Warra mettaa

Warra mettaa " the one i love the most is the one who tells me my faults" Umar Ibnal Khattab

Permanently closed.
የማልኮም ኤክስ የሐጅ ምስክርነት እና ገጠመኞች ወደ  ቤተሰቡና ጓደኞቹ የተላኩ ደብዳቤዎችና የአመለካከት ለውጥ ጥሪ መልዕክት 🖋 Mohammedawel Hagos  "በነቢይ ኢብራሂምና በነቢይ ሙ...
05/06/2025

የማልኮም ኤክስ የሐጅ ምስክርነት እና ገጠመኞች ወደ ቤተሰቡና ጓደኞቹ የተላኩ ደብዳቤዎችና የአመለካከት ለውጥ ጥሪ መልዕክት 🖋 Mohammedawel Hagos

"በነቢይ ኢብራሂምና በነቢይ ሙሐመድ አገር ውስጥ ሆኜ አላህ ዓይኖቼን ከፍቶልኝ ስለ ትክክለኛው የእስልምና ሃይማኖት ተገለጸልኝ፤ በአሜሪካ ያለውም አጠቃላይ የዘርና የቀለም ልዩነት ሁኔታ ጥርት ብሎ ታየኝ"ቀደም ሲል የጥላቻና የኃይለኛነትን ንግግር ሲያደርግላቸው የሚያውቁት ሁሉ ስለ አዲስ አሁን ስላለው አቋሙ ምን ይሉ ይሆን የሚለው ጥያቄ እራሱን አስገረመው። ጥቂት ካሰበበትና "በቃ ሕይወቴ በሙሉ በተለያዩ የለውጥ ሂደቶች የተሞላ ነው፤ ምን አዲስ ነገር አለ?!" ብሎ እራሱ ለራሱ ጥያቄውን መለሰለት።

"አሜሪካ የእስልምና ሃይማኖትን ምንነት መረዳት አለባት፤ ምክንያቱም እስልምና በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ያለውን የዘርና የቀለም ችግር መንግሎ የሚጥል ሃይማኖት ነው።"

በአሜሪካን አገር ቢሆን "ነጮች" ልንላቸው የምንችላቸውን ሰዎች በአረብ አገሮች ቆይታው አግኝቷል፣ አነጋግሯል፣ አብሮም ቆይቷል። "እነዚህ 'ነጮች' እንኳ ነጭ መሆናቸውን ከውስጣቸው ፈቅደዋል። ይህም የሆነው የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ስለሆኑ ነው። ሌላው ቀርቶ የተለያየ ቀለምና ዘር ባለቤቶች የሆኑ ሆነው ሳለ ያንን ልዩነታቸውን ባለማጠንከር እንዲያውም ከነአካቴው ዘንግተውት ወይም ቦታ ሳይሰጡት ሁሉም በአንድነት ተሰባስበው በፍቅር፣ በደስታና በወንድማማችነትና በእኅትማማችነት መንፈስ ሆነው መመልከቱ እጅግ አስደስቶኛል። እምነታችን በአንድ አምላክ በመሆኑና ሁላችንም በወንድማማችነት ስለምንተያይ የቆዳ ቀለማችንን ምንነት ረስተናል። ቀለም ዋጋ ሊሰጠው የሚገባ ነገርም እንዳልሆነ አውቀናል።"

"እናም ከዚህ ቀደም ያራመድኩትን የጥላቻ ዓይነት ፍልስፍና አሁን ባገኘሁት ግንዛቤ አኳያ አስተካክዬ በአዲስ መልክ አዲስ አስተሳሰብን ማስኬድ አስፈልጎኛል። አዲስ ልምድንና አዲስ እውነትን ተቀብሎ ያለፈውን በማሻሻል ለውጥን ማራመድ ከሰው ልጅ የሚጠበቅ ነገር ነው። ትክክለኛው እውነት ጋር ሲደረስ ደግሞ ያንን የቀድሞውን የተሳሳተ ሁኔታ አሽቀንጥሮ መጣል እጅግ አስፈላጊ ነው።"

