዲሆኑ እንደሚያግዝ ተገልጸዋል፡፡

12/03/2026

Ethiopia Leads Africa’s Hotel Construction Rate for 2026 🇪🇹🏨

March 12/2026

​Ethiopia has taken the top spot in Africa for hotel project ex*****on, with 79.9% of its pipeline currently under construction. According to the 2026 W Hospitality Group report, Ethiopia outpaces regional neighbors Kenya (79.5%) and Tanzania (77.5%).


​Regional Hub: East Africa is now the continent's most dynamic region for hotel development.

​Capacity: Ethiopia ranks 5th overall in pipeline volume with 34 hotels and 5,964 rooms planned.

​Market Leaders: 80% of Africa's new projects are driven by Marriott, Hilton, Accor, IHG, and Radisson.

​Continental Growth: Africa’s total hotel pipeline has surged by 18.6% this year, reaching over 123,000 rooms.

​Addis Ababa continues to solidify its status as a premier business and tourism gateway through this massive infrastructure expansion.

የጥንቃቄ መልዕክት
27/02/2026

የጥንቃቄ መልዕክት

የቱሪዝም ዘርፍ የ6 ወራት አፈጻጸም ግምገማ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ::​የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ምበአርባምንጭ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የቱሪዝም ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት ...
27/02/2026

የቱሪዝም ዘርፍ የ6 ወራት አፈጻጸም ግምገማ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ::

​የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም

በአርባምንጭ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የቱሪዝም ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ፣ የዘርፉን ስድስት ወራት የሥራ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ዝርዝር ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግና ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል።

በቀረበው ሪፖርት ላይ የመዳረሻ ልማት ስራዎች፣ የቱሪስት አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ገበያ ትስስር፣ የቅርሶች ጥበቃ፣ የብሔራዊ ፓርኮች አያያዝ እንዲሁም በዘርፉ እየተገነቡ ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ያሉበት ደረጃ ለጉባኤው ተሳታፊዎች ቀርቦ ገለጻ ተደርጎባቸዋል።

​በውይይት መድረኩ ላይ ከክልልና ከተማ አስተዳደሮች የመጡ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ሪፖርቱን መሠረት በማድረግ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ሰንዝረዋል። በተለይም ከዘርፉ አደረጃጀት፣ በመዳረሻዎች አካባቢ የሚስተዋሉ የመሰረተ ልማት ችግሮች፣ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የጥራት ደረጃና በፓርኮች አካባቢ የሚታዩ ተግዳሮቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ ማብራሪያዎች ተጠይቀዋል።

ተሳታፊዎቹ በዘርፉ የታዩ ስኬቶችን በማስቀጠልና የታዩ ድክመቶችን በማረም ረገድ የፌደራልና የክልል ተቋማት ይበልጥ ተቀናጅተው መስራት እንደሚገባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል።

​ለተነሱት ጥያቄዎችና ማብራሪያ ለሚሹ ጉዳዮች የቱሪዝም ሚኒስትር ክብርት ሰላማዊት ካሳ፣ የማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) እንዲሁም የመዳረሻ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ክብርት ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ማጠቃለያ ሲሰጡም፣ በቀጣይ ስድስት ወራት በትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራባቸው ይገባል ባሏቸው የሪፎርም ስራዎችን ማጠናከር፣ በመስህብ ሀብቶች ላይ ፈጠራ የታከለባቸውና እሴት የሚጨምሩ ስራዎችን ማከናወን፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ልህቀትን ማረጋገጥ እንዲሁም ለሀገር ውስጥ ቱሪዝም እድገት አዳዲስ እይታዎችን መከተል እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የሃዘን መግለጫ​በኢትዮጵያ የቱሪዝም ውስጥ ለረጅም ዓመታት በጋዜጠኝነት ሙያው ሲያገለግል የነበረው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ግርማ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እንገልጻለን።​ጋዜ...
06/02/2026

የሃዘን መግለጫ

​በኢትዮጵያ የቱሪዝም ውስጥ ለረጅም ዓመታት በጋዜጠኝነት ሙያው ሲያገለግል የነበረው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ግርማ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እንገልጻለን።

​ጋዜጠኛ ዘሪሁን ግርማ በሙያው የሀገራችንን የቱሪስት መስህቦች፣ ታሪካዊ ቅርሶችና ባህላዊ እሴቶች ለዓለም ለማስተዋወቅ በነበረው ከፍተኛ ፍቅርና ቁርጠኝነት ይታወቃል። በሙያው ባበረከተው አስተዋጽኦ በዘርፉ ዕድገት ላይ የራሱን አሻራ ጥሎ አልፏል።

​ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለሥራ ባልደረቦቹ መጽናናትን እንመኛለን።

​የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር

የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ተሳታፊዎች የቱሪስት መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ እንዲጎበኙ አዲስ አበባ ተሰናድታለች***መዲናችን አዲስ አበባ በቅርቡ ለሚካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ...
30/01/2026

የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ተሳታፊዎች የቱሪስት መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ እንዲጎበኙ አዲስ አበባ ተሰናድታለች

***

መዲናችን አዲስ አበባ በቅርቡ ለሚካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችላትን ሁለንተናዊ ቅድመ ዝግጅት አጠናቃለች።

ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎትና ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት የተዋቀረ የጋራ ግብረ-ሃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ገልፀዋል።

የጸጥታ ስራው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ (CCTV እና የሰውነት ካሜራዎች) የታገዘ መሆኑን ያብራሩት ኮማንደር ማርቆስ፤ ህብረተሰቡም እንደተለመደው ለጸጥታ አካላት ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ሆቴል ባለንብረቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወይዘሮ አስቴር ሰለሞን እንደገለጹት፤ ሆቴሎች ወቅቱን ጠብቆ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። የቋንቋ እጥረት እንዳያጋጥምም ተርጓሚዎችን እና የትርጉም ቴክኖሎጂዎችን የማደራጀት ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል እንግዶች ከጉባኤው ጎን ለጎን የከተማዋን የቱሪስት መዳረሻዎች እንዲጎበኙ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን የቱሪስት አገልግሎቶች ብቃት ማረጋገጥ ዳይሬክተር ወይዘሮ ገነት ይመር አስረድተዋል።

እንግዶች የአድዋ ሙዚየም፣ የወዳጅነት፣ የሳይንስ እና እንጦጦ ፓርኮችን እንዲጎበኙ የውጭ ቋንቋ ተናጋሪ ባለሙያዎች እና የጉብኝት አውቶቡሶች ተዘጋጅተዋል።

ጉባኤው ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተቀባይነት የሚያጎላ በመሆኑ ነዋሪዎች የተለመደውን ኢትዮጵያዊ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል እንዲያሳዩ ጥሪ ቀርቧል።

ዘንድሮ የሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓትን ማረጋገጥ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት" በሚል መሪ ቃል ነው። ከየካቲት 3 እስከ 4 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ፤ ከየካቲት 7 እስከ 8 ደግሞ የመሪዎች ጉባኤ እንደሚካሄድ መርሀ-ግብሩ ያመለክታል።

28/01/2026

በዋትሳፕ፣ በቴሌግራም እና በሌሎች የመልዕክት መላላኪያ ፕላትፎርሞች የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችን አስመልክቶ የቀረበ የጥንቃቄ መልዕክት

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ)፤ በሀገራችን የዲጂታል ትስስር መስፋፋትን ተከትሎ በዋትሳፕ (WhatsApp)፣ በቴሌግራም (Telegram) እና በሌሎች የመልዕክት መላላኪያ ፕላትፎርሞች አማካኝነት በዜጎች ላይ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶችና የማጭበርበር ድርጊቶች በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመሩ መምጣታቸዉን በተለያዩ መንገዶች ማረጋገጥ ችሏል።

በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የሚካሄዱ የተለያዩ ሲምፖዚየሞችን፣ ዓለም አቀፍ መድረኮችን እና የኦንላይን ስብሰባዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ የሳይበር ወንጀለኞች የእነዚህን ኩነቶች ስም ለሀሰተኛ ድርጊቶቻቸው መጠቀሚያ እያደረጉት ይገኛሉ።

እነዚህ አካላት የማህበረሰቡን የግል መረጃ ለመስረቅ፣ የባንክ ሂሳቦችን ለመመዝበር እና የዲጂታል ደህንነትን ለማናጋት በተቀናጀ መልኩ እየሰሩ መሆኑን አስተዳደሩ በክትትልና በምርመራ አረጋግጧል።

እነዚህ የሳይበር ጥቃቶች የሚፈጸሙት ማህበረሰቡ ትኩረት የሚሰጣቸውን "ተፈላጊ" እና "ወቅታዊ" የሆኑ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ በተዘረጋ ስልታዊ የማታለያ ዘዴ ነው።

አጭበርባሪዎቹ "ለሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች የተዘጋጀ ነጻ የኢንተርኔት ፓኬጅ"፣ "ልዩ የስራ ቅጥር" ወይም "ይህ የስብሰባ መሳተፊያ ሊንክ ነው፤ ከፍተው ይግቡ" የሚሉ አሳሳችና ማራኪ መልዕክቶችን በማሰራጨት ተጠቃሚዎች በመልዕክቱ ውስጥ የተካተተውን ሊንክ (Link) እንዲጫኑ ያደርጋሉ።

ይህ ድርጊት ተጠቃሚው ሳያውቀው ወደ አጥፊ ተልዕኮ ወዳላቸዉ ድረ-ገጾች እንዲያመራና ለጥቃት ተጋላጭ እንዲሆን የሚያደርግ የመጀመሪያው የወንጀለኞች እርምጃ እንደሆነ አስተዳደሩ ይገልጻል።
ጥቃት አድራሾቹ የአንዳንድ ግለሰቦች የግንዛቤ እጥረትና ትኩረት ማጣት የተነሳ የሚላኩላቸውን ሊንኮችና መልዕክቶች በጥንቃቄ የመመርመር ዕድላቸው አነስተኛ መሆኑን ተከትሎ ወንጀለኞቹ ይህን ሁኔታ እንደ ምቹ አጋጣሚ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።