የቆዳ ቀለማቸው ከነጭም ነጭ የሆነ፣ የፀጉራቸውም ቀለም ከብሎንድም ብሎንድ ወርቃማ የሆነ፣ እንደዚሁም የዓይኖቻቸው ቀለም ከሰማያዊም በላይ ሰማያዊ ከሆኑ ፈረንጅ አረቦች ጋር አብሮ በልቷል፣ ጠጥቷል፣ አብሮም አንዱን ፈጣሪያችንን አላህን አመስግኗል። "የእነዚህ ነጮች አረቦች ሥነምግባራዊ ሁኔታ፣ የአንደበታቸው ቁጥብነት፣ በጎ አስተሳሰባቸውና ተግባራቸው በናይጀሪያ፣ በሱዳንና በጋና ተዘዋውሬ ካየኋቸው ጥቁር ሙስሊም ወገኖቻችን ጋር በጣም ተመሳሳይ ነ

"እናም ከዚህ ሁኔታ ተነስቼ ስለ አሜሪካ መናገር የምፈልገው ምንድነው ብትሉኝ ነጭ-አሜሪካ የተባለችው አገር የፈጣሪን አንድ መሆን በሙሉ ልቧ መቀበል ይኖርባታል። ይህን ካደረገች ብቻ ነው የሰውን ልጅ አንድ የመሆን እውነት መረዳት የምትችለው። ይህን ካደረገች ደግሞ በቆዳ ቀለም ልዩነት ሳቢያ በሌሎች የአላህ ፍጥረቶች ላይ የምታደርገውን ጥላቻ፣ ጉዳትና ማሰናከል ማቆም ይቻላታል።"

"የቀለም ልዩነትና ዘረኝነት አሜሪካንን የወረረ የማይድን ነቀርሳ መስሎ ሲያጠቃን እያየነው ነው። ክርስቲያን ተብዬዎቹ ነጮች አሜሪካውያን እስካሁን ከተከተሉት አጥፊ ፍልስፍና እውነተኛውንና ለሰው ልጅ እኩልነት በፍቱንነት የሚሰራውን ሃይማኖት ወጥተው መቀበል ይኖርባቸዋል። ይህ ከተደረገ ምናልባትም አሜሪካ ካንዣበበባት ውድመት ለማምለጥ ትችል ይሆናል። አለበለዚያ ግን ልክ ይኸው ዘረኝነቷ ወደ ቁልቁል እንደነዳ እንዳወደማት ጀርመን ትሆናለች።"

በዚች ቅድስት አገር ውስጥ ሆኖ - አሜሪካን አገር በነጮቹና በእኛ በጥቁሮቹ መካከል ስላለው አስከፊ ግንኙነት አወጣለሁ፣ አወርዳለሁ ብሏል። "የአሜሪካን ኔግሮ በፈረንጆች ላይ በጠላትነት ተነሳህ ተብሎ ሊወቀስ አይገባም። ነጮቹ ለአራት መቶ ዓመታት ያደረጉበትንና አሁንም እየተደረገበት ያለውን ግፍ 'አልፈልግም፤ ሁሉ በቃኝ፣ መረረኝ፣ አሻፈረኝ፣ ነፃነት ጠማኝ' ነው ኔግሮው የሚለው። እናም የነጮቹ አሜሪካውያን ምርጫ ትክክለኛው፣ መንፈሳዊውና ሐቀኛው የእስልምና መንገድ መሆን ይኖርበታል።"

"እዚህ በቆይታዬ ሙስሊሞች ቤታቸውን ሰጥተውኝ፣ ምግብ፣ መጠጥ፣ መግዣ፣ እንደዚሁም ሾፌርና ረዳት መድበውልኝ ለአንድ ኔግሮ ሳይሆን ለአንድ ንጉሥ የሚገባውን ክብር ሰጥተው አስተናግደውኛል። 'የዓለሞቹ ሁሉ የበላይ ጌታ ለሆነው ለአላህ ክብርና ምስጋና ይገባው።'"

የናንተዉ
"አል-ሐጅ ማሊክ አል-ሻባዝ" አላህ ይዘንለት 🤲

🖋 Mohammedawel Hagos

Sunday💚የወሎዋ ፈርጥ ሰንበቴ ከተማ እሁድ ላይ የሚውለው የሰንበቴ ደማቅ የሜዳ ላይ ገበያ ከአራት በላይ ብሔረሰቦች የሚገበያዩበት የጦፈ ንግድ የሚከናወንበት ረዥም እድሜ ያስቆጠረ ትልቅ ገ...
18/05/2025

Sunday💚
የወሎዋ ፈርጥ ሰንበቴ ከተማ እሁድ ላይ የሚውለው የሰንበቴ ደማቅ የሜዳ ላይ ገበያ ከአራት በላይ ብሔረሰቦች የሚገበያዩበት የጦፈ ንግድ የሚከናወንበት ረዥም እድሜ ያስቆጠረ ትልቅ ገበያ ነው። ይህ ገበያ ከገበያነት ባለፈም ልዩ መስህብ የሆነ ብዙ ጎብኚዎችን የሚስብ የቱሪዝም ቦታ ነው።

ልጅ እያሱ ከሸዋ ወደ አባታቸው በአዳል በኩል አድርገው ሲያልፉ ጤናዬ ብለው በፈረሳቸው ስም የሰየሟት ከተማ ዛሬ ሰንበቴ ትባላለች፣ ወረዳዋ ደግሞ ጅሌ ጥሙጋ፣ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 265 ኪሎ ሜትር ያክል ትርቃለች።

የሰንበቴ ገበያ እሁድ እንደመሆኑ የከተማዋ ስም ከጤናዬ ወደ ሰንበቴ የተቀየረ ይመስላል። ሰንበታ( እሁድ ) ላይ ሰንበቴ ትደምቃለች ኮረብታ ላይ የተመሰረተው የሰንበቴ ገበያ በርካታ ብሄረሰቦችን የሚያገናኝ ሲሆን በባህል ልብስ የደመቁ የኦሮሞ ልጃገረዶች ደስስስ በሚል የአሪቲ መአዛ ገብያውን ያውዱታል ።

ፍየል እና በጎች እየነዱ ወደ ገብያው የሚተሙት የአፋር ልጃገረዶችም በአፋር ባህላዊ አለባበስ እና በቀጫጭኑ ተገምዶ ፊታቸውን በሚሸፍነው ባህላዊ የፀጉር አሰራር አምረው እና ደምቀው፣ በወገባቸው ለገብያ የሚያውሉትን ጓዝ ተሸክመው ሲታዩ እንደጠዋት ፀሀይ አይንን ያሳሳሉ ። የተጠቀለለ ጉፍታ ራሳቸው ላይ አስረው እጅና እግራቸውን በእንሶስላ በሂና አስውበው ገብያውን የቁንጅና ውድድር መድረክ የሚያስመስሉት ወይዛዝርቶች፣ ህፃናትና እናቶች ለገብያው የተመረጡ የሙዚቃ ቀለሞች ናቸው።

ረዘም ያለ ጎፈሬ፣ ቅቤ የጠገበ ዱላ፣ አጠር ያለ ሽርጥ አገልድሞ፣ በገብያው እምብርት የሚዘዋወረው ወጣት ደግሞ ሌላው የሰንበቴ ገብያ ግርማ ሞገስ ነው። አርጎባው፣ አማራው ፣ አፋሩ ኦሮሞው፣ ሁሉም በራሱ ባህላዊ አለባበስና ቋንቋ ተገበያይቶ አትርፎና ተደስቶ ወደ ቤቱ የሚመለስበት ገብያ ነው። የሰንበቴ ገብያ ወጥ፣ ያልተበረዘ ባህላዊ እሴትና ማህበረሰባዊ አኗኗር
የሚስተናገድበት ህያው ኢግዚቢሽን ነው።በርካታ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ካሜራ ይዘው ለአደን እንደወጣ አዳኝ የሚመሽጉበት መስክም ነው።

ብዘሃነት ህያው ሆኖ የሚገማሸርበት ቦታ ጎራ ይበሉና ከዚህ ከባለ-ብዙ ሕብረ-ቀለም ባለቤት ከሆነው ከሰንበቴ ገበያ ፍቅርና መቻቻልን፤ ሕብረ-ብሄራዊነትን … ይሸምቱ!!