ይህ አይነቱ ጥቃት ከግለሰቦች መረጃ ስርቆት ባለፈ፣ በእጃቸው የሚገኙ ሚስጥራዊ መረጃዎች በጠላፊዎች እጅ እንዲወድቁ በማድረግ በሀገር ደህንነትና ሉዓላዊነት ላይ ከፍተኛ አደጋ የሚጋርጥ መሆኑን አስተዳደሩ በጥብቅ ያሳስባል።

በዚህም ተጠቃሚዎች የተላከላቸውን ሊንክ ሲጫኑ ወይም የተጠየቁትን መረጃ ሲሞሉ፣ የዋትሳፕ ወይም የቴሌግራም አካውንታቸው ወዲያውኑ በጠላፊዎች ቁጥጥር ስር እንዲዉል ያደርጋል።

ወንጀለኞቹ አንዴ የአንድን ሰው አካውንት ከተቆጣጠሩ በኋላ፣ የተጠለፈውን አካውንት በመጠቀም በተጎጂው ስም ለቅርብ ወዳጅ ዘመዶቹና ለስራ ባልደረቦቹ "ድንገተኛ ችግር አጋጥሞኛል" የሚሉ የሀሰት የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄዎችን ይልካሉ።

ይህም ድርጊት በማህበረሰቡ መካከል ያለውን መተማመን ከመሸርሸሩ ባለፈ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በማጭበርበር እንዲመዘበር በማድረግ መጠነ-ሰፊ የኢኮኖሚና የስነ-ልቦና ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

ከላይ የተጠቀሱና መሰል የሳይበር ደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ፣ የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲሁም ማህበረሰቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ያሳስባል።

ከማይታወቁ ወይም ካልተረጋገጡ አድራሻዎች በዋትሳፕ፣ በቴሌግራም እና በሌሎች መድረኮች የሚላኩ ሊንኮችን ካለመክፈት ባለፈ፣ አጠራጣሪ መልዕክቶች ሲደርሱ ወዲያውኑ "Report" እና "Block" በማድረግ የጥቃቱን ስርጭት መግታት ይገባል።

በተጨማሪም ማንኛውንም አይነት ሚስጥራዊ የይለፍ ቃል ወይም በስልክ የሚላክ የማረጋገጫ ኮድ (Verification Code) ለማንም አካል አለመስጠት ለዲጂታል ደህንነታችን ወሳኝ መሆኑን አስተዳደሩ በድጋሚ ያስገነዝባል።

አስተዳደሩ እያንዳንዱ ተጠቃሚ በተለይም ማህበረሰቡ በመተግበሪያዎቹ ላይ የሁለትዮሽ ማረጋገጫ (Two-Step Verification) በአስቸኳይ እንዲተገብር ይመክራል።

ይህ የቴክኖሎጂ የመረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን አካውንት በቀላሉ እንዳይቆጣጠሩ የሚያደርግ እና ተጨማሪ የደህንነት ቁልፍ የሚፈጥር አስተማማኝ የመከላከያ ዘዴ ነው። ዜጎች ይህንን ቀላል ግን ውጤታማ የሆነ የደህንነት ጥንቃቄ ተግባራዊ በማድረግ፣ ራሳቸውን በቴክኖሎጂ ከታገዙ የማጭበርበር ድርጊቶች ሊታደጉና የሳይበር ወንጀለኞችን ሴራ ሊያከሽፉ እንደሚገባ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ይመክራል።

በመጨረሻም፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እነዚህን የሳይበር ወንጀለኞች በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከሚመለከታቸው የጸጥታና የፍትህ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።

ማህበረሰቡ ማንኛውም የሳይበር ጥቃት ሙከራ ሲያጋጥመው ወይም አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት በነጻ ስልክ መስመር 933 በመደወል ለኢመደአ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ እናቀርባለን።

የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የአንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን የሁላችንም የጋራ ሀላፊነት በመሆኑ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችንን በንቃትና በጥንቃቄ በመምራት የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት በጋራ እንጠብቅ።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ጥር 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ

በቱሪዝም ሚኒስቴር አዘጋጅነት መጪው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ መገንባት በሚያስችል መልኩ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል ለሆቴል ባሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡      ...
21/01/2026

በቱሪዝም ሚኒስቴር አዘጋጅነት መጪው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ መገንባት በሚያስችል መልኩ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል ለሆቴል ባሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

Address

Megenagna Near To Belvue Hotel Lion Bldg 5th Floor Office No 503
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Hotel Owners Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ababa Hotel Owners Association:

Share