ወሎ የነገዋ ኢትዮጵያ መሰረት ጣይ ተምሳሌት!
ፎቶ፦ አሹ ሀበሻ

~ኡመር አብደላ (ወረ ሜታ)

SATURDAY💚ከጭሱ ጋር አዋይቱ ወሎ ሰንበቴይሄ ፍል ውሃ ከልጅ እያሱ ባህር ዛፍ አጠገብ ነበር ይላሉ አንዳንዶች ግን በጊዜ ሂደት እየሸሸ ከ4 ኪሎ ሜትር ጉዞ በኋላ አዋይቱ ላይ ከተመ። በዚ...
17/05/2025

SATURDAY💚
ከጭሱ ጋር አዋይቱ ወሎ ሰንበቴ
ይሄ ፍል ውሃ ከልጅ እያሱ ባህር ዛፍ አጠገብ ነበር ይላሉ አንዳንዶች ግን በጊዜ ሂደት እየሸሸ ከ4 ኪሎ ሜትር ጉዞ በኋላ አዋይቱ ላይ ከተመ። በዚያ በኩል መሬት ስትተነፍስ ማየት ይቻላል። የመሬት ትንፋሽ እንዴት ይሞቃል መሰላችሁ ጭሱ ደግሞ ለሰውልጅ ፈውስ እንዲሆን ከመሬት እምብርት የተሰጠ መድሃኒት ነው።

አዋይቱ የልጅነት እግራችን ማረፊያ ነው። አዋይቱ ለመሄድ ቀጠሮ ስንይዝ ቅዳሜ ይርቅብን ነበር፣ አሳ ለማጥመድ ሸንበቆ ቆርጠን መንጠቆ ስናዘጋጅ፣ ዳቦ፣ እንቁላል፣ ሻይ ቅጠል ለመግዛት ሳንቲም ስናዋጣ፣ ብቻ ልዩ ነው፣ መንገድ ስንጀምርም ወሬው ሁሉ አዋይቱ ነው፣ ጭሱ ፍልውሃው መልክአ ምድሩ፣ ለመፋቂያ የምንቆርጠው ዘንባባ፣ ድንጋዩ አዳልጦን እንዳንወድቅ የሚንሰጠው ማስጠንቀቂያ፣ በመንገዱ ካሉት እርሻዎች ላይ የምንቆርጠው ጥንቅሽ፣ መስኩ ላይ፣ ቄጠማው ላይ የምንነሳው ፎቶ፣ በሩቅ የሚጠራው የፍል ውሃው ሽታ ልዩ ብቻ አይገልፀውም።

የአዋይቱ ፍል ውሃ የኤፌሶኑ ናዘሮ ወንዝና የሰንበቴ ወንዝ አዋሽ ለመድረስ የሚያስችላቸውን ህብረት ለማግኘት የሚዋሀዱበት ስፍራ ነው። ለውህደታቸው ምልክቱ ደግሞ ከመሬት እምብርት ውስጥ ባለው እሳት ተፍለቅልቆ ወደ ላይ የሚተፋው የአዋይቱ ፍል ውሃ ነው። አዋይቱ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ብዙ ንግርቶች አሉት።

የሰንበቴ ከተማ ለአዋይቱ ፍል ውሃ ቅርብ የሆነች ከተማ ስትሆን አዋይቱ ደግሞ ለማህበረሰቡ የተሰጠ የነፋስ እና የልዩ ልዩ በሽታ መድሀኒት ነው። ሰንበቴና አዋይቱን ተፈጥሮ ድንቅ አድርጎ አጎራብቷቸዋል። ታዲያ የኔም አድናቆት ከሁለቱም እንዳይቀር ሆኖ በአጭሩ የተፃፈ ነው። ከጭሱ ጋር አዋይቱ፣ ይምጡ ደስ እየተሰኙ ይመለሳሉ። የእንዳይቀርባችሁ ማስታወቂያ ነው።

📷 በባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዶ/ር አሚር አማን የተመራዉ ልዑካን ቡድን አዋይቱ ፍል ውሃ ሲጎበኝ
~ኡመር አል-ፋሩቅ ( Warraa Mettaa)

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Warra mettaa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